እኔ ግን አላፍርም ያመንሁትን አዉቃለሁና።፪ኛ ጢሞ ፩፡፩፪

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • እኔ ግን አላፍርም ያመንሁትን አዉቃለሁና።፪ኛ ጢሞ ፩፡፩፪

እኔ ግን አላፍርም ያመንሁትን አዉቃለሁና።፪ኛ ጢሞ ፩፡፩፪ Dear eternal brothers and sisters, the
Peace, Grace and Love of Our Lord
Jesus Christ be with you. W

06/02/2024
10/07/2023

"ነፍሴ ኾይ! የምትድኝበትን እኔ እነግርሻለኹ። ከዚኽ ኹሉ ይልቅ ወደ ቅድስት ድንግል ጩኺ፥ እንዲኽም በይ! የብርሃን እናት ኾይ! በልጅሽ ፊት በደልኹ ኃጢአቴን አስተስርይልኝ፡፡"

" ስቅለት "በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው። ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ...
14/04/2023

" ስቅለት "

በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።

ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦

✝ ዓርብ ጠዋት

ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

✝ በ3 ሰዓት

ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።

✝ በ6 ሰዓት

ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።

✝ በ9 ሰዓት

በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።

✝ 11 ሰዓት

ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።

09/03/2023

ጠራጊውን አየኸው?!

ድምጽ አልባ ስብከት መድረክ የሌለው አገልግሎት ሰው ያልከበበው ጽድቅ አቧራ ያልናቀ ጸጋ ማዕረግ የሌለው ግብር መንገድ ጠራጊ እምነት አባሽ ቤ/ክ መጥረግ::
በታላቁ ንግሥ ላይ ዘማሪውን ሰባኪውን ጓግተው ያዩታል ጠራጊውን ግን አየኸው?! ደሞዝ የሌለው መሬት መሬት እያዩ ከሞት ፍጻሜ ከትንሣኤ ተስፋ ጋር እየተመኙ ሚያገለግሉበት አንገት ደፍተው የሚያገለግሉበትን ጠራጊውን አየኸው?!

ትንንሽ መሳይ ትልልቅ አገልግሎት ጣዕም አላቸው
ሳይታዩ መስበክ ሳይሰሙ መዘመር

/ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ ታህሳስ 13

የተወገዙት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ ይቅርታ ጠይቀዋል ቋንቋ ብሄር ከሀይማኖት በታች ነው ሁሉም በአፍ መፍቻው ቋንቋው እስካሁንም ወደፊትም ይገለገላል
15/02/2023

የተወገዙት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ ይቅርታ ጠይቀዋል
ቋንቋ ብሄር ከሀይማኖት በታች ነው ሁሉም በአፍ መፍቻው ቋንቋው እስካሁንም ወደፊትም ይገለገላል

" በኢትዮጵያ በመከራ የሚሰቃዩ ወገኖቻችን  የሚያሳዩት የመንፈስ ጥንካሬ የክርስትና እምነት በኢትዮጵያ ምድር ህያው እና ጠንካራ ለመሆኑ ማረጋገጫ ሆኖ ያገለግላል::"ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል...
12/02/2023

" በኢትዮጵያ በመከራ የሚሰቃዩ ወገኖቻችን የሚያሳዩት የመንፈስ ጥንካሬ የክርስትና እምነት በኢትዮጵያ ምድር ህያው እና ጠንካራ ለመሆኑ ማረጋገጫ ሆኖ ያገለግላል::"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ

05/02/2023

የካቲት 5 ሰልፍ የጠራው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ አይደለም:: ሰልፉን የጠራው ዛሬ ጠዋት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ክብር በግፍ የተሠዋው ሰማዕት ደም ድምፅ ነው::

ዛሬ ቤታቸው ሳይገቡ እህል ሳይቀምሱ ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ውለው በስናይፐር የተመቱ ምእመናን ደም እኔና አንተ ክርስትና ለተነሣንባት ኃጢአታችንን በንስሓ ለምናራግፍባት የምንቆርብባት የምንዳርባት ስንታመም የምንጠመቅባትና ስንሞት የምንቀበርባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳናጣ ብለው ነው::

ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያልሆነችው የለም:: ትምህርት ሚኒስቴር ሆና ከድንቁርና ጤና ሚኒስቴር ሆና ከበሽታ መከላከያ ሚኒስቴር ሆና ከቅኝ ግዛት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሆና ከተራነት ኢትዮጵያን የታደገች ቤተ ክርስቲያን ናት::

ውለታዋ ተረስቶ የተሳዳቢዎች አፍ መፍቻ የሐሰተኞች ትንቢት መለማመጃ ሆና በንዋየ ቅድሳትዋ ተቀልዶ በከበሮዋ ተጨፍሮ ዕረፍት እንድታጣ ሆና መቆየትዋ ሳያንስ አሁን ደግሞ በግልፅ ተዘምቶባታል::

ቅዱስ ሲኖዶስ በቀጣዮቹ የምህላ ቀናት ያቀረበው ቅድመ ሁኔታ ካልተፈጸመ እንደሚካሔድ ያወጀው የጾም አዋጅና የካቲት 5 የጠራው ሰልፍ አባቶቻችን አባት ሆነው የተገኙበት ነው:: ልጆች ሆነን መገኘት የእኔና አንተ ፋንታ ነው:: ሕጋዊነትዋን ይዛ በሰላማዊ መንገድ የጠራችው ተቃውሞ ነውና የተሻለው መንገድም ይኼ ነው:: ከዚህ ቀደም ተጀምሮ የቀረ ሰልፍ ምን ዋጋ እንዳስከፈለን እናውቀዋለን:: አሁን በምንም ወደ ኋላ ማለት የለብንም:: በጎበዝ አለቃ መመራት በተባራሪ ወሬ መነዳት ትተን ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን እንቁም:: ጉዳዩ የሐዋርያዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ጉዳይ ሆኖ ሳለ የዘርና የቋንቋ ጉዳይ ለማድረግ የሚጥሩ ሰዎችን ጆሮ ባለ መስጠት በማያምኑባት ቤተ ክርስቲያን ውድቀትዋን ተመኝተው የሚሳደቡ እነ "ብጥብጥ አማረኝ"ን በቻልነው ሁሉ ብሎክ በማድረግ ጆሮአችንን ለቤተ ክርስቲያን ብቻ እንሥጥ::

ድርድር ሽምግልና ወዘተ የሚሉ የማዘናጊያ ሃሳቦች ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም:: ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች እጃችሁን አስገቡ ብትባሉም እንኳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አክብራችሁ እጃችሁን ሰብስቡ:: መነጋገር ካለበት አካል ጋር ሊነጋገር መብት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ሲሆን ከሰልፉ በኋላ የሚለንን እንሰማለን:: የእኛ ድርሻ ቤተ ክርስቲያን ያለችንን ብቻ ማድረግ ነው::





ይህን ሲያይ የማያነባ ካለ መቼስ 😢አቤቱ ማረን!  #አንድ ሲኖዶስ  #አንድ ፓትርያርክ
05/02/2023

ይህን ሲያይ የማያነባ ካለ መቼስ 😢
አቤቱ ማረን!

#አንድ ሲኖዶስ
#አንድ ፓትርያርክ

በወሊሶው ህገ ወጥ ቡድን ተሹመው ለምዕራብ አርሲ ሀገረስብከት የተመደቡት መኖክሴ 225,000 ብር ከዘጸአት አፓስተሊክ ቸርች ከሹመት ማግስት ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል***በቀደመው ስማቸው አባ ገ...
02/02/2023

በወሊሶው ህገ ወጥ ቡድን ተሹመው ለምዕራብ አርሲ ሀገረስብከት የተመደቡት መኖክሴ 225,000 ብር ከዘጸአት አፓስተሊክ ቸርች ከሹመት ማግስት ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል
***

በቀደመው ስማቸው አባ ገ/እግዚአብሔር ታደለ ተብለው ይጠሩ የነበረው በአባ ሳዊሮስ(የቀደመ ስማቸው) የብጽኡ አቡነ ጳውሎስ ተብለው የተሾሙት ግለሰብ

ጥር 14 በህገወጥ መልኩ ከተሾሙ በኃላ ዘጸአት አፓስተሊክ ቸርች ከሚባል የፕሮቴስታንት ተቋም 225,000 ብር ማበረታቻ ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል።

ይህኝ ግለሰብ ለምዕራብ አርሲ ሀገረስብከት(ሻሸመኔ) ሊቀጳጳስ ተብለው የተመደቡ ሲሆን ይህን ግለሰብ ሻሸመኔ ላይ ለማንገስ ከትላንት ጀምሮ የሀገረ ስብከት የአስተዳደር ገባኤ አባላት እየታሰሩ እንደሆነ ታውቃል።

እንግዲህ በኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎት ለምድ ስም የሌላ ቤተ እምነት አስተሳሰብ እና ተልዕኮ ለመፈጸም የሚመጣ ግለሰብን በመቀበል ቤተክርስቲያንን አይን አንውጋ!!!

📍📍 ሰበር📍📍ከደቂቃዎች በፊት የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ጉባኤ ከዚህ በታች ያሉት ውሳኔ አስቀምጧል።ኤጲስ ቆጶሳት ነን ብለው በተገኙ ፳፮ መኖከሳት ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አ...
24/01/2023

📍📍 ሰበር📍📍
ከደቂቃዎች በፊት የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ጉባኤ ከዚህ በታች ያሉት ውሳኔ አስቀምጧል።
ኤጲስ ቆጶሳት ነን ብለው በተገኙ ፳፮ መኖከሳት ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላለፈ
***
የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት የአስተዳደር ጉባኤ ዛሬ ማለዳ ላይ በዋለው ስብስባ ትላንት ጥር 14 በወሊሶ ከተማ በተደረገው ህገ ወጥ ሲመት
እራሳቸውን ኤጴስ ቆጶሳት ብለው የገለጡ ከተለያዩ አድባራት እና ገዳማት የተውጣጡ ፳፮ መኖኮሳት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላልፏል።
በእዚህ መሰረት
፩ኛ .ሁሉም መኖከሳት ከደምወዝ ታግደው እንዲቆዩ
**
፪ኛ. የሚያንቀሳቅሱት የገዳማት እና አድባራት ሂሳብ ካለ እንዲታገዱ
**
፫ኛ. ከእዚህ በፊት ወደሚያገለግሉት የአገልግሎት መዋቅር እንዳይመለሱ
**
፬ኛ.በየትኛው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት እንዳይገኙ ውሳኔ አስተላልፏል።
ፍትሕ መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣይ በሚያደርገው ስብሰባ ይወስናል ተብሎ ይጠብቃል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እኔ ግን አላፍርም ያመንሁትን አዉቃለሁና።፪ኛ ጢሞ ፩፡፩፪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to እኔ ግን አላፍርም ያመንሁትን አዉቃለሁና።፪ኛ ጢሞ ፩፡፩፪:

Share