ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ- Holy Trinity University

ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ- Holy Trinity University ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ- Holy Trinity University

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን መመረቃቸውን አስመልክቶ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መርሐ ግብር ተካሔደ________ቅስዩ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. — በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ...
05/09/2026

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን መመረቃቸውን አስመልክቶ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መርሐ ግብር ተካሔደ
________
ቅስዩ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. — በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ/ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪ ምርቃት መርሐ ግብረሰ በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ በልዩ ሁኔታ ተከበረ።

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የክፍል ኃላፊዎች፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የአስተዳደር ሓላፊዎችና ሠራተኞች፣ የተጋበዙ እንግዶች፣ ቤተሰቦችና ወዳጆች ተገኝተዋል።

የበዓሉ መርሐ-ግብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቃውንትና ካህናት በቀረበ ጸሎተ ወንጌል ተጀምሯል። በመቀጠልም በመልአከ ኃይል አባ ጽጌ ድንግል ፈንታሁን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ቀርቧል።

በመርሐ-ግብሩ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቃውንትና መምህራን ያቀረቡት ወረብ የዝግጅቱን መንፈሳዊ ድባብ ያጎላ ሲሆን፣ "ፍኖተ ሕይወት" መጽሔት ምርቃትም በመስተንግዶ ኮሚቴ አቅራቢነት በብፁዓን አባቶች ተከናውኗል።
በዕለቱ የብፁዕ አቡነ ፊልጶስን የትምህርት ጉዞ፣ የአካዳሚክ ዝግጅትና የዶክትሬት ምረቃ ሂደት የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም በራማ ሚዲያ ቀርቧል። ፊልሙም ብፁዕነታቸው በትምህርት የተጓዙበትን ሂደትና በእውቀት ፍለጋ ያሳለፉትን የትጋት ጉዞ በምስልና በድምፅ ዳስሷል።

በመቀጠልም የብፁዕነታቸው የዶክትሬት ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ ዳሰሳ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት በሆኑት በፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ፣ የዶክትሬት ጥናቱን ይዘትና አካዳሚክ ጠቀሜታ ያስቃኘ ሆኖ ቀርቧል።

በዚሁ መርሐ-ግብር መምህር ክነፈ ርግብ ያቀረቡት ቅኔ ለዝግጅቱ ያማረ ድባብ ሰጥቷል። ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ከተለያዩ አካላት የተዘጋጀው የስጦታ መርሐ-ግብርም ተከናውኗል።

ከስጦታ መርሐ-ግብሩ በኋላ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) መልእክትና ምስጋና አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው በትምህርት ቆይታቸው ያሳለፉትን ሂደት፣ በጥናት ያገኙትን ዕውቀትና የዶክትሬት ጥናታቸውን በማስመልከት ገለጻ አድርገዋል። እምነት፣ እውነትና ዕውቀት የትምህርት መሠረታዊ መርሆች መሆናቸውንም አጽንዖት ሰጥተዋል።

በተለይም በትምህርት ሒደት ላይ ያለ ሰው ለስኬት ሊከተላቸው የሚገቡ አምስት ዋና ዋና ነጥቦችን አብራርተዋል። እነዚህም፦
1. ግልጽ ዓላማና ግብ መያዝ፤
2. ጽናትና ራስን መግዛት፤
3. ጊዜን በውጤታማነት መጠቀም፤
4. ትክክለኛ የጥናት ስልትና ዕቅድ መከተል፤
5. የአካባቢና የማኅበራዊ ድጋፍን በአግባቡ መጠቀም ናቸው።
ብፁዕነታቸው እነዚህ መርሆች በትምህርት ጉዞ ላይ ላሉ ተማሪዎችና ዕውቀትን ፍለጋ ላይ ለሚገኙ ሁሉ አስፈላጊ መሠረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው በዶክትሬት ትምህርታቸውና በምረቃው ሂደት የተሳተፉ መምህራንን፣ የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ፣ በዕለቱ የተገኙ አባቶችን፣ ዕንግዶችንና በሒደቱ የተሳተፉትን ሁሉ አመስግነዋል።

የመርሐ-ግብሩ መጨረሻ ላይ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስን ቃለ ምዕዳንና ቃለ በረከት እንዲሰጡ ጋብዘዋል።

ብፁዕ አቡነ ማርቆስም በቃለ ምዕዳናቸው ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደረሱበት የትምህርት ደረጃ ለሌሎች ወጣት ሊቃነ ጳጳሳትና ለትውልዱ አርአያ መሆኑን ገልጸዋል። ብፁዕነታቸው በትምህርትና በአገልግሎት የተገነባው የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጉዞ፣ "ዘመኑን ዋጁ" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በተግባር የሚያሳይ ምሳሌ መሆኑን መስክረዋል።

የዶክትሬት ዲግሪውን በማግኘታቸውም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስን አድንቀውና አመስግነው፣ ይህ ስኬት ለሌሎች ወጣት ሊቃነ ጳጳሳትና ለቤተ ክርስቲያን ልጆች በትምህርት የበለጠ እንዲገሰግሱ የሚያነሣሣ አርአያ መሆኑን ገልጸዋል። ብፁዕነታቸውም ቃለ በረከት በመስጠት መርሐ-ግብሩን በጸሎት አጠናቀዋል።

ይቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!!
02/09/2026

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!!

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ትንሣኤ(ፍለሰታ ለማርያም) በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል !!
22/08/2026

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ትንሣኤ(ፍለሰታ ለማርያም) በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል !!

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ...
06/08/2026

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!

የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤
ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡

ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው!

ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል
ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣

ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣

በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤
የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡

ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤

በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣

እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤

ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው!

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡

በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡

በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት  አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።...
25/07/2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦
እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።"
(መዝሙር ፻፪፥፮)

ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት።

በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው።

መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው።

በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ።

በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሓላፊ/ሊቀ ጳጳስ እና የደቡብ ኦሞና አሪ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንኳን ለ፱ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላም አደረሰዎ!ቡራኬዎ አ...
16/07/2026

ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሓላፊ/ሊቀ ጳጳስ እና የደቡብ ኦሞና አሪ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንኳን ለ፱ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላም አደረሰዎ!

ቡራኬዎ አይለየን!

የጨረታ ማስታወቂያ
10/07/2026

የጨረታ ማስታወቂያ

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++ https://youtu.b...

08/07/2026

Address

Holy Trinity University
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ- Holy Trinity University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share