Life Centered Holistic Ministry,Ethiopia

Life Centered Holistic Ministry,Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Life Centered Holistic Ministry,Ethiopia, Religious organisation, Addis Ababa.
(1)

ላይፍ ሴንተርድ ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ/Life Centered Holistic Ministry በገንዘብ ለመርዳት እና ከእኛ ጋር በወንጌል ስርጭት በስልጠና ለመቆም የምትፈልጉ እነሆ የሚኒስትሪ ባንክ አካውንት።
1000709106981,CBE Life Centered Holistic Ministry
1601990107104,Birahan Bank
1071100071841,Cooperative Bank/COOP.

03/04/2026
በጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ/ፋውንዴሽን በአድዋ ሙዝየም በተዘጋጀው የሙሉ ቀን ስልጠና ስለ ጊዜ ወይም Reading the Signs of the time"በሚል ርዕስ የተሰጠን ስልጠና እጅግ አስገራሚ ጊዜ...
15/08/2025

በጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ/ፋውንዴሽን በአድዋ ሙዝየም በተዘጋጀው የሙሉ ቀን ስልጠና ስለ ጊዜ ወይም Reading the Signs of the time"በሚል ርዕስ የተሰጠን ስልጠና እጅግ አስገራሚ ጊዜ ነበረን።ይህንን ስልጠና የሰጡት ዶክተር ለማ ደገፋ,ዶክተር ምህረት ደበበ,ዶክተር ቄስ ሳሙኤል ዮናስ,ዶክተር ገለታ እና ሌሎችም።ቄስ ጉዲና ቱምሳ የምድር ቆይታቸው በጣም አጭር ጊዜ ቢሆንም የሰሩት ሥራ እስከ አሁን እያወራ ነው።የእኝህ ጀግና የእግዚአብሔር አገልጋይ ለብዙዎቻችን ጠቃሚ ትምህርት ሆኖልናል።

"የዘመኑን ምልክቶች ማንበብ የሚለው ቃል ለሁሉም ሰው ወሳኝ መልዕክት ነው።“የእግዚአብሔር ወቅት,ጊዜ ወይም ዘመን”የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ በደንብ አብራርተው አስተምሮናል።ከተማሪነው ውስጥ ጥቅቱን እነሆ።የእግዚአብሔር ጊዜ ወይም ዘመን የሚለው ቃል በግሪክ ቃል እንዲህ ይጠራል,“ካይሮስ” (καιρός)፣ ስሆን እሱም "በእግዚአብሔር የተወሰነ፣ በመለኮት የተወሰነ ጊዜን ወይም ዘመንን ያመለክታል።ይህም ሁነኛና እና ዕድለኛ ጊዜን(Opportune) ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ"ክሮኖስ" (χρόνος) የሚለው ደግሞ ተቆጣሪ እና ተቀማሪ ጊዜ,(Calendar),ሰው የምኖርበትን,በምድር ላይ ያለውን ጊዜ ያሳያል።

የካይሮስ ጽንሰ-ሀሳብ በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ጊዜ የመረዳት እና የመለየት አስፈላጊነትን የሚያሳይ እና እግዚአብሔር የሰጠንን በአገባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። በክሮኖስ ዙሪያ የተዋቀሩ ዕቅዶች ሊኖረን ቢችልም፣ የእግዚአብሔርን ግብአት መፈለግ እና ካይሮስን ማወቃችን በእሱ ዋና ዓላማ እና ጊዜ ውስጥ እንድንመላለስ ያስችለናል።

ይህ አጠቃላይ እይታ “የእግዚአብሔር ወቅት” በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የካይሮስን በአማኝ ሕይወት ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድንና ፕሮግራሙን እንድንረዳ ያስችለናል።እግዚአብሔር ሆይ የአንተ ካይሮስ እንዳያመልጠን አንተ እርዳን።በሰጠን ዘመንና ጊዜ የአንተን ዕቅድ እንድንፈጽም አንተ እርዳን።

በትጋት ወደ ስኬት በሚል መርህ ቃል በትጋት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ሥራ/ማህበር በሳሮማሪያ(Saro Maria)ሆቴል ያዘጋጀውን ስልጠና የሚኒስትሪያችን ደይሬክተር እና የርኆቦት አ...
31/07/2025

በትጋት ወደ ስኬት በሚል መርህ ቃል በትጋት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ሥራ/ማህበር በሳሮማሪያ(Saro Maria)ሆቴል ያዘጋጀውን ስልጠና የሚኒስትሪያችን ደይሬክተር እና የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት የመንፈሳዊ ዘርፍ ደይሬክተር የሆኑት መጋቢ ኤልያስ ጳውሎስ ተካፍለዋል።

በዚህም ስልጠና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል መሪዎችን ጨምሮ ከተለያዬ አብያተክርስቲያናት የመጡ መሪዎች እና አገልጋዮች ተካፋይ ሆነዋል።

ለአገልጋዮች እና ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ስለሆነ የትጋት አባል እና ደንበኛ ይሁኑ።በጎሮ,በመገናኛ,በአየርጤና,በጆሞ እና በሌሎችም አካባቢ ቅርንጫፎች ስላሉ ፈጥሮ ይመስገቡ።

የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት መሪዎች እና የህብረቱ ፕረዚዳንት ፓስተር ካሳሁን እምሩ ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ።እንዲሁም መጋቢ ዶክተር አዲስ ተባረክልኝ።

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ባዘጋጀው "ፕሮጀክት ዜሮ" የሚል ስያሜ የተሰጠውን  በ2030 እ.ኤ.አ,በአምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በወንጌል ያልተደረሱ ሕዝቦች ...
16/07/2025

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ባዘጋጀው "ፕሮጀክት ዜሮ" የሚል ስያሜ የተሰጠውን በ2030 እ.ኤ.አ,በአምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በወንጌል ያልተደረሱ ሕዝቦች ሁሉ ተድርሰው ማየት የሚል አዲስ የወንጌል ንቅናቄ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከተለያዩ ቤተ-እምነቶች,አብያተክርስቲያናት,ሚኒስትሪዎች,የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች,እና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች ገለጻ ተድርጓል።
የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረትን በመወከል ፓስተር ኤልያስ ጳውሎስ (የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት መንፈሳዊ ዘርፍ ደይሬክተር እና ዶክተር ቶማስ መለሰ(የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ምክትል ፕረዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ ግንኘነት ኃላፍ ፕሮግራሙን ተካፍለዋል።ቀጣይም በአንድነት ለመስራት በመነጋገር አቅጣጫ በማስቀመጥ ፕሮግራሙን ተጠናቋል።

"ተስፋ በሰቆቃ ውስጥ"በሚል ርዕስ በቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኀበር(Billy Graham Evangelical Association)ያዘጋጀውን የሙሉ ቀን ስልጠና በጣም ጠቃሚ ትምህርት እና ስልጠና ...
27/06/2025

"ተስፋ በሰቆቃ ውስጥ"በሚል ርዕስ በቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኀበር(Billy Graham Evangelical Association)ያዘጋጀውን የሙሉ ቀን ስልጠና በጣም ጠቃሚ ትምህርት እና ስልጠና ተሰጥቶናል።መቀጠል ያለበት ጥሩ ስልጠና ነው።

በISA60 International Ministry አዘጋጅነት ለርኆቦት አብያተክርስቲያናት ለቦርድ አመራሮች,ለጽ/ቤት ሠራተኞች,እና ለቤተክርስቲያን መሪዎች "ተነሽ እና አብሪ" በሚል ርዕስ የሁለ...
12/06/2025

በISA60 International Ministry አዘጋጅነት ለርኆቦት አብያተክርስቲያናት ለቦርድ አመራሮች,ለጽ/ቤት ሠራተኞች,እና ለቤተክርስቲያን መሪዎች "ተነሽ እና አብሪ" በሚል ርዕስ የሁለት ቀናት ሰልጠና ተሰጥተዋል።በዚህ ስልጠና የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ፕረዚዳንትን ጨምሮ ወደ 25 የሚሆን አገልጋዮች ስልጠናውን አግኝተዋል።
በዚህ ስልጠናም ደስተኞች መሆናቸውንና እና የህብረቱ አባል ቤተክርስቲያኖችም ስልጠናውን እንድያገኙ ለማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ,የISA60 International Ministry ስልጠና ወሳኝ, ጠቃሚ,ለታላቁ ተልዕኮ የሚያነሳሳ መሆኑን አንስተዋል።
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን,ዶክተር ቶማስ እና ስልጠናውን ሰጥተናል።በመጨረሻም ስልጠናው Certificate በመስጠት ተጠናቀቀ።

"በሕንድ አይሮፕላን አደጋ ከ242 ተሳፋሪዎች ውስጥ በ11A መቀመጫ ላይ የተቀመጠ አንድ እንግሊዛዊ ተሳፋሪ መትረፉ ተገለጸ" ?✍️1. መቼ? ዬት? እንዴት? ጌታ እንደሚመጣ ስለማናውቀው  ሁሉ...
12/06/2025

"በሕንድ አይሮፕላን አደጋ ከ242 ተሳፋሪዎች ውስጥ በ11A መቀመጫ ላይ የተቀመጠ አንድ እንግሊዛዊ ተሳፋሪ መትረፉ ተገለጸ"

?
✍️1. መቼ? ዬት? እንዴት? ጌታ እንደሚመጣ ስለማናውቀው ሁሉ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ንስሐ እየገባን መጠበቅ አንዳለብን። ወደ ዘላለሙ መንግስት ለመግባት ክርስቶስ እየሱስ በመስቀሉ በሰራው ስራ በእርሱ አምኖ ዳግም በመወለድ በክርስቶስ የመንግሥት ወራሽ በመሆን መጠበቅ አለብን። እንደሚኖር ሰው መልካሙን የምስራቹን ወንጌል በመስበክና ፤ ጌታችን እየሱስን ፊት ለፊት ለማየት አሁን በቅርቡ እንደሚመጣ ደጅ ደጁን እያየን መጠበቅ አንዳለብን።
✍️2. በእኛ ላይ ልስራ ያለውን የወንጌል አገልግሎት ሳንጨርስ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ ሰማይ ዝቅ ብል ምርት ከፍ ብል ምንም አንሆንም። አልፎ ማለፍ ይሆናል።
✍️3. ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን ልብ መኖር እንዳለብን እንማራለን።

.

ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ ከሚመጣ ከማንኛውም ከክፉ አደጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የተሸፈናችሁ እንድትሆኑ እጸልያለሁ።
(Mulatu Defare)

  ለታላቁ    !
31/05/2025

ለታላቁ
!

31/05/2025
  ስልጠና ይሰጣል !
30/05/2025

ስልጠና ይሰጣል
!

በወንጌል ብርሃን አለምአቀፍ ቤተክርስቲያን ዋና መሪ በሆኑት በሐዋርያው ዳንኤል መኮንን ራዕይ ተቀባይነት " እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል።”   — ዘፍጥረት 50፥24,በሚል ርዕስ ለሀ...
27/05/2025

በወንጌል ብርሃን አለምአቀፍ ቤተክርስቲያን ዋና መሪ በሆኑት በሐዋርያው ዳንኤል መኮንን ራዕይ ተቀባይነት " እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል።” — ዘፍጥረት 50፥24,በሚል ርዕስ ለሀገር መሪዎች ,ለቤተክርስቲያን መሪዎች እና ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በተዘጋጀው የግማሽ ቀን ኮንፈረንስ ላይ ተካፈለናል።የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምተን ተደስተን ለቀጣይ አገልግሎት በመዘጋጀት ተመልሰናል።ዶክተር ቄስ ቶሎሳ ጉዲና(የኢትዮጵያ መንፈሳዊ አባት),ሐዋርያው ዳንኤል መኮንን(የኢትዮጵያ መንፈሳዊ አባት),ዶክተር መጋቢ አበራ ሀብቴ(የእልሻዳይ ቴለቪዥን መስራች እና ባላቤት),ቄስ ሳሙኤል ኃይሉ(የሚሊኒየም የፀሎት እና የምልጃ አገልግሎት መሪ)መልዕክት አስተላልፏል።እንዲሁም በፀሎት እና በምክር አገልግሎናል።ኃያላን ተባረኩ,ለሚነሳው ሪቫይቫል እንዘጋጅ።ሚኒስትሪያችን የዚህ ፕሮግራም አካል በመሆን እና በመገኘት የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ የተዘጋጀን መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

Address

Addis Ababa
22/1033

Telephone

+251913465995

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Life Centered Holistic Ministry,Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Life Centered Holistic Ministry,Ethiopia:

Share