Arcane Grace International Church

Arcane Grace International Church To edify, exhort and council many people !

20/03/2023

የወንጌላዊ ጂሚ ስዋጋርት አሳዛኝ ታሪክ

04/02/2023

ሴቶች ወንድን ሲመርጡ መውሰድ ያለባቸው ጥንቃቄ!

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ከፌስቡክ በቀጥታ ሰብስክራይብ ያድርጉ። ወደ ኢሜል account መለያዎ መግባት አያስፈልግዎትም።  Arcane Media ሞኒታይዝድ እንዲሆን ይተባበሩ😇❤️ ዘርፈ ብ...
20/12/2022

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ከፌስቡክ በቀጥታ ሰብስክራይብ ያድርጉ። ወደ ኢሜል account መለያዎ መግባት አያስፈልግዎትም። Arcane Media ሞኒታይዝድ እንዲሆን ይተባበሩ😇❤️ ዘርፈ ብዙ እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞችን ወደ እናንተ ለማድረስ በዝግጅት ላይ ነን። ተባረኩ!!👇👇👇
https://youtube.com/.churchoffic9572?sub_confirmation=1

22/04/2022
 :-✍ ወንጌልን በተመለከተ ብዙዎች ብዙ ነገር ሲሉ ይስተዋላል፤ በዚህም የተነሳ የብዙዎችን ግራ መጋባት ከማስወገድና ጭፍን ተቃዋሚ እንዳይሆኑ ከማድረግ አንፃር ይህ ፅሁፍ ተፃፈ። ?  ? 👍ወ...
02/03/2022

:-

✍ ወንጌልን በተመለከተ ብዙዎች ብዙ ነገር ሲሉ ይስተዋላል፤ በዚህም የተነሳ የብዙዎችን ግራ መጋባት ከማስወገድና ጭፍን ተቃዋሚ እንዳይሆኑ ከማድረግ አንፃር ይህ ፅሁፍ ተፃፈ።

? ?
👍ወንጌል የሚለው ቃል ዩአንገሊዮን ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን በዘመኑ የነበሩ ግሪካውያን ጦርነት ተዋግተው አሸንፈው ሲመለሱ የምስራች አብሳሪዎች(ወሬ ነጋሪዎች) ከጦርነቱ ስፍራ ወደ ከተማቸው በመሮጥ መለከት እየነፋ ዩአንገሊዮን/euangelion ይሉ ነበር የቃሉም ትርጓሜ፦ መልካም ዜና ጦርነቱ በድል ተጠናቋል መንግስታችን አሸንፋል ማለት ነው። ወንጌል ከሳጥናኤልና መላእክቱ አመፅ ጀምሮ በእግዚአብሔር መንግሥት እና በዲያብሎስ መንግሥት መካከል በተፈጠረው ጦርነት ብሎም በአዳም ውድቀት ምክንያት ሰው ተቀምቶ የነበረውን ምድርን የማስተዳደር ስልጣን የእግዚአብሔር መንግሥት የዲያብሎስን መንግሥት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ድል በመንሳቱና የዲያብሎስን፣ የሞትንና የሲኦልን ስልጣን ሙሉ በሙሉ ገፍፎ ውጊያውን በማሸነፉ ዘመናቸውን ሙሉ በሞት ፍርሃት የሚሰቃዩትን ነፃ ሊያወጣቸው እንደሚችል ሁሉ እንደተፈጸመ የሚያበስር መልካም ዜና ነው።
ዜናውን ማብሰር ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ባለማወቅ በሞት ፍርሃትና በባርነት የሚሰቃዩ ይድኑና ያመልጡ ዘንድ ነው። በመሆኑም ወንጌል መልካም ዜና የምስራች ነው።

? ለመሆኑ የብልፅግና እና የድህነት ወንጌል ምንድን ነው?

1.) :-
👍በበሽታ እንድንታመም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እርሱን መታዘዝና በእርሱ መታመን እንድንችል እግዚአብሔር በሽታን ያዛል።
👍 ከዚህ ዓለም ነገር ዓይኖቻችንን እንድናነሳ ስለሚፈልግ እግዚአብሔር ድሆች ያደርገናል ብለው ያምናሉ። ያልታመመ ወይም ያልደኸዬ ሰው እምነት የጎደለው ወይም ለእግዚአብሔር ትእዛዝ የማይገዛ ሰው ነው ብለው ያምናሉ። በክርስቶስ ያመነ ሰው ያለውን ሁሉ በመሸጥ ድሃ ሆኖ መኖር አለበት ብለው ያምናሉ።
ለዚህም የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች፦
“ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።”
— ማቴዎስ 19፥21፤ ማቴ 6: 19- 21፤ 1ጢሞ 6: 10፤ ያዕ 2: 6- 7
👍በድህነት ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሀብታሞችን በሀብታቸው ምክንያት ብቻ ሀጢያተኛ እንደሆኑ በመናገር ይኮንኗቸዋል።

2.) ፦
👍በክርስቶስ ያመነ በጤና፣ በሀብት እና በስኬት የተባረከ ስለሆነ እነዚህ ነገሮች የጎደሉት ሰው ወይ እምነት ጎድሎት ነው ወይም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሕግ ስላልተገዛ ነው ብለው ያምናሉ።
👍 ድህነት፣ በሽታ እና አለመከናወን የመርገም ውጤቶች ናቸው ብለው ያምናሉ። በመሆኑም ያልበለፀገ ሰው፣ ጤናማ ያልሆነ ሰው፣ ስኬታማ ያልሆነ ሰው ወይ እምነት የለውም ወይም ደግም የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰራ አላደረገም ብለው ያምናሉ።
👍የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች፦
ፊል 4: 19፤ ዘዳ 8: 18፤ 2 ቆሮ 9: 8፤ ገላ 3: 13- 16

👍በብልፅግና ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች አለመበልጸግን እንደ መንፈሳዊ ብስለት ጉድለት ይመለከታሉ።

3.) (Kingdom Gospel)፦
👍 ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ወንጌል ሲናገር እንዲህ ብሏል፦
ማቴ 4: 23፤ 9: 35
“ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።”
— ማቴዎስ 24፥14

(የሐዋ 20: 24)፣ (ማቴ 24: 14) እና (ሮሜ 1: 1- 4፤ ገላ1: 15- 16) ልዩነት አላቸው?
👍ልዩነት የላቸውም፦ በመሆኑም መፅሐፍ ቅዱስ ወንጌል ጸጋ ነው ሲል ነፃ ስጦታ ነው እያለን ነው፤ ወንጌል የእግዚአብሔር ነው ሲል ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው እያለን ነው፤ ወንጌል ስለመንግሥቱ ነው ሲል ስለእግዚአብሔር መንግሥት ነው እያለ ነው፤ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ነው ሲል በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ንጉሡ ኢየሱስ ነው እያለ ነው።

/ማጠቃለያ፦
👍 ወንጌል የብልፅግና ወይም የድህነት አይደለም። ነገር ግን በወንጌል ልንበለፅግ ብሎም ስለወንጌል ልናጣ እንችላለን።
👍 መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ድሆችም ሀብታሞችም እንዳሉ ይነግረናል።
(1ኛ ጢሞቴዎስ 6: 17- 18፤ ያዕቆብ 2: 1- 6)
👍ፊልጵስዩስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።
¹² መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ።
¹³ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
2 ቆሮ 8: 11- 16፤ 9: 10
👆👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇
ጳውሎስ በዚህ ክፍል "ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" ሲል ማጣትንም ሆነ ማግኘትን በክርስቶስ ኃይል እኩል አስተዳድራለሁ እያለ ነው። ማለትም በማጣቴ አልመረርም በማግኘቴ ደግሞ አልታበይም/አልፈተንም እያለን ነው።
👍 ሀብታም ሀብት ሲሰጠው ድሆችን በመርዳት እኩልነት እንዲፈጥር እና ወንጌልን እንዲደግፍ ነው። 2ቆሮ 8: 11- 16፤ 9: 10
👍 ድሀም በድህነት ሲኖር ሀብታሞችን እንደክፉ በመቁጠር ሙሉ ለሙሉ ሀብታቸውን ካልሸጡና ድሃ ካልሆኑ ማለት የለበትም። ነገር ግን ሀብታሞች የሚበቃቸውን ያክል ከያዙ ማለትም ጎተራቸው ከሞላ በኋላ የሚተርፈው የእነርሱ እንዳልሆነ በማሰብ ሽጠው ለድሆች ቢሰጡ(ከእርዳታ ድርጅቶች/ከቤተክርስቲያን ጎን በመቆም ወይም ድርጅት በማቋቋም በቋሚነት እንዲረዱ የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ነው።
👍ጎተራችን ከሞላ በኋላ “እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤”ሉቃስ 12፥18 ማለት የለብንም። እግዚአብሔር ጎተራችን በመሙላቱ(ሀብታም በመሆናችን) ሳይሆን የሚቃወመን ከጎተራችን የተረፈውን ሰብስበን ለመያዝ በማሰባችን ነው፤ ምክንያቱም የእኛ አይደለምና። ይህም ሀብትን ማከማቸት(possessing wealth) ይባላል። በዚህም ውስጥ ስግብግብነት/greed ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል።
?
ከጊዜ እና ካለንበት አካባቢ አንፃር ይወሰናል። ለምሳሌ ድሮ ድሮ መኪና መግዛት እንደ ቅንጦት(luxury) ይታይ ነበር። አሁን አሁን ግን በተለይ ወደ ከተማና ያደጉ አገሮች መሠረታዊ ነገር እየሆነ መጥቷል። ስለዚህ 1 ወይም እንደአስፈላጊነቱ 2 መኪና መግዛት ቅንጦት አይደለም! ነገር ግን 7 መኪኖችን ገዝቶ በየቀኑ መቀያየር ቅንጦት ነው። ለትምክህት በየሀገሩ የመኖሪያ ቤት መስራት ቅንጦት ነው።
👍 እምነታችን በእግዚአብሔር እንጂ በገንዘባችን ብዛት ሊሆን አይገባም።
👍ስላገኘን ብቻ ሳይሆን በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ያስፈልጋል።
👍 ገንዘብ ስናገኝ በራሳችን ዛቢያ ብቻ ከመሽከርከር ነፃ ወጥተን ገንዘቡን የሰጠንን ጌታ ማንን እንድረዳ ትወዳለህ እንበለው።
👍በመጨረሻም ያለኝ ይበቃኛል ማለትን እንማር።
✍ ከፍቅረአብ ደግፌ

Address

Goro
Addis Ababa

Telephone

+251974724753

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arcane Grace International Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share