የ መዝሙር ግጥሞች

የ መዝሙር ግጥሞች 🇪🇹 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ መዝሙራት መገኛ

https://t.me/joinchat/AAAAAE5K_dyT2-AYoTAW5A

✞የምስራች እንበል✞የምስራች እንበል (፪) እናመስግን ጌታንበመስቀል ላይ ውሎ ከኃጢአት ላነጻንሞትን ድል አድርጎ ለሰጠን ትንሳኤንታላቁ ጌታችን የዓለም መድኃኒትአደረ በመቃብር ሦስት ቀን ሦስት...
16/04/2023

✞የምስራች እንበል✞

የምስራች እንበል (፪) እናመስግን ጌታን
በመስቀል ላይ ውሎ ከኃጢአት ላነጻን
ሞትን ድል አድርጎ ለሰጠን ትንሳኤን

ታላቁ ጌታችን የዓለም መድኃኒት
አደረ በመቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት
አዝ= = = = =
ፈጣሪ ሆኖ ሳለ የፍጥረታት ጌታ
በሰው ፊት ተዋረደ በፍጹም ተንገላታ
አዝ= = = = =
አሳልፎ ሰጠ ስለኛ ራሱን
በመስቀል ተቸንክሮ መረጠ መሞትን
አዝ= = = = =
አይሁዶች ተሞኙ ትንሳኤን ሳያምኑ
ሳያምኑ መቃብሩን ወታደር አስጠበቁ
አዝ= = = = =
ዘቦችም ወደቁ ሞትም ተሸነፈ
ሰይጣንም ተዋረደ ስልጣኑ ተገፈፈ
አዝ= = = = =
በማለዳ ሄዳ ማርያም መግደላዊት
የጌታዋን ትንሳኤ መላዕክት አበሰሯት

https://t.me/joinchat/AAAAAE5K_dyT2-AYoTAW5A

✏️"ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን" ሮሜ=6፥5 ⛪️  ወድ የ መዝመር ግጥሞች ቻናል ተከታታዮች እንኳን ለጌታችንና...
16/04/2023

✏️"ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን" ሮሜ=6፥5

⛪️ ወድ የ መዝመር ግጥሞች ቻናል ተከታታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ አደረሳችሁ↪️ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

📍 መልካም የትንሳኤ በዓል 📍

https://t.me/joinchat/AAAAAE5K_dyT2-AYoTAW5A

✞ በሚፈርደው ፈረዱበት ✞በሚፈርደው ፈረዱበትበሚምረው ጨከኑበትበቁጣ ጎተቱት ቀይ ግምጃ አለበሱት      አዳምን የፈጠረ እጅ በመስቀል ቀኖት ተቸነከረቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከወንበዴ ጋር ተ...
13/04/2023

✞ በሚፈርደው ፈረዱበት ✞

በሚፈርደው ፈረዱበት
በሚምረው ጨከኑበት
በቁጣ ጎተቱት ቀይ ግምጃ አለበሱት

አዳምን የፈጠረ እጅ በመስቀል ቀኖት ተቸነከረ
ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከወንበዴ ጋር ተቆጠረ
ህይወት እፍ ያለውን አፍ ጨክነው ሀሞት አጠጡት
በሞቱ ሞትን ይሽር ዘንድ ጌታን በመስቀል ሰቀሉት

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት
አዝ= = = = =
በመፍራትና በመራድ መላዕክት ፊቱ ለሚሰግዱለት
የአለሙን ሁሉ ጌታ በአደባባይ ላይ አቆሙት
ለሱራፌል የክብር ዘውድ ያቀዳጃቸውን ጌታ
ፍቅር ያነበብንበት ፊቱን በክፉ ባርያ ተመታ

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት
አዝ= = = = =
ፅድቅና የፀና ሰላም የሀጥያት ስርየት በሰጠን
እንደ ክፉ ሰው ተቆጥሮ በእሾህ አክሊል አጌጠ
ለኪሩቤል የግርማን ልብስ የሚያለብሳቸውን እርሱን
እርቃኑን ይሰቀል ብለው እጣ ተጣጣሉበት ልብሱን

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት
አዝ= = = = =
በኢየሱስ መንገላታት አለም እንዲድን ከፍዳ
ቅዱሱ ደምና ውሀ ከአምላካችን ጎን ተቀዳ
ሰላም ለእናንተ ሲለን እጅና እግሩን አየን
ሙስና መቃብር ጠፋ ይኸው በአዲሱ ኪዳን

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት

ዘማሪ
ገብረዮሐንስ ገብረ ጻድቅ

https://t.me/joinchat/Tkr93JPb4BihMBbk

✞ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ✞ለተክለሃይማኖት ጻድቅ መጠነ ብዝኃ ህማሙ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ(፪)እምነ አድባራት ኵሎን ዘተለአለት በስሙ(፪)ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ(፪)እስመ በውስቴታ ...
02/04/2023

✞ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ✞

ለተክለሃይማኖት ጻድቅ መጠነ ብዝኃ ህማሙ
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ(፪)

እምነ አድባራት ኵሎን ዘተለአለት በስሙ(፪)
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ(፪)
እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሠተ ሥጋሁ ወአጽሙ
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ(፪)

ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሳ በደሙ
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ(፪)

ትርጉም፦
ጻድቁ ተክለሃይማኖት ብዙ ህማም የተቀበለባት ቅዱስ አጽሙ ያረፈባት በስሙ ከታነጹት አድባራት ሁሉ ከፍ ያለች ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የቀደሳት ደብረ ሊባኖስ ታመሰግነዋለች።

የምክሐ ደናግል ሰ/ት/ቤት መዝሙር

ለ ተጨማሪ መዝሙሮች
https://t.me/joinchat/Tkr93JPb4BihMBbk

✞የይሁዳ ጉዞ✞የይሁዳ ጉዞ አያዋጣም እናዴማስ ወደ ህይወት እባክህ ቶሎ ናበወንጌል ገበታ መመገብ ጀምረህወንድሜ ተመለስ ወዴት ትሄዳለህ(፪)ይጠራሃል እና መስቀሉን ተመልከትየወንጌል ቡቃያ እውነ...
28/03/2023

✞የይሁዳ ጉዞ✞

የይሁዳ ጉዞ አያዋጣም እና
ዴማስ ወደ ህይወት እባክህ ቶሎ ና

በወንጌል ገበታ መመገብ ጀምረህ
ወንድሜ ተመለስ ወዴት ትሄዳለህ(፪)
ይጠራሃል እና መስቀሉን ተመልከት
የወንጌል ቡቃያ እውነተኛው ህይወት
አዝ= = = = =
ቸርነቱን አይተህ ፍቅሩን ቀምሰኸዋል
በረድኤት ህይዋት ደስታ ሞልቶሃል
ቅዳሴው ዝማሬው እጣኑ ሸቶሃል
ዴማስ ሆይ ተመለስ ሕይወት ይሻልሃል
አዝ= = = = =
ብዙ ክርስቲያኖች መንገዱን ጀምረው
የዓለም አሸንክታብ ድንገት ሲጠራቸው
ፈተና ሲመጣ ወንጌሉን ወርውረው
ሞትን ይመርጣሉ ሕይወትን ሰርዘው
አዝ= = = = =
የመስቀሉ ሕትመት ከልብህ ሳይጠፋ
በእግዚአብሔር ጉባዔ መስክረህ በይፋ
ልጄ የተባልከው በጥምቀት ቀለበት
እንዴት ትሄዳለህ ተነድተህ ወደ ሞት(፪)
አዝ= = = = =
የክብር አክሊሉ ተዘጋጅቶልሃል
አምላክ ለሽልማት ዴማስ ሆይ ይልሃል
ወዴት ትሄዳለህ እባክህ ተመለስ
ክብርህ አትተው ከጫፉ ስትደርስ(፪)

መዝሙር
ይልማ ኃይሉ

"ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤"
፪ጢሞ፲፥፬

🎧በዓቢይ ጾም የማንን የንስሐ መዝሙር ማዳመጥ ትፈልጋላችሁ የፈለጉትን መርጠው ያዳምጡ‼️ 👇👇👇 http://t.me/yamazemur_getemoche 📢በዚህ ቻናል የተለያዩ የመንፈሳዊ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለማሰ...

✞ ኪዳነ ምሕረት እናቴ ✞ ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛ ጓዳዬየጎደለኝን ታውቂያለሽከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ(፪)አልፏል መናኛው ኑሮምልጃሽ ውኃውን ቀይሮመልካሙ ወይን ደረሰእንባዬ ባንቺ ታበሰ(...
25/03/2023

✞ ኪዳነ ምሕረት እናቴ ✞

ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ(፪)

አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ ባንቺ ታበሰ(፪)
አዝ= = = = =
ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልረሳሽም እናቴ(፪)
አዝ= = = = =
አልልም መቼ ነው ቀኑ
የኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደሚፈፀም አውቃለው
ሁሉን በጊዜው አያለው(፪)
አዝ= = = = =
የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂ(፪)

መዝሙር በ
ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

❤23❤የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት ይደርብን 🙏
01/04/2019

❤23❤
የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት ይደርብን 🙏

✨✨✨   #መዝሙር   ✨✨✨የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ዝማሬዎች በአይነት ከፋፍሎ ያቀርብሎታልለምን መዝሙር በግጥም ብቻ እናጠናለን ኑ ከኛ ጋ አብረን ከነ  #ዜማው እናጥና...
15/04/2018

✨✨✨ #መዝሙር ✨✨✨
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ዝማሬዎች በአይነት ከፋፍሎ ያቀርብሎታል
ለምን መዝሙር በግጥም ብቻ እናጠናለን ኑ ከኛ ጋ አብረን ከነ #ዜማው እናጥና እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን {መዝ 150-6
⚡️በቴሌግራም የመጀመሪያው የመዝሙር ቻናል⚡️
👇 ይ ቀ ላ ቀ ሉ 👇

የ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የ መዝሙር ግጥሞች ከነዜማቸው አንደየጊዜአቸው ልታገኙበት የምትችሉበት ቻናል የመዝሙር ግጥም መላክ ለምትፈልጉ ወይም ሀሳብ አስተያየት ካሎት በ ...

23/12/2016

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የ መዝሙር ግጥሞች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share