Abenezer Teklu Diyakon

Abenezer Teklu  Diyakon Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abenezer Teklu Diyakon, Convent and monastery, addis abeba, Addis Ababa.

“በአርባምንጭ ተሐድሶ ሙሉ ለሙሉ መቀጠል አይችልም” (“ዲያቆን” አበባው ምስክር)የተሐድሶ ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር እንጂ ሰውም ኾነ አንዳች ተቋም አይደለም። እግዚአብሔር አምላክ ይህን የሚያ...
25/08/2026

“በአርባምንጭ ተሐድሶ ሙሉ ለሙሉ መቀጠል አይችልም” (“ዲያቆን” አበባው ምስክር)
የተሐድሶ ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር እንጂ ሰውም ኾነ አንዳች ተቋም አይደለም። እግዚአብሔር አምላክ ይህን የሚያደርገው ደግሞ በምሕረቱ ብዛት ነው። በባቢሎን ምርኰ ሳሉ እግዚአብሔር በተሐድሶ እንዴት ያለ ጕብኝት ለእስራኤል እንዳደረገላቸው፣ ነቢይና ካህን የነበረው ዕዝራ ሲናገር፣ “ … አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም የሕይወት መታደስን ይሰጠን ዘንድ፥ የአምላካችንንም ቤት እንሠራ ዘንድ፥ የተፈታውንም እንጠግን ዘንድ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ቅጥር ይደረግልን ዘንድ …” (ዕዝ. 9፥9) በማለት፣ የሕይወትን መታደስ ወይም የሕይወት ተሐድሶ የሚሰጠው ራሱ እዚአብሔር ብቻ እንደ ኾነ ገልጦአል።
እግዚአብሔር እንደ ወደደ ተሐድሶን ለሕዝቡ ይሰጣል፤ የተሐድሶ ጥሪ ደግሞ ለየትኛውም ቤተ ክርስቲያን የሚኾን መለኮታዊ ዐሳብ ነው። በእግዚአብሔር ቃል መሠረት የማትኖር የትኛዋም ቤተ ክርስቲያን አካሄዷንና ትምህርቷን በእግዚአብሔር ቃል የማረም ጥሪ ሲደርሳት፣ ይህን ጥሪ የመታደስ ጥሪ ልንለው እንችላለን። ይህ ጥሪ ደግሞ የእግዚብሔር ሥራ እንጂ፣ የሰው ሥራ ሊኾን አይችልም። እናም የተሐድሶ ባለቤቱ እግዚአብሔር ስለኾነ፣ ተሐድሶን እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሰጠው መልካም ዕድል አድርገን እንመለከታለን። እኛም እንኳ ሐዳስያን ነን ስንል፣ በፈቃዳችን ለእግዚአብሔር ዐሳብ መገዛታችንን ለማሳየት እንጂ የተሐድሶ ጀማሪያን ነን ለማለት አይደለም። ደግሜ እላለሁ፣ የተሐድሶ ባለቤት እግዚአብሔር ብቻ ነው።
እናም ይን የተሐድሶ ጥሪ ዕድሉን ለማባከንም ኾነ እኛ ባለቤቶቹ መስለን ለመታየት ምንም ዓይነት ጥረት አናደርግም። ለእግዚአብሔር ክብርና ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ቤተ ክርስቲያን፣ ወደ እግዚአብሔር ቃል በእውነትና በመንፈስ ወደሚደረግ አምልኮ እንድትመለስ ዘወትር በጸሎትና በእምነት ኾነን ዐሳባችን ዘወትር ባለመታከት እናቀርባለን። “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የኾነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትኖ ለማወቅ በመታደስ የተለወጠ ልብና ይህን ዓለም አለመምሰል” ያስፈልጋልና፤ (ሮሜ 12፥2)።
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግን በተደጋጋሚ ይህን የከበረና የእግዚአብሔር ሥራ የኾነውን ተሐድሶ፣ ስትቃወምና ላለመቀበልም ሐዳስያንን ስታሳድድ መመልከት እንግዳ ነገር አይደለም። በተለይ ደግሞ በአርባምንጭ ከተማ ከዓመታት በፊት ይህን የተሐድሶ ዐሳብ በመቃወምና በአገልግሎት ላይ የነበሩትን ወንድሞችና እህቶች በመደብደብ፣ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ ንብረት በመዝረፍና ሰዎችን በማሳሰር “ተሐድሶን ላለመቀበል” ግልጥ የኾነ ተቃውሞ አሳይታለች፤ ከዚህም ባለፈ በግልጥ ማኅበረ ቅዱሳን በቲቪው እንደ ሠራው “ዘገባ”፣ “ተሐድሶ ከቶውንም በአርባምንጭ ከተማ ዳግም የመቀጠል አንዳች ተስፋ እንደሌለው” በመዘበት ሲናገር ተደምጦአል።
እውነታው ግን ተሐድሶ አስቀድመን እንደ ተናገርን የእግዚአብሔር ዐሳብ እንጂ የሰው ስላይደለ፣ ሰዎችም ኾኑ ማናቸውም የተደራጀ ተቋም ሊያግደው አይችልም። ለዚህም ነው ባለፉት ሳምንታት ከአርባ ምንጭ ከተማ አልፎ በዙሪያቸው ባሉ ከተሞችና ወረዳዎች ጭምር የተደረጉት “የኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ” ጉባኤያት ተስፋፍተው ለብዙዎች የወንጌል ብርሃን ማየት ምክንያት ኾኖ የምናገኘው።
ከጥንት ጀምሮ ወንጌልን በግልጥ የሚሰብኩ የወንጌል ባላደራ ቅዱሳን፣ መከራን መቀበል የሚጀምሩት ከገዛ ወገናቸው ወይም ከሚያቀውቋቸው ዘመዶቻቸው ነው፤ ይህ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተናገረው፣ ወንጌል ልዩነት በማድረግ የምትታወቅ መኾኑን ትልቅ ማሳያ ነው። በአርባ ምንጭ የሚገኙ የማኅበረ አኀው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አማኞችና የመንግሥቱ ባለሟሎችም በዚህ በረከት ስለ ተጐበኛችሁ፤ አኹንም እየተጐበኛችሁ ስለኾነ ስለ እናንተ እጅግ ደስ ብሎናል፤ ጌታችን ኢየሱስ አብዝቶ ይባርካችሁ፤ አሜን።
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመጥፋት ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን።” (ኤፌ. 6፥24)።
My telegram link - https://t.me/ebenezertek
My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2026/08/blog-post_25.html

24/08/2026

"... ጥበብ ግን መድኃኒታችን ነው፤ በሥጋው መቆረስ የተቤዠን፤ በደሙ መፍሰስ የዋጀን፤ ለመንግሥቱም የመረጠን ለዘለዓለሙ ..." አሜን።

(ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)

24/08/2026

በምክክር ኮሚሽኑ ኢትዮጵያን ከድህነት ያላቅቃሉ ከተባሉ ውሳኔዎች አንዱ፣ ከዓመተ ምሕረት ወደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በሚል መቀየሩ ነው¡ [ያልታደልን ሕዝቦች]

22/08/2026

ብዙ ኦርቶዶክሳውያን፣ "የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤" የሚለውን ቃል ለድንግል ማርያም ቢጠቅሱም፣ በዐውዱ ውስጥ ያለውን፣ "በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና" የሚለውን ቃል በአብሮነት መጥቀስ አይወዱም። ምክንያቱም ክፍሉ ለድንግል ማርያም እንደማይናገር ይገልጥባቸዋል አልያ ድንግል ማርያም መች በቁጣ እንደ ተቀሰፈች ማስረዳት አይችሉምና።

የቅዱስ ቃሉና የቃሉ ዐውድ በትክክል ይከበር።

https://t.me/ebenezertek

21/08/2026

አንድ "ሰባኪ" 'የእውነት ቃል አገልግሎት' ቡድንን ተከታይ መኾኑ ከሚታወቅባቸው ዐይነተኛ መንገዶች አንዱ፣ ራሱን ኦርቶዶክስም፣ ተሐድሶም፣ ጴንጤም ነኝ ብሎ መግለጥ አይፈልግም። 'የእውነት ቃል አገልግሎት' የተባሉት እንኳ፣ ከመንግሥት ፈቃድ ለማግኘት ሲባል እንጂ ፈልገውት አይመስለኝም።

አርባምንጭ ከተማ ላይ፣ አኀው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአከባቢው ያሉ ልጆችዋን ሰብስባ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዴት ማጥናት እንዳለባቸው፣ ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ ምን እንደኾነ፣ ስለ አገልጋይ፣...
20/08/2026

አርባምንጭ ከተማ ላይ፣ አኀው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአከባቢው ያሉ ልጆችዋን ሰብስባ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዴት ማጥናት እንዳለባቸው፣ ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ ምን እንደኾነ፣ ስለ አገልጋይ፣ ስለ ቤተክርስቲያን አስተዳደርና ስለ ጌታ ተልእኮ እያሰለጠነች ትገኛለች።

እኛ የታሪካዊው ኦርቶዶክስ አካልና ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊ አማንያን ነን!

የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek

19/08/2026

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን "ጥንታዊነት" ባልክድም፣ የሰ'ነበተ ነገር ኹሉ ግን ቅዱስ ነው ብዬ አላምንም።

19/08/2026

"... ፍኖት ለኀበ አቡሁ አንቀፅ ዘመንገለ ወላዲሁ ዉእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ።"

"... ወደ አባቱ የሚወስድ መንገድ ወደ ወለደውም የሚያስገባ በር እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"

(ሰአታት ዘሌሊት)

19/08/2026

" ... በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋራ ሰላም አለን።" (ሮሜ 5፥1) አዎን አለን።

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Telephone

+251920893099

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abenezer Teklu Diyakon posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share