28/12/2025
የእውነት ድምፅ
"በሰላም አረፈ/ች" የምንለው ለሁሉም ሰው አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ የዘላለም ሰላም የሚገኘው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ ይናገራል።
የዮሐንስ ወንጌል 14፤27
14፤27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።
ለመዳን
• ንስሐ መግባት፦ ከኃጢአት መንገድ ዞር ብሎ ወደ እግዚአብሔር መመለስ።
• ማመን፦ ኢየሱስ ስለ እኛ ኃጢአት እንደሞተና በሦስተኛው ቀን እንደተነሳ በልብ አምኖ በአፍ መናገር።
ወደ ሮሜ ሰዎች 10፤10
10፤10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
• መቀበል፦ ኢየሱስን የግል ጌታና መድኃኒት አድርጎ መቀበል።
የዮሐንስ ወንጌል 1፤12-13
1፤12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
1፤13 እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
ስለዚህ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።
ወደ ዕብራውያን 4፤7
4፤7 ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ .......።
የድነት (የመዳን) ጸሎት
ይህን ጸሎት አሁን ከጸለይክ/ሽ ከጨለማ ወደ ብርሃን የምትሻገሩበት ድልድይ ነው፦
"ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ እኔ ኃጢአተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ። ዛሬ ግን ንስሐ ገብቼ ወደ አንተ እመጣለሁ። ስለ እኔ በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደምህ ከኃጢአት ሁሉ ያነጻኛል። በሞትህና በትንሳኤህ አምናለሁ። ዛሬ የሕይወቴ ጌታና መድኃኒት አድርጌ እቀበልሃለሁ። በሕይወት መዝገብ ላይ ስሜን ጻፍልኝ። በአንተ ዘንድ ለዘላለም እንድኖር አዲስ ፍጥረት አድርገኝ። ስለተቀበልከኝ አመሰግንሀለሁ በኢየሱስ ስም አሜን!"