Gojam ethiopia news

Gojam ethiopia news Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gojam ethiopia news, Addis Ababa.

ጥልቅ ማጭበርበር (Deep Fake) ምንድን ነው?ጥልቅ ማጭበርበር (Deep fake) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመጠቀም የተፈጠረ የማጭበርበሪያ መንገድ ሲሆን በተለይም ዲፕ ለርኒንግ (...
17/06/2025

ጥልቅ ማጭበርበር (Deep Fake) ምንድን ነው?
ጥልቅ ማጭበርበር (Deep fake) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመጠቀም የተፈጠረ የማጭበርበሪያ መንገድ ሲሆን በተለይም ዲፕ ለርኒንግ (deep learning) ተብሎ የሚጠራ የAI ቅርንጫፍ የሚዘጋጅ ነው። ይህም የአንድን ሰው ፊት፣ ድምጽ ወይም ድርጊት በቪዲዮ፣ በምስሎች ወይም በድምጽ ሌላ እንዲመስል ማድረግን የሚያካትት ሲሆን ብዙውን ጊዜ በጣም እውነተኛ በሚመስል መልኩ ይዘጋጃል።
በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የዲጂታል ምህዳር ግንዛቤ (Digital Literacy) ብዙም ባላደገበት ሁኔታ በጥልቅ ማጭበርበር የሚዘጋጁ የቪዲዮ፣ የጽሁፍ እና የድምጽ ይዘቶች በሀገር እና በህዝብ ላይ የሚያደርሱት የሥነ ልቦና፣ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ከፍተኛ እንደሆነ አያጠያይቅም ፡፡
የጥልቅ ማጭበርበር (Deep fake) ይዘቶች ብዙውን ጊዜ የሚፈጠሩት ከእውነተኛ ቪዲዮዎች ወይም ፎቶዎች በመነሳት አዳዲስ የሀሰት ይዘቶችን በማመንጨት ነው፡፡
በጥልቅ ማጭበርበር (Deep fake) የተዘጋጁ ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት እንችላለን?
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተፈጠሩ ሃሰተኛ ቪዲዮዎች አሁን ላይ ከእውነተኛ ቪዲዮች ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ቀጥሎ የቀረቡት ምልክቶች በጥልቅ ማጭበርበር የተዘጋጁ ቪዲዮዎችን ለመለየት የሚያስችሉ ናቸው፤
• የእይታ ወጥ አለመሆን፡- በጥልቅ ማጭበርበር የተዘጋጁ ቪዲዮዎች ብዙውን ጊዜ ከተፈጥሯዊ የዓይን አንቅስቃሴዎች ጋር ጉልህ ልዩነቶች አላቸው፤
• ደካማ የከንፈር ማመሳሰል (Poor lip sync): - ቃላቱ በትክክል ከአፍ እንቅስቃሴዎች ጋር አለመመሳሰል፤
• ደብዛዛ ወይም ያልተዛመዱ የፊት ገጾች:- ፊት፣ ጆሮ ወይም የፀጉር መስመር ዙሪያ፤
• ተፈጥሯዊ ያልሆኑ የብርሃን ውህዶች ወይም ጥላዎች፤
• የሮቦቲክ ወይም ሞኖቶን ድምጽ፡- በAI የመነጨ ንግግር ብዙውን ጊዜ የስሜት መለዋወጥ ይጎድለዋል፤
• ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ የሚጎተት አነባበብ ዘይቤ፤
• የድምጽ እና የቪዲዮ አብሮ አለመሄድ፡- የሚወጣው ድምጽ ከተናጋሪው/ዋ የፊት ገጽታ ጋር ሙሉ በሙሉ ያለመዛመድም፤

06/03/2025

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የስራ መደቦች ሰራተኞችን በቋሚነት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ዝቅተኛ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያ ከወጣበት የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመመዝገቢያ አድራሻ https://recruitment.insa.gov.et/ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
• ፀሃፊ
• የአሰራር ስርዓት ጥናት፣ ትንተና እና ምርመራ
• የውስጥ ኦዲት
• የስራ አከባቢ ደህንነት እና ጤንነት
ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8qBKkyp092r&_r=1
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio
• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር፡ 933

በአድዋ ጦርነት የታየዉ ተምሳሌታዊ ተግባር የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሊደገም እንደሚገባ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገለጹአዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017፡ ኢትዮጵ...
03/03/2025

በአድዋ ጦርነት የታየዉ ተምሳሌታዊ ተግባር የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሊደገም እንደሚገባ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017፡ ኢትዮጵያ በ1888 በአድዋ ጦርነት በወራሪዎች ላይ የተቀዳጀችዉ ድል የአፍሪካ ቀጣይ የታሪክ ጅረት ዉስጥ ወሳኝ ሚና መዉጣቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናገሩ።
በአድዋ ጦርነት የታየዉ ተምሳሌታዊ ተግባር የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሊደገም እንደሚገባ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ ጠቁመዋል።
ድሉ ቀኝ ገዢዎችን አንገት ያስደፋ ኢትዮጵያን ነፃነት ያጎናፀፈና ለጥቁር ህዝብ የይቻላል መንፈስ የፈጠረ ትልቅ የታሪክ ክስተት ነው ብለዋል።
ዛሬ ጦርነቱ ስፍራዉን ቀይሯል ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት ጦርነቱ ድንበር ወደሌለዉ፣ ዉስብስብና ኢ-ተገማች ወደሆነዉ ሳይበር ጦርነት መምጣቱን ገልጸዋል።
የኛ ትዉልድ የነጻነት ተጋድሎ ሀገራችን በምታደርገዉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በመደገፍና ይህን ተከትሎ የሚከሰቱ የሳይበር ጥቃቶችን በመመከት እና የሳይበር ጦርነቶችን በበላይነት በመወጣት የሚገለጽ መሆኑን አንስተዋል።
የዛሬ 129 ዓመት ኢትዮጵያውያን አርበኞች በአድዋ ጦርነት ባደረጉት ተጋድሎ መሬታቸውን ከወራሪዎች እንደተከላከሉ ሁሉ ኢመደአም ጠንካራ የሳይበር መከላከል አቅም በመፍጠር፣ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማበረታታትና ከዉጪ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በመቀነስ የራሱን ሚና እየተወጣ ነዉ ብለዋል።
ከዉጭ በሚገቡ የቴክኖሎጂ ምርቶችና ፕላትፎርሞች ላይ ጥገኛ በመሆን የብሄራዊ ደህንነትንና ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ፤ የዲጂታል ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እንደማይቻል ወ/ሮ ትዕግስት ገልጸዋል።
የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅም ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ማበልጸግና መጠቀም፣ የሳይበር ደህንነት እውቀቶችን ማሳደግ፣ ብቁ የሰዉ ሀይል ማልማትና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ማሳደግ ወሳኝ ነዉ ብለዋል።
የአድዋ ድል ለአሁኑ ትዉልድ ካስተማረን ትምህርቶች ዉስጥ ነፃነት የሚገኘው በስትራቴጂያዊ እሳቤ፣ በጽናት እና በራስ በመተማመን መሆኑን አሳይቶናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ የአድዋ መንፈስ ወደ ሳይበር ምህዳር በማምጣት የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ በኢትዮጵያውያን እጅ እንዲቆይ ማድረግ እንደሚገባ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ ገልጸዋል።
“አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል”

ተቋማትን ለሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ ዋና ዋና ክፍተቶችተቋማት ስራቸውን ለማቀላጠፍና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል ቴክኖሎጂውን በእጅጉ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ከቴክኖሎ...
28/02/2025

ተቋማትን ለሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ ዋና ዋና ክፍተቶች

ተቋማት ስራቸውን ለማቀላጠፍና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል ቴክኖሎጂውን በእጅጉ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት እድገት ጋር የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትም አብሮ የሚያድግ በመሆኑ ተቋማት የዲጂታል ቴክኖሎጂውን ከመጠቀም ባለፈ ለሳይበር ጥቃት የሚዳርጉ ክፍተቶችን ማወቅና መድፈን ላይ በትኩረት መስራት ይገባል። ተቋማትን ለጥቃት እንዲጋለጡ ከሚያደርጓቸዉ ዋና ክፍተቶች መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል፦
👉ተገቢ የአመራር ፣ የአስተዳደር ማዕቀፎ እና የአሠራር ሥርዓት አለመዘርጋት፣

👉ተገቢ አደረጃጀትና የሰው ኃይል አለመኖር፣

👉ዝቅተኛ የሳይበር ደህንነት አቅም ፣

👉የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ዝቅተኛ መሆን፣

👉የሳይበር ደህንነት ማስጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ያለመኖር፣
👉ለጥቃት ተጋላጭ ሲስተሞችና መሠረተ-ልማቶች መኖር፣
👉ዝቅተኛ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና

ሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መጥቷል: የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድአዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራ...
27/02/2025

ሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መጥቷል: የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መምጣቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናገሩ።
ዋና ዳይሬክተሯ በተቋሙ የሪፎርም ስራዎች፣ እየተገኙ ባሉ ውጤቶና ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅና የመከላከል አቅምን ማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ የለውጥ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
ከለውጥ ስራዎቹ መካከል የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉን አስታውሰዋል።
ኮምፒውተርን በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ መውጣቱን ጠቅሰው፣ ይህም ወንጀልን የመከላከል ሀገራዊ አቅምን ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ከውጭ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን ከደህንነት አኳያ በአግባቡ ተፈትሸው ወደ ሀገር እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ያብራሩት ዋና ዳይሬክተሯ ከቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት ጥበቃ ጋር በተያያዘ አስቀድሞ የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ተቋማት የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል የሚችሉበት አቅም እንዲገነቡ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የተሻለ የአሰራር ስርዓት እንዲኖራቸው አስተዳደሩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የጠቆሙት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ማሳደግ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ እንደመሆኑ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በዘርፉ የሰው ሃይልን ለማፍራት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ለአብነትም ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ታዳጊዎች በክረምት መርሃ ግብር እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አማራ ንቃ፣ ተደራጅ፣ ታጠቅ!   የሚባል ፅንፈኛ እና ጠባብ ብሔርተኛ  አገው ህዝብ ላይ   እያወጀ ነው። እባካችሁን ምከሩት
13/04/2022

አማራ ንቃ፣ ተደራጅ፣ ታጠቅ!
የሚባል ፅንፈኛ እና ጠባብ ብሔርተኛ አገው ህዝብ ላይ እያወጀ ነው። እባካችሁን ምከሩት

Ethiopian DJ  ድድብና!!    የሙታን ስብስብ ኛችሁ😂😂😂  is the correct spelling in   English, while in   English   is correct. meaning...
13/04/2022

Ethiopian DJ ድድብና!! የሙታን ስብስብ ኛችሁ😂😂😂
is the correct spelling in English, while in English is correct. meaning a place used for a particular purpose.

 #በዉሻ መደንገጥ  #በአንበሳ ቤተሰብ ነውር ነው።
08/04/2022

#በዉሻ መደንገጥ #በአንበሳ ቤተሰብ ነውር ነው።

Aman Gessessን ተውት። ጀማሪና ለታይታ የሚኳትን እውቀትም ታሪክም የከዱት የስሜት ሰው ነው። አማራና አገው ላይ ያልሆነ አጀንዳ እየወረወረ በህዝብ መካከል ቅሬታ ለመፍጠር እየሞከረ ነው...
25/02/2022

Aman Gessessን ተውት። ጀማሪና ለታይታ የሚኳትን እውቀትም ታሪክም የከዱት የስሜት ሰው ነው። አማራና አገው ላይ ያልሆነ አጀንዳ እየወረወረ በህዝብ መካከል ቅሬታ ለመፍጠር እየሞከረ ነው። በምንም ሁኔታ ማምለጥ አይችልምም ። የሚደርስበትን መገመት አይችልም

 /ዘሮች/ ከበርካታቹ የአገዉ ጥንተ ነዋሪ ሕዝቦች መካከል የተወሰኑት ክፍሎች የሴም ነገድ ሕዝቦች ጋር ባህላቸውን በማቀላቀልና በማስዋጥ የጥንቱን የኢተዮጵያ ሥልጣኔ በመመሥረት የዚያ አካል ሆ...
24/02/2022

/ዘሮች/ ከበርካታቹ የአገዉ ጥንተ ነዋሪ ሕዝቦች መካከል የተወሰኑት ክፍሎች የሴም ነገድ ሕዝቦች ጋር ባህላቸውን በማቀላቀልና በማስዋጥ የጥንቱን የኢተዮጵያ ሥልጣኔ በመመሥረት የዚያ አካል ሆነው በአገውነታቸው ቀርቶ የአክሱም ሥልጣኔ ሕዝቦች በሚል የወል መጠሪያ ከሌሎች ተጣምረው ቀርተዋል ።በሌላ በኩል ግን የባህል ማንነታቸውን ሳያስነኩ ከአክሱም ማዕከላዊ መንግሥት ጋር ጦር በመማዘዝ ሲጠቁ ወደ ደቡብ አቅጣጫ እየፈገፈጉ የተከዜን ወንዝ ዙሪያገብ ነፃ ግዛት በመኖሪነት አጠናክረው ይዘው የቆዪ በርካታ ቁጥር የነበራቸው የአገው ህዝቦች ነበሩ።ከ አክሱም ሥልጣኔ ጋር ከተቀላቀሉት ውጭ የአገው ሕዝቦች አካላት እንደሆኑ በታሪክ ጸሐፊዎች የተዘረዘሩት ቁጥር የተለያዬ ቢሆንም በአማካይ የተያዘው ከሞላ ጎደል የሚከተለውን ይመስላል፦ 👌ቅማንቶች(በቤጌምድር ጎንደር የሚኖሩ)

👌ፈላሻዎች(በቤጌምድር ጎንደር የሚኖሩ)

👌አዊዎች( በጎጃም ዳሞት ዳንግላ የሚኖሩ)

👌 ኩንፈሎች(በቋራ ጎንደር የሚኖሩ)

👌ኽምራዎች(በላስታ በዋግ በሰሃላና በአበርገሌ የሚኖሩ)

👌ብሌኖች(በኤርትራ የሚኖሩ)

Address

Addis Ababa
124498

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gojam ethiopia news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share