18/07/2026
❤️ #ሜምፊቦስቴ❤️
==================
✍️ንጉስ ዳዊት እና ሜምፊቦስቴ ፦
2ሳሙ 4፡4, 9፡4-13
✍️ሜምፊቦስቴ የሳኦል የልጅ ልጅ የዮናታን ልጅ ነው፡፡
ሽባ የሆነበትም ምክንያት የአያቱን እና የአባቱን ሞት የሰማች ሞግዚት ይዛው ለመሸሽ ስትሞክር ከእጇ በመውደቁ ነው፡፡
2ሳሙ 4፡4
✍️የሜምፊቦስቴ አያት የሆነው ሳኦል የንጉስ ዳዊት ቀንደኛ ጠላት እንደነበር ይታወቃል፡፡
✔️እንዲሁ የሰው ልጆች ምንጭ የሆነው አዳም በሀጥያት ምክንያት የእግዚአብሔር ጠላት ሆነ፡፡ ሮሜ 5፡9
✍️የሜምፊቦስቴ ሞግዚት ይዛው ልትሸሽ ስትሞክር ነው በ 5 አመቱ ወድቆ ሽባ የሆነው፡፡
✔️እንዲሁ የሰው ልጅ በክርስቶስ በማመን በፀጋ ብቻ እንጂ ሞግዚት በሆነው በሙሴ ህግ ህይወት ሊያገኝ እና ሊፀድቅ አይችልም፡፡
ገላ 2፡16, 3፡17-21,ሉቃ 14፡15
✍️የሜምፊቦስቴ አባት ዮናታን የንጉስ ዳዊት የልብ ጓደኛ ከመሆኑ የተነሳ ንጉሱ ስለ ዮናታን ቸርነት እና ምህረት ማድረግ ፈለገ፡፡ 2ሳሙ 9፡7
✔️እግዚአብሔር ለሀጢያተኛው ሰው በክርስቶስ በኩል ምህረት ማድረግ እና ከቁጣው ሊያድነው ፈለገ።
ዮሐ 3፡14-18,ሮሜ 3፡21,ሮሜ 4፡22- ,5:1, ኤፌ 2፡4-6
✍️ሜምፊቦስቴ ይኖር የነበረው ሎዶባር (ምድረበዳ) በሚባል ቦታ ነበር፡፡ 2ሳሙ 9፡4
✔️የሰው ልጅም በሀጥያቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር መገኝት እና መግቦት ርቆ ይኖር ነበር፡፡ ኤፌ 2፡11, 1ጴጥ 2፡25
✍️ሜምፊቦስቴ ካለበት ቦታ ወደ ንጉስ ዳዊት እንዳይሄድ እግሩ ሽባ ነው ንጉስ ዳዊት ግን መልዕክተኛ በመላክ ወደ እርሱ እንዲመጣ አደረገው፡፡ 2ሳሙ 9፡1-2
✔️ሀጥያተኛ የሆነውም የሰው ልጅ በራሱ መልካም ስራ በአምላክ ፊት ተቀባይነት ማግኘት ስለማይችል እግዚአብሔር ግን በክርስቶስ ወደ ራሱ ማቅረብ ፈለገ፡፡ ኤፌ2፡8, ሮሜ 3፡21-24,ሮሜ 5፡6-10,
✍️ንጉስ ዳዊት ስለ ዮናታን ሲል ለሜምፊቦስቴ ቸርነትን በማድረግ
2ሳሙ 9፡7
1) እንደ ንጉስ ልጅ ሆነ
2) ከንጉሱ ጋ በማእድ ተቀምጦ ንጉሱ የሚበላውን በላ
3) በኢየሩሳሌም ከንጉሱ ጋር መኖር ጀመረ
4) የአያቱን ምድራዊ ርስት መለሰለት
✔️እንዲሁ እግዚአብሔር ለሀጥያተኛው በክርስቶስ ምክንያት
1) ልጅ አደረገው
2) በክብር በክርስቶስ በቀኙ አስቀመጠን
3) የሕይወት እንጀራ የሆነው ክርስቶስ ምግቡ ሆነለት
4) በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም በክርስቶስ መኖር ጀመረ
5) በአዳም ምክንያት ያጣነውን ከዚያም በላይ በክርስቶስ ባረከን ፡፡ ኤፌ 1፡3, ዮሐ 1፡12,1ዮሐ 3፡1-,ዮሐ 6
ኤፌ 2:6-7,ዕብ12:22-24
🤔🤔ቅዱሳን ልብ ሊሉት የሚገባ ፦
✍️ሜምፊቦስቴ በንጉስ ዳዊት ቸርነት እንዲህ ቢሆንም አሁንም ግን #እግሩ #ሽባ #ነው፡፡
✔️ሰው በክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኃላ ለመኖር መፍጨርጨር የለበትም ይልቅስ ጻዲቅ በእምነት በሕይወት ይኖራል፡፡ Dawit Fassil