Trinity School, Addis Ababa Unoffical Page

Trinity School, Addis Ababa Unoffical Page The Holy Trinity Cathedral School is situated next to the famous Holy Trinity Cathedral in Aratkilo area, Addis Ababa

Has anyone been to Trinity School recently. Please let us know how the school is doing.በቅርቡ የሥላሴን ትምህርት ቤት የጎበኘ አለ? ካላችሁ...
28/04/2022

Has anyone been to Trinity School recently. Please let us know how the school is doing.

በቅርቡ የሥላሴን ትምህርት ቤት የጎበኘ አለ? ካላችሁ እስቲ ያለበትን ሁኔታ አጋሩን።

እናመሰግናለን

I visited my school in May. I met the school directors both elementary and upper school. I met the children during the m...
23/06/2019

I visited my school in May. I met the school directors both elementary and upper school. I met the children during the morning procession and did a speech to inspire them. I told them that education changes their life for better. I also donated around 35 books that can help them develop their reading ability. The books are ranging from fiction to children poems and to science.

17/02/2017

የ9 ዓመት ብላቴና ሳሉ ከእናታቸው ጋር በመሆን በፋሺስት የተሰነዘረብንን ወረራ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፣ አፍቃሪ ኢትዮጵያው የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክረስት 22 የታሪክ ድርሳናት፣ ከ4 መቶ የሚበልጡ መጣጥፎች እና ሌሎችም ፅሁፎችን አቅርበዋል … ተዘርፈው ከኢትዮጵያ የወጡ ታሪካዊ ቅርሶችን ለማስመለስ ደክመዋል…

ሳይወለዱባት በደም ሳይጋመዷት ነገር ግን ከልክ በላይ ለኢትዮጵያ የደከሙላት አትርፈውም የለፉላት እውነተኛው የኢትዮጵያ ወዳጅ ሊቀ ሊቃውንት የታሪክ ተመራማሪውና አጥኚው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ…

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ለ60 ዓመት የኖሩባትን የሚያከብሯትን ሀገር በ90 ዓመት እድሜያቸው ነው የተሰናበቱት፡፡

በበርካታ የታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ከፍ ያለ የክብር ማዕረግና ተቀባይነት የነበራቸው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ከቀዳሚው ቤተሰባቸው ጀምሮ ለኢትዮጵያ በብዙ የታገሉ እና ሀገሪቱን ያከበሩ ስለመሆናቸው መስካሪዎቻቸው ብዙዎች ናቸው፡፡

ፕሮፌሰር ሪቻርድ እድሜያቸውን ሙሉ ለቁጥር በሚያታክቱ የታሪክ ጥናትና ምርምሮች ላይ የተጉ፣ ከፍ ያለ ዋጋ የሚሰጣቸውን ታሪካዊ ሰነዶችና መዛግብት አድራሻ በማፈላለግ ኢትዮጵያ የተሟላ ታሪክ እንዲኖራት በብርቱ የደከሙ ሰፊና ብዙ ርዕሰ ጉዳዬችን የዳሰሱ ፅሁፎች በማቅረብ ከበሬታን የተጐናፀፉ እውነተኛው ሊቅ እንደሆኑ ይነገራል፡፡

የቆዳ ቀለማቸውና የዘር ሀረጋቸው ከአውሮፓ የሚመድባቸው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት እንደሌሎቹ የውጭ ሀገር የታሪክ ፀሀፍትና ተመራማሪዎች የኢትዮጵያን ታሪክ በማዛነፍ በማመሳቀልና በሌላ ሌላውም ስማቸው ለትችት የሚቀርብ አለመሆኑን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት የአዲስ አበባው ዩኒቨርስቲ ሳይቀር እማኝነቱን ሰጥቶናል፡፡

ፕሮፌሰር ሪቻርድ የታዋቂዋ የሴቶች መብት ተሟጋች በፀረ ፋሽስት አቋማቸው ፅኑ ትግል ያደረጉት የግራ ዘመም ፅንሰ ኃሣብን ያሰረፁት የእንግሊዟ ስልቪያ ፓንክረስት ልጅ ሲሆኑ በፋሽስት ኢጣሊያ ተወራ ለነበረችው ኢትዮጵያ ገና የ9 ዓመት ብላቴና ሳሉ ከሲልቪያ ፓንክረስት ጋር ወረራውን በመቃወም ሰልፍ የወጡ፣ የኢትዮጵያን በደል በአደባባይ ያወገዙ፣ ኢትዮጵያን እናት ሀገር ብለው የተቀበሉ ምሁር መሆናቸውን የታሪክ ተመራማሪዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተውናል፡፡

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ከእናታቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ በያኔው በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋምን አቋቁመዋል፡፡
በዩኒቨርስቲው የማህበራዊ ሣይንስ የትምህርት መስኮችን ታሪክና ሂውማኒቲስን ከማቋቋም አልፈው መሰረት እንዲይዙ የለፉም ናቸው፡፡

በታሪክ ተመራማሪዎች እምብዛም ትኩረት ያልተሰጠውንና ለመዘንጋት የቀረበውን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክ ታሪክ ዘርፍ ለማጥናት የቀደማቸውም አይገኝም፡፡

በዚሁ የትምህርት መስክ ከለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የኢኮኖሚያዊ ታሪክ ዶክትሬት የነበራቸው ሪቻርድ ፓንክረስት በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ብዙ ተማሪዎችን በዚሁ መስክ አስተምረው ለፍሬ አብቅተዋል፡፡

እኚህ ሊቅ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ታሪክ ብቻ ሣይሆን ሌሎች የታሪክ ጉዳዮችንም መርምረዋል፤ ሰነዶችንም ሰብስበዋል፡፡

ይህ ደግሞ ከሌሎች የታሪክ ተመራማሪዎች ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡

ከአክሱም ዘመን ጀምሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ታሪክ በዘርፍ በዘርፍ የመረመሩት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ያላነሱት ርዕሰ ጉዳይ የለም ይሏቸዋል ስለ እሳቸው በጥልቀት የሚያውቁ፡፡

ስለ ጦር መሣሪያዎች፣ ስለ በሽታና ድርቅ፣ ስለ አመጋገብ ፕሮቶኮል፣ ስለ ንግድና እርሻ፣ ስለ ገንዘብ፣ ስለ ኢትዮጵያ የእጅ ሙያዎች፣ ስለ እንስሣትና አገልግሎቶቻቸው፣ ስለ ኢትዮጵያ ሀይማኖትችና የእምነት አይነቶች፣ ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥነ-ጥበብና ሌሎችም ጉዳዮች ሣይቀር ብዙ ፅፈዋል፡፡

22 የታሪክ ድርሳናት፣ ከ4 መቶ የሚበልጡ መጣጥፎች ሌሎችም ፅሁፎች በማቅረብ የሚስተካከላቸው እንደሌለ ይነገርላቸዋል፡፡

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስትን ሥራዎች ቁጭ ብሎ የቆጠረ የለም እንጂ የምርምር ውጤቶቻቸው እነዚህ ብቻ አይሆንም ይላሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ክፍል ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ ለሸገር በሰጡት ምስክርነት፡፡

የኢትዮጵያን ታሪክ በዘመን ሳይወስኑ የተመራመሩት እኚህ ሰው የኢትዮጵያን የጥናት ጉባዔዎች በማሰናዳት ተሣታፊ፣ አዘጋጅ፣ አርታኢ፣ አደራጅና አቅራቢ በመሆን የኢትዮጵያ ጥናት በአለም አቀፍ ደረጃ ጭምር እንዲታወቅና ተቀባይነት እንዲኖረው ለፍተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወዳጅ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በውጭ ሀገር በተለያየ ጊዜ ተዘርፈው የወጡ የኢትዮጵያን ሀብቶችና ቅርሶች ወትውተው በማስመለስ ስማቸው ከፊተኞቹ ጐራ ይጠራል፡፡

በእናታቸው እንግሊዛዊ፣ በአባታቸው ጣሊያናዊ የሆኑት ሪቻርድ እንግሊዞች ከአፄ ቴዎድሮስ ሞት በኋላ የወሰዱትን ቅርሶችም በማስመለስ ይታወሣሉ፡፡

ከእነዚህ መካከል የአፄ ቴዎድሮስን አሽንክታብ፣ መስቀሎች፣ ታቦት እንዲመለስ ታግለው ተሣክቶላቸዋል፡፡

የአክሱም ሃውልት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ከብዙ ከጣሩ መካከልም ናቸው፡፡ በዚህ አስተዋፅኦዋቸው ምስጋናና ሽልማትም አግኝተውበታል፡፡

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ለኢትዮጵያ ባደረጉት ሰፊ አበርክቶ እውቅናና ሞገስ ተችሯቸዋል፣ ተቋማትም አክብረዋቸዋል፡፡

ለምሣሌ ያህልም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሽልማት ድርጅት ሽልማት ሰጥቷቸዋል፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ አበርክቶላቸዋል፡፡

ከመሠረቱ ያቋቋሙትና በዳይሬክተርነት የመሩት የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም በስማቸው ቤተ-መፅሐፍት የማቋቋም ኃሳቡን ይፋ አድርጓል፣ መፀሐፍትም አሳትሞላቸዋል፡፡

ከካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ ለላቀ ልፋታቸው የቢቂላ አዋርድን ተቀብለዋል፡፡
ሪቻርድ ፓንክረስት በደርግ ዘመን ከሀገር ለመውጣት ተገደው ለጥቂት ዓመታት በውጭ ሀገር ከመቆየታቸው በቀር ለሚወዷት፣ ሥለ ክብርና ዝናዋ ባገኙት አጋጣሚ በሚዘክሩላት ኢትዮጵያ ረጅሙን የእድሜያቸውን ክፍል ኖረዋል፡፡

ሁለቱንም ልጆቻቸውን አሉላና ሄለን ፓንክረስትን በኢትዮጵያዊ ወግ ማሳደጋቸውም ነው የሚነገረው፡፡

የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ የነበሩት ሲልቪያ ፓንክረስት ላደረጉት የነፃነት ተጋድሎ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግሥት የክብር ሜዳይ ሰጥቷቸዋል፡፡

ከፍተኛ የክብር መገለጫዎችንም ማድረጉ በታሪክ መዛግብት ጭምር ሰፍሯል፡፡

የሲልቪያ ፓንክረስት ቀብር በልዩ ሥነ-ሥርዓት ንጉሱና የወቅቱ ጳጳስ አቡነ ባሲሊዬስ በተገኙበት በአርበኞች አጃቢነት በጊዜው አርበኞች ብቻ ይቀበሩበት በነበረው የቅድስት ስላሴ ካቴድራል መካነ መቃብር ተከናውኗል፡፡

የታሪክ መዛግብት መርማሪውና ሰናጁ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ሥነ-ሥርዓትን በሚመለከት የብሔራዊ ሙዚየምና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ሸገር በእኚህ ታላቅ ሊቅ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለሚያከብራቸው ህዝብና ቤተሰቦቻቸው ፈጣሪ መፅናናትን ያድል ዘንድ ይመኛል፡፡

(ሕይወት ፍሬስብሃት)

10/03/2016

Has anyone got any news about our school? I want to hear from specially from those those who are in Ethio or who went back home and visited the school.

26/02/2011

If anyone got pictures or anything that can be posted here regarding Trinity School please do let us know. Will give you admin privilages so that you can post it urself. Please make sure they are not offending or causes upset to people.

12/07/2010
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴቤተ ክርስትያን፡ አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ  ‘‘የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርንመፍራት ነው።’’THE HOLY TRINITY CATHEDRAL, ADDIS ABABA, ET...
12/07/2010

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ
ቤተ ክርስትያን፡ አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ


‘‘የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን
መፍራት ነው።’’



THE HOLY TRINITY CATHEDRAL, ADDIS ABABA, ETHIOPIA

06/07/2010

Has any one got school photos from trinity school? If anyone wants to add, please welcome.

10/03/2010

Be a fan, invite friends to become fans, specially those who had a good memory of our elementary school, Trinity School

Address

Trinity School
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Trinity School, Addis Ababa Unoffical Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share