መዝሙር እንወቅ

መዝሙር እንወቅ ውዳሴን እናቅርብ

18/08/2026

ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ
በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)

ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ
አዝ======
ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ
አዝ======
በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ - - ሆ ወልደማርያም ነው - -ሆ
ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ
የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ
አዝ======
አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ
ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ
አዝ======
የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ
ከተከመረው - ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ
ከደብረ ታቦር - - ሆ ጌታ ሰለመጣ - ሆ
የተጋገረው - ሆ ሙልሙሉ ይምጣ - ሆ
አዝ======
ኢትዮጵያውያን - -ሆ ታሪክ ያላችሁ - ሆ
ባህላችሁን - ሆ ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ
ችቦውን አብሩት -ሆ እንዳባቶቻችሁ -ሆ
ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ
አዝ======
አባቶቻችን - - ሆ ያወረሱን - - ሆ
የቡሄን ትርጉም - - ሆ ያሳወቁን - - ሆ
እንድንጠብቀው - ሆ ለእኛ የሰጡን - ሆ
ይህን ነውና - - ሆ ያስረከቡን - - ሆ
አዝ======
ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን - - ሆ የሞሉብሽ - - ሆ
በረከታቸው - - ሆ ያደረብሽ - - ሆ
ሁሌም እንግዶች - ሆ የሚያርፉብሽ -ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር -ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
አዝ======
ለሐዋርያት - - ሆ የላከ መንፈስ - - ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ -ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር - ሆ እንድንታነጽ - - ሆ
በቅን ልቦና - ሆ በጥሩ መንፈስ - - ሆ
በረከተ ቡሄ - ሆ ለሁላችን ይድረስ - ሆ
= = = = = =
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
= = = = = =

እንዲሁ እንዳላችሁ - -በፍቅር አይለያችሁ - - በፍቅር
ላመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሳችሁ - - በፍቅር
ክርስቶስ በቀኙ - - በፍቅር ያቁማችሁ - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርጋችሁ - - በፍቅር
እንዲሁ እንዳለን - - በፍቅር አይለየን - - በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሰን - - በፍቅር
አማኑኤል በቀኙ - - በፍቅር ያቁመን - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርገን - - በፍቅር
= = = = = =

26/07/2026

ከጥፋት ሰውረኝ ድረስልኝ ና ና
ምሥራችን ይዘህ የደስታውን ዜና
በእሳቱ መካከል ቆሜ ምዘምረው(፪)
ገብርኤል ኃያሉ ስለረዳኸኝ ነው(፪)

በዕንባ በሐዘን በልቅሶ ውስጥ ያሉ
ገብርኤል ስትደርስ ባንተ ይጽናናሉ
ቂርቆስ ኢየሉጣ ድነዋል ከጥፋት
በውሃው ብትገባ ቀድመህ ከእነርሱ ሞት

ሰላም ለከ ገብርኤል
በነደ እሳት ሥዑል
ሰላም ለከ ገብርኤል
በጌራ ብርሃን ክሉል
አዝ............................
አለብኝ ውለታ ገብርኤል አባቴ
ፈጥነህ ሳትዘገይ ስትደርስ በሕይወቴ
አልሻም ምሥክር ስለ ምልጃህ ስራ
እኔ ጋር ብዙ አለ ስለንተ የሚወራ

ሰላም ለከ ገብርኤል
መልአከ መዊዕ ወኃይል
ሰላም ለከ ገብርኤል
እንተ ክንፍከ ቀሊል
አዝ............................
እነዚያ ወጣቶች ስላንተ ምን አሉ
በባቢሎን ምድር ከእሳት ሲጣሉ
ምስጋናን ሲያቀርቡ ገብተው ከእቶኑ
ስትደርስላቸው ከጥፋት ሲድኑ

ሰላም ለከ ገብርኤል
ጸዋሬ ምሕረት ወሣዕል
ሰላም ለከ ገብርኤል
መልአከ ሰላም ወኃይል
አዝ............................
አለብኝ ውለታ ገብርኤል አባቴ
ፈጥነህ ሳትዘገይ ስትደርስ በሕይወቴ
አልሻም ምሥክር ስለ ምልጃህ ስራ
እኔ ጋር ብዙ አለ ስለንተ የሚወራ

ሰላም ለከ ገብርኤል
መልአከ መዊዕ ወኃይል
ሰላም ለከ ገብርኤል
እንተ ክንፍከ ቀሊል
አዝ............................

ዘማሪት ጽጌ ማርያም ባዬ

ወደ ጋኑ ከመጣላቸው በፊት ቅዱስ ቂርቆስ ወደ እግዚአብሔር ረጅም ጸሎት አደረገ በዚያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የጋኑን መቅለጫ አቀዘቀዘው፣ እሳቱንም እንደ ጠዋት ...
26/07/2026

ወደ ጋኑ ከመጣላቸው በፊት ቅዱስ ቂርቆስ ወደ እግዚአብሔር ረጅም ጸሎት አደረገ በዚያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የጋኑን መቅለጫ አቀዘቀዘው፣ እሳቱንም እንደ ጠዋት ጤዛ አደረገው::

✨ለቂርቆስ ወእየሉጣ የደረስክ ገብርኤል ሆይ እኛንም ከጭንቁ የፈተናው ንዳድ በብስራታዊው ዜናህ አውጣን።🙏✨

21/07/2026

ምን ብዬ የእርሱን ደግነት ልናገር
ወዶኛል ከሁሉ አብልጦ እግዚአብሔር
ተመስገን ክበር ዘለዓለም ልበለው
አምላኬ ያደረገልኝ ብዙ ነው
አዝ..........
አይ የእርሱ ሥራ የእርሱ ደግነት
በየትኛው ቋንቋ ልመስክረለት
ክብሩን እያሰብኩ ልዘምርለት
የልቤን መሻት ፈፅሞልኛል
ይክበር አምላኬ እኔን ወዶኛል
ዘመኔን ሁሉ እጠራዋለሁ
ምስጋናን እንጂ ምን እሰዋለሁ
አዝ..........
ጨለማው ዓለም ብርሃን ሆነ
ጌታ በልቤ ገብቶ ገነነ
ሞቴን በሕይወት እየሸፈነ
ባሪያ አደለሁም ልጁ ነኝ ዛሬ
ያስጎነበሰኝ የለም ቀንበሬ
ተድላና ደስታን ሞላኝ ጌታዬ
ያፌ ምስጋና ውዴ ዜማዬ
አዝ..........
መራራው ኑሮ በእሱ ጣፈጠ
ሳበኝ በፍቅሩ ልቤ ቀለጠ
አዲስ አረገኝ እየለወጠ
ቸር ነው መሃሪ በቀል የለበት
ሁሉን ያዳነ በተገኘበት
ለኔ መልሷል ገጹ ምህረቱን
ዓይኔም አየችው አዳኝነቱን
አዝ..........
ከጠላት ፍርሃት ነፍሴን አድኖ
በጸጋው ግምጃ በደሌን ከድኖ
ከጎኔ ቆሟል ታዳጊ ሆኖ
መታመኛዬ ኃይሌ ጉልበቴ
የማይደፈር አለት ነው ቤቴ
ይክበር አምላኬ በዘመን ሁሉ
የሚወዱትም አሜን ይበሉ

✨የቃል ኪዳንዋ እመቤት የእግዚአብሔር የህጉ ታቦት የሀዲስ ኪዳን ጽላት አንቺ ነሽ አሁንም መድኃኒት ሥጋ ወነፍስ የሚሆን የልጅሽን ደም ከእግር እስከ ራስ ፀጉሬ ቀቢኝ የልጅሽ ደም የነፍስ ደዌ...
23/06/2026

✨የቃል ኪዳንዋ እመቤት የእግዚአብሔር የህጉ ታቦት የሀዲስ ኪዳን ጽላት አንቺ ነሽ አሁንም መድኃኒት ሥጋ ወነፍስ የሚሆን የልጅሽን ደም ከእግር እስከ ራስ ፀጉሬ ቀቢኝ የልጅሽ ደም የነፍስ ደዌ ይፈውሳልና❤️‍🩹✨

20/06/2026

✨መድኃኔዓለም አለ✨

20/06/2026

♡ በቸርነት በይቅታው አሰበን ♡

በቸርነት በይቅርታው አሰበን
በፍቅሩና በምሕረቱ ጎበኘን
አምላካችን በሞቱ ወደደን
አምላካችን በሞቱ ወደደን

ተነጥቆ ሰላም እረፍታችን
ላያድን ላይፈውስ ጽድቃችን
ተጥለን ስንኖር በሞት
በደምህ ወጣን አርነት
በደምህ ወጣን ነጻነት

የጭንቀት የመከራ ዓመት
ተረሳ በኢየሱስ ሞት
በፍጹም ፍቅሩ ወደደን
በሞቱ ከሞት አዳነን
በሞቱ ከሞት አዳነን

ህዝቡን ሲያስጨንቅ የነበረ
የጠላት ቅጥሩ ተሰበረ
ማልቀስ ቀረልን መቅበዝበዝ
ገነት ገብተናል በእርሱ ወዝ
ገነትን ወረስን በእርሱ ወዝ

ሰማይና ምድር ተስማሙ
ታጥበዋልና በደሙ
ነፃነት አዋጅ ተሰማ
አዜምን የጽድቅን ዜማ
ዘመርን የጽድቅ ዜማ

ህዝቡን ሲያስጨንቅ የነበረ
የጠላት ቅጥሩ ተሰበረ
ማልቀስ ቀረልን መቅበዝበዝ
ገነት ገብተናል በእርሱ ወዝ
ገነትን ወረስን በእርሱ ወዝ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

“መሰደጃችን ተሰደደች! ማንቢያችን እራሷ አነባች! በመርበትበት ሄደን በመረጋጋት የምንመጣባትን እሷን መናወጥ አገኛት! ከዓለም ሁከት ማረፊያዋን የዕረፍት ቤት ማረፊያ አሳጧት!ክብር መሄጃ መቀ...
06/06/2026

“መሰደጃችን ተሰደደች! ማንቢያችን እራሷ አነባች! በመርበትበት ሄደን በመረጋጋት የምንመጣባትን እሷን መናወጥ አገኛት! ከዓለም ሁከት ማረፊያዋን የዕረፍት ቤት ማረፊያ አሳጧት!
ክብር መሄጃ መቀመጫ አጥተው እንኳን እምነት ማረፊያቸውን ይዘው ለተሰደዱት ይሁን!
የጥላቻ አበጋዞች አስደንጋጭ ፍርድ ያገኛቸዋል! ለዘላለምም ይዋረዳሉ!”

✨‘’ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥
እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም
ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም ?’’✨

(ራዕ 6:10)

አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)ቅኔ ማህሌቱ በደምህ ረሰረሰመቅደስ ተቃጥሎ መሰውያዉ ፈረሰጮሁ ደናግላን ደም እንባ አለቀሱበቅድሱ ስፍራ ታርዷልና ቄሱአቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር...
03/06/2026

አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
ቅኔ ማህሌቱ በደምህ ረሰረሰ
መቅደስ ተቃጥሎ መሰውያዉ ፈረሰ
ጮሁ ደናግላን ደም እንባ አለቀሱ
በቅድሱ ስፍራ ታርዷልና ቄሱ
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
ሰላም መስሎን ነበር መዉጣት መግባታችን
ለካስ በሾህ ታጥሯል ዙርያው ጎዳናችን
የፅዮን መንገዶች በዕንባ ተሞልተዋል
የሚያምሩት ግንቦችዋ በሌሊት ፈርሰዋል
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
የቁጣህን በትር ማን ይቋቋመዋል
የኃይልህን ጽናት ማንስ ይችለዋል
የሽማግሌው ፊት አልታፈረምና
ከፊት ቀና እንበል እንዴት እንፅናና
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
እንደ ዘካርያስ እንደ እግዚአብሔር ወዳጅ
ወደቁ ብዙዎች ገቡና ካንተ ደጅ
ህፃን አዛዎንቶች ጎበዦቹ ሁሉ
ተሰዉ ለፍቅር አንክድም እያሉ
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
ለዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ

Address

Sentayhubelete@gmail. Com
Addis Ababa

Telephone

+251938594903

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መዝሙር እንወቅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to መዝሙር እንወቅ:

Shortcuts

Share