Lisan z Orthodox.com

Lisan z Orthodox.com ወቅቱን የተመለከቱ የኢ፞ኦተ ትምሕረቶች፣ ዜናዎችና አስተያየቶች ይቀርቡበታል።

“በከንቱ ስለምን ይገድሉናል? በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ 21 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አስታወቁ።EOTCMK TV የካቲት 20 ቀን 2016 ...
27/02/2026

“በከንቱ ስለምን ይገድሉናል?

በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ 21 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አስታወቁ።

EOTCMK TV የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

በምሥራቅ አርሲ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ቀጥሎ ትላንት የካቲት 19 ቀን 2018ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በጀመረ ጥቃት 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌና ምሥራቅ አርሲ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።

ከሞቱት 21 ምእመናን መካከል አንደኛው ካህን ሲሆኑ
የሁሉም ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት የካቲት 20/2018 ዓ/ም መፈጸሙንም ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተናግረዋል።

እንደብፁዕነታቸው ተጨማሪ መረጃ ሁለት ምእመናን መታፈናቸውንና ስምንቱ ደግሞ የት እደደረሱ አይታወቅም።

በተጨማሪም የበርካቶች ንብረት መዘረፉንና በዚህ ሰዓት ላይ ከፍተኛ ውጠረት በመንገሱ በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደማይቻል ብፁዕነታቸው አሳውቀዋል። የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ባስተላለፉት መልእክት የልጆቻችን ሞት የእኛም ሞት ነው ያሉ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኘተዋል።

አያይዘውም ገዳዮቻችን “በከንቱ ስለምን ይገድሉናል? የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ተጨማሪ የሰው ነፍስ እንዳይጠፋ የመከላከሉ ሥራ ሊሠራ ይገባል” በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

ትላንት በአንድ ቀን በአርሲ 21 ኦርቶዶክሳዊያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል!-ነፍስ ይማር!
27/02/2026

ትላንት በአንድ ቀን በአርሲ 21 ኦርቶዶክሳዊያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል!
-
ነፍስ ይማር!

የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ🎤ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜናዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና/2/🙏💖†                †                 †...
26/02/2026

የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ🎤
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና/2/🙏💖
† † †
ገብርኤል መልአከ ራማ /2/
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እንስማ

የብፁዕነታቸውን ጽናት ፣ የመጻሕፍትን ጉልበት ፣ የእኛን ድክመት የምንመለከትበት አስተማሪና መካሪ ምስል ነው። ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት           ሊቀ ጳጳ...
26/02/2026

የብፁዕነታቸውን ጽናት ፣ የመጻሕፍትን ጉልበት ፣ የእኛን ድክመት የምንመለከትበት አስተማሪና መካሪ ምስል ነው።

ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት
ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ።

በረከታቸው አይለየን በእድሜ ይጠብቅልን
---------------------

ምንኵስና ታሟልና መድኃኒት እንፈልግለት!!አሁን ያለው ምንኵስና የአባቶቻችንም የታሪካቸውም አሰር የለውም ምናልባት ከሆነ ልብሱ ብቻ ነው የሚሆነውምንኵስና መስመሩን ከሳተ ቆይቷል ብዙዎቹ ማስተ...
22/02/2026

ምንኵስና ታሟልና መድኃኒት እንፈልግለት!!

አሁን ያለው ምንኵስና የአባቶቻችንም የታሪካቸውም አሰር የለውም ምናልባት ከሆነ ልብሱ ብቻ ነው የሚሆነው
ምንኵስና መስመሩን ከሳተ ቆይቷል ብዙዎቹ ማስተካከል ያልቻሉና ለማስተካከልም ትንሽ ድካም ያልደከሙ ሰዎች በምንኵስና ሲቀለድበት ዝሙት ሲፈጸምበት በየግሮሰሪው ሲጨፈርበት እውነቱን ከመመስከር ይልቅ ጸሓፊና ሰባኪ በመምሰል ከሌላ ቤተ እምነት የመጡ ናቸው ምንኵስናን ክህነትን ለማስጠላት ነው ቄስ ዲያቆን መነኩሴ እየመሰሉ ይህን የሚያደርጉ በማለት አለባብሰው ለማለፍ እና ምእመኑ ሌላው መነኩሴ ጥሩ እንደ ሆነ እንዲረዳ እየነቃ የነበረውንም ማደንዘዣ ለመውጋት የሚሞክሩ ልብ እንዲቀረው እና በመነኰሳት ላይ ተስፋ እንዲኖረው የሚያደርጉ አስመሳዮች ጸሓፊዎችን ሰባኪ ነን ባዮችን እያየሁ ነው
ከአጥፊዎቹ ይልቅ ይህ አይነት አረዳድ ይከፋል መፍትሔ ባንሆን እንኳን ማደንዘዣ መሆን ግን አላስፈላጊ ነው እላለሁ እየነቃ ያለውን እያንዳንዱን የመነኰሳት እንቅስቃሴ በመረዳት ላይ ያለውን ምእመን ከሌላ የመጡ ሰርጎ ገቦች ናቸው በማለት ለማስረሣት መሞከር ተገቢ አይደለም
ከዚህ በላይስ እየተደረገ አይደለም ወይ?
የሌላ ቤተ እምነቶች ናቸው በማለት የሚቀየር ነገር አይኖርም ይልቁንስ ለመፍትሔ መዘጋጀት

የሌላ ቤተ እምነቶች በዚህ መልኩ ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ? አዎን ይችላሉ
ግን ቤተ ክርስቲያን ላይ አሁን ያለው ምንኵስና ምንኵስና እየሆነ ነው ወይ? ወይስ ሁሉም ከሌላ ቤተ እምነት የመጣ ነው ወይ?
ይህ ከሆነስ ማንም ሰባኪ ነኝ ባይ ጸሓፊ ነኝ ባይ ተቆርቋሪ ነኝ ባይ መሬት ላይ እየሠራ ነው ወይ?
እሽ የሌላ ቤተ እምነቶች ከሆኑስ? በመነኰሳት ልብስ ሲጨፈርበት ዝሙት ሲፈጸምበት ይህን አድራጊውን አካል ለፍርድ የሚያቀርብ አለ ወይ?
ሌሎቹ ይሰድቡናል የሚል ሁሉ አለ ዝም ካልናቸውማ የበለጠ ይሰድቡናል
በቤተ ክርስቲያን እንዲህ መነኩሴ ሆኖ ይህን ማድረግ ይቻላል ማለት ነው ቤተ ክርስቲያን ትፈቅዳለች? ይሉናል ሌሎቹ የእኛዎቹም ይሉናል
ጉዳዩ እንዲህ ይሉናል ከመባል አልፏል
ችግሩ ያለው እንዲህ አይነቶቹን አሰዳቢዎች ሳያክሙ የቤተ ክርስቲያን አካል ማድረግ ነው
ለምንስ ዝም እንላለን? ሌሎቹ እኮ ቀድመው አይተውታል እኔ እንዲህ አይነት መነኩሴ የቤተ ክርስቲያን አባል አይደለም ብዬ ከመመስከር ወደ ኋላ አልልም

ምንኵስና ስል ገዳማውያንን እንደማይጨምር ብዙ ጊዜ እናገራለሁ አዲስ የሚሆንበት እንዳይኖር

ይቅርታ ወንጌል መሆንን መኖርን እንጂ ማስመሰልን ሲናገሩባት አትወድም ከመነኰሳት ጋር የሥራ ጉዳይ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያገናኛችሁ ልትኖሩ ትችላላችሁ ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥባችሁ ግን አይኑር

ምንኵስና ታሟልና መድኃኒት እንፈልግለት!!

የሊቢያ ሰማዕታት መታሰቢያ❤
18/02/2026

የሊቢያ ሰማዕታት መታሰቢያ❤

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”===================በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!በሀገር ውስጥና በልዩ ልዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፡...
15/02/2026

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
===================
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

በሀገር ውስጥና በልዩ ልዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፡-

በመዋዕለ ጾሙ ሰይጣንንና መስሓቲ ተግባሩን ድል በማድረግ ድል እንድንነሣ ያደረገን ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ኣርብዓ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
‹‹ወልበሱ ወልታ እግዚአብሔር በዘትክሉ ተቃውሞቶ ለመናግንተ ሰይጣን፤ የሰይጣንን ሽንገላ መቃወም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ጋሻ ልበሱ›› (ኤፌ.፮፥፲፩)

እኛ ሰዎች ቀዋሚና ምሕረት የለሽ ጠላት እንዳለን እናውቃለን። ይህ ጠላት ሰይጣን፣ ዲያብሎስ፣ክፉ መንፈስ፣ ርኩስ መንፈስ ተብሎ እንደሚጠራም ቅዱስ መጽሐፍ ነግሮናል። ዲያብሎስ ከጥንት ጀምሮ በክፉ ሽንገላው ሰዎችን ሲጥል ኖሮኣል። አሁንም ከዚህ ክፉ ተግባሩ አልታቀበም። ለወደፊቱም ይታቀባል ተብሎ አይጠበቅም። ጌታችን በዚህ ዓለም በሥጋ በተገለጠ ጊዜም ይህ ክፉና ርኩስ መንፈስ በሽንገላ ቃሉ ጌታችንን ሊጥል ያልተሳካ ሙከራ አድርጎአል፡፡ ርኩሱ መንፈስ ጾም መንፈሳዊ ኃይልን እንደሚያቀዳጅ ያውቃልና፣ ጌታችን ምንም ሳይበላና ሳይጠጣ ኣርባ ቀንና አርባ ሌሊት መጾሙን ተመልክቶ፣ በሽንገላ ቃሉ ሊጥለው ሙከራ አድርጎአል።

ይህንን ያደረገበት ዋና ምክንያትም ጾም መንፈሳዊ ኃይል መሆኑን በውል ያውቃልና በጾም ኃይል ከእጄ ያመልጣል ብሎ በማሰቡ ነው። ይሁን እንጂ ሰይጣን የሰውን ደካማ ጠባይ በመጠቀም ያስለመደው ሽንገላ በተዋሕዶ ሰውም አምላክም በሆነው ጌታችን ላይ ሊሳካለት ባለመቻሉ ተሸንፎና ተስፋ ቆርጦ ሊሄድ ችሎአል፡፡

የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን!
የጌታችን ድል አድራጊነት ያስተማረን ብዙ ነገር አለ። በዚህ ተግባራዊ ትምህርቱ እኛ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስን ድል የምናደርግባቸው ሁለት መሣሪያዎችን በዋናነት አሳይቶናል። እነሱም የእግዚአብሔርን ጋሻ መልበስና በጾም መንፈሳዊ ኃይልን መቀዳጀት ናቸው፡፡

ሁሌም እንደምንማረው በውስጣችን ሁለት ተቃራኒ ነገሮች አሉ። እነሱም ፍትወተ ሥጋና ፍትወተ መንፈስ ናቸው። እነኝህ ሁለት ነገሮች አንዱ ላንዱ ፍጹም ተቃራኒ መሆናቸውን ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ በማለት ያስረዳል። "እስመ ሥጋኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ መንፈስ፤ ወመንፈስኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ ሥጋ፤ ወይትአበዩ በበይናቲሆሙ ከመ ኢትግበሩ ዘትፈቅዱ፤ ወባሕቱ እብለክሙ በመንፈስ ሑሩ ወፍትወተ ሥጋክሙ ኢትግበሩ" ማለትም "ሥጋ መንፈስ የማይወደውን ይወዳል። መንፈስም ሥጋ የማይወደውን ይወዳል። እርስ በርሳቸውም ይቀዋወማሉ። ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ምኞት ግን ከቶ አትፈጽሙ" (ገላ.፭÷፲፮‐፲፰)፡፡

እነኝህ የውስጣችን ጠባዮች በዚህ ደረጃ እርስ በርስ የሚቃረኑ መሆናቸው ለምናስተውላቸው በግልጽ የሚታወቁ ናቸው። ከዚህ አንጻር ሰይጣን ይህንን ክፍተት ተጠቅሞ የሥጋችንን ፍላጎት እንድንከተል ይገፋፋናል። መሣሪያዎቹ ደግሞ ፍቅረ መባልዕት፣ ፍቅረ ንዋይና ፍቅረ ሢመት ናቸው። ይህም በመሆኑ ነው ሰይጣን በነዚህ ጌታችንን ሊሸነግለው የሞከረው። ይሁንና ጌታችን እነኝህን የሽንገላ መሣሪያዎች ሰባብሮ ጥሎአቸዋል። የጣላቸውም በጾምና በእግዚአብሔር ቃል ነው።

ጾም መጾም ማለት ከፍቅረ መባልዕት፣ ከፍቅረ ንዋይና ከፍቅረ ሢመት ፍላጎት ጨርሶ መራቅ ማለት ነው። ይህንን አደረግን ማለት ደግሞ ሥጋችን የማይወደውን፣ መንፈሳችን ግን የሚወደውን ነገር አደረግን ማለት ነው። ይህ ሲሆን ሰይጣን ከሰረ፤ ድልም ሆነ ማለት ነው። በዚህ መንፈሳዊ ኃይል ዲያብሎስ ተሸንፎና ተስፋ ቆርጦ ይሄዳል፡፡

ከዚህ አኳያ እኛም በቃለ እግዚአብሔር እየተመራን የምንጾምበት ምክንያት የሥጋችንን ፍላጎት በመግራት ለነፍሳችን ፍላጎት ለማደርና በዚህ ኃይለ መንፈስ ሰይጣንን በማሸነፍ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ለመሆን ነው፡፡

የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን!
የጾም ዋና ዓላማ ሥጋዊ ፍላጎትን መግራት፣ በምትኩ ደግሞ መንፈሳዊ ፍላጎትን ማጐልበት እንደሆነ ተነግሮናል። በመሆኑም ይህንን መርሕ ጠብቀን መጾም ግዴታችን ይሆናል። ዛሬ ባለንበት ዓለም ሥጋዊ ፍላጎታችን ያየለበት፣ መንፈሳዊ ፍላጎታችን ግን የተዳከመበት ዘመን ላይ እንገኛለን። ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ፣ ከአንድነት ይልቅ መለያየት፣ ከመራራት ይልቅ ጭካኔ፣ ከእምነት ይልቅ ክሕደትና አስመሳይነት በዓለማችን ላይ የበላይነቱን ይዞ መገኘቱ ለዚህ ማሳያ ነው፡፡

ይሁንና ዓለም ቢሰማም ባይሰማም፣ ሐቁም ጠቃሚውም የመንፈስን ፍላጎት ማጎልበት ስለሆነ የመንፈስ ፍሬዎች የሆኑትን ማለትም ፍቅርን፣ ሰላምን፣ አንድነትን፣ ርኅራኄንና ሃይማኖትን ማስፈን ምርጫችን ልናደርግ ይገባል። ቤተ ክርስቲያንም እንድንጾም የምታስተምረን እነዚህን ለመተግበር ጾም ፍቱን መሳሪያ ሆኖ ስለሚገኝ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር የጾም ዓላማውና ግቡ ጽኑዕ ሃይማኖትን፣ እውነተኛ ፍቅርን፣ ዘላቂ ሰላምን፣ ልባዊ አንድነትን፣ የማይናወጽ ፍትሕንና እኩልነትን፣ ወሰን የሌለው ርኅራኄን በውስጣችን ብሎም በዓለማችን ማሥረጽ እንደሆነ በውል ተገንዝበን ጾሙን መጾም ይገባል። ልንለብሳቸው የሚገቡ እነዚህ የመንፈስ ፍሬዎች የእግዚአብሔር ጋሻዎች ናቸውና፡፡ ይህንን ካደረግን እንደ ጌታችን የሰይጣንን ሽንገላ በጣጥሰን በመጣል በአስተማማኝ ሁኔታ ድል ማድረግ እንችላለን፤ የተጠራነውም ለዚሁ ነው፡፡

በመጨረሻም፡-
የሕዝባችንና የሀገራችን የራስ ምታት ሆኖ የሚገኘውን ያለመግባባት ዝንባሌ ለመቅረፍ ከልብ በመጸለይ፣ እንደዚሁም የተራቡትን በማጒረስ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ፍትሕ ለተነፈጉትም እውነተኛ ፍትሕን በመስጠት፣ መዋዕለ ጾሙን እንድንጾመው በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፡፡

የካቲት ፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

እጅግ ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ዜና ከአሰቦት ገዳም! በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ገዳም ለዓመታት በብህትውና ተወስነው የኖሩት ባሕታዊ አባ መብራቱ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በበዓታቸው...
08/02/2026

እጅግ ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ዜና ከአሰቦት ገዳም!

በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ገዳም ለዓመታት በብህትውና ተወስነው የኖሩት ባሕታዊ አባ መብራቱ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በበዓታቸው (በመኖሪያቸው) ውስጥ በግፍ ተገድለው ተገኝተዋል።

ባሕታዊው በዓለማዊ ኑሮ ተለይተው፣ በገዳም ዘግተው ለሀገርና ለቤተክርስቲያን በጸሎት የሚተጉ አባት ቢሆኑም፤ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በመሳሪያ ተደብድበው መገደላቸውን ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በር ዘግተው፣ ዓለምን ንቀው ለሰው ልጆች በሚጸልዩ መናንያን ላይ እንዲህ ያለ ዘግናኝ ድርጊት መፈጸሙ መላውን ምዕመንና የገዳሙን ማህበረሰብ በታላቅ ሀዘን ላይ ጥሏል።

የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን ጋር ያሳርፍልን። ለቤተክርስቲያንና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣል!
"ጻድቃን በሞቱ ጊዜ ሰላም ይሆናሉ፤ በመኝታቸውም ያርፋሉ።" (ኢሳይያስ 57፡2)

በረከታቸው ይደርብን። 🙏🕯️

Via የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ Kutaa Lallabaa Go/Harargee lixaa

አሰቦት ገዳም!  😭😭 የክርስቶስ እንደራሴ የሆኑ ራሳቸው ከሰው ለይተው በበረሃ የሚኖሩ አባቶች  እንዲህ ስገደሉ ከማየት በላይ ሕመም የለም  ይግባኝ ለክርስቶስ ።«ከአቤል ጀምሮ በመሠዊያው እ...
08/02/2026

አሰቦት ገዳም! 😭😭

የክርስቶስ እንደራሴ የሆኑ ራሳቸው ከሰው ለይተው በበረሃ የሚኖሩ አባቶች እንዲህ ስገደሉ ከማየት በላይ ሕመም የለም ይግባኝ ለክርስቶስ ።

«ከአቤል ጀምሮ በመሠዊያው እና በቤተ መቅደሱ ውስጥ እስከ ጠፋው የዘካርያስ ደም ድረስ፥ ከዚኽ ትውልድ እንዲፈለግ፥ በእውነት እላችኋለኹ፤ ከዚኽ ትውልድ ይፈለጋል።» (ሉቃ. ፲፩፥፶፩)።

“Dhiiga Abeelii jalqabee hamma dhiiga Zakaariyaas isa iddoo aarsaa fi balbala mana qulqullummaa gidduutti harka namaatti du'eetti, dhugumaan isinittan hima, dhiigni isaanii dhaloota kana irraa in barbaadama.”Luq 11:21

የከበረች በረከታችሁ፤ድል የማትነሳ ረድኤታችሁ፤ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታችሁ ከኛ ጋር ትሁን።

"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ለዓለም ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት ።

ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ፤ ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ፤ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ።

ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁ፮

የሰማዕታቱ በረከት አይለየን !
Informer

07/02/2026

« አቤቱ አንደበቴ በሞት ሳይዘጋ በፊት የመስቀልህን ምስጋና እናገር ዘንድ አብቃኝ፤ አቤቱ የማይፈታ ሰንሰለት ከመታሠሬ በፊት የደጅህን በር አንኳኳ ዘንድ አብቃኝ። »

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
Birhan

ቤተክርስቲያን የማትፈቅዳቸው በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰሩ ሊወገዙ የሚገባቸው አሁናዊ  ሕገ ወጥ (አሳፋሪ)  አሰራሮች"፩, በየጎዳናው የጥሬና የቆሎ ሽያጭ፣ይህ ነገር አሁን አሁን በየመንገዱ ...
03/02/2026

ቤተክርስቲያን የማትፈቅዳቸው በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰሩ ሊወገዙ የሚገባቸው አሁናዊ ሕገ ወጥ (አሳፋሪ) አሰራሮች"

፩, በየጎዳናው የጥሬና የቆሎ ሽያጭ፣
ይህ ነገር አሁን አሁን በየመንገዱ የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡ የሰው ፍሰት በሚበዛበትና መኪኖቹ በሚንቀሳሱበት አካባቢ (በመስመር ጥግ) የሚገነባም የማይገነባም ቤተክርስቲያን ካለ ወጣቶች የደንብ ልብስ የመሰለ የሆነ ቢጫና ቀይ ወይም አረንጓዴና ቀይ ከለር ያለው ልብስ ይለብሱና መኪና አስቁመው የበቆሎ ንፍሮ ይይዙና ዓርብም ይሁን ረቡዕ ዐቢይ ጾምም ይሁን ጾመ ነነዌ ለበረከት ያዙ ይላሉ አንዱ ጥሬ ሲያሳፍስ አንዱ የሳንቲም መለመኛውን ይዞ ጠጋ ይላል ።
የሚገርመው ደግሞ ስሙ ለበረከት ያዙ ነው የምን በረከት?
👉ጥሬ እየሸጡ በረከት አለ እንዴት?
👉 ጾም እያሻሩ በረከት አለ እንዴት?
👉በሥርዐትውጭ የገንዘብ ልመና የምን በረከት?
👉ሰውን እያሸማቀቁ ሽያጭ እንጂ? በረከት የለም።
ምን አይነት የልመና ስልት ነው? ያሳፍራል ያሸማቅቃልም ሕገ ቤተክርስቲያንም አይደለም።
ይህ ድርጊት ፈጽሞ ሊቆም የሚገባው ነው ።

፪, በየመንገዱ ጥላ ዘቅዝቆ መለመን።
ማንኛውም ንዋየ ቅድሳት የገንዘብ መለመኛ መሆን አይችልም። ምክንያቱም በዓለም ገበያ ላይ የሚውለው ማንኛውም እቃ ወደቤተክርስቲያን እስኪገባ ተራ እቃ ነው ወደቤተክርስቲያን ከገባ በኋላ ግን ቅዱስ ንዋይ ነው። ልብሱም ታቦቱም መስቀሉም ጥናውም... ሁሉም ነገር የቤተ መቅደስ ቅዱስ እቃ የእግዚአብሔር መገልገያ እንጂ የገንዘብ መሰብሰቢያ ሊሆን አይገባም።
ማንኛውም ሰው የክህነት ልብስ መልበስ የክህነት ጥላ ማንጠልጠል? ሥርዐተ ቤተክርስቲያን መጣስ ነው እኮ ስለዚህ በየኬላው ተሰልፋችሁ ቅዱሱን ስዕል በፀሐይ እያከሰላችሁ የአቧራ ማራገፊያ እያደረጋችሁ ጥላውን እየዘቀዘቃችሁ ያለመዓርጋችሁ ይዛችሁ የገንዘብ ድቃቂ የልብስ እላቂ የምትለምኑ ሰዎች እባካችሁ ቤተክርስቲያንን አታዋርዷት?

፫,መስቀል ጨብጠው በየመኪናው እየገቡ ገንዘብ ካላመጣችሁ እያሉ ሃይማኑቱን ስንኳን ሳይለዩ ገንዘብ የሚለምኑ ካህናት ማቆም አለባቸው።
በጣም የሚገርመው ደግሞ መኪናው ውስጥ ገብተው የግድ መስቀል ካልተሳለማችሁ ይላሉ የሚያሳዝነው ሙስሊም ይሁን ፕሮቴስታንት ፓጋን ይሁን ይሁዲዝም ሳይለዩ መስቀሉን ወደያንዳንዱ ግንባር ይልኩታል ጎበዝ በጣም አፈርን እኮ!!?
ምን አለ ለገንዘብ እንዲህ ከመፋጠን ለወንጌል አገልግሎት እንዲህ ብትፋጠኑ ? ምዕመናንም እባካችሁን ለምን የሚል ጥያቄ አንስታችሁ አባሯቸው ይህ የቤተክርስቲያንን ክብር ማስጠበቅ ነው።
በመናኸሪያው መስቀል ይዞ ልመና
በየኬላው ጥላ ዘቅዝቆ ልመና
በየመኪናው መስቀል ጨብጦ ልመና
በየፌርማታው ቃጭል ይዞ ልመና .... በቃን።

፬, በቅዳሴ ወንጌል መሳለም ጊዜ ሙዳየ ምጽዋት ይዞ መዞር፣
በየጊዜው ቤተክርስቲያንን ውጫዊ ፈተና ባያጣትም አሁን ላይ ያለው ውስጣዊ ፈተና ግን ነውርም መሳለቂያም እያደረገን መጥቷል ሥርዐተ ቅዳሴው አልቆ ወንጌል ተነቦ ጻዑ ንዑሰ ክርስቲያን ተብሎ ሕዝቡን ወንጌል ለማሳለም አንዱ ሲወጣ ሁለተኛው ሙዳየ ምፅዋት ይዞ ገንዘብ ይለምናል።
👉ከመቼ ወዲህ የመጣ ሕግና ሥርዐተ ነው?
👉ወንጌል መሳለም ገንዘብ እየከፈሉ የሆነስ መቼ ነው?
👉ወንጌል ተሸክሞ ሙዳየ ምፅዋት ማስከተል ማን የሰራው ሥርዐት ነው?
👉ተዉ እንጂ የሚያስቀድሰውን ሕዝብ አታሳቁት?
👉እኔ እነዚህን ፈጽሜ እቃወማለሁ።
ዘመልአክ ዳግም

የጥምቀት ትምህርት በ፮ ጉዳዮች ይጠቃለላል፡፡ ፩. የጌታን ትሕትና የሚያሳይዮሐንስን አስመጥቶ መጠመቅ ሲችል ርሱ ወደ ዮርዳኖስ መሄዱ፣ ጌታ ሲሆን በባሪያ እጅ መጠመቁ፣ ንጹሐ ባሕርይ ሲሆን እ...
20/01/2026

የጥምቀት ትምህርት በ፮ ጉዳዮች ይጠቃለላል፡፡

፩. የጌታን ትሕትና የሚያሳይ
ዮሐንስን አስመጥቶ መጠመቅ ሲችል ርሱ ወደ ዮርዳኖስ መሄዱ፣ ጌታ ሲሆን በባሪያ እጅ መጠመቁ፣ ንጹሐ ባሕርይ ሲሆን እንደ ኃጥአን መጠመቁ ጥልቅ የሆነውን ትሕትናውን ያሳየናል፡፡

፪. ትስብዕቱን ያስረዳል
በሁሉ የመላ ሲሆን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መሄዱ፣ በክበበ ትስብዕት መጠመቁ ሰው ቢሆን ነው እንጅ በመለኮቱማ ቢሆን ማን ይቀርበዋል? ማንስ ያጠምቀዋል? በምንስ ይጠመቃል?

፫. ትንቢተ ነቢያትን መፈጸሙን ለማጠየቅ
ዮሐንስ ያጠምቃል ጌታ ይጠመቃል እየተባለ ትንቢት ይነገር ነበር፡፡ ወይደልወነ ከመ ንፈጽም ኵሎ ጽድቀ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል ማለቱ ትንቢተ ነቢያትን ልንፈጽም ይገባናል ማለቱ ነውና፡፡

፬. ቤዛነት ስለ እኛ መዳን መጠመቁ
ጌታ መጠመቁ ኀጢአት ኑሮበት አይደለም፡፡ አኮ እንዘ ይጽሕቅ ኅጽበተ ጥምቀት ዘኀጢአት እንዳለ ሊቁ፡፡ ክብር ሽቶም አይደለም፡፡ አኮ ፈቂዶ ለተጠምቁ እንደተባለ፡፡ በመጠመቁም ጸጋ፣ ክብር አላገኘበትም፡፡ አኮ ዘነሥአ ጸጋ ወክብረ በተጠምቆቱ እንዲል፡፡ ለምን ተጠመቀ ቢሉ? ስለ እኛ ተጠመቀ፡፡ እሱ ሲጠመቅ ርኵሰታችን ተወግዶ ንጽሕናን ገንዘብ አደረግን፤ ውኆችን ቀደሳቸው፤ ኀይል አሳደረባቸው፤ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅጸን አደረጋት፡፡

፭. አርአያነት
እናንተም ተጠመቁ ለማለት፣ ጥምቀትን ለመመሥረት ተጠመቀ፡፡ አብ ልጄ ነህ ብሎ መሰከረለት፤ ብትጠመቁ ልጆቼ ናችሁ ሲለን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ተቀመጠበት የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ለመግለጥ ነው፡፡ ብትጠመቁ መንፈስ ቅዱስን እሰጣችኋለሁ ሲል ነው፡፡ ሰማይ መከፈቱም ወደ ሰማያዊት ሀገራችን እንደ ጠራን የሚያጠይቅ ነው፡፡ ይኸ ሁሉ ለእኛ ጥምቀት አርአያ ለመሆን የተከናወነ ነው፡፡

፮. የሥላሴ መገለጥ
የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ አካላዊነት፣ ሦስትነት፣ አንድነታቸው ተገልጧል፡፡ የወልድ የባሕርይ ልጅነት ታውቋል፡፡
እነዚህ ነጥቦች በስፋትና በጥልቀት የሚተነተኑ ናቸው፡፡ ይኸ ትምህርት የራሱ ሥርዐት አለው፡፡ የራሱ ታሪካዊ ሂደት አለው፡፡ ከዚያ ውስጥ የተፈጠረ የሃይማኖታዊና ሥርዐታዊ ትምህርቱ ነጸብራቅ የሆነ ባህል አለ፡፡ በዚህ ሁሉ የታጀበው በዓለ ጥምቀታችን ውበት ነው፡፡

@ሰሎሞን ላመስግን

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912010337

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lisan z Orthodox.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Lisan z Orthodox.com:

Share