17/10/2025
✝️ የቤተ ክርስቲያን ሰማዕታት ዝምታ?
የ43ኛውና የ44ኛው የሰበካ ጉባኤ ሪፖርቶች ንጽጽር አሳሳቢነት! 🕯️
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 44ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጥቅምት 2018 ዓ.ም. በድምቀት ተጀምሯል። ሆኖም የብዙዎች ጥያቄ የዓምናው አስደንጋጭ ሪፖርት ዘንድሮም ተገቢውን ትኩረት አግኝቷል ወይ የሚለው ነው።
የሰማዕታት ደም በጉባኤው አደራሽ ውስጥ ዝም ሊባል አይገባም!
ለምን ዝምታ? የሰማዕታቱ ደም ይጮኻል!
ባለፈው ዓመት እንደዚህ ያሉ ከባድ ሪፖርቶች ሲቀርቡ፣ ዘንድሮ በኦርቶዶክስ ምእመናን ላይ ግፍ የተፈጸመባቸው አካባቢዎች ቢኖሩም፣ የዝርዝር መረጃዎች በአደባባይ አለመቅረባቸው የሚከተሉትን ጥያቄዎች ያሰነሳል፡-
❓ የጉዳዮቹ ክብደት ቀንሷል? በየአካባቢው የሚፈጸሙት ግፎች (እንደ የምሥራቅ ሸዋ የመነኮሳት ጉዳይ) አልቆሙም!
❓ ፖለቲካዊ ጫና ነው? ቤተ ክርስቲያን የሰማዕታቶቿን ደም መርሳት የለባትም፤ ጫና ቢኖርም እንኳን የእውነት ድምፅ መሆን ይጠበቅባታል!
❓ የሪፖርት ለውጥ? የጉዳዩን ክብደት ለቅዱስ ሲኖዶስና ለዓለም ማቅረብ ዋናው ዓላማ ነው። ዝምታ ለሰማዕታት ግፍ መጨመር በር ይከፍታል።
📢 ጥሪ ለኦርቶዶክሳውያን ምእመናን:
“በጎች በግፍ ሲያልቁ እረኛ በዝምታ አይታይም። ቅዱስ ሲኖዶስ የልጆቹንና የአብያተክርስቲያናቱን መከራ በድፍረትና በግልጽ እንዲያቀርብ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
👉 ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ የዝምታውን ግድግዳ እንስበር!