Nejashi Mesjid & Medresa ነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ

Nejashi Mesjid & Medresa ነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ ነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ

12/08/2026
የቢሻራ 4ኛው ዙር ከዘቢብ መልኬ ጋር የነበረው መሰናዷችን ይህን መስሎ ተከናውኗል። ስለመጣችሁ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። ሰው - ቤተሰብ - ማህበረሰብ - ሀገር - ዑማ
26/07/2026

የቢሻራ 4ኛው ዙር ከዘቢብ መልኬ ጋር የነበረው መሰናዷችን ይህን መስሎ ተከናውኗል። ስለመጣችሁ እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

ሰው - ቤተሰብ - ማህበረሰብ - ሀገር - ዑማ

በዶ/ር ኢድሪስ ሙሀመድ አወያይነት እና በዶ/ር ሙሐመድ ሚፍታህ አቅራቢነት 8ኛው ዙር የማይንድስ ፕሌዠር ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።የመጀመሪያውን የቅዱስ ቁርኣን አማረኛ ትርጉም (በሸይ...
19/07/2026

በዶ/ር ኢድሪስ ሙሀመድ አወያይነት እና በዶ/ር ሙሐመድ ሚፍታህ አቅራቢነት 8ኛው ዙር የማይንድስ ፕሌዠር ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

የመጀመሪያውን የቅዱስ ቁርኣን አማረኛ ትርጉም (በሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ሳዲቅ እና በሸይኽ ሙሐመድ ሳኒ ሀቢብ) ተንተርሶ ለፒኤችዲ ማሟያ የተሰናዳውን የዶ/ር ሙሐመድ ሚፍታህ የተዘጋጀውን ጥናታዊ ፅሁፍ (Grammatic shifts in Arabic - Amharic translation of The Holy Quran) በሰፊው ተዳሷል። ስለተሳትፏችሁ እጅግ እናመሰግናለን።



የማይንድስ ፕሌዠር መሰናዷችን ሰዐቱን ጠብቆ ተጀምሯል።
19/07/2026

የማይንድስ ፕሌዠር መሰናዷችን ሰዐቱን ጠብቆ ተጀምሯል።

ነጃሺ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ከነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ እና ከነጃሺ ዑለማ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የማይንድስ ፕሌዠር መሳናዶ ነገ እሁድ ሐምሌ 12 ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በነጃ...
18/07/2026

ነጃሺ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ከነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ እና ከነጃሺ ዑለማ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የማይንድስ ፕሌዠር መሳናዶ ነገ እሁድ ሐምሌ 12 ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ ይካሄዳል። በዕለቱ የመጀመሪያውን አማረኛ የቁርኣን ትርጉም ላይ ያሉ የቋንቋ ዝግጅቶች በጥልቅ የሚዳሰሱ ሲሆን በዚህ ላይ ጥልቅ ጥናት እና ምርምር ያደረጉትን ዶ/ር ሙሐመድን (ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ጋብዘናል። ፕሮግራሙን በመምራት (ሞደሬት) ለማድረግ ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ (ረዳት ፕሮፊርሰር) አብረውን ያረፍዳሉ። የነገ ቀጠሯችሁ ከኛ ጋር ይሁን።

ቢሻራ 3 ከዘቢብ መልኬ ጋር ደምቆ ተከናውኗል። በመሰናዶው:-የቤተሰብ ምንነት፣ የቤተሰብ አባላት ስፋት እና ጥበት በህይወት ውስጥ የሚኖረው አጠቃላይ አንድምታ እና የሚፈጥሩት አዎንታዊ እና አ...
12/07/2026

ቢሻራ 3 ከዘቢብ መልኬ ጋር ደምቆ ተከናውኗል።

በመሰናዶው:-

የቤተሰብ ምንነት፣ የቤተሰብ አባላት ስፋት እና ጥበት በህይወት ውስጥ የሚኖረው አጠቃላይ አንድምታ እና የሚፈጥሩት አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖዎች እንዲሁም ጥንዶች ከሁለት ወደ ሶስት እና አራት ... የሚሸጋገሩበት የእርግዝና በተለይም ከወሊድ በኃላ የሚያልፉባቸውን ሂደቶች በተለያየ መንገድ ተዳሰዋል። መሰናዶው በታዳሚያን ተሳትፎ እና በተለያዩ የሃሳብ ልውውጦች ደምቆ አሳታፊ ሁኖ አልፏል።

ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁ እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

ቀጣይ መሰናዶ ቢሻራ 4 ከ15 ቀን በኃላ ሀምሌ 19 እሁድ ይካሄዳል። ሁላችሁም ተጋብዛቹኃል።

ነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ

ነገ እሁድ በሶስተኛው የቢሻራ መሰናዶ ዘቢብ መልኬ ጋር እንጠብቃቹኃለን።
11/07/2026

ነገ እሁድ በሶስተኛው የቢሻራ መሰናዶ ዘቢብ መልኬ ጋር እንጠብቃቹኃለን።

ቢሻራ 2 በዶ/ር አብዱልሀሚድ ናስር (አቅራቢ) እና በአ/ረህማን ሁሴን (አወያይ) ባማረ መልኩ ተከናውኗል። ቤተሰብ እና ወላጅነት ዋናው የዝግጅቱ ማጠንጠኛ ነበር። ስለመጣችሁ እናመሰግናለን።
28/06/2026

ቢሻራ 2 በዶ/ር አብዱልሀሚድ ናስር (አቅራቢ) እና በአ/ረህማን ሁሴን (አወያይ) ባማረ መልኩ ተከናውኗል። ቤተሰብ እና ወላጅነት ዋናው የዝግጅቱ ማጠንጠኛ ነበር። ስለመጣችሁ እናመሰግናለን።

በትዳር፣ በቤተሰብ እና በልጆች አስተዳደግ ላይ የሚያተኩረው ቢሻራ ልዩ የቤተሰብ መሰናዶ ቀጠሮውን ጠብቆ ነገ ይካሄዳል። ሁላችሁም ትገኙ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛቸኋል። ነገ እሁድ ሰኔ 21 ከ...
27/06/2026

በትዳር፣ በቤተሰብ እና በልጆች አስተዳደግ ላይ የሚያተኩረው ቢሻራ ልዩ የቤተሰብ መሰናዶ ቀጠሮውን ጠብቆ ነገ ይካሄዳል። ሁላችሁም ትገኙ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛቸኋል።

ነገ እሁድ ሰኔ 21 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ
በነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ
(መገናኛ 24)

*************************ቢሻራ ልዩ የቤተሰብ ፕሮግራም*************************ቢሻራ ልዩ የቤተሰብ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መሰናዶ  በዛሬው ዕለት ተከናውኗል። በመ...
14/06/2026

*************************
ቢሻራ ልዩ የቤተሰብ ፕሮግራም
*************************

ቢሻራ ልዩ የቤተሰብ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መሰናዶ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል። በመሰናዶው ላይ ሸይኽ ዓብዱልዐዚዝ ሙሐመድ እና ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ትዳር፣ ልጆች እና ቤተሰብን ያማከሉ የተለያዩ ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን የነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ ኢማም ሸይኽ ሙሀመድ የህያ ፕሮግራሙ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለውን ፋይዳ በማብራራት ታዳሚዎች በዚህ እና መሰል መሰናዶዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አደራ ብለዋል።

ቀጣይ የቢሻራ መሰናዶ ከ15 ቀን በኃላ ሰኔ 21 በነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ የሚካሄድ ይሆናል።

Address

Bole Sub-sity, Megenanga , Woreda 5, Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251911342156

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nejashi Mesjid & Medresa ነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Nejashi Mesjid & Medresa ነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ:

Shortcuts

Share