Impact Worship Center - የክርስቲያኖች መቅደስ ቤ/ክ

Impact Worship Center - የክርስቲያኖች መቅደስ ቤ/ክ … ወደ ክርስቶስ ፍፁም ሙላት!

30/07/2026
በአመራር ጥበብ የማደግ አስፈላጊነት!በአመራር ሳንበስል ምንም ነገር ማሳካት አንችልም፡፡ከሁሉም በፊት ራሳችንን መምራት መማር አለብን፡፡ ይህንን ማድረግ በሌሎች ሰዎች ላይ መልካም የምሳሌ ተጽ...
22/07/2026

በአመራር ጥበብ የማደግ አስፈላጊነት!

በአመራር ሳንበስል ምንም ነገር ማሳካት አንችልም፡፡

ከሁሉም በፊት ራሳችንን መምራት መማር አለብን፡፡ ይህንን ማድረግ በሌሎች ሰዎች ላይ መልካም የምሳሌ ተጽእኖ እንድናሳድር ከማስቻሉም በላይ፣ በአጉል ሰዎች ክፉ ተጽእኖ ስር እንዳንወድቅ ያግዘናል፡፡

ሲቀጥል ሌሎችን ሰዎች መምራት መማር አለብን፡፡ ይህንን ማድረግ ከቤታችን ጀምሮ እስከ ቤተክርስቲያን ሌሎች ማሕበራዊ ሂደቶች ውስጥ ሰዎችን በትክክለኛው መንገድ እንድንመራቸው ያሳድገናል፡፡

በመጨረሻ ስራን መምራት መማር አለብን፡፡ ይህንን ማድረግ የግል ስራን፣ የቅጥር ስራ ሃላፊነትንም ሆነ ንግዳችን በተዋጣለት መልክ እንድንመራና እንድናስተዳድር በሳል ደርገናል፡፡

በእነዚህ መስኮች ለመብሰል ከፈለጋችሁ፣ በቅርቡ የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- የአመራር ጥበብ እና ስልት
(መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ)

The Art and Strategy of Leadership
(A Biblical Perspective)

✝️ ራስን መምራት (Leading Self)
✝️ ሰዎችን መምራት (Leading Others)
✝️ ሥራን መምራት (Leading Work)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በአካል በመገኘት

የስልጠናው ቦታ፡- IMPACT የአምልኮ ማዕከል (አዲስ አበባ)

የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 16፣ ነሃሴ 23 እና ነሃሴ 30 (ሶስት ቅዳሜ ከሰዓቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለሶስቱም ቅዳሜዎች ከ9፡00 እስከ 12፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:- ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

በሚገባ ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች Certificate ይሰጣል፡፡

የትኩረት ለውጥ!በዚህች ምድር ላይ ስትኖሩ፣ በየእለቱ በምትሰሯቸው ስራዎችም ሆነ ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ትኩረታችሁን የምትጥሉባቸው ነገሮች ወሳኝ ናቸው፡፡ ማተኮር ከሚገባችሁ ነገር ላይ...
16/07/2026

የትኩረት ለውጥ!

በዚህች ምድር ላይ ስትኖሩ፣ በየእለቱ በምትሰሯቸው ስራዎችም ሆነ ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ትኩረታችሁን የምትጥሉባቸው ነገሮች ወሳኝ ናቸው፡፡

ማተኮር ከሚገባችሁ ነገር ላይ ይልቅ የማገባችሁ ነገር ላይ ስታተኩሩ አቅማችሁን ታጣላችሁ፣ ከመስመር ትወጣላችሁ፣ በጌታ ጸጋ ማለፍ የምትችሏቸው ነገሮች ሁሉ ያደክሟችኋል፡፡

የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ዘርፎች አስታውሱ፡፡

1. ያልሆናችሁት ላይ ሳይሆን የሆናችሁት ላይ አተኩሩ፡፡

ያልሆናችሁት ላይ ስታተኩሩ የሆናችሁትን እውነተኛ ማንነት መኖር ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት እንዳገኛችሁት ሰው ሁኔታ ያልሆናችሁትን ማንነት እየለዋወጡ መኖር ነው፡፡

“አሁን እኔ ተቀባይነት ለማግኘት የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሠኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሠኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁ ነበር” - ገላ. 1:10

2. የሌላችሁ ላይ ሳይሆን ያላችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

የሌላችሁ ነገር ላይ ስታተኩሩ ያላችሁን ነገር በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት ከሌላችሁ ነገር በመነሳት በዝቅተኝነት ስሜት የመመታት ሁኔታ ነው፡፡

“ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን፣ ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ። ብጠግብም ሆነ ብራብ፣ ባገኝም ሆነ ባጣ፣ በማንኛውም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር ተምሬአለሁ። ኀይልን በሚሰጠኝ በርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ” - ፊል. 4:11-13

3. የማታውቁት ላይ ሳይሆን የምታውቁት ላይ አተኩሩ፡፡

የማታውቁት ላይ ስታተኩሩ የምታውቁትን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት እውቀታችሁን ተጠቅማችሁ ከማደግ ይልቅ ስለማታውቁት ነገር በማሰብ ጊዜን መፍጀት ነው፡፡

“ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ እንከተል ዘንድ ለዘላለም የእኛና የልጆቻችን ነው” - ዘዳ. 29:29

ወሳኙና ጨዋታውን የሚለውጠው ነገር ትኩረታችሁ ነው፡፡ የሆናችሁት፣ ያላችሁና የምታውቁት ነገር ላይ ስታተኩሩና ቀና ብላችሁ በድፍረት ስትኖሩ፣ ያልሆናችሁት፣ የሌላችሁና የማታውቁት ነገር ላይ የመስራትና የማደግም እድላችሁ የሰፋ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ሕይወታችሁን ጠብቁ (Guard Your Life)“ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና” - ምሳሌ 4:23የሕይወታችን ጥራትና አቅጣጫ በአብዛኛው ወደ ሕይወታችን፣ ወደ ሰውነታችን ...
11/07/2026

ሕይወታችሁን ጠብቁ (Guard Your Life)

“ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና” - ምሳሌ 4:23

የሕይወታችን ጥራትና አቅጣጫ በአብዛኛው ወደ ሕይወታችን፣ ወደ ሰውነታችን እና ወደ አእምሯችን በሚገቡ ነገሮች ይወሰናል። እግዚአብሔር ወደ ሕይወታችን የሚገያስገቡ በሮችን ሁሉ በጥንቃቄ እንድንጠብቅ ይፈልጋል፡፡

1. ወደ ሕይወታችሁ የሚገባውን ሰው በጥንቃቄ ምረጡ

በሕይወታችን ውስጥ ካጋጠሙን ታላላቅ በረከቶች ወይም ጥልቅ ቁስሎች ብዙዎቹ የመጡት በሰዎች አማካኝነት ነው። አንዳንድ ግንኙነቶች ከቁጥጥራችን ውጪ ነበሩ፤ ብዙዎቹ ግን የራሳችን ምርጫ ውጤቶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ግንኙነቶች የባሕሪያችንን፣ የእጣ ፈንታችንን እና የመንፈሳዊ ሕይወታችንን ሁኔታ እንደሚቀርጹ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቀናል።

“አትሳቱ፤ መጥፎ ጓደኛነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል” - 1ቆሮ. 15:33

ግንኙነቶች በሮች ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ጥበብን፣ ማበረታቻን እና ዓላማን ይዘው ይመጣሉ፤ ሌሎች ግን ግራ መጋባትን፣ ፈተናን እና ጥፋትን ይዘው ይመጣሉ።
ያለፈው አልፏል፤ ከዛሬ ጀምሮ ግን ወዳጅነቶችን፣ አጋርነቶችን፣ አማካሪዎችን እና የቅርብ ግንኙነቶችን በጸሎት እና በጥበብ ምረጡ።

2. ወደ ሰውነታችሁ የሚገባውን ነገር በጥንቃቄ ምረጡ

ሰውነታችን በተከታታይ የምንሰጠውን ነገር ያንጸባርቃል። ምግብ፣ መጠጥ፣ ልማዶች፣ ሱሶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች ሁሉ በጤንነታችን፣ በጉልበታችን እና የእግዚአብሔርን ዓላማ የመፈጸም ችሎታችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እግዚአብሔር ሰውነታችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይጠራናል።

“ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ 20በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ” – 1ቆሮ. 6:19-20

ሰውነታችን የራሳችን ብቻ አይደለም፤ በእግዚአብሔር የተሰጠን ቤተ መቅደስ ነው። ቸል ማለት ለእርሱ አገልግሎት ያለንን ብቃት ሊገድብ ይችላል።
ያለፈውን መቀየር አይቻልም፤ ከዛሬ ጀምሮ ግን ጤናን እና እግዚአብሔርን መምሰል የሚያበረታቱ ምርጫዎችን ለማድረግ ተግተን እንስራ።

3. ወደ አእምሯችሁ የሚገባውን ሃሳብ በጥንቃቄ ምረጡ

ወደ አእምሯችን የሚገቡ ፍልስፍናዎች፣ እምነቶች፣ ምስሎች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ ትምህርቶች እና ሃሳቦች በመጨረሻ ስሜታችንን፣ አመለካከታችንን እና ድርጊታችንን ይቀርጻሉ። የሕይወት ጦርነት በአብዛኛው የአእምሮ ጦርነት ነው።

“ሐሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን” - ቈላ 3:2

በተደጋጋሚ ወደ አእምሯችን የሚገባው ነገር በመጨረሻ ጠንካራ ምሽግ ይሆናል፤ ይህም የባህሪያችን መለኪያ ነው። የተሳሳተ አስተሳሰብ፣ የተሳሳተ ሕይወትን ያስከትላል፤ የታደሰ አስተሳሰብ ግን የተለወጠ ሕይወትን ይፈጥራል።

በአእምሯችሁ ውስጥ የገቡት የተሳሳቱ ሃሳቦች ወይም አሰቃቂ ትዝታዎች ምንም የከፉ ቢሆኑ፣ እግዚአብሔር አእምሮአችሁን ሊያድስና ሕይወታችሁን ሊለውጥ ይችላል።

ማጠቃለያ

የተጠበቀ ሕይወት የጥበበኛ ሰው ሕይወት ነው።

• ግንኙነታችሁን ጠብቁ፤ ሰዎች በእጣ ፈንታችሁ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉና።

• ሰውነታችሁን ጠብቁ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነውና።

• አእምሯችሁን ጠብቁ፤ ሃሳባችሁ ሕይወታችሁን ይቀርጻልና።

ዛሬ ከሕይወታችሁ የሚወጣው ነገር ሁሉ ወደ ውስጥ እንዲገባ በተፈቀደለት ነገር የተገናኘ ነው። ስለዚህ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ የሕይወታችሁን በሮች በጥበብ ጠብቁ።

Dr. Eyob ነኝ!

የምታልፉበት ነገርና የተልእኳችሁ ግንኙነት✔️ አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ምግብ በእሳት ውስጥ ካላለፈና ካልበሰለ አይፈለግም፣ ለጥቅምም አይውልም፡፡✔️ አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ አይስክሬም በ...
10/07/2026

የምታልፉበት ነገርና የተልእኳችሁ ግንኙነት

✔️ አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ምግብ በእሳት ውስጥ ካላለፈና ካልበሰለ አይፈለግም፣ ለጥቅምም አይውልም፡፡

✔️ አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ አይስክሬም በበረዶና በቀዘቀዘ ሁኔታ ውስጥ ካላለፈ አይፈለግም፣ ለጥቅምም አይውልም፡፡

✔️ አንዳንዱ ነገር ልክ እንደቆዳ ካልለፋና ካልለሰለሰ አይፈለግም፣ ለጥቅምም አይውልም፡፡

✔️ አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ጥሬ መሬት ላይ ተጥሎ ካልተረገጠ፣ ካልተቀበረና ካልተረሳ ጊዜ ጠብቆ አድጎና አፍርቶ አይፈለግም፣ ለጥቅምም አይውልም፡፡

የምታልፉበት ሁኔታ ዋጋና ትርጉም አለው!

“እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን” - ሮሜ 8:28

“ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ” - ኢዮ. 23፡10

የምታልፉበትን ሁኔታ ካለፋችሁ በኋላ ጌታ ሊጠቀምባችሁ ወደ ሚፈልገው ውብ ወደ ሆነ ነገር ያወጣችኋል!

በርቱ!!!

ይህንን የተስፋ ቃል ለአንድ ሰው forward በማድረግ share አድርጉ!

Dr. Eyob ነኝ!

“ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘውን የሐምሌ ወር ንባብ ቀጥለናል፡፡ በተለያየ ምክንያት ያመለጣችሁ ብዙ ርቀን ሳንሄድ ዛሬ በመቀላቀል ከነገ ማለዳ ጀምሮ አብራችሁን መጓዝ ትችላላችሁ፡፡የንባብ ወር - ...
09/07/2026

“ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘውን የሐምሌ ወር ንባብ ቀጥለናል፡፡

በተለያየ ምክንያት ያመለጣችሁ ብዙ ርቀን ሳንሄድ ዛሬ በመቀላቀል ከነገ ማለዳ ጀምሮ አብራችሁን መጓዝ ትችላላችሁ፡፡

የንባብ ወር - ሐምሌ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ጀምሮ መጨረስ”

ንባቡ የጀመረት ቀን - ትናንትና ሮብ ሐምሌ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሐምሌ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!

ነጻ የስልጠና እድል!የስልጠናው ርእስ፡- የአመራር ጥበብ እና ስልት(መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ) The Art and Strategy of Leadership(A Biblical Perspective)✝️ ራ...
08/07/2026

ነጻ የስልጠና እድል!

የስልጠናው ርእስ፡- የአመራር ጥበብ እና ስልት
(መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ)

The Art and Strategy of Leadership
(A Biblical Perspective)

✝️ ራስን መምራት (Leading Self)

✝️ ሰዎችን መምራት (Leading Others)

✝️ ሥራን መምራት (Leading Work)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በአካል በመገኘት

የስልጠናው ቦታ፡- IMPACT የአምልኮ ማዕከል (አዲስ አበባ)

የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 16፣ ነሃሴ 23 እና ነሃሴ 30 (ሶስት ቅዳሜ ከሰዓቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለሶስቱም ቅዳሜዎች ከ9፡00 እስከ 12፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:- ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

በሚገባ ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች Certificate ይሰጣል፡፡

እናመሰግናለን!

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም...
08/07/2026

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://t.me/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo

የአገልግሎት ስልጠና እድል"የበዛ ሕይወት እና አገልግሎት”“ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም”- ዮሐ. 10:10ከበዛና ከተትረፈረፈ ሕይወት የሚወጣና ለሌሎች የሚፈስስ አገልግሎት!ስልጠናው ...
17/03/2026

የአገልግሎት ስልጠና እድል

"የበዛ ሕይወት እና አገልግሎት”

“ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም”- ዮሐ. 10:10

ከበዛና ከተትረፈረፈ ሕይወት የሚወጣና ለሌሎች የሚፈስስ አገልግሎት!

ስልጠናው የሚመለከታቸው ሰዎች፡-

✝️ ከዚህ በፊት በመንፈሳዊ አገልግሎት ተሳትፋችሁ ካላወቃችሁ!

✝️ ከዚህ በፊት ከነበራችሁ አገልግሎት አቁማችሁ ከሆነ!

✝️ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ ካላችሁና ስለአገልግሎት ያላችሁን ምልከታ ለማስፋትና ጸጋን ለመካፈል ፍላጎት ካላችሁ!

ለመመዝገብ፦
➡️ በቴሌግራም፡- በዚህ የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ስምና ስልክ ቁጥር ያስቀምጡ፡፡

➡️ በስልክ፡- በ 0933729694 በመደወል ሙሉ ስምና ስልክ ቁጥር ይስጡ፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ስልጠናው የሚሰጠው ለተመዘገቡ ብቻ ነው፡፡

የስልጠኛው note በየሳምንቱ በቴሌግራም ስለሚለቀቅ ለስልጠናው ተመዝጋቢወች የሚከፈተውን የቴሌግራም ግሩፕ መቀላቀል የግድ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ፖስተሩን ይመልከቱ!

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Tuesday 09:00 - 20:00
Wednesday 09:00 - 20:00
Thursday 09:00 - 20:00
Friday 09:00 - 20:00
Saturday 09:00 - 20:00
Sunday 09:00 - 14:00

Telephone

+251114670154

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Impact Worship Center - የክርስቲያኖች መቅደስ ቤ/ክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Impact Worship Center - የክርስቲያኖች መቅደስ ቤ/ክ:

Shortcuts

Share