Ethiopian Orthodox Tewahedo Church(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ethiopian Orthodox Tewahedo Church(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (Amharic: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን) It is not connected with the Ethiopian Catholic Church, a Chalcedonian church.
(452)

Religion

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (Amharic: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን; Transliterated Amharic: Yäityop'ya ortodoks täwahedo bétäkrestyan) is the predominant Oriental Orthodox Christian church in Ethiopia. The Ethiopian Church was administratively part of the Coptic Orthodox Church until 1959, when it was granted its own Patriarch by Coptic Orthodox Pope of Alexandria and Patriarc

h of All Africa, Cyril VI. One of the few pre-colonial Christian churches of sub-Saharan Africa, the Ethiopian Church has a membership of between 40 and 45 million, the majority of whom live in Ethiopia, and is thus the largest of all Oriental Orthodox churches. The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is a founding member of the World Council of Churches. Tewahedo (Ge'ez ተዋሕዶ) is a Ge'ez word meaning "being made one" or "unified". This word refers to the Oriental Orthodox belief in the one single unified Nature of Christ; i.e., a belief that a complete, natural union of the Divine and Human Natures into One is self-evident in order to accomplish the divine salvation of humankind, as opposed to the "two Natures of Christ" belief (unmixed, but unseparated Divine and Human Natures, called the Hypostatic Union) which is held by the Roman Catholic and Eastern Orthodox churches. According to the Catholic Encyclopedia article on the Henotikon, around 500 bishops within the Patriarchates of Alexandria, Antioch and Jerusalem refused to accept the Dyophysitism (two natures) doctrine decreed by the Council of Chalcedon in 451, thus separating themselves from the main body of the Christian Church (which would later split in the 11th century, for different reasons, into the Roman Catholic and Eastern Orthodox churches). The Oriental Orthodox Churches, which today include the Coptic Orthodox Church of Alexandria, the Armenian Apostolic Church, the Syriac Orthodox Church, the Malankara Orthodox Church of India, the Ethiopian Orthodox Church, and the Eritrean Orthodox Tewahedo Church, are referred to as "Non-Chalcedonian", and, sometimes by outsiders as "monophysite" (meaning "One Single Nature", in reference to Christ). However, these Churches themselves describe their Christology as miaphysite (meaning "One United Nature", in reference to Christ; the translation of the word "Tewahedo").

21/08/2025
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጸባዕት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ገ...
14/01/2025

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጸባዕት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ገብቷል፡፡
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ተጠናቆ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቡራኬ ተመርቋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች፣ እና የገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አመ ፲ ወ፬ ለየካቲት ወበዛቲ ዕለት አእረፉ ፬ቱ  ገዳማውያን ዘደብረ ከዋክብት ዘትሰመይ ዝቋላ እንተ ይዕቲ መካኑ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ...
23/02/2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አመ ፲ ወ፬ ለየካቲት ወበዛቲ ዕለት አእረፉ ፬ቱ ገዳማውያን ዘደብረ ከዋክብት ዘትሰመይ ዝቋላ እንተ ይዕቲ መካኑ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወብዙኃን ገዳማውያን ይነብሩ ውስቴታ በተፋቅሮ ወበሰላም እንዘ ይጼልዩ ለኲሉ ዓለም ወኲሎሙ ምእመናን ይመጽኡ ኃበ ዛቲ መካን ከመ ይንስኡ በረከቶ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወጸሎቶሙ ለአበው ገዳማውያን ወኅቡረ ያከብሩ በዓሎ ለአቡሆሙ ወይትመየጡ በፍሥሐ እንዘ ይዜምሩ ወይሴብሁ

ወተንሥኡ እኩያን ሰብእ ላዕለ ሀገር ዘይጸልእዋ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ዘይብሉ ኢንርዐያ ለቤተ ክርስቲያን ወኢነኃስስ ከመ ንርዓይ ዘኰነ ክርስቲያናዌ በውስተ ምድርነ ወኮኑ ዘይቀትልዎሙ ለንጹሐን ምእመናን ኲለሄ እንበለ አበሳ ቦ ዘአውዓይዎ በእሳት ወቦ ዘጠብህዎ በመጥባህት ቦ ዘወገርዎ በእብን ወቦ ዘሰሀብዎ በሀብል ላዕለ ምድር ወየዐግቱ ንጹሐነ ወይብልዎሙ ለአዝማዲሁ አምጽኡ ብሩረ ከመ ንህድጎ ወይትዌከፉ ብዙኀ ብሩረ ወእምድኅረ ተወክፉ ብሩረ ኢየሀድግዎ ለዘዐገትዎ አላ ይቀትልዎ በግፍዕ

ወመጽዑ እሙንቱ እኩያን ሀበ መካኑ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እንተ ይእቲ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት ወይቤልዎሙ ለመነኮሳት ሁሩ ኀዲገክሙ ዘንተ መካነ አቡክሙ ወአምጽኡ ንዋየ ገዳም ወበከዩ መነኮሳት እንዘ ይብሉ አይቴ ነሐውር ሐዲገነ መካነ አቡነ ገብረ ሕይወት ወንዋየ ገዳምኒ ንዋየ ምእመናን ውእቱ ወኢንሁቦ ለባእድ ወሶበ ሰምኡ ዘንተ እኩያን ሰብእ ተምዑ ላዕለ ገዳማውያን ወአጥፍኡ ትእምርተ ሀገር እምላዕለ ከኒሳሁ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወመነኮሳትሂ ጸንዑ በእምነቶሙ ወመሰልዎ ለአቡሆሙ ገብረ ሕይወት ወእኩያንሂ ወሰኩ እከየ ላዕለ እከይ ወወሰዱ መንገኒቀ ዘገዳም ዘይእኅዝዎ አቃብያነ ገዳም ወንዋየ ገዳም ወእምድኅረዝ አመ ፲ወ፫ ለየካቲት ወሰዱ ፭ተ መነኮሳተ እምዝንቱ መካን ወቀተልዎሙ ለመጋቤ ገዳም ወጸኃፌ ማኅበር ወመምኅረ መጽሐፍ ወረድዕ ዘኁልቆሙ ፬ቱ ወለ አሐዱሰ ሰደድዎ እንዘ ይብሉ ሑር ንግር ከመ እፎ ቀተልናሆሙ ወመነኮሳትሰ መሰልዎሙ ለሰማእታት ቅዱሳን በሰማዕትና ወኪያነሂ ይምሐረነ በጸሎቶሙ ለእሙንቱ ሰማእታት ለዓለመ ዓለም አሜን

ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ በጾመ ነነዌ  የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ...
05/02/2023

ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ

በጾመ ነነዌ የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡

በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜንከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅበመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክር...
04/02/2023

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡
መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡
ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤
2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ
4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በምህላ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

'' ንቁም በበሕላዊነ ''''በእያለንበት እንቁም''ቅዱሳን መላክት ማን እንደፈጠራቸው በጠየቁበት ግዜ አሳቻው ዲያቢሎስ (ሳጥናኤል) እኔ ነኝ የፈጠርኳችው ብሎ በተናገረበት ሰዐት ቅዱስ ገብርኤ...
22/01/2023

'' ንቁም በበሕላዊነ ''

''በእያለንበት እንቁም''

ቅዱሳን መላክት ማን እንደፈጠራቸው በጠየቁበት ግዜ አሳቻው ዲያቢሎስ (ሳጥናኤል) እኔ ነኝ የፈጠርኳችው ብሎ በተናገረበት ሰዐት ቅዱስ ገብርኤል ፈጣሪያችንን እስክናቅ ድረስ ''በእያለንበት እንቁም'' እንዳለው ።
እውነትን እስክናቅ ድረስ በአባቶቻችን ቃል ፀንተን እንቁም።

''ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ክብርት ቤተክርስቲያን እናምናለን ''

12/01/2023

kuskammaryam's short video with ♬ original sound

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ :የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ...
04/11/2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ :
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻውን ሥርዓተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ዕድገት ለአገራችን ማህበራዊና ልማታዊ ክንውን እንዲሁም ለመላው ሕዝባችን ሰላምና አንድነት ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡

በዚሁመሠረት፡-

1.የዚሁ የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መከፈቱን በማስመልከት የተደመጠው የመክፈቻ ንግግር

2.የሕዝባችንና የቤተ ክርስቲያናችን ሰላም ተጠብቆ እንዲኖር ማድረግ እንዲቻል፣

3.በአገራችን በሰሜኑ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ከቀያቸው ስለተፈናቀሉና በአጠቃላይ በችግር ላይ ስለሚገኙ ወገኖቻችን መደረግ ስለሚገባው እገዛ፣

4.በቀጣይም የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ዕድገት ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ በመሆኑ ምልዓተ ጉባኤው በዚሁ ላይ በስፋት ተነጋግሮ ለተግባራዊነቱ የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

5.የ2015ዓ.ም. የመንበረ ፓትርያርክ አለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ያሳለፈውን የጋራ መግለጫ በመመርመርና አስፈላጊ ማሻሻያዎችን በማድረግ የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ጉባኤው አጽድቋል፡፡

6.የ2015ዓ.ም. የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የዓመቱን በጀት ድልድል አስመልክቶ ጉባኤው በስፋት ከተነጋገረ በኋላ የቀረበውን በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

7.ከ2007ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውን ሕገ ቤተክርስቲያን ወቅቱን በዋጀ መልኩ በማስጠናት መልካም አስተዳደርን ሊያሰፍን በሚችል ሁኔታ ተሻሽሎ በቀረበው ረቂቅ ላይ በመነጋገር ማሻሻያዎችን በማድረግ ረቂቅ ደንቡን አጽድቋል፡፡ በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

8.የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ካህናትና ምእመናን የሚያጋጥሟቸው ችግሮች ቀኖና ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ በመንፈሳዊ ዳኝነት መታየትና ፍትሕ ማግኘት እንዲችሉ ለማስቻል በባለሙያ ተዘጋጅቶ የቀረበው የመንፈሳዊ ፍ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በምልዓተ ጉባኤ ጸድቋል፡፡

ከዚሁ ጋር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ማህበራዊና መንፈሳዊ የሥራ ሂደት ጠቃሚ የሆኑ ልዩ ልዩ ረቂቅ ደንቦችን መርምሮ በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡

8.በቤተ ክርስቲያናችን ሕጻናትና አስተዳደግ ድርጅት አገልግሎት የሚገኘው ምግባረ ሠናይ ሆስፒታል በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል የማሻሻያ ሥራ እንዲሠራ በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያናችን በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ሆስፒታል እንዲገነባ የቀረበውን ጥናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጽድቋል፡፡

9.በአገራዊ ሰላምና አንድነት ላይ የተነጋገረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰላም ለአገራችን ሕዝቦች አንድነትና ለቀጣይ በልማታዊ እድገት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማየት መሠረት መሆኑን ሁሉም ተገንዝቦ አገራዊ እርቀ ሰላም እንዲወርድ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ ከዚሁም ጋር አገራዊ ሉአላዊነትን በሚዳፈር መልኩ እየታየ ያለውን የውጭ መንግሥታት ጣልቃ ገብነት እንዲቆም ጉባኤው አሳስቧል፡፡


10.በሰሜኑ አገራችንም ሆነ በውጭው ዓለም አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያናችን ማዕከላዊ አሠራር ላይ እያሳዩት ያለው አካሄድ ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለአገራዊ አንድነታችን መጠበቅ ሲባል እንደገና በሰከነ መንፈስ ታይቶ ወደነባሩ ማዕከላዊ አስተዳደርና አሠራር እንዲመለሱ ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ መልካም አስተዳደር በሁሉም አቅጣጫ እንዲሰፍን አገራዊ አንድነትና ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አህጉረ ስብከት ከምንግዜውም በላይ ተጠናክረው እንዲሠሩ ለማስቻል ምልዓተ ጉባኤው በሰፊው መክሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

10.የቤተ ክርስቲያኒቱ አእምሮአዊ ሀብት ንብረትና የቱሪዝም ቅርሶቻችንን አስመልክቶ በቀረበው የባለሙያ ጥናት ላይ የተነጋገረው ምልዓተ ጉባኤ ጥናቱን በማጽደቅ በተግባር እንዲተረጐም ወስኗል፡:

11. አገራችንን በልማት አሳድጐ ሕዝባችንን ከረሀብና ከድህነት ለማላቀቅ በማሰብ ግንባታው ከዓመታት በፊት ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ሕዝባችን እየተረባረበ ያለበት የዓባይ ግድብ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እስከሚደርስ በቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በሁሉም ዘንድ አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር እንዲቀጥል ምልዓተ ጉባኤው ጥሪ አቅርቧል፡፡
12.እስከአሁን ድረስ በቤተ ክርስቲያናችን የሚገኙ መንፈሳዊ ኮሌጆች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን በመገንዘብና ለትምህርት አስፈላጊው ትኩረት እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ባስቀመጠው አቅጣጫ ተጨማሪ ከሦስት ያላነሱ መንፈሳዊ ኮሌጆች መጨመራቸው ሥራም መጀመራቸውን ጉባኤው ተመልክቶ ኮሌጆቹ በቀጣይም በእቅድና የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ በጠበቀ መልኩ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝቧል፡፡

13. ልማት ለቤተ ክርስቲያናችን ብሎም ለአገራችን እድገት ለሕዝባችን የኑሮ መሻሻል በእጅጉ አስተዋጽኦው የጐላ መሆኑን በመገንዘብ በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓመታዊ በዓላትን ለማክበር ለሚገኙ ምዕመናን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሠረታዊ ልማት ለመተግበር እንዲቻል ጉባኤው ተነጋግሮ ለተግባራዊነቱ የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

14. ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው ጦርነት አገራችንና ሕዝባችን ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ቤተ ክርስቲያናችንም የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ ሆና ካህናቶቿና ምእመናን ተከታዮቿ ለሞትና ለስደት መዳረጋቸው አብያተ ክርስቲያናት መፍረሳቸውና መቃጠላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም በአሁኑ ጊዜ ይኸው ጦርነት እንዲያበቃ አገራዊ ሰላምና አንድነት እንዲጠበቅ ትኩረት ባደረገ መልኩ በደቡብ አፍሪካ የተደረሰውን ስምምነት ቤተ ክርስቲያናችን በእጅጉ የምትደግፈውና በተደረሰው ስምምነት መሠረት ሰላሙ ፍጻሜ እንዲያገኝ የበኩሏን አስተዋጽኦ የምታበረክት ሲሆን ሁሉም አካል ለሰላሙ መገኘት በትኩረት እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ በኦጽንኦት ያስገነዝባል፡፡ ይህ በቅዱስ ሲኖዶሱ ሁልጊዜም በጉጉት ሲጠበቅ፣ ጸሎት ሲጸለይበትና የሰላም ጥረት ሲደረግበት የቆየ በመሆኑ አሁንም በየአቅጣጫው አገራዊ ሰላም እንዲሰፍን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

15. በየአህጉረ ስብከቱ ያለውን መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት ክንውን የገመገመው ምልዓተ ጉባኤ ለአብያተ ክርስቲያናት መልካም አስተዳደር ዕድገትና ለሰላም መስፈን ትኩረት በመስጠት በአንዳንድ አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶች ዝውውርና ምደባ አድርጓል፡፡



16. በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙት የሶሪያ አንጾኪያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የግብጽ አሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የቂልቅያ ሊባኖስ መንበር የሆኑት እነዚህ ሦስቱ አብያተ ክርስቲያናት በግብፅ ሀገር ከጥቅምት 8-10 በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከኦክቶበር 18 እስከ 20 ድረስ ባካሄዱት የመሪዎች ጉባኤ በሰጡት መግለጫ በቅድሰት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ይዞታችን አስመልክቶ የሰጡት አሳዛኝ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በትኩረት ተመልክቶታል፡፡

እነዚሁ አብያተ ክርስቲያናት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የቤተ ክርስቲያናችን በሆነ የይዞታ ላይ የሰጡት የተሳሳተ መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንና የአገራችንን ኢትዮጵያ ክብር የሚነካ ስለሆነ ጉባኤው በእጅጉ ተቃውሞታል፡፡ አብያተ ክርስቲያናቱም የሰጡትን መግለጫ መልሰው እንዲያጤኑትና የማረሚያ መግለጫ እንዲሰጡ የኢፌዲሪ መንግሥትም በጉዳዩ ጥብቅ ክትትል እንዲያደርግበት ጉባኤው ጥሪውን ቅርቧል፡፡



17. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከጥቅምት 21-27/2015 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ዕለታት ለምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ማስፈጸሚያ ባዘጋጀው የአንድ ሱባዔ የጸሎት ሳምንት፡-

- ለአገራችንና ብሎም ለአለማችን ፍጹም ሰላም፣

- ለሕዝቦች አንድነትና ሰላማዊ ኑሮ መገኘት፣

- በጦርነት ምክንያት ከቄያቸው ለተፈናቀሉና

- በልዩ ልዩ ወረርሽኝ በሽታ ለተያዙ ምሕረትና ጤና እንዲያገኙ፣

እንዲሁም በጦርነትና በማንኛውም አጋጣሚ ውድ ሕይወታቸው ያጡ ወገኖቻችን እረፍተ ነፍስን እንዲሰጣቸው ሁሉን ቻይ ወደሆነው እግዚአብሔር በሱባኤ የሰነበተ ሲሆን በቀጣይም ለአገራችንና ለሕዝባችን ፍጹም ሰላም መገኘት መላው ካህናትና ምእመናን በጸሎት እንዲተጉ ጉባኤው አሳስቧል፡፡

በመጨረሻም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በስብሰባ በሰነበተባቸው ዕለታት በቤተ ክርስቲያናችን የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ላይ በስፋት በመነጋገር መንፈሳዊ አገልግሎቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ልማታዊው ተግባር ትኩረት ተሰጥቶት እንዲከናወን ለህብረተሰቡ ሊደረግ የሚገባው ማህበራዊ ጉዳዮች አስፈላጊው ክትትል እንዳይለያቸው በተለይም በአገራዊ ሰላምና አንድነት ላይ በሁሉም አካባቢዎች የተጠናከረ ሥራ እንዲሠራ በማስገንዘብ ከጥቅምት 11 ቀን 2015 እስከ ጥቅምት 25 ድረስ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት ዘግቷል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!! አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Address

Addis Ababa
1592

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Orthodox Tewahedo Church(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share