EECMY Gogale congregation ጎጋሌ ከተማ መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • EECMY Gogale congregation ጎጋሌ ከተማ መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን

EECMY Gogale congregation ጎጋሌ ከተማ መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን እንዲህም አላቸው፦ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፡ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።

 :- የዛሬዉ ዕለት ጥቅስ    ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም         ጎጋሌ
25/08/2026

:- የዛሬዉ ዕለት ጥቅስ

ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም
ጎጋሌ

የሚያስጨንቀንን የትኛዉንም ነገር በእርሱ ላይ እንጣል ፣እርሱ ስለእኛ ያስባልና!!መልካም ምሽት!
23/08/2026

የሚያስጨንቀንን የትኛዉንም ነገር በእርሱ ላይ እንጣል ፣እርሱ ስለእኛ ያስባልና!!

መልካም ምሽት!

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆች ቀን በማህበራችን በድምቀት ተከበረ።የዕለቱ መሪ ጥቅስ:- ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። ም...
23/08/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆች ቀን በማህበራችን በድምቀት ተከበረ።

የዕለቱ መሪ ጥቅስ:- ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። ምሳሌ 22÷6 ያለዉ ክፍል ስሆን ፣ርዕስ:- ጠንካራ ቤተሰብ; ስኬታማ ትዉልድ በሚል መሪ ቃል በመላው ሀገራችን ማህበረ ምዕመናን የሚከበረዉ የልጆች ቀን በማህበራችን በተለያዩ ዝግጅቶች ማለትም በአምልኮ ፣በእግዚአብሔር ቃል በመካፈል በድራማና ጭዉዉት እንዲሁም ስጦታ በማቅረብ በድምቀት ተከብሮ ዉሏል።

በዕለቱ የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈሉልን ቄስ በድሉ ፈለቀ ስሆኑ 1ኛ ጴጥሮስ 5÷6-7 ያለዉን ስፍራ ከእግዚአብሔር ባህሪያት አንዱ የሆነዉን እግዚአብሔር በራሱ ግዜ የሚሰራ አምላክ ነዉ በሚል ርዕስ በዝርዝር አስተምሮናል። በቃሉ መገለጥ ያስደነቀን እግዚአብሔር አምላክ ክብሩን ጠቅልሎ ይዉሰድ። ክብር ሁሉ ለኢየሱስ ይሁን!!

በዛሬዉ ዕለት የሚገርም ግዜ እግዚአብሔር ሰጥቶናል በቃል ተናግሮናል ፣በዝማሬ አገልግሎት አስደንቆናል ፣በልጆች ድራማ የራሱን ክብር ገልጦልናል በሁሉም ነገር አብሮነቱን አሳይቶልናል። ይህን ሁሉ አድርጎ ያስደነቀን ሀያሉ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረስ!!

ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
ጎጋሌ

በማስተባበሪያዉ ጽ/ቤት አማካኝነት ተዘጋጅቶ ስሰጥ የነበረዉ የመሪዎችና ወንጌላውያን ቄሶች ሥልጠና ተጠናቀቀ።ባለፉት ሶስት ቀናት ከነሐሴ 15 እስከ 17/2018 ዓ.ም ድረስ በማርታ ማሌ ማስተ...
23/08/2026

በማስተባበሪያዉ ጽ/ቤት አማካኝነት ተዘጋጅቶ ስሰጥ የነበረዉ የመሪዎችና ወንጌላውያን ቄሶች ሥልጠና ተጠናቀቀ።

ባለፉት ሶስት ቀናት ከነሐሴ 15 እስከ 17/2018 ዓ.ም ድረስ በማርታ ማሌ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በጎጋሌ ከተማ ለማህበረ ምዕመናን መሪዎች ፣ወንጌላውያንና ቄሶች በመሪነት ፣በማስተዳደር እና ስለጋብቻ ዙሪያ ስሰጥ የቆየዉ ሥልጠና ተጠናቋል።

ሥልጠናዉን በማስተባበሪያዉ ስር ካሉ ማህበረ ምዕመናን መሪዎች ፣ወንጌላዊያንና ቄሶች ተገኝተዉ የተከታተሉ ስሆን በተሰጡ ሥልጠና ርዕሶች በቂ ትምህርትና ግንዛቤ ያገኙ መሆናቸዉን በሰጡት አስተያየት የገለጹ ስሆን በቀጣይም በዚህ ልክ ሥልጠናዎች ተዘጋጅተው መሰጠት እንዳለበትም ጭምር ገልጸዋል።

ሥልጠናዉ ከደቡብ ኢትዮጵያ ርሆቦት በመጡት ቄስ በድሉ ፈለቀ አማካኝነት የተሰጠ ስሆን ከላይ በተጠቀሱ ርዕሶች ዙሪያ ከሥልጣኙ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት አጠቃለዋል።

ይህንን ሥልጠና የተለያዩ ርዕሶች አዘጋጅቶ በቂ ትምህርትና ግንዛቤ የሰጡትን የስኖዶሳችን ቄስ የሆኑትን ቄስ በድሉ ፈለቀን ከልብ እናመሰግናለን እንላለን።

ስለነበረን አስደናቂ ግዜ የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን። ክብር ሁሉ ለኢየሱስ ይሁን።

ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
ጎጋሌ

ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም የልጆች ቀን በማህበራችን በድምቀት ይከበራል!እንኳን ለልጆች ቀን በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን!
22/08/2026

ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም የልጆች ቀን በማህበራችን በድምቀት ይከበራል!

እንኳን ለልጆች ቀን በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን!

22/08/2026
ሁለተኛ ቀኑን የያዘዉ የመሪዎች ሥልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል።የመሪዎችና ወንጌላዊያን ቄሶች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ የሚሰጠዉ ሥልጠና ዛሬ ሁለተኛ ቀን ዉሎ ስለጋብቻ ዙሪያ እየተሰጠ ይገኛል።    ...
22/08/2026

ሁለተኛ ቀኑን የያዘዉ የመሪዎች ሥልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የመሪዎችና ወንጌላዊያን ቄሶች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ የሚሰጠዉ ሥልጠና ዛሬ ሁለተኛ ቀን ዉሎ ስለጋብቻ ዙሪያ እየተሰጠ ይገኛል።

ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም
ጎጋሌ

ወንድም ኤፍሬም ታሪኩ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆችና ወጣቶች መምሪያ ዳይሬክተር ሆነው ተመርጠዋል።መልካም የአገልግሎት ግዜ እንድሆንለት እንመኛለን!!
22/08/2026

ወንድም ኤፍሬም ታሪኩ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆችና ወጣቶች መምሪያ ዳይሬክተር ሆነው ተመርጠዋል።

መልካም የአገልግሎት ግዜ እንድሆንለት እንመኛለን!!

  የዕለቱ ጥቅስተግተን እንጠብቅ!!            ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም                  ጎጋሌ
22/08/2026

የዕለቱ ጥቅስ

ተግተን እንጠብቅ!!

ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም
ጎጋሌ

Address

Gogale, Garda Marta
Addis Ababa

Telephone

+251919322193

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EECMY Gogale congregation ጎጋሌ ከተማ መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share