ኦርቶዶክስ እለታዊ/Ethiopian Orthodox Daily

ኦርቶዶክስ እለታዊ/Ethiopian Orthodox Daily በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ የሚታሰብ ቅዱሳን፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት እና ሌሎች መንፈሳዊ ነገሮች ይቀርቡበታል https://t.me/ethiopianorthodoxs on Telegram

29/09/2025

"ስጋህ አንተ እንጂ ያንተ አይደለም" ከኤፌሶን ወንዝ መፅሐፍ

26/09/2025

✞መስቀል ሀይላችን ነው✞

በጊደሮች ደም ፤ በሚሰዋ ጠቦት
በቅዱሳን እንባ ፤ በነቢያት ጸሎት
በዳዊትም ወንጭፍ ፤ ያልተረታውን ሞት።
አንዱ እግዚአብሔር ወልድ ፤ ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ማርያም ፤ ያለ ህማም ተወልዶ።
ስጋውን ቆርሶ ፤ ደሙን አፍሶበት
የሀጢያትን ችንካር ፤ ከእኛ ያራቀበት።
ሰይጣንን አጥሞዶ ፤ የያዘበት መረብ
ነብሳትን ከሲኦል ፤ ያዳነበት መርከብ
መስቀል ዓርማችን ነው ፤ የድላችን ማህተብ።
ለሚጠፉት አይሁድ ፤ ነቅዞ የሚሰበር
ሲያዩት ሞኝነት ነው ፤ የመስቀሉ ነገር።
ለእኛ ለምንድን ግን ፤ ዋጋ ተከፍሎበት
የአምስት ሺ ዘመን ፤ ጥል የፈረሰበት
የእዳ ደብዳቤያችን ፤ የተቀደደበት
የህይወት እንጀራ ፤ የተቆረሰበት
የህይወት መጠጥ ፤ የፈለቀበት
የእግዚአብሔር ፍቅር ፤ የተገለጠበት
የተሰቀለውን ፤ የምናስብበት
እናቱን በአደራ ፤ የተቀበልንበት
የዳቢሎስን መርዝ ፤ የምናረክስበት
መስቀል ሀይላችን ነው ፤ የምንመካበት ።

✝️✝️✝️እንኩዋን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝️✝️✝️

https://youtu.be/Qw7jDjuppY4?si=yacZ8HaOqsJIv1q3
08/08/2025

https://youtu.be/Qw7jDjuppY4?si=yacZ8HaOqsJIv1q3

“አቤቱ ድውይ ነኝና ፈውሰኝ” መዝ ፮፥፪በሚል መሪ ቃል ፈውስ መንፈሳዊ ዘጣና ቅዱስ ቂርቆስ በአይነቱ ልዩ የሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ተነስተናል። እርሶም ለዚህ ፕሮጀክት ከታ....

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ:-አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ:: የጌታችን የ...
07/07/2025

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ::

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው የሐዲስ ኪዳን ደግሞ የመጀመሪያው ነቢይ ነው።

ስለ ወላጆቹም ስለ ካህኑ ዘካርያስና ስለ ቅድስት ኤልሳቤጥ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ብሎ ተመስክሮላቸዋል።

"በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበር፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስሟም ኤልሳቤጥ ነበረ። ሁለቱም በጌታ ትዕዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፉ እየሔዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።" ሉቃስ 1፡ 5-6።

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው::

ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው::

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች::

ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለ እርሷ ደስ አላቸው::

በ8ኛ ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት::

እናቱ ግን ዮሐንስ ይባል አለች::

ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት::

አባቱንም ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት::

እሱም ብራና ላይ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ:: ሁሉም አደነቁ::

ያን ጊዜ የአባቱ አንደበት ተፈታ እግዚአብሔርንም አመሰገነ::

ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተነገረ::

ሄሮድስ ሕፃናትን ሊገድል አዋጅ ባወጀ ጊዜ አባቱ ወደ ቤተ መቅደስ ወስዶ ደበቀው።

በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው::

ሄሮድስ የላካቸው ጭፍሮች ዮሐንስን ባጡት ጊዜ ዘካርያስን ገደሉት::

ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ::

የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ነው::

ሚልኪያስም በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ ብሎ ተናግሮለታል::

በአማላጅነቱ ተማምነን መታሰቢያውን እናድርግ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን::

የተባረከ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳዊያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን::

እንሆ ሰኔ ወር በሰላም ተፈጸመ::

በዚህ በሰኔ ወር በእምነታችን ታምነን ከኃጢአታችን ነፅተን በንሰሐ ሳሙና ታጥበን በቅዱሳኑ አማላጅነት ተማፅነን ወሩን ተጠቅመንበታል?

ሁሉ ነገራችን የሚያውቅ በቸርነቱ ለዚህ ቀን አድርሶናል::

አልረፈደም በዚህች በተሰጠች ቀሪ ዘመን መልካም እንድንሰራባት ከሃይማኖታችን በአፋ ከምታስወጣን ኃጢአት የምንርቅበት እንዲሆንልን እንግዲህ እንንቃ አምላከ ተክለ ሃይማኖት ቸርነቱን ያብዛልን የሁላችንም መጨረሻችን ያሳምርልን ለዘላለሙ አሜን::
🇪🇹⛪️⛪️

ግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች:: እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት:: ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ...
09/05/2025

ግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች::

እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት::

ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ::

ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መባዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበር::

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኀዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር::

ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ::

ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው::

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት:: ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት::

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርግ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች::

ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ማለት ነው::

ደግሞም ሀብትና ሥጦታ ማለት ነው:: በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት:: ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነት ያገኘንባት::

እንግዲህ እዚህ ጋር ልብ ይሏል::

በዚህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ የኛ ልጅነት የኛ የመዳንችንን መንገድ እግዚአብሔር እንዴት እንዳከናወነልን እንረዳለን::

እግዚአብሔር ሰውን ሲያድን ማዳኑን የፈጸመው እጅግ በጣም ልዩ በሆነ ሁኔታ ነው::

ይህም ገናናነቱን ከእኛ ታናሽነት ጋር አዋሕዶ፤ ከሃሊነቱን ከእኛ ነፃነት ጋር አስማምቶ በመሆኑ ነው::

ይህ ማለት ምን ማለት ነው?

ሊያድነን ሲነሣ እንዲሁ በማንኛውም መንገድ ቢያድነን ታላቅ ቸርነትና ደግነት ሆኖ ሳለ እርሱ ግን ከዚያም በላይ በሆነ መንገድ እኛን አሳትፎ ፈቃዳችንን ተቀበሎ አስፈቅዶ አስወድዶ ያዳነን::

እርሱ ሁሉን ማድረግ ስለሚችል ብቻ ያለ እኛ ፈቃድ ሱታፌ እንዲሁ አፍአዊ በሆነ ሁኔታ እና ያለ ፈቃዳቸው አላዳነንም::

ባሕርያችንን ሲዋሐድም ያለ እኛው ፈቃድና ሱታፌ አላደረገውም:: የሚጠቅመንን የመዳናችንን ነገር ሲፈጽም እኛን አስወድዶና አሳትፎ ነው::

አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ሲወርድ መከራ ተቀብሎ እኛን የሚያድንበትን መሣሪያ የወሰደው ከእኛው መዳኑ ከሚያስፈልገንና ከሚደረግልን ከሰዎች ነበር::

ይህ እንዲሆን ደግሞ ሰዎችን የሚወክልና እኛን ሁሉ ወክሎ የሚሳተፍ አንድ ሰው ያስፈልግ ነበር::

በዚህም ያ የሚያስፈልግ አንድ ሰው በዛሬዋ ቀን የተወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: በእወነት ምስጋና ይድረሳትና።

ከዚህ በኋላ ነው እንግዲ የነቢያት ትንቢታቸው ከተፈጻሚነት የደረሰው:: ታዲያ የዛሬውን በዓል ስናከብርና ተድላ ደስታ ስናደርግ ከመንፈሳዊነት ሳንወጣ ልንጠነቀቅ ይገባል::

ይህን በዓል ስናከብርም ሌሊት በቤተ ክርስቲያን በማኅሌት÷ በዝማሬ÷ ጠዋት በኪዳንና በቅዳሴ÷ ታምሯን በመስማት÷ ወንግል በመማር ነው:: ክርስቲያኖች ከዚህ የወጣ ባዓል የላቸውም::

ብዙዎች የእኛን መንፈሳዊ በዓል ይዘው የራሳቸውንና የቤታቸውን ጣጣ ይዘውና አስታከው መንፈሳዊ በዓላ ላይ ለጥፈው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ከመንፈሳዊነታችን ጋርም የሚፃረር ነገር ሲፈጽሙ ይታያል ይህ አግባብ አይደለም::

የበግና የፍየል ከለር እየመረጡ÷ ቄጣና ፈንዲሻ እየረጩ÷ የቡና አተላ እየገለበጡ የሚከበር መንፈሳዊ በዓል የለም:: አስፀያፊም የተወገዘም ግብር ነው።

እስኪ አንድ በዓለም ያለ ሰው ልደቱን ሲያከብር ወይ ሲደግስ የበግ ከለር መርጦ የሚያርድ ማን አለ? ወይ ቡና እያንቃረረ ቂጣና ፈንዲሻ በየጥጋ ጥጉ የሚጥል ማን አለ? ታዲያ እንደዚህ ያለን ኮተታ ኮተት ከየት የመጣ ነው::

የኛ አይደለም እንዲህ ያለ ነገር እንዲህ የሚያደርጉ ካሉ ፈጥነው ንሰሐ ሊገቡና ከክርስቲያኖች ማኅበር ሊገቡ ይገባል::

የእመቤታችንን የልደቷን በዓል ግን የምናከብረው በዝማሬ÷ በማኅሌት÷ በኪዳን÷ በቅዳሴ ጊዜ ሥጋወ ደሙ እየተቀበልን÷ ወንጌልን እየተማርን÷ የተራበ እያበላንና የታረዘ እያለበስን እየዘመርን ነው::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

በሰሙነ ህማማት ወቅት የምንሰማቸው እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸውበግብረ ሕማማት ውስጥ በግዕዝም ሆነ በኋላ በአማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የእብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ። የእነዚህ ...
14/04/2025

በሰሙነ ህማማት ወቅት የምንሰማቸው እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸው

በግብረ ሕማማት ውስጥ በግዕዝም ሆነ በኋላ በአማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የእብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ። የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፦

#ኪራላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ
< ኪርዬ ኤሌይሶን> ነው። #ኪሪያ ማለት እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፤ማረን" ማለት ነው።
#እብኖዲ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው። "እብኖዲ ናይናን" ሲልም " አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።
#ታኦስ ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣አምላክ" ማለት ነው።
#ማስያስ ፦ የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሲህ" ማለት ነው።
#ትስቡጣ ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "ደግ ገዥ" ማለት ነው።
፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ- አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነው።
፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግስትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነው።
፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግስትከ -የሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን " ማለት ነው።

05/04/2025



"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡”

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡››

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ››

‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡››

Ethiopian Orthodoxs Daily:አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጋቢት አምስት በዚህች ቀን ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማ...
14/03/2025

Ethiopian Orthodoxs Daily:
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጋቢት አምስት በዚህች ቀን ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቱ ቀን መታሰቢያ ነው::

እንግዲህ የዚህን ብፁዕ ወቅዱስ አባታችንን ገድል ለበረከት እንሆ በጥቂቱ የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆንም በትዕግሥ እናነብ ዘንድ እጋብዛችኋለሁ::

የባሕታዊያን አለቃ የሚሆን የታላቁ ጻድቅ የአባታችን የገብረ መንፈስ ቅዱስ የአባታቸው ስም ስምኦን የእናታቸው ስም አቅሌስያ ይባላሉ::

ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው የሚፋቀሩ በጾምና በጸሎት ተወስነው የሚኖሩ እንደ አብርሃምና ሣራ እንግዳዎችን የሚቀበሉ ደጋጎች ነበሩ::

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በብዙ ጸሎት የተገኙ የጸሎት ፍሬ ናቸው:: ጌታ በቅዱስ ወንጌሉ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ነው ብሎ እንደተናገረው::

ይህም ቅዱስ አባት በተወለደበት ቀን ድንቅ የሆነ ሥራን ሠራ ተነሥቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኽኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን እያለ ለሥላሴ ሰግዷልና ምስጋና አቅርቦልና::

እንደተወለዱ እንዲያመሰግኑትና ቃሉን እንዲናገሩ ያደረገ ፈጣሪ ይህንን ምስጋና እንደምግብ ቆጠረላቸው::

ሕፃኑም ሦስት ዓመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልክተኛ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ እቅፍ አንሥቶ ብዙ ባሕታውያን ወዳሉበት ገዳም ወስዶ በደጅ አኖረው ወደ አበምኔቱ ወደ አባ ዘመደ ብርሃንም ገብቶ ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ነገረው::

በዚያን ጊዜም ነገሩ እውነት እንደሆነ ይረዳ ዘንድ አባ ዘመደ ብርሃን ተነሥቶ ወደ ደጅ ወጣ:: መልአኩም እንደ ነገረው ሕፃኑ ከበር ተቀምጦ ፈገግታን ተመልቶ አገኘው:: እጅግም ደስ ብሎት ለእግዚአብሔር ሰገደ ሕፃኑንም አንሥቶ ሳመው ታቅፎም ወደ በአቱ አስገባው::

በፍቅር በሥነ ሥርዓት አሳደገው:: የዳዊትን መዝሙርና ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸውን መጻሕፍት ሁሉ ብሉይንና ሐዲስን አስተማረው::

ከዚያ በኋላም ክህነት ይሰጠው ዘንድ ስሙ አብርሃም ወደሚባል ጳጳስ ወሰደው ጳጳሱም በአየው ጊዜ ደስ አለው:: የዲቁና ማዕረግንም ሾመው እንደ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስም ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ::

ከጥቂት ቀኖች በኋላም በጌታችን ትእዛዝ ቅስና ተቀበለ:: በጾም በጸሎት በስግደት በብዙ ትጋትም እየተገደለ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ኖረ::

በበረሀም ብዙ ዘመናትን ሲኖር ነፍሱን ነፍሴ ሆይ እወቂ በእግዚአብሔር ፊት ትቆሚ ዘንድ እንዳለሽ እንግዲህስ ጽኚ በርቺ ታገሺ ይላት ነበር ቆዳው ከአጥንቱ እስኪጣበቅ ያለ መብልና ያለ መጠጥ በእንዲህ ያለ ግብር በገድል ተጠምዶ ኖረ:: ከዕፅዋት ፍሬዎች ወይም ከእንጨት ሥሮች አልተመገበምና ለሥጋውም የሚጠቅም ምንም ምን ምክንያት አልፈለገም::

ከብዙ ዘመናት በኋላም ለአባታችን ለገብረ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ አለው ከእንግዲህ በዓለም ካሉ ሰዎች ከመነኰሳት ከካህናት ከሕዝባዊያን ከምእመናን እንዳያውቁክ አደርግሃለሁ:: እንዳንተ ካሉ በቀር አንተ ራስህ ብትፈቅድ እንጂ መላእክትም ይጎበኙሃል::

የብርሃን ሠረገላም ይሁንልህ መድረስ ወደምትሻበት ሁሉ ብረር እኔንም ማየትን በፈለግህ ጊዜ ከአባቴና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሦስትነቴ ታየኛለህ::

አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሒድ በዚያም ከደይን የምታወጣቸው ነፍሳት አሉህ አለው::

ከዚህም በኋላ ስልሳ አንበሶች ስልሳ ነብሮች በፊት በኋላ አጅበውት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ተጓዝ::

የእግዚአብሔር መልክተኛ ቅዱስ ገብርኤልም ከአንበሶችና ከነብሮች ጋራ በነፋስ ሠረገላ አሳፍሮ ይመራው ነበር:: ወደ ምድረ ከብድም አደረሰው ከዚያም ወደ ልዩ ተራራ ወደ ደብረ ዝቋላ ወሰደው::

አባታችንም በባሕሩ ቁሞ ምሥራቁን ምዕራቡን ሰሜኑን ደቡቡን አራቱን ማዕዘን ተመለከተ:: የኢትዮጵያ ሰዎች የሚሠሩትን ኃጢአታቸውን በዐይኖቹ ፊት የተገለጠ ሁኖ አየ::

በራሱም ተዘቅዝቆ ተወርውሮ ወደ ባሕሩ ውስጥ ገባ እሊህን የእጅህ ፍጥረቶች የሆኑትን ካልማርካቸው ከእዚህ ባሕር እንዳልወጣ በእግሮቼም እንዳልቆም በሕያው ስምህ እምላለሁ እያለ ማለ እንዲሁም ሁኖ አርባ ሌሊት ኖረ::

ስምህን የጠራውን መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ የሚል ቃል በመልአክ አማካይነት ወደ አባታችን መጣ::

አባታችንም መልአኩን መላውን የኢትዮጵያን ሰው ካልማረልኝ ከዚህ ባሕር አልወጣም አለው መልአኩም ከአጠገቡ ሔደ::

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም በዚያ ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ኖረ ሥጋው ሁሉ አለቀ ደሙም በባሕሩ ውስጥ ፈሰሰ አጥንቶቹም እንደበረዶ ነጭ ሁነው ታዩ::

አጋንንትም ከአራቱ ማእዘን በየቀኑ ሰባት መቶ ሽህ ሦስት መቶ ሽህ እየሆኑ በመምጣት በቀስታቸው ይነድፉትል እስከ መቶ ዓመትም አጥንቶቹን በሻፎ ድንጋይ ይፍቁታል ይህን ሁሉ መከራ በትዕግሥት ሲቀበል ኖረ::

ከዚህ በኋላ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ ከባሕር ዳር ቆመ:: አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስንም መላውን የኢትዮጵያ ሰው ምሬልሃለሁ ተነሥተህ ውጣ አለው ያን ጊዜም ወጣ አጥንቶቹም እንደ ወንፊት ቀዳዳ የተበሳሱ ሆነው ተገኙ ጌታም ዳሠሠውና ጤነኛ አደረገው ወደ ምድረ ከብድም ሰደደው::

ከዚያም ወደ ላይ ወጥቶ ከፀሐይ በላይ ከሰማይ በታች እስከ ሰባት ዓመት ኖረ::

ዳግመኛም ወደ ምድረ ከብድ ተልኮ እንደ ዓምድም የተተከለ ሁኖ ሰባት ዓመት ቁሞ ኖረ:: ወደ ሰማይም ሲመለከት ቅንድቦቹን አልከደነም ራሱንም ወደ መሬት ዝቅ አላደረገም ነበር እጆቹን ወደ ሰማይ ተዘርግተዋል::

እነሆ ሰይጣንም በቁራ ተመስሎ መጣ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ ያንጋጠጡ ሁነው አገኛቸው በራሱ ላይም ተቀምጦ ሁለቱን ዐይኖቹን አንቍሮ አሳወረው::

እርሱ ግን ምንም ሳያጓድል እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ እንደ ቀድሞው በመትጋት ሲጸልይ ኖረ::

ከዚህም በኋላ ሚካኤልና ገብርኤል መጥተው በፊቱ ቆሙ በሁለቱ ዐይኖቹ ላይም እፍ አሉበት ብርሃንም ተሰጥቷቸው እንደ ቀድሞው አዩ:: ከሰማይ ታላቅ ኃይል ተሰጥቶሃልና ጠላቶችህን ትበቀላቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ሒድ አሉት ከዚያም መላእክት ከአጠገቡ ሔዱ::

እርሱም ተነሥቶ ወደ ዝቋላ ተጓዘ በጎዳናም ሲጓዝ ሦስት ሽማግሌዎች ከዕንጨት ጥላ በታች ተቀምጠው አየ አባታችንም በአያቸው ጊዜ ልሠወራቸው ብሎ በልቡ አሰበ:: እነርሱም ፈጥነው ለእግዚአብሔር ዙፋን ተማጥነናል ሦስታችንንም በጀርባህ እያዘልክ አንዳንድ ምዕራፍ ሸኘን እንጂ አትተወን ብለው ተጣሩ::

በመጣም ጊዜ ሁለመናቸው ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሸማግሎች ሁነው አገኛቸው አንደኛውንም አንሥቶ በጀርባው አዘለው ወደ አንድ ምዕራፍም አደረሰው ሽማግሌውም ከዚህ አሳርፈኝ አንተ ደክመሃል የማትበላ የማትጠጣ ስለሆንክ አለው አባታችንም ሽማግሌ ሆይ በምን ዐወቅከኝ አለ::

ሽማግሌው ሒደህ ባልንጀሮቼን አምጣልኝ አለው:: ተመልሶ ሁለቱ ወደአሉበትም ደርሶ ሁለተኛውን ሽማግሌ በጀርባው አዝሎ ወደ ቀደመው ሽማግሌ አድርሶ አብሮ አስቀመጠው ሦስተኛውን ሽማግሌ አዝሎ ሁለቱ ወዳሉበት አድርሶ በአንድነት አኖረው::

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም እነዚያን አረጋዊያን እናንተ ከወዴት ናችሁ መዓዛችሁ ልብ ይመሥጣል እጅግም ደስ ያሰኛል አላቸው::

እነርሱ ግን ተነሥተው ቆሙ አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸውን ገለጡለት የአባቶች አለቃ አብርሃም እንዳየ::

ያን ጊዜም የእግዚአብሔርን የጌትነቱን ክብር አየ የእሊያ አረጋውያንም ፊታቸው ተንቦገቦገ ከፀሐይና ከመብረቅ ብልጭታም ሰባት እጅ

በራ አባታችንም በምሥጢራት ጎርፍ የተዋጠ ሆኖ ፈራ ተንቀጠቀጠ በምድር ላይም ወደቀ::

ሕልምን የሚአልምም መሰለው ከዚያም ጌታችን አባታችንን አነቃውና መቶ ዓመት ያህል ሥጋህን ሲነድፉህ ዐጥንቶችህን ሲፍቁህ የኖሩ አጋንንትን ታጠፋቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ተራራ ውጣ አለው::

እኔ እንደ ወሰድኩህ ባለማወቃቸው በባሕር ውስጥ አለ በማለት በትዕቢት ላይ ናቸው ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ይረዱሃል መባርቅትም በፊት በኋላ ሁነው ይከተሉሃል አለው::

ያን ጊዜ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመብረቅ ላይ ተጭኖ በረረ እነዚያ አጋንንት ወደአሉበትም ወረደ ደመናትም ከበቡአቸው መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው በመብረቅም አጨዱአቸው አመድም ሁነው በነፋስ በተኑአቸው::

የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባት ሰባት መቶ ሺህ እልፍ ከአንድ ሺህ ነበር::

ከዚህም በኋላ ጌታ ክርስቶስን የካዱ ወዳሉበት ወደ ምዕራብ ሀገር ወሰደው ነገሥታቱና መሳፍንቱ መኳንንቱም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጎዳና ብዙ መከራ ያገኝሃል ግን በርታ ታገሥ ብሎት በዚያ ተወው::

በዚያን ጊዜም የዓረብ ንጉሥ ጣዖታቱን አስይዞ መኳንንቱንና ሠራዊቱን አስከትሎ በዚያች ጎዳና መጣ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በጎዳና ውስጥ በተገናኙት ጊዜ ጣዖታቱ ወድቀው ተሰባበሩ::

ንጉሡም አባታችንን በአየው ጊዜ አንተ ጠጉር ለባሽ ምንድ ነህ ሰው ነህን አለው:: አባታችንም አዎን ክብር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያው የሆንኩ ሰው ነኝ ብሎ ለከሀዲው ንጉሥ መለሰለት::

ንጉሡም ዳግመኛ አባታችንን በዚያ አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህን አለው:: አባታችንም በሰው ፊት አምንበታለሁ:: ስለ እኔ ብቻ የተሰቀለ አይደለም ስለ አንተና ከአንተ ጋር ስላሉትም ጭምር ነው እንጂንጉሥ ሆይ የዘላለም ሕይወትን ታገኛላችሁ እመኑበት አለው::

ንጉሥም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሠራዊቱንም ጠርቶ በፍጥነት እሳትን አንድዱ ለተሰቀለው ለናዝሪቱ ሰው ባሪያው ነኝ የሚለውን ጠጉረ ለባሽ ወስዳችሁ ጨምሩት አላቸው:: የእሳቱን ነበልባል በረጅም ዛፍ መጠን ከፍ ከፍ እስከሚል አነደዱ::

አባታችን ግን ንጉሡና ሠራዊቱ ሁሉ እያዩት አልፎ በፈቃዱ ወደ እሳቱ ገባ እሳቱም እንደወንዝ ውኃ ሆነ ሠራዊቱም እጅግ አደነቁ እኩሌቶቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ::

ንጉሡም ሲያደንቁ በአየ ጊዜ ፈጽሞ ተቆጣ ከሰባ ሰባት አርበኞች ጋራ በቁጣ ተነሥቶ ያደነቁትንና ያመኑበትን አንገታቸውን ቆረጠ::

በዚያችም ቀን የተቆረጡ አርባ መቶ ሺህ ሁነው ተቆጠሩ:: ንጉሡም የአባታችንን አንገት ሊቆርጥ ተወርውሮ ሔደ:: ያን ጊዜም ከመብረቅና ከነጎድጓድ ጋር ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ንጉሡም ከሠራዊቱ ጋር አጠፋው ከከሃዲው ንጉሥ ጋር የሞቱት ቍጥራቸው አራት ሺህ እልፍ ሆነ::

ጌታችንም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጠላቶችህንና የኔንም ጠላቶች አጠፋውልህ አለው:: አባታችን ግን በመብረቅ የሞቱትን ሬሳቸውን ነፍሳቸውንም መላእክተ ጽልመት ወደ ሥቃይ ሲወስዱአቸው በአየ ጊዜ መድኃኒታችንን እሊህን ስሑታን ማርልኝ ሰው ስሑትና ከዳተኛ ነውና አቤቱ አንተ ግን መሐሪ ይቅር ባይ ታጋሽም ነህ አለው:: አባታችንም ይህን ሲናገር ጌታችን ተሠወረ::

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም ከዚያ ሔዶ ታላቅ ገድልም አገኘ እግሮቹን በገመድ አሥሮ በገደሉ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ ሰይጣንም መጥቶ ያቺን ገመድ ቆረጣት ወደ ታችም ተወርውሮ ወረደ::

ቅዱስ ሚካኤልም ቀድሞ አባታችንን ያዘው በእግርህ ላቁምህ ወይም በራስህ አለው በራሴ እቆም ዘንድ ተወኝ አለው ትቶት ሔደ::

በዚያም በራሱ ቆመ በጥርሶቹም ደንጊያ ነክሶ ሠላሳ ዓመት ኖረ አንጀቱና ናላው ሁሉ እየፈሰሰ አልቆ መላ አካሉ እንደ እንጨት ቅርፊት ሆነ::

ከሠላሳ ዓመትም በኋላ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችንን ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለ ሦስት ጊዜ ጠራው::

እርሱም እንሆኝ ጌታዬ አለ ጌታችንም እነዚያን ከሀዲዎች ምሬልሃለሁ ከዚህ ተነሣ አለው:: ያን ጊዜ የነከሰውን ደንጊያ ትቶ ተነሣ:: ጥርሱም ተነቅሎ ቀረ::

ክንፎችም ተሰጥተውት እየበረረ ከእግዚአብሔር ፊት ደረሰ ጌታውንም ከማርክልኝ ከሥጋቸው ጋር ተነሥተው በመጠመቅ ክርስቲያኖች ይሁኑ ብሎ ለመነው::

መድኃኒታችንም በሽተኞችን ልትፈውስ ሙታንን ልታስነሣ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ አሁንም ወደተገደሉት ሔደህ በመስቀል ምልክት በላያቸው አማትብ ሕይወት መድኃኒት በሆነ ስሜም አስነሣቸው አለው::

ያን ጊዜም በድኖቻቸው ወዳሉበት ሒዶ አስነሣቸው አጥምቆም ክርስቲያኖች አደረጋቸው ከእርሳቸውም ሔደ::

ከዚህ ዓለም የሚለይበት በቀረበ ጊዜ እንሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተገለጠለት:: ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያው ለሚያደርግ እስከ አሥራ አምስት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጠው:: የዕድሜውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን በሰላም በፍቅር አረፈ::

ጌታችንም ነፍሱን ተቀበለ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጉት::

የጸሎቱ ኃይል ሁላችንን የክርስቲያን ወገኖችን በተለይ በዚህ ጊዜ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም አንድነት ፍቅር መተሳሰብን ያድለን::

ሃሌ ሉያ ምስጋና ሁል ጊዜ ለአምላካችን ይገባል የአባታችን ጸሎቱና በረከቱ የረድኤቱ ስጦታና የይቅርታ አማላጅነቱ ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን!
🇪🇹⛪️

የዕለቱ መልእክት ሮሜ  121፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እ...
28/02/2025

የዕለቱ መልእክት ሮሜ 12
1፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።

2፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ቃና ዘገሊላ:-አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ዐሥራ ሁለት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በሆነች በቃና በሠርግ ቤት የሠራው...
20/01/2025

ቃና ዘገሊላ:-
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ዐሥራ ሁለት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በሆነች በቃና በሠርግ ቤት የሠራው የተአምራቱ መታሰቢያ ይደረግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓት ሠሩ::

ቅዱስ ወንጌል እንደ ተናገረ ይህች የተአምራቱ መጀመሪያ ናት::

የእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት የተገለጠበት ዕለት ነው:: ውኃውን ለውጦ መዓዛው የሚጥም ጣፋጭ ወይን አድርጎታልና::

በዚህም አሳዳሪው ምስክር ሆነ::

ሙሽራው በጠራው ጊዜ ሰው ሁሉ መልካሙን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል ከሰከሩም በኋላ ዝቅተኛውን ያጠጣል:: አንተ ግን የተሻለውን ጠጅ ወደ ኋላ አቆይተህ አጠጣህ አለው::

ጌትነቱንም ገለጠ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት::

ዳግመኛም በዚህ ዕለት የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው::

በዚህች ቀን እስራኤል ወደተባለ ያዕቆብ እግዚአብሔር ልኮታልና ከወንድሙ ከኤሳው ፈርቶ ሳለ አዳነው:: ዮርዳኖስንም አሻግሮ ወደ እናቱ ወንድም ወደ ላባ ሔደ::

እርሱም ሁለቱን ልጆቹን ልያንና ራኄልን አጋባው ከዚህም በኃላ ከብዙ ገንዘብና ከልጆቹ ጋር መንገዱን እየጠረገና እያቀና በሰላም በጤና ወደ አገሩ መለሰው:: ወንድሙ ኤሳውም በፍቅር በሰላም ተቀበለው::

ስለዚህም የሊቀ መላእክት ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ አማላጅነት ይማረን::

ለርሱም ከቸር አባቱ መሐሪና ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን::

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክስ እለታዊ/Ethiopian Orthodox Daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share