ነገረ መለኮታዊ ምልከታ

ነገረ መለኮታዊ ምልከታ we will see about some biblical and theological explanation and to share some sound doctrinal issues

"ቤተክርስቲያን የሌላቸው የቤተክርስቲያን አቃቤ እምነቶች" (Churchless Apologists)በአሁኑ ዘመን በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ እያደገ የመጣ አንድ ትልቅ ትዝብት አለ፤ እርሱም ስለ ክ...
14/07/2026

"ቤተክርስቲያን የሌላቸው የቤተክርስቲያን አቃቤ እምነቶች"

(Churchless Apologists)

በአሁኑ ዘመን በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ እያደገ የመጣ አንድ ትልቅ ትዝብት አለ፤ እርሱም ስለ ክርስትና እውነትነት በአደባባይና በማህበራዊ ሚዲያ የሚሟገቱ፣ ነገር ግን ራሳቸው ከተጨባጩ የቤተክርስቲያን ኅብረትና ሥርዓት ውጪ የሆኑ ወገኖች ጉዳይ ነው።

"ብልት ያለ አካል" አይኖርም ፦ ሐዋርያው ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን ከአካል ጋር ያነጻጽራታል ።

ዐይን ወይም እጅ ብቻውን ሊኖር እንደማይችል ሁሉ ፣ አማኝም ምንም ያህል እውቀት ቢኖረው ከአካሉ (ከቤተክርስቲያን) ተለይቶ ሕያው ሊሆን አይችልም (፩ኛ ቆሮ. ፲፪፥፲፬-፳፯) ።

ቤተክርስቲያን "የእውነት ዓምድና መሠረት" ናት (፩ኛ ጢሞ. ፫፥፲፭ ) ።

ራስን ከዚህ ዓምድ አውጥቶ እውነትን ለመከላከል መሞከር መሠረተ-ቢስ መሆን ነው ።

የጥንት አባቶች ለእውነት ሙግት ትልቅ ቦታ ቢሰጡም፣ ከቤተክርስቲያን ውጪ የሚደረግን ሩጫ ግን ፈጽሞ አይቀበሉትም ነበር ።

ሰማዕቱ ቅዱስ ቆጵሪያኖሱ (Cyprian of Cahtrage ) ፦ "ቤተክርስቲያንን እናቱ ያላደረገ፣ እግዚአብሔርን አባቱ ሊያደርግ አይችልም።"

ቅዱስ አውግስጢኖስ (St Augustine of Hippo) ፦ በሰዎች ድክመት ምክንያት ሰበብ ፈጥሮ ከጉባኤ መውጣትና በውጪ ሆኖ መሟገት መንፈሳዊ ዕውርነት ነው ።

ጆን ካልቪን (John Calvin ) ፦ ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ቤተክርስቲያን "እናት" መሆኗንና ከእሷ ጉባኤ መለየት እጅግ አደገኛ ነው ።

የአውግስበርግ መግለጫ (1530) ፦ እውነተኛ ቤተክርስቲያን ወንጌል በንጽሕና የሚሰበክባትና ቅዱሳት ምስጢራት (Sacraments) በአግባቡ የሚታደሉባት ስፍራ ናት ።

ከዚህ ውጪ "የክርስቲያን ኑሮ" የለም።

💭 የእኔ ትዝብት ፦ "የቤትን ችግር እየተከላከሉ በሜዳ ላይ ማደር የብስለት ችግር ነው "

ቤተክርስቲያን የሌለው አቃቤ እምነት መሆን፣ ስለ አንድ ቤት ጥንካሬ በጽኑ እየተከራከሩ ፣ ራስ ግን በሜዳ ላይ በብርድ ከመቀመጥ ጋር ይመሳሰላል ።

በማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ ማፍራት ለአጥቢያ እረኞች የመገዛትን አስፈላጊነት አሳጥቶታል ።

ክርስትናን ከተግባራዊ የፍቅር ሕይወት ይልቅ ወደ ፍልስፍናዊ ሙግት ብቻ ማሳነስ ።

በአጥቢያ ውስጥ ካሉ "ደካማ" ወንድሞች ጋር መኖር ትሕትናን ይጠይቃልና ።

አቃቤ እምነትነት (Apologetics) የሚጀምረውና የሚጠናቀቀው በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ።

እውነተኛ አቃቤ እምነትነት በቃላት ጥበብ መርታት ብቻ ሳይሆን ፣ ክርስቶስ በደሙ በዋጃትና ድክመት ባለባት የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፍቅርን በተግባር በመኖር የሚገለጥ ሕይወት ነው ።

ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉት !

 #ዝምታ  #የማያድንበት  #ጊዜ  #ሙሉ  #ወንጌል  #ቤተክርስቲያን  #ዝምታው  #ይበቃል !!!ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት በሌሎች ስሞች ሲጠራ⏰⏳⏳ “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ይላሉ ...
18/05/2026

#ዝምታ #የማያድንበት #ጊዜ
#ሙሉ #ወንጌል #ቤተክርስቲያን #ዝምታው #ይበቃል !!!

ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት በሌሎች ስሞች ሲጠራ

⏰⏳⏳ “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ይላሉ አበው ። እውነት ነው ፤ አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከክርክር ይሻላል ። ነገር ግን ዝምታ ሐሰትን እውነት እንዲመስል ሲያደርግ ፣ ያ ዝምታ አደገኛ ይሆና ል ።

ዛሬ 🔥🔥 በጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊት ቤተክርስቲያን ሙሉ ወንጌል ላይ ብዙ ድንጋይ እየተወረወረ ነው ። አንዳንዶች የጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነትን መንፈስ ከ“ሶስተኛው ሞገድ” እንቅስቃሴ፣ ከ“እምነት ቃል” አስተምህሮ፣ እና ከ“ብልጽግና ወንጌል” ጋር በአንድ ሙቀጫ ውስጥ ለመክተት ይሞክራሉ ።

🤔🤔 የሚገርመው ግን ከዚህ ሁሉ በላይ የቤተ እምነቱ ኃላፊዎች የመረጡት ዝምታን መሆኑ ነው ።

ግን ጥያቄው ይህ ነው ❓❓፦ እውነት ስትደበደብ ዝም ማለት ትሕትና ነው ? ወይስ ኃላፊነትን መሸሽ ? ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት ምንድን ነው ?

🙌🙌 ብዙ ሰዎች ጴንጤቆስጣዊነትን ሲሰሙ ወዲያው የሚያስቡት ጩኸት ፣ ተአምራት ፣ ወይም የብልጽግና ስብከት ነው ። ❗❗ ነገር ግን ይህ የጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት እውነተኛ መልክ አይደለም ።

🔥🔥🔥 ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት በመሠረቱ ወደ ሐዋርያት ዘመን የሚመለስ እምነት ነው ። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ያምናል ፤ ነገር ግን ከቃሉ ውጭ አይሄድም ።

የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ያስተምራል ፤ ግን ከመስቀል ሕይወት አይለይም ። ተአምራትን ይቀበላል ፤ ግን ቅድስናን ከተአምራት በላይ ያስቀምጣል ።

በእርግጥ ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት የተገነባው በሦስት ነገሮች ላይ ነው ፦
👉👉👉 በመጽሐፍ ቅዱስ
👉👉👉 በመንፈስ ቅዱስ
👉👉👉 በመስቀል ሕይወት

“ብልጽግና ወንጌል” እና ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት አንድ አይደሉም ፤ ይህ በግልጽ መነገር አለበት ።

⚡⚡“ብልጽግና ወንጌል” ብዙ ጊዜ ሰውን ወደ ሀብት ፣ ስኬት ፣ እና ምድራዊ ምቾት ያመራል ። ሰው ካልተባረከ እምነቱ ጎድሎበታል የሚል ድብቅ መልእክት አለው ።

🔥🔥🔥 ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት ግን ይህን አያስተምርም።

የጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊ አባቶች ስብከት #ስለ መስቀል ነበር ፣ #ስለ ንስሐ ነበር ፣ #ስለ ቅድስና ነበር ፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ነበር ። ብዙዎቹ በመከራ አገለገሉ ፤ በድህነት ተመላለሱ ፤ በስደት ኖሩ ።

#ስለዚህ ዛሬ የሚታየውን “ሀብት = በረከት” አስተሳሰብ ከእነርሱ ጋር ማያያዝ ታሪካዊ ፍትሕ አይደለም ።

የችግሩ ዋና ምክንያት — የሥነ-አፈታት ችግር
ዛሬ ብዙ ሰዎች ጥቅስ ያነባሉ ፤ ነገር ግን ቃሉን አይተረጉሙም።

🏛🏛 ትክክለኛ ሥነ-አፈታት (Hermeneutics) ማለት ጥቅስን ከአውዱ ፣ ከታሪኩ ፣ ከጻፈው ሰው ዓላማ ፣ እና ከመላው የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጋር አያይዞ ማንበብ ነው ።

🔥🔥🔥ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊያን የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ቢያምኑም ፣ “ማንኛውንም መንፈሳዊ ልምምድ ተቀበሉ” አይሉም። ይልቁንም ፦ ልምምድ በቃሉ ይፈተናል ፣ ስሜት ከእውነት በላይ አይሆንም ፣ መንፈስ ቅዱስ ከጻፈው ቃል ጋር አይጋጭም ።

የቤተ እምነቱ ዝምታ 🤔🤔 እዚህ ጋር ነው ሕመሙ ያለው ። ነገር ግን ብዙ ጊዜ የተመረጠው ዝምታ ሆነ ።

👉👉 ዝምታው ግን ችግሩን አልፈታውም ፤ ይልቁንም ሌሎች ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነትን በፈለጉት መልኩ እንዲተረጉሙት አደረጋቸው ። እውነት ሲጠፋ ባዶ ቦታውን ሐሰት ይሞላዋል ።

የዛሬ ጥሪ 🕢🕢🕢
ዛሬ የሚያስፈልገው ጩኸት አይደለም ፤ ግልጽ ድምፅ ነው ። ጥላቻ አይደለም ፤ እውነት ነው ። ስሜት አይደለም ፤ ጥልቅ ሥነ-መለኮታዊ መሠረት ነው ።

🔥🔥🔥 ጥንታዊ ጴንጤቆስጣዊነት ራሱን ከስህተት አስተምህሮዎች በግልጽ መለየት አለበት። ከ“ብልጽግና ወንጌል” ጋር አንድ አይደለም። ከማይመዘን መንፈሳዊነትም ጋር አንድ አይደለም ።

❗❗❗ ምክንያቱም እውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ሁልጊዜ ወደ ክርስቶስ ይመራል፤ ወደ ሰው ክብር አይደለም።


በዘመናችን ብዙ ሰዎች “ሐሰተኛ ሐዋርያት” እና “ሐሰተኛ ነቢያት” በሚል ስም ሁሉንም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ለመዝጋት መሞከር አደጋ አለው ።ለተሰነዘረው ትችት እና መግለጫ መልሰ ለመስጠት...
14/05/2026

በዘመናችን ብዙ ሰዎች “ሐሰተኛ ሐዋርያት” እና “ሐሰተኛ ነቢያት” በሚል ስም ሁሉንም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ለመዝጋት መሞከር አደጋ አለው ።

ለተሰነዘረው ትችት እና መግለጫ መልሰ ለመስጠት የመጡት በውል ቤተክርስቲያን አይደለም ፡ ሊወኩሉ መሠረታዊ የክርስትና የሃይማኖት ትምህርት (catechism) ወስደው እንደገና ጌታን ሳይሆን ክርስትና መቀበል አለባቸው ።

"ሐይቁ ዳር ላይ የሚንጫጩ እንቁራሪቶች ባህሩ ሁሉ የእነርሱ ይመስላቸዋል ፡ ለክብራቸው ዝም ያሉ አሳዎች በእዛው ውስጥ አሉ ። "

ነገር ግን የሐሰት መኖር እውነቱን አያጠፋም ። በመጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛ ነቢያት እንዳሉ ተጽፎአል እንዲሁም ሐዋርያት ፣ እንዲሁም መምህራን ፤ ነገር ግን እውነተኛ ነቢያትና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችም እንዳሉ ተጽፎአል ።

“መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ።” (1 ተሰሎንቄ 5:19-21)

እንደ አንድ ጥንታዊ የጴንጤቆስጤ ልምምድ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ዛሬም ፤ ዘወትርም እምናለሁኝ !!!!

ነገር ግን ያለ ፈተና አንቀበልም ። ጸጋን ከስርዓት ጋር ፣ መንፈስን ከቃል ጋር ፣ ስጦታን ከፍሬ ጋር እናያይዛለን ።

“በቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈስ የሚናገሩ፣ ትንቢት የሚናገሩ እና ለሰዎች ጥቅም የሚሆኑ ስጦታዎች አሉ።”

(Against Heresies, Book V.6.1) ቅዱስ ኤሬኒዮስ

ቤተክርስቲያን የመንፈስ ኃይል ያለባት ናት ፤ ይህም ለማስተማር ፣ ለመገሰጽ እና ለማጽናናት ይሰጣል ።

ስለዚህ መፍትሔው ሁሉንም ማጥፋት አይደለም ፤ በቃሉ መፈተን ነው ።

አንዱ ለሌላው ሚዛን ነው !!!

ሐሰተኛ አስተማሪዎች ካሉ እውነተኛዎችም አሉ ።
ሐሰተኛ ትንቢት ካለ እውነተኛ ትንቢትም አለ ።
ሰው ስለተሳሳተ መንፈስ ቅዱስን አንክድም ።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የቃልና የመንፈስ ቤተክርስቲያን ነበረች ።

ዛሬም እኛ የምንፈልገው በእውነት ፣ በትሕትና ፣ በቅድስና እና በፍቅር የሚሠራ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው ።

06/09/2018 ✍✍✍

መስቀል የእግዚአብሔር አብ መልስ ነው  !!! 🙏✝️ለዚህ ለከንቱ እና  ውድቅ እና  ብሽቅ ዓለም ኑሮ አይደለም  🤔🤔ለዘላለም ፣ ማለቂያ ለሌለው የክብር እና የሰላም ህይወት  🌍🕊️።የእግዚአብ...
12/05/2026

መስቀል የእግዚአብሔር አብ መልስ ነው !!! 🙏✝️

ለዚህ ለከንቱ እና ውድቅ እና ብሽቅ ዓለም ኑሮ አይደለም 🤔🤔
ለዘላለም ፣ ማለቂያ ለሌለው የክብር እና የሰላም ህይወት 🌍🕊️።

የእግዚአብሔር ወልድ መስቀል !!
የእግዚአብሔር አብ መልስ ነው !!


የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል መልስ ነው ደግሞ የመጨረሻው መልዕክት ነው !! 💯

ዛሬም ለዚህች ምድር የጥቂት ዘመን ጉዞዬ በመስቀሉ ያለፈውን እያየሁ እኖራለሁ 🚶‍♂️🙌።

የጌታ እራት የጠረጴዛው ትርጉም 🍞🍷የጌታ እራት የሃይማኖት ሥርዓት ወይም ተደጋጋሚ የቤተክርስቲያን ወግ ብቻ አይደለም ።ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ጊዜ የሰበከበት ጣዕም ...
29/04/2026

የጌታ እራት የጠረጴዛው ትርጉም 🍞🍷

የጌታ እራት የሃይማኖት ሥርዓት ወይም ተደጋጋሚ የቤተክርስቲያን ወግ ብቻ አይደለም ።

ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ጊዜ የሰበከበት ጣዕም እና በክርስቲያናዊ አምልኮ ማከል ነው ። ✨

ከቀድሞት አማኞች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቤተክርስቲያን በጠረጴዛው ዙሪያ እንደ አንድ የእምነት ተግባር ተሰብስባለች ።

እንዲሁም እንደ ቅዱሳት ጸሐፊዎች የተናገሩት ፣ እራት ጊዜ ሁሉም አማኞች በመንፈሳዊ እና ሚስጥራዊ ስላሴ ውስጥ እንደሚዋሃዱ ይታሰባል ። 🕊️

የምናምነው እና የምንቀበለው ነገር እርሱ በእውነት ይሆናል ፣ የምንሳተፍበትም ነገርም ሙሉ በሙሉ እውነት ነው ።

እንጀራው እና ሥጋው ወደ ተሰጠን የክርስቶስ ሥጋ እና ወደ ፈሰሰው ደሙ ያሳይናል ፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ወደ ሕያው ግንኙነትም ይሳቡናል ። 🙏

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ይህንን በጥልቀት ተረድታዋለች ።

ለእነሱ ፣ የእራቱ ጠረጴዛ ባዶ ምሳሌያዊ ብቻ አልነበረም ፤ በክርስቶስ የተገኙበት እና የተገናኙበትም እንዲሁም ፣ የአንድነት እና የለውጥ ጊዜ ነበር ።🌟

ኋላ እንደተገለጸው ፣ አማኞች በሚቀበሉት ነገር ነው ።

ይህ ማለት የጌታ እራት ቢያንስ ሶስት ነገሮችን ያደርጋል ማለት ነው ፡-" 📜

👉 ክርስቶስን ራሱን ለሕዝቡ ይገልጣል ።

👉 ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድ አካል ይመሰርታል ።

👉 እምነትን በሚታይ መንገድ ይመግባል ።

ክርስቶስ ሕዝቡን የሚያገኝበት እና ቤተክርስቲያን በእውነት የምትሆንበት የተቀደሰ ጊዜ ነው ። 🙌🕊️

With Facika Facika – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
29/04/2026

With Facika Facika – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mesfin Abera, Yididiya Yacob, Abraham Zewude, Yonas Abrah...
26/04/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mesfin Abera, Yididiya Yacob, Abraham Zewude, Yonas Abraham, Jemal Bati, Arega Teshome, Adane Agalo, Gedion Girma Gisa, Samssoon Beka, Bergene Bekele, Getachew Gabiso, Facika Facika, Tegegn Wadha, Dawit Ye Fikre Lij, Enuka Mali, Wonde Geme, Faxno Ardyo, Wotasa Wonke, Tesfahun Lenta, Màŕkos Mark, Asrat Mesel, Shimelis Tamene, Singer Andu, Prophetic Tesfa, ቤተሌም ቶሾሜ, Temesgen Danial, Zekariyas Mengesha, Tegegn Bogale, Tamenech Abeba, Mitiku Gebire, Bek Man Abebe, Betii M Man, Mesfin Kusse Yadessa, Dechasa Guta, Natye Abera, Asegid Eledias, Mebiratu Geremu, Admasu Adisu, Kifile Birhanu, Mekibeb Tsegaye, Yiso Garse, Nage Sewu Dache, Altamo Kafala, Wondex Kefyalew, Abebe Feyisa, Moges Abebe, Beti Mengistu, Gizaw Tema Teka, Alazer Man Kuma, Sool Birhanu

👀 የሚያዩ ሁሉ  እንዳያስተውሉ 👀                                  ደግሞ            👩‍🦯🧑‍🦯 የማያዩም  እንዲያስተውሉ 👩‍🦯🧑‍🦯 ደቀ መዛሙርትና ህዝቡ የናዝሬቱ ...
26/04/2026

👀 የሚያዩ ሁሉ እንዳያስተውሉ 👀
ደግሞ
👩‍🦯🧑‍🦯 የማያዩም እንዲያስተውሉ 👩‍🦯🧑‍🦯

ደቀ መዛሙርትና ህዝቡ የናዝሬቱ እየሱስ እያለፈ ነው ይላሉ ፤ የጠሜውስ ልጅ በርጠሜዎስ የዳዊት ልጅ ብሎ ይጮሀል ።

አንድ ምስኪን የናዝሬት ሰው በእንጀራናና መብል እጦት የሚያገፉት ብዙ ዱኩማን ሰዎች በዝተዋል የምስኪኑን አይነ-ስውር ጩኸት አፍነውታል ፤ እርሱ ግን አብዝቶ ይጮሀል የጥሪውም ድምጽ መድሐኒተ-ዓለሙንና መሲህውን የሚያስቆም ነበር ።

እርሱ ፈውሱን ከብሉይ ኪዳን ተስፋ ውስጥ ከናዝሬት መንደር ሳይሆን ከዳዊት ቤት ይጠብቅ ነበር ። ሁሉም ጩኸቶች ምክኒያታዊ ላይሆኑ ይችላሉ ምክኒያታዊ ጩህት ግን መልስ ያመጣል ።

በሳምንት አንድ ቀን አዳራሽ ዝግቶ መጮህ ፤ ጆሮ ከማደንቆር ያለፈ እንድምታ የለውም ይልቅ በዝምታ ውስጥ ያለውን ጩኸት መስማት እንዴት ያለ ፈውስ ነው ።

“ኢየሱስም ቆመና፦ ጥሩት አለ። ዕውሩንም አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት።”
— ማርቆስ 10፥49

አንድ ቦታ ላይ በአንድ ጉዳይ ግን ሁለት አይነት እውቀት ።

ከመቅደስ ሰዎች ሰውሮ ለመንገድ ዳር ነድያን ገለጠላቸው።

ዳዊት ተነበየ በርጠሜዎስ ተቀበለ

❤❤❤ “ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።”
— መዝሙር 34፥6

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912357038

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ነገረ መለኮታዊ ምልከታ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ነገረ መለኮታዊ ምልከታ:

Shortcuts

Share