Eshtaol, the life of awakening

Eshtaol, the life of awakening The life of awakening!! Judge 13:24_25

18/11/2023

መንፈስ ቅዱስ እንዳንተ ያለ መካሪ የለም🙏

አብራችሁኝ ጸልዩ 👇👉🏻ከመጠን ያለፈ ጭንቀት በሽታ አይደለም መንፈሳዊ ውጊያ ነው። ምነው አመናፈስከው ልትሉኝ ትችላላችሁ ልንገራችው መንፈሳዊው ዓለም አይናችሁ ተከፍቶ ካላያችሁት አይገባችሁም።...
18/10/2023

አብራችሁኝ ጸልዩ 👇

👉🏻ከመጠን ያለፈ ጭንቀት በሽታ አይደለም መንፈሳዊ ውጊያ ነው። ምነው አመናፈስከው ልትሉኝ ትችላላችሁ ልንገራችው መንፈሳዊው ዓለም አይናችሁ ተከፍቶ ካላያችሁት አይገባችሁም። 24 ሰዓት ያለማቋረጥ መንፈሳዊ ውጊያ ይደረጋል። ነፍሳችን በዚህ መሃል ትጨነቃለች ያ ነው ጭንቀት(depression) የምንለው።

👉🏻ነፍሳችሁ በእንደዚ አይነት ጭንቀት ውስጥ ያላችሁ ሰዎች በተለይ ወጣቶች ወደ ጸሎት፣ቃሉን ማንበብ እና ማሰላሰል፣ ከመንፈስ የሆነ አምለኮ ማደረግ፣ መንፈሳዊ ህብረቶችን ከ ክርስቲያን ወንደሞች እና እህቶች ጋር ማድረግ መንፈስ ቅዱስ ባናንተ ውስጥ የሚታይን ለውጥ እንዲያመጣ በር ይከፈታል ምክኒያቱም መንፈስ ቅዱስ ጨዋ አምላክ ነው የኛን ፍቃደኝነት ይፈለጋል።

👉🏻ይህንን ጸሁፍ የምታነቡ ወንደሞቼ እና እህቶቼ በእንደዚ አይነት ችግር ውስጥ ያላችው ነፍሳችሁ በጣም በጭንቀት ውስጥ ያለች ግራ የገባችሁ እቤት ውስጥ ተኝታችሁ ያላችሁ፣ ጨለማ ውስጥ ብቻችሁን ተቀምጣችሁ ይህንን ጸሁፍ ምታነቡ፣ መታዋዩት ዘመድ፣ ጓደኛ የሌላችሁ፣ ለሰው በታወሩም ሊረዷችሁ የማይችሉት ጉዳይ ይዛችሁ የተቀመጣችሁ ዛሬ እነግራችኋለው በዛ ባላችሁበት ሁኔታ መንፈስ ቅዱስ ይንካችሁ ✋አሁን በዚህ ሰአት እጁ ያቺ ነጻ መታወጣው የምህረት እጁ ነጻ እንደታወጣችሁ እጸልያለው ✋

የማቴዎስ ወንጌል - Matthew 11 - መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን
".. ቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም። 28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

10/07/2023

ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው?

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ነች፣ ሁሉም ሰዎች የክርስቶስን የድነት ስጦታ ተቀብለው የክርስቶስን ትምህርት በመከተል ከህንጻ በላይ ናት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "ቤተክርስቲያን" ሕንፃን ፈጽሞ አያመለክትም. ሁልጊዜ የሚያመለክተው ክርስቶስን የሚከተሉ ሰዎችን ነው 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13

እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን እንዴት መለየት እንችላለን?

በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እምነቶች ክርስቶስን እንከተላለን ይላሉ። እርስ በርሳቸው የሚጋጩ አስተምህሮዎችና ተግባራት ስላሏቸው ሁሉም ትክክል ሊሆኑ አይችሉም። በኢየሱስ የሚያምን ሰው የቤተ ክርስቲያኑን ማንነት የመለየት ፈተና ይገጥመዋል። የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ከሰው ቤተ እምነቶች የሚለዩት የትኞቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባህርያት ናቸው? የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መለያ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

1, እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በክርስቶስ ነው እርሱም ብቻ ራስ ነው። ማቴዎስ 16፡18፣ ኤፌሶን 1፡22፣23፣ ዮሃንስ 10፡16

2, እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን በመከተል የቀደመውን እምነት ትጠብቃለች። ይሁዳ 3፡2፣ 2 ጢሞቴዎስ 3፡13_17

3, የክርስቶስ ትምህርት ለእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን መደበኛ ነው (ከተፃፈው አይበልጥም) 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡6

4, እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን በፍቅሯ ትታወቃለች። ይሁዳ 1፡2፣ 1 ዮሃንስ 5፡3፣ ኤፌሶን 4፡15፣ ዮሃንስ 13፡34_35

5, የእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን አምልኮ በመንፈስና በእውነት ነው። ዮሐንስ 4፡24፣ ማር 7፡6_7

6, እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያውን ወንጌል ትሰብካለች። ገላ 1፡6_9

እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ መፅሐፍቅዱሳዊ እዉነቶች ካላሟላ እዉነተኛ ቤተክርስቲያን ሊባል አይችልም!!

"ፓስተር ቢሊ ግራም በኢትዮጲያ!!" የተከበሩ የእግዚአብሔር ባሪያ ቢሊግራም በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት በአዲስ አበባ ስቴዲየም ወንጌልን ጃንሆይ በተገኙበት ሠብከው ብዙዎች በዚያን ጊዜ ጌታን...
06/05/2023

"ፓስተር ቢሊ ግራም በኢትዮጲያ!!"

የተከበሩ የእግዚአብሔር ባሪያ ቢሊግራም በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት በአዲስ አበባ ስቴዲየም ወንጌልን ጃንሆይ በተገኙበት ሠብከው ብዙዎች በዚያን ጊዜ ጌታን የተቀበሉ ወጣቶች ለእግዚአብሔር ቤት በረከት ሆነዋል።

በጊዜው ስብከቱን በትርጉም ለብዙዎች ያደርሱ የነበሩትና አሁን ልጆቻቸው ጌታን በብዙ የሚያገለግሉት የፓስተር እንድሪያስ፤ ፓስተር ዓብይና፤ የዘማሪ እንዳልካቸው አባት አቶ ሃዋዝ ነበሩ። የወንጌል አሻራቸው እኛም አገር አለ።
ክብር ለስሙ ይሁን!!

ኔሽን መጽሔት

🔥🔥🔥 what a worship!!!
24/01/2023

🔥🔥🔥 what a worship!!!

ቅዱስ | ቸሊና እና ይድነቃቸው የአምልኮ ጊዜ | Halwot Emmanuel United Church

Address

Bole
Addis Ababa

Telephone

+251946330807

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eshtaol, the life of awakening posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Eshtaol, the life of awakening:

Share