Apostolic Father's ሐዋርያነ አበው

Apostolic Father's  ሐዋርያነ አበው ⛪️ቤተክርስቲያንን አንተውም የክርስቶስን አካል አንረሳም We will not forget the church and the body of Christ✝️🥰

+ሰባቱ ፡ምስጢራተ ፡ቤተ፡ ክርስቲያን+~~~~~~~~ምሥጢር ፡ ማለት ፡ቃሉ ፡የግሪክ፡ ቋንቋ ሆኖ ፡ቃሉ ፡ከግዕዝና ከአማርኛ፡ በቀጥታ ፡የተወረሰ ፡ሲሆን ፡ትርጉሙም፡ ድብቅ ፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ...
29/12/2025

+ሰባቱ ፡ምስጢራተ ፡ቤተ፡ ክርስቲያን+
~~~~~~~~
ምሥጢር ፡ ማለት ፡ቃሉ ፡የግሪክ፡ ቋንቋ ሆኖ ፡ቃሉ ፡ከግዕዝና ከአማርኛ፡ በቀጥታ ፡የተወረሰ ፡ሲሆን ፡ትርጉሙም፡ ድብቅ ፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ረቂቅ ፣ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን ይኸውም የፍጡር ሚሥጢርና የፈጣሪ ሚስጥር በመባል ይታወቃል፡፡ የፍጡር ምስጢር ሁለት ይዘት አለው፡፡ የሰውና የመላዕክት ምስጢር ይባላል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የፈጣሪ #የእግዚአብሔር ሚስጥር ይህ የከበረ የተወደደ የሚናፈቅ የበረከት ስጦታ ነው፡፡ ብርሃነ አለም ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል በከበረ ቃሉ ገልፆታል፡፡ “እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ /በክርስቶስ/ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱን የነብሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይናገርና ክብር በሞላበት ሀሴት ደስ ይበላችሁ”፡፡ በማለት ስውር ረቂቅ ከሆነው ጸጋ እግዚአብሔር የምንሰጠው ሀብት መሆኑን በማብራራት ገልፆታል፡፡ በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከሚፈጸሙት ሚስጥራት በቁጥር 7 ተወስነው ተቀምጠዋል፡፡ ውሳኔነታቸው ለሰባቱ ሰማያት ስብዐተ እግዚአብሔር ለማይከፈልባቸው ከተሞች ገላጭ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባት ሚስጥራት ቤተክርስቲያን የሚስጥርነታቸው ምክንያት በአይናችን ልናያቸው በእጃችን ልንዳስሳቸው የማንችል ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በእነዚህ ሚስጥራት አማካኝነት የሚሰጡን ስለሆነ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ በንባብ የተሰወረ ብሂል ምስጢር ይባላል ብለው ስውርነቱን ረቂቅነቱን ይናገራሉ፡፡ ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
1. ጥምቀት
~
2. ሜሮን
~
3. ቁርባን
~
4. ክህነት
~
5. ንስሀ
~
6. ቀንዲል
~
7. ተክሊል ናቸው፡፡

1. ሚስጢረ ጥምቀት 👈

ይህ ምሥጢረ ጥምቀት ከኃጢያት ነፃ የምንሆንበት ከዲያቢሎስ አገዛዝ አርነት የምንወጣበት ከእግዚአብሔር በጸጋ የምንወለድበት የምስጢር አይነት ነው፡፡ በቅሰዱሳት መጻህፍት እንደተገለጸው በነብየ እግዚአብሔር በቅዱስ ሕዝቅሌል ት.ሕዝ 36፡25 “ጥሩ ውሀንም ጥምቀትን እረጫችኋለሁ፡ እናንትም ትጠራላችሁ ከርኩስነታችሁም ሁሉ ከጣኦቶቻችሁ ሁሉ አጠራችኋለሁ አዲስ ልብ እሰጣችኋለው” በማለት የዚህን ምስጢር ክብርነት በረከትነት አምልቶ አስፍቶ ተናገሯል፡፡ በዚህ ሀሳብ ሌሎች ንፁሐን አበው ሀዋርያት ተባብረውታል፡፡ በምልአት ሰብከውታል፡፡ የሐዋ.2፡38 ፣ 1ቆሮ 6፡11 ፣ ዮሐ. 3፡5 ፣ ኤፌ 5፡26 ፣ ገላ 3፡27 ፣ ቲቶ 3፡5 ጥምቀት ዳግመኛ ተወልደን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበት ምስጢር ነው፡፡ ከመጸሕፍ #ቅዱስ ውስጥ ጥምቀት ብዙ ምሳሌዎች ይኖሩታል፡፡ እነሆ ከማየአይኅ የዳነበትን መርከብ ቅዱስ ጴጥሮስ የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ገልጾታል፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ምዕመናን ከሐጢያት ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ነውና
ቅዱስ ጳውሎስም እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባህር ተሻግረው ወደምድረ ርስት ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀትን ምሳሌ አድርጎ አመስጥሮታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 10፡1-2 ምዕመናን ባህረ ኃጢያትን ተሻግረው ምድረ ርስተ መንግስተ ሰማያትን የሚወርሱት በጥምቀት ነውና፡፡ ዳግመኛም ይህ ብርሃናዊ ሐዋርያ ጥምቀትን በሞትና በመቃብር ይመስለዋል፡፡ ሮሜ 6፡3-4 ቆላ 2፡12 በሞት ጊዜ ነፍስና ስጋ እንደሚለያዩ በጥምቀትም አሮጌው ሰውነት ይሞታል ይቀበራል አዲስ ሰውነት አዲስ ሕልውናን ይጀምራልና፡፡

2. ምስጢረ ሜሮን👈

#ይህ #ቃል የጽርዕ ቋንቋ #ነው ትርጉሙም መአዛ ያለው የሚያውድ ፣ የሚጣፍጥ፣ #ልብ የሚመስጥ ፣ ጣዕም ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት ነው፡፡ በግዕዝ ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ ከብዙ እጽዋት ተቀምሞ የሚሰራ ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤልን የሚያስተዳድሩ የእግዚያብሔር እንደራሴዎች ነገስታትን መሲሀን የሚባሉት ለዚህ ቅብ ተቀብተው ስለሚነግሱ ነው፡፡ ዘፍ 20፡23 1ኛ ሳሙ 10፡1 ዘዳ 28፡41 1ኛ ሳሙ 9፡6 1ኛ ነገስት 1፡34 ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የቤተመቅደስ ነዋያተ ቅድሳትን አስቀድሞ በዚህ መታተም አለባቸው፡፡ ከተቀቡ በኋላ ለቤተ መቅደስ እንጂ ለተራ አገልግሎት አይውሉም ስለ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ መጽሐፍን የፃፉ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዐት ይሉታል፡፡ 2ኛ ቆሮ 1፡21 ዮሐ 2፡20 ቅብዕን በመንፈስ ቅዱስ ማህተምን ይሉታል፡፡ ኤፊ 1፡13 ፣4፡30 ይህ ቅብዓ ማህተመ ሕይወት በመሆኑ ለአገልግሎት ይውላል፡፡

3. ምሥጢረ ቁረባን👈

ይህ ቃል የሱርስት ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም አምኃ #ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ ሳይገባን በችሮታ ነውና፡፡ በቤተክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መደምደሚ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዜ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና ለእግዚአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡ ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳ ሆነው አልፈዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ሳይታይ የሚወደድን ሕይወት ለማግኘት ከቁርባን በፊት ንስሐ መግባት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም አለበት፡፡ ንጽሕናውን በጠበቅ አለበት፡፡ መምክረ ካህን ጸንቶ መገኘት ያስፈልጋል፡፡

4. ምሥጢረ ክህነት👈

ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ ክህነት የተጀመረው በአባታች አዳም ነው፡፡ ክህነት የአገልግሎት #ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ) በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ 20፡22 ማሬ 18፡18 1ኘና ቆሮ 4፡1 ማሬ 28፡20

5. ምሥጢረ ንስሐ👈

ይህ ቃል የግዕዝ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በሰሩት ኃጢያት መጸጸት ምነው ባልሰራሁት ባላደረኩት ብሎ ማልቀስ ወደ ኃጢያት ላለመመለስ መወሰን፣ በሕጉ ጸንቶ ለመኖር ቃል መግባት፡፡ ክርስቲያን በጥምቀት ከአለም ክፉ ስራዎች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ህይወቱ ለክርስቶስ የተሰጠ ነው፡፡ ሮሜ 12፡1 የመጨረሻው ግቡና ዓላማው ሥርየተ ኃጢያትን ማግኘት እና የዘላለም ሕይወት መወረስ ነው፡፡ አካሉ የመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ 1ቆሮ 6-19

6. ምሥጢረ ቀንዲል👈

ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ ቀንዲል ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩ ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች እየተቀቡ ይፈወሱ ነበር፡፡ ኢሳ 1፡6 ሉቃ 10፡34 ራዕ 3፡18 ማር 6፡13 ይህ ቅብዓተ በሐዲስ ኪዳን ለሚጠመቁ ከሚደረግ ቅብዐ ሜሮን ጋር ግንኙነት የለውም ራሱን የቻለ ሕሙማነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ሕሙማነ ነፍስ ኃጥአን የሚቀቡት ፈውስ የሚያገኙበት ነው፡፡ ማር 6፡13 ያዕ 5፡13-15 ራዕ 1፡17፡፡

7. ምሥጢረ ተክሊል👈

ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም ተከተል መሰረት በመተጫጨት #እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡

ለዚህም ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲረዳን የወላዲተ አማላክ አማላጅነት እንዳይለየን የጻድቃን ፀሎት የቅዱሳን በረከት እንዳይለየን ፈቃዱ ይሁንልን #አሜን

👈 አድርጉት ያላነበበ ያንብበው

https://t.me/Apostolicfathers1

26/12/2025

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን እንሰግዳለን ✝️☦️❤🥰
Apostolic Father's ሐዋርያነ አበው

ከአግማስ ኢትዮጵያ ጀርባ ያለው ድብቅ አጀንዳ (ልዩ መረጃ) ​በደብረብርሃን መጠለያዎች ለዓመታት በረሃብ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን የተላከ 15 ሚሊዮን ብር ሳይደረስ ተመልሷል!​ታዋቂው ባለሀብት አ...
26/12/2025

ከአግማስ ኢትዮጵያ ጀርባ ያለው ድብቅ አጀንዳ
(ልዩ መረጃ)
​በደብረብርሃን መጠለያዎች ለዓመታት በረሃብ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን የተላከ 15 ሚሊዮን ብር ሳይደረስ ተመልሷል!
​ታዋቂው ባለሀብት አቶ ወርቁ አይተነው ለወገኖቻቸው የላኩትን ይህን ግዙፍ እርዳታ "አግማስ ኢትዮጵያ" የተባለው ድርጅት "አልቀበልም" ብሎ ዘግቶባቸዋል።
​ለመሆኑ እርዳታ አልቀበልም የሚል ድርጅት አለ? ለምን?
​የዚህን እንቆቅልሽ መልስ ለማግኘት ወደ ድርጅቱ ቁንጮ እንሂድ። ድርጅቱን የመሰረቱትና የሚመሩት አብዱሰላም ሸፌው ናቸው። ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት በብልፅግና ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው ቢሆንም፣ ታሪካቸው ግን ሌላ ታሪክም ይናገራል

"የድሮው "የወሎ ህብረት" ሴራ
ከአምስት ዓመታት በፊት ወሎን ከአማራ ክልል የመገንጠልና አማራን የማዳከም ስራ ሲያቀነቅኑ ከነበሩት መካከል ዋነኛው ናቸው። ያ የወሎን ህዝብ የመለያየት አጀንዳቸው ሳይሳካ ሲቀር፣ ዛሬ በ"እርዳታ ድርጅት" ስም ብቅ ብለዋል።

"ያልተመለሱ ጥያቄዎች
​የአማራን ህዝብ የመበታተን ሴራ በአዲስ መልክ ቀጥሏል?
​በረሃብ ለሚማቅቁ ወገኖች የመጣን ገንዘብ ማገድ የማን ትዕዛዝ ነው?
​"አግማስ ኢትዮጵያ" የእርዳታ ድርጅት ነው ወይስ የፖለቲካ መጠቀሚያ?
​ህዝቡ እውነታውን ሊያውቅ ይገባል። ይህን መረጃ ለሌሎች በማጋራት (Share በማድረግ) የበኩላችሁን ተወጡ።
Ethio info
​ #አማራ

????
26/12/2025

????

22/12/2025

ለምን እንደሚከፋን ታውቃላችሁ.....
Apostolic Father's ሐዋርያነ አበው

https://user294675.psee.ly/7weny2
17/07/2025

https://user294675.psee.ly/7weny2

ማርያምወለላዬ ማርያም ገመናዬ ማርያምላወድስሽ እኔ ልጅሽ ያለድካም አዝከታናሽነቴ ማርያምጣፍጦኝ እስከዛሬ ማርያምአመሰገንኩሽ ማርያምከዕቅፍሽ ከርሜ ማርያ.....

07/07/2025

ሰኔ 30/2016

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በቅዱስ #ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ #ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

"እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል
ከመጥመቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም" ማቴ.11፥11
በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ሉቃ.1፥14

👉 #ዮሐንስ ፅንሰቱ በብሥራተ መልአክ ነው በወንጌል ተጽፎ እንደምናገኘው ይህ ድንቅ ሁኔታም የአባቱን አንደበት አዘግቷል

👉ሊቀ መላእክት የመጥምቁን አባት ካህኑ #ዘካርያስን ልጅ እንደሚወልድ ባበሠረው ጊዜ ዘካርያስ እድሜ ልኩን ይለምነው የነበረው ልመና በሽምግልናው ወራት ቢፈፀም እውነት አልመስልህ ብሎት የመልአኩን ቃል ለመቀበል ዘገየ በዚህም የተነሳ ልጁ እስኪወለድ ድረስ ዲዳ ሆነ

👉 ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቱ ቅድስት ኤሳቤጥን ልትጠይቅ በመጣች ጊዜ የሰላምታዋን ድምፅ ሰምቶ በደስታ የዘለለ ለክብሯም የሰገደ እድለኛ ነው ይህን ከእርሱ በፊት ማን አድርጎታል ከእርሱ በኋላስ የትኛው ቅዱስ ደግሞታል

👉 ብዙዎች ደስ የተሰኙለት የጌታን መምጣት አብሣሪ ፣ የመንገዱም ጠራጊ ለመሆን በመመረጡ ታላቁ መጽሐፍ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱ መካከል አልተነሳም

👉ብሎ የመሰከረለት ፃድቅ ደስታን የሰጠ ንፁሕ በፅንሰቱ ጊዜ የተዘጋውን የአባቱን አንደበት ስሙን በፅሑፍ እያስከተበ ፊደሉን በቃል አናብቦ ዲዳነቱን ያስፈታ በቤታቸውም ተድላን የሞላ

👉አባታችን መጥምቀ መለኮት ድንግላዊ ካህን፣ባህታዊ፣ነብይ፣አጥማቂ ፣ሐዋርያ፣ሰማእት ነዉ

👉 ከልጅነቱ ጀምሮ በበረሀ የኖረ መናኝ ባህታዊ ነው የፊቱን አውቆ የተናገረ ነቢይ ነው መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሀ ግቡ እያለ የሰበከ ቀዳሚ ሐዋርያ ነው አንገቱን በሰይፍ የተቀላ ሰማእት ነው

👉ዛሬ ሰኔ 30 ልደቱን እናከብራለን በረከትና ረድኤቱ በእኛ ላይ ይሆንልን ዘንድም እንለምነዋለን የቅዱሳን ፀሎታቸው ይጠብቀን የተባረከ ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ምሥጢረኛዬ ነሽ

ሰኔ 30/2016   👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   በቅዱስ  #ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ  #ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት ክብረ በዓል እንኳን ...
07/07/2025

ሰኔ 30/2016

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በቅዱስ #ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ #ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

"እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል
ከመጥመቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም" ማቴ.11፥11
በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ሉቃ.1፥14

👉 #ዮሐንስ ፅንሰቱ በብሥራተ መልአክ ነው በወንጌል ተጽፎ እንደምናገኘው ይህ ድንቅ ሁኔታም የአባቱን አንደበት አዘግቷል

👉ሊቀ መላእክት የመጥምቁን አባት ካህኑ #ዘካርያስን ልጅ እንደሚወልድ ባበሠረው ጊዜ ዘካርያስ እድሜ ልኩን ይለምነው የነበረው ልመና በሽምግልናው ወራት ቢፈፀም እውነት አልመስልህ ብሎት የመልአኩን ቃል ለመቀበል ዘገየ በዚህም የተነሳ ልጁ እስኪወለድ ድረስ ዲዳ ሆነ

👉 ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቱ ቅድስት ኤሳቤጥን ልትጠይቅ በመጣች ጊዜ የሰላምታዋን ድምፅ ሰምቶ በደስታ የዘለለ ለክብሯም የሰገደ እድለኛ ነው ይህን ከእርሱ በፊት ማን አድርጎታል ከእርሱ በኋላስ የትኛው ቅዱስ ደግሞታል

👉 ብዙዎች ደስ የተሰኙለት የጌታን መምጣት አብሣሪ ፣ የመንገዱም ጠራጊ ለመሆን በመመረጡ ታላቁ መጽሐፍ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱ መካከል አልተነሳም

👉ብሎ የመሰከረለት ፃድቅ ደስታን የሰጠ ንፁሕ በፅንሰቱ ጊዜ የተዘጋውን የአባቱን አንደበት ስሙን በፅሑፍ እያስከተበ ፊደሉን በቃል አናብቦ ዲዳነቱን ያስፈታ በቤታቸውም ተድላን የሞላ

👉አባታችን መጥምቀ መለኮት ድንግላዊ ካህን፣ባህታዊ፣ነብይ፣አጥማቂ ፣ሐዋርያ፣ሰማእት ነዉ

👉 ከልጅነቱ ጀምሮ በበረሀ የኖረ መናኝ ባህታዊ ነው የፊቱን አውቆ የተናገረ ነቢይ ነው መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሀ ግቡ እያለ የሰበከ ቀዳሚ ሐዋርያ ነው አንገቱን በሰይፍ የተቀላ ሰማእት ነው

👉ዛሬ ሰኔ 30 ልደቱን እናከብራለን በረከትና ረድኤቱ በእኛ ላይ ይሆንልን ዘንድም እንለምነዋለን የቅዱሳን ፀሎታቸው ይጠብቀን የተባረከ ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Address

Adis Ababa
Addis Ababa
1000

Telephone

+251909537593

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apostolic Father's ሐዋርያነ አበው posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Apostolic Father's ሐዋርያነ አበው:

Share