Awde Tewahdo - አውደ ተዋሕዶ

Awde Tewahdo - አውደ ተዋሕዶ Ethiopian Orthodox church organization

11/12/2024
 ኀዳር 11 በዚህችም ቀን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ፣ፀሐይን እና ጨረቃን ለሚገዛ ፣ ሰውን በአርያውን በመልኩ ለፈጠረ ፈጣሪያችን አያት የሆነች ፣ ለእመቤታችን ለቅድስት ቅዱሳን ድንግል ማርያም...
19/11/2024


ኀዳር 11 በዚህችም ቀን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ፣ፀሐይን እና ጨረቃን ለሚገዛ ፣ ሰውን በአርያውን በመልኩ ለፈጠረ ፈጣሪያችን አያት የሆነች ፣ ለእመቤታችን ለቅድስት ቅዱሳን ድንግል ማርያምም እናቷ የሆነች የተመሰገነች እና የከበረች ቅድስተ ሐና ዕረፋቷ ነው፡፡
ያድርጉ
በኢየሩሳሌም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሚልኪ ልጅ ለሆነው የማጣት ልጅ ናት፡፡
____
#ማጣትም 3 ልጆች አሉት እነርሱም ፤
#የመጀመሪያይቱ ስሟ ማርያም ነው፤ አዋላጅ የነበረች ስትሆን ቅድስት ሰሎሜን ወልዳለች ፤ ሰሎሜም እመቤታችን መድኃኒታችንን ከወለደችው ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ያገለገለቻት ናት፡፡
#ሁለተኛይቱ ስሟ ሶፍያ ነዉ ፤ ይህቺ ቅድስተ ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እናት የሆነችውን ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች፡፡
#ሦስተኛይቱም ስሟ ሐና ነው፤ ይህች ቅድስት ሐና ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙም ኢያቄም ከሆነ ጋር ተጋብታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት፡፡
ሰሎሜና ቅድስት ኤልሳቤጥ የእመቤታችን እናት ለሆነች ለቅድስት ሐና እኀትማማች ናቸው፡፡
_
ቅድስት ሐና መካነ እያለች አምላክን ልጅ እንዲሰጣት እጅግ አብዝታ ትለምን ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኀነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችን የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡
ጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቆጠሩ ሁሉ ክቡራን ናቸው የመጨረሻዎቹ አያቶቹ ደግሞ የመጨረሻው ክብር ይገባቸዋል እነርሱም ሐና እና ኢያቄብ ናቸው:: አምላካችንን የልጅ ልጅቻችን ነው ለማለት ተገብተዋልና፡፡
ቅድስት ሐና ከሴቶች ሁሉ የምትከብርና የምትበልጥ መሆኗን አምላክን ለወለደችልን ለቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም እናት ሆና አይተናል፤ ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ጸጋ ባልተገባት ነበር፡፡ አባቶችም ታጋድሎዋ እጅግ ብዙ እንድሆነ ነግረውናል፡፡
---ምልጃዋ አይለየን ፡፡
ሃገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን እና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ትጠብቅልን
አሜን!
አርኬ
ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኵሉ ምዕራጋ፡፡
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ፡፡
ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ፡፡
እስመ ረከብኪ ምገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ፡፡
እምሔውተ አምላክ ትኵኒ በሥጋ፡፡

በቦታው ሄዳቹ በዓሉን ማክበር ለምትፈልጉ👇🏼
ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. እና በሌሎች የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያተ ክርስቲያናት ...
፠ ኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ ፡
፠ ደብረ ንግስት መንዝ ቅድስት ሐና::
፠ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በደብረ መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በደባልነት ትገኛለች
ሌሎች በዓሉ የሚከብሩባቸውን ቦታዎች ኮሜንት ላይ ያጋሩን

19/11/2024


ኀዳር 11 በዚህችም ቀን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ፣ፀሐይን እና ጨረቃን ለሚገዛ ፣ ሰውን በአርያውን በመልኩ ለፈጠረ ፈጣሪያችን አያት የሆነች ፣ ለእመቤታችን ለቅድስት ቅዱሳን ድንግል ማርያምም እናቷ የሆነች የተመሰገነች እና የከበረች ቅድስተ ሐና ዕረፋቷ ነው፡፡
ያድርጉ
በኢየሩሳሌም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሚልኪ ልጅ ለሆነው የማጣት ልጅ ናት፡፡
____
#ማጣትም 3 ልጆች አሉት እነርሱም ፤
#የመጀመሪያይቱ ስሟ ማርያም ነው፤ አዋላጅ የነበረች ስትሆን ቅድስት ሰሎሜን ወልዳለች ፤ ሰሎሜም እመቤታችን መድኃኒታችንን ከወለደችው ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ያገለገለቻት ናት፡፡
#ሁለተኛይቱ ስሟ ሶፍያ ነዉ ፤ ይህቺ ቅድስተ ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እናት የሆነችውን ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች፡፡
#ሦስተኛይቱም ስሟ ሐና ነው፤ ይህች ቅድስት ሐና ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙም ኢያቄም ከሆነ ጋር ተጋብታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት፡፡
ሰሎሜና ቅድስት ኤልሳቤጥ የእመቤታችን እናት ለሆነች ለቅድስት ሐና እኀትማማች ናቸው፡፡
_
ቅድስት ሐና መካነ እያለች አምላክን ልጅ እንዲሰጣት እጅግ አብዝታ ትለምን ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኀነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችን የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡
ጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቆጠሩ ሁሉ ክቡራን ናቸው የመጨረሻዎቹ አያቶቹ ደግሞ የመጨረሻው ክብር ይገባቸዋል እነርሱም ሐና እና ኢያቄብ ናቸው:: አምላካችንን የልጅ ልጅቻችን ነው ለማለት ተገብተዋልና፡፡
ቅድስት ሐና ከሴቶች ሁሉ የምትከብርና የምትበልጥ መሆኗን አምላክን ለወለደችልን ለቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም እናት ሆና አይተናል፤ ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ጸጋ ባልተገባት ነበር፡፡ አባቶችም ታጋድሎዋ እጅግ ብዙ እንድሆነ ነግረውናል፡፡
---ምልጃዋ አይለየን ፡፡
ሃገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን እና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ትጠብቅልን
አሜን!
አርኬ
ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኵሉ ምዕራጋ፡፡
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ፡፡
ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ፡፡
እስመ ረከብኪ ምገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ፡፡
እምሔውተ አምላክ ትኵኒ በሥጋ፡፡

በቦታው ሄዳቹ በዓሉን ማክበር ለምትፈልጉ👇🏼
ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. እና በሌሎች የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያተ ክርስቲያናት ...
፠ ኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ ፡
፠ ደብረ ንግስት መንዝ ቅድስት ሐና::
፠ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በደብረ መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በደባልነት ትገኛለች
ሌሎች በዓሉ የሚከብሩባቸውን ቦታዎች ኮሜንት ላይ ያጋሩን

በዓለ ደብረ ታቦር እና ቡሄነሐሴ ፲፫ ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን!ደብረ ታቦር የሚውለው በነሐሴ 13 ቀን በመሆኑ ለጾመ ፍልሰታ ሱባዔ ል...
19/08/2024

በዓለ ደብረ ታቦር እና ቡሄ
ነሐሴ ፲፫
ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን!
ደብረ ታቦር የሚውለው በነሐሴ 13 ቀን በመሆኑ ለጾመ ፍልሰታ ሱባዔ ልዩ ምዕራፍ ሆኖ በታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦና ማኀሌት ይከበራል። ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን በዓላት አንዱ ነው። ምን አድርጎበታል ቢሉ ብርሃነ መለኮቱን ለሐዋርያት በደብረ ታቦር ገልጾበታል። ደብር ተራራ ታቦር የተራራ ስም ነው። ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ ብዙውን ጊዜ የሚያስተምረው ተአምራት የሚያደርገው በተራራ ላይ ነበር። በዚህም ዕለት ዘጠኙን ከእግሩ ደብር ትቶ ሶስቱ ጴጥሮስን ዮሐንሰንና ያዕቆብን አስከትሎ ከርእሰ ደብር ወጣ። ወተወለጠ ራዕዩ በቅድሜሆሙ ወአብርሀ ገጹ ከመ ፀሐይ ወአልባሲሁኒ ኮነ ጸዓዳ ከመ በረድ ይላል መልኩ ተለውጦ ፊቱ እንደ ጸሐይ አብርቶ ልብሱ እንደ በረድ ነጽቶ ሙሴና ኤልያስ በቀኝ ሆነው ታዩአቸው። ሙሴንና ኤልያስን መምረጡ ስለምንድነው ቢሉ ሙሴ 570 ጊዜ ቃል በቃል ተነጋግሮ ባይህ እወዳለሁ አለው ፊቴን አይቶ አንድ ሰዓት እንኳ መቆም መቆየት የሚቻለው የለም አለው ።

ይህማ ካልሆነማ ባለሟል መባሌ ምኑ ላይ ነው። ቢለው ኃላ ሰው ሆኜ ስመጣ እታይሃለው ብሎት ነበርና ዘጸ 33:18-23 ነው። ያን ለመፈጸም ኤልያስም እንዲሁ ተስፋ ነበረውና አንድም ጌታ ዕውር ቢያበራ ሙት ቢያነሳ ሙሴ ነው ኤልያስ ነው ብለውት ነበርና የኛን ጌታ ማን ሙሴ ማን ኤልያስ ይልሀል የሙሴ የኤልያስ ጌታ ይበሉህ እንጂ ብለው እንዲመሰክሩ አምጥቷቸዋል። ፍጻሜው ግን ደብረ ታቦር የመንሥተ ሰማያት ምሳሌ ናት። ሕጋውያንም ደናግልም እንዲወርሷት ለማጠየቅ ከሕጋውያን ሙሴን ከደናግል ኤልያስን አመጣ። ጴጥሮስ እመሰ ትፈቅድ ንንበር ዝየ ወንግበር ሠለስተ ማኅደረ አሐደ ለከ አሐደ ለሙሴ ወአሐደ ለኤልያስ ብትወድስ አንዱን ላንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ ሶስት ጎጆ ሠርተን በዚህ እንኑር አለው። መጽአ ደመና ብሩህ ወጸለሎሙ ይላል ። ይህን ሲናገር ብሩህ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው ወዲያውም ዝንቱ ውእቱ ዘአፈቅር ወሎቱ ስምዕዎ ቢሉ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው። እሱን ስሙት የሚል ድምፅ ከወደ ላይ ተሰምቷል ።እነ ጴጥሮስ ደንግጠው ወደቁ ተንሥኡ ወኢትፍርሁ ብሎ አንስቷቸዋል ። ከርእሰ ደብር ሲወርዱም ያዩትን የሰሙትን እስከ ትንሳኤው 133 ለማንም እንዳይናገሩ አዟቸዋል ።ማቴ 17 :3-9 ዘጠኙን በእግረ ደብር ትቶ ሶስቱን አስከትሎ መውጣቱ ስለምንድነው ቢሉ ከዘጠኙ ብርሃነ መለኮት ሊያይ የማይገባው ይሁዳ ነበርና ትቶትም ቢሄድ ለየኝ ባለ ነበርና አንድም ጴጥሮስ እሞታለሁ እነሣለሁ ቢለው ካንተ ይራቅ ብሎት ነበርና እሱን ስሙት የሚለውን እንዲሰማ አምጥቶታል። ዮሐንስና ያዕቆብንም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ በቀኝ በግራ መቀመጥን ሽተው ነበርና ነው። ያስ ቢሆን ከተራሮች ሁሉ ታቦርን ስለምን መረጠ ቢሎ ዳዊት ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ መዝ 87:12ብሎ ያን ለመፈጸም ነው።
ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበ ዕለት ስለ ኾነ ‹የብርሃን› ቡሄ ይባላል
ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፤ ወደ መፀው የሚገባበት፤ ወገግታ የሚታይበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚሸጋገርበት ወቅት በመኾኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናቱ ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮኹ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለዚህ በዓል የሚኾን ዳቦ ለመጋገር ስንዴያቸውን ሲያጥቡ፣ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ (ነሐሴ ፲፪ ቀን) ሕፃናት በየቤቱ እየዞሩ ‹‹ቡሄ ና በሉ፤ ቡሄ በሉ፡፡ ቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ፤ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ …›› እያሉ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሡ ይሰጧቸዋል፡፡ ሕፃናቱ ‹ቡሄ› የሚሉትም ዳቦውን ነው፡፡
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡ የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
መምህረ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ በደብረ ታቦር ምሥጢር መግለጡን በማስታዎስ የአብነት ተማሪዎች ከመምህራቸው ጋር በመኾን በዓለ ደብረ ታቦርን (ቡሄን) ያከብራሉ፤ ስሙን ይጠራሉ፡፡ የአብነት ተማሪዎች ‹‹ስለ ደብረ ታቦር›› እያሉ እኽል ከምእመናን በመለመንና ገንዘብ በማዋጣት ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምእመናን በመጋበዝና እርስበርስ በመገባበዝ፣ እንደዚሁም ቅኔ በማበርከት በዓለ ደብረ ታቦርን በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህም እስከ አሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሠራበት ነባር ትውፊት ነው፡፡
ነገር ግን በአንድ አካባቢዎች በተለይ በከተማ ዙሪያ በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) ሃይማኖታዊ ትውፊቱን የለቀቀ ይመስላል፡፡ ለዚህም ልጆች የሚጫወቱበት መዝሙር ግጥሙና ዜማው ዓለማዊ መልእክት የሚበዛበት መኾኑ፤ በወቅቱ ችቦ ከማብራት ይልቅ ርችት መተኮሱና በየመጠጥ ቤቱ እየሰከሩ መጮኹ፤ ወዘተ. የበዓሉን መንፈሳዊ ትውፊት ከሚያደበዝዙ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም በዚህ በዓል ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሚሽቀዳደሙ ነገር ግን የበዓሉን ታሪካዊ አመጣጥ የማያዉቁ ልጆችም ጥቂቶች አይደሉም፡፡
ስለዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የበዓለ ደብረ ታቦርን መንፈሳዊነት፣ የመዝሙሮቹን ያሬዳዊነትና አከባበሩን ከቤተ ክርስቲያን መምህራን በመጠየቅ ማስተማር፤ ልጆችም ከወላጆች ወይም ከመምህራን በመጠየቅ የበዓሉን አከባበር መረዳትና የዚህን በዓል መንፈሳዊ ትውፊት ሳይበረዝ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡ ‹‹ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና፤ የቡሄው ብርሃን ለእኛ በራልን …›› የሚለውንና ይህን የሚመስሉ መንፈሳውያን መዝሙራትን እየዘመሩ በየቤቱ በመዘዋወር የሚያገኙትን ዳቦና ገንዘብ ለነዳያንና ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ልጆችንም ማበረታታትና አርአያነታቸውን መከተል ይኖርብናል፡፡
መልካም በዓል ይኹንልን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ምንጭ፡-
መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መ/ር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ ገጽ ፫፻፲፭-፫፻፲፯፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ፤ ፳፻፯ ዓ.ም፣ ገጽ ፻

✨ ነሐሴ 10✨👉  በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ማኀበረ በኵር ወመጥራ ሰማዕት ወሐርስጥፎሮስ ወቢካቦስ ወዮሐንስ፡፡☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ👉 ዲያቆንዕብራው. 12፥22 :- ወ...
16/08/2024

✨ ነሐሴ 10✨
👉 በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ማኀበረ በኵር ወመጥራ ሰማዕት ወሐርስጥፎሮስ ወቢካቦስ ወዮሐንስ፡፡

☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ

👉 ዲያቆን
ዕብራው. 12፥22 :- ወአንትሙሰ በጻሐክሙ ኀበ ጽዮን፡፡

👉 ንፍቅ ዲያቆን
1ኛጴጥ. 1፥6፦ወባሕቱ ኀዳጠ ይእዜ ሀለወክሙ፡፡

👉 ንፍቅ ካህን ሓዋ.ሥራ 4፥31፦ ወእንዘ ይጼልዩ አድለቅለቀ ውእቱ መካን

👉 ምስባክ ዘቅዳሴ ፦ መዝ 73፥2፦
ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ።
ወአድኃንከ በትረ ርስትከ።
ደብረ ጽዮን ዘኃደርከ ውስቴታ።

ትርጒም፦
አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን አስብ።
የተቤዠሃትንም የርስትህን በትር።
በርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ።

👉 ወንጌል ዘቅዳሴ ሉቃስ.16፥9 ፦

ወአነሂ እብለክሙ ግበሩ ለክሙ አዕርክተ፡፡
፱. እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።
፲.*ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው።
፲፩. እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?
፲፪. በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ የእናንተን ማን ይሰጣችኋል?
፲፫. ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
፲፬. ገንዘብንም የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው ያፌዙበት ነበር።
፲፭. እንዲህም አላቸው። ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና።
፲፮. ሕግና ነቢያት እስከ ዮሐንስ ነበሩ፤ ከዚያ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ በኃይል ይገቡባታል።
፲፯. ነገር ግን ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ሊያልፍ ይቀላል።
፲፰. ሚስቱንም የሚፈታ ሁሉ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፥ ከባልዋም የተፈታችውን የሚያገባ ያመነዝራል።

👉 በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) (በግዕዝ ዜማ)

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አውደ ተዋሕዶ
👉 subscribe በማድረግ ይቀላቀላሉ https://www.youtube.com/channel/UCuJhXSWStN9ivcYZCKIOyGw?sub_confirmation=1

አውደ ተዋሕዶ ሚዲያን ይቀላቀላሉ
28/07/2024

አውደ ተዋሕዶ ሚዲያን ይቀላቀላሉ

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awde Tewahdo - አውደ ተዋሕዶ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share