Christ Community International Church -CCI

Christ Community International Church -CCI Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Christ Community International Church -CCI, Religious organisation, Addis Ababa.

29/05/2022

ዘመናችንን አድስ!!!!
ክፍል 3
የሆነብንን አስብ!!!
በሰቆቃው ኤርሚያስ መፅሐፍ ላይ ****እንዴት**** ይሄ ሆነብን እያለ የሚጠይቅ የሚማፀን ወደ እግዚአብሔር የሚያለቅስ ነብይ ፅሁፍ ነው!!! ሰቆ.ኤር 5:1
"አቤቱ የሆነብንን አስብ" ብሎ ይጮሃል!!! ይሄን ደስ የማይል ነገር ዝም ብሎ በህይወታችን እና በዘመናችን ሲሆን ቁጭ ብሎ መመልከት የለብንም!!! እየሆነልን ሳይሆን እየሆነብን ሲቀጥል እግዚአብሔር የሆነብንን አስብ???ማለት መልካም ነው?? የሚሆኑትን መጥፎ ነገሮች መላመድ እና አብሮ መቀጠል የለብንም!!እስኪ የሆነብንን ምንድነው???
1.ስድብ(ክብር አልባ ሕይወት)
"ስድባችንንም እይ" ቁ 1
ንቀትና ስድብ እንዲሁም ውርደት ሲሆንብን ዝም አይባልም!!!
2.ንጥቂያ(የእኛ የሆነ ነገር ሌሎች ሲወስዱት)
"ርስታችን ለእንግዶች
ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ" ቁ2
በሕግም በተፈጥሮም የእኛ የሆኑ ነገሮች በሌሎች ሲወስዱት እና ስንቀማ ዝም አይባልም??
3.ምንጭ እና ከለላ አልባ ስንሆን!!!
"አባት የሌለን ሆነናል" ቁ 3
አባት ምንጭ ነው አባት ከለላ ነው ከለላ እና ምንጭ አልባ መሆን ሲመጣ ዝም ብለን መመልከት የለብንም!!
4.ለትንንሽ ነገሮች ብዙ ዋጋ መክፈል!!
"ውኃችንን በብር ጠጣን
እንጨታችንን በዋጋ ገዛን" ቁ 4
ለሕይወት የሚያስፈልጉ ትንንሽ ነገሮች በጣም ብዙ ዋጋ እንድንከፍልባቸው ስንጠየቅ ይሄንን ዝም ማለት የለብንም!!!
እናም አቤቱ የሆነብንን አስብ??? ማለት አለብን እንጂ ዝም ብለን ማየይት የለብንም!!! ደግሞም ዘመናችንን አድስ ማለት ይጠበቅብናል!!! ቁጭ ብለን የሆነብንን እያየን ብናማርር መፍትሄ አይሆንም!!! ዘመን ይታደሳል!!!

09/05/2022

ዘመናችንን አድስ!!!
ክፍል ሁለት!!
በመጀመሪያው ክፍል እንዴት?? እንደዚህ ሆንን ብለን እንጠይቅ የሚለውን መንደርደሪያ አንሰተናል!! እናም ጥያቄ ማንሳት የለውጥ የታሃድሶ መደርደሪያ ነው ብለናል!!!
2. ወደ አንተ መልሰን???
የውድቀት የሽንፈት እና የኪሳራ ሁሉ ምክንያት እኛ ከእግዚአብሔር በመራቃችን የመጣ ነው ብሎ የደመደመ ይመስላል ነብዩ? ሰቆ 5:21
" አቤቱ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን" ይላል
የመራቅ ከእግዚአብሔር የመሸሽ ኪሳራው ብዙ ነው!!! ስለዚህ **መልሰን** እያለ ይማፀናል!!! የዘመን መታደስ ያለው እያንዳንዳችን ከዕራቅንበት የዕርቀት መጠን መመለስ ስንችል ነው! ***መልሰን*** ብቻ እኮ አይደለም የሚለው??
መልሰን ይልና ***እኛም እንመለሳለን*** ይላል!!!
መመለስ የሚፈልገው በዘመኑ እና በትውልዱ የሚመለከተው ውድቀት ሁሉ ከእግዚአብሔር በመራቃችን የመጣ እንደሆነ በመገነዘብ ይመስላል!! ነገር ግን ለመመለስ አቅም ያጣ ሰው ??
ወገኖቼ የምናስተናግዳቸው ውድቀቶች ሁሉ በመራቃችን የመጡ እንደሆኑ እናስተውል !!! በግል ሕይወታቸውን በአገር ደረጃ በቤተክርስቲያን ደረጃ እንዴት ይሄ ሊሆን ቻለ የምንለው ነገር ሁሉ በመራቃችን የመጡ ናቸው!!
ስለዚህ የዘመን መታደስም በግል ወደ እግዚአብሔር ከመመለስ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው!!! መመለስ የሚፈልግ ለዚህም ደግሞ ውሳኔ ያለው ግን አቅም ብቻ የሚፈልግ ሰው ፀሎት ፀለየ መልሰን እንመለሳለን ብሎ!!!
ሐዋ 3:26" ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን
አስነስቶ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ
ይባርካችሁ ዘንድ ሰደደው።"
ሳንመለስ መታደስ የለም!!! የተሃድሷችን ዘመን እና የመታደሳችን ልክ ያለው በመመለሳችን ልክ እና መጠን እንደሆነ ልናስተውል ይገባናል!!!የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛልን!!

03/05/2022

ዘመናችንን...አድስ!!!!
ክፍል አንድ!!
ሰቆ.ኤር 5:22" ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።" ይሄ የአዘን እንጉርጉሮ ማሰሪያ የሆነውን መንፈሳዊ ተማፅኖ በእኛም ልብ ጎልቶ እንዲጮህ ይሄን መንፈሳዊ ሐሳብ እናነሳለን።
1.እንዴት.... እንዴት....እንዴት!!!!!
አስቀድሞ ይሄ መፅሐፍ "" ሰቆቃው ኤርሚያስ""" ተብሎ ከመተርጎሙ በፊት በእብራይስጥ **ekah** ተብሎ ይጠራ ነበር!! ይሄውም ምን ማለት ነው??*** How*** እንዴት??? ይህ ሆነ?? የሚለውን ትርጉም ይይዛል!!! ይሄም ኤርምያስ ከሚያነሳቸው መንፈሳዊ ጥያቄዎች በመነሳት ነው ይሄን ትርጉም ያገኘው!!! ሰቆ.ኤር 1:1
ሰቆ.ኤር 2:1
ሰቆ.ኤር 4:1
በዘመኑ የነበረውን መንፈሳዊ ውድቀት **እንዴት** ብሎ ይጠይቃል??
"...ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ *እንዴት* ብቻዋን
ተቀመጠች"
" ጌታ የጺዮንን ልጅ በቁጣው *እንደምን*አጠቆራት"
" ጥሩው ወርቅ **እንዴት** ደበሰ(ተለወጠ)"
እንዴት ይሄ ሁሉ መከራ መጣ ??? የነበረን መልካም ነገር እንዴት ጠፋ?? እያለ ይጠይቃል??? የተሃድሶ መጀመሪያ አንዴት እንደዚህ ሆንን ??? ብሎ ከመጠየቅ ይጀምራል!!
እንዴት እንደዚህ ልንሆን ቻልን?? ብሎ እራስን መጠየቅ ለመታደስ ለመለወጥ በር ይከፍታል!!! በሐገር ደረጃ በቤተክርስቲያን ደረጃ እና በግል ሕይወት ደረጃ ያለውን ውድቀት ቆሞ መተቸት የዘመኑ ፋሽን ከሆነ ቆይቷል!! ግን **እንዴት** እንበል ጌታ ማስተዋልን ይስጠን!!! አቤቱ ዘመናችንን አድስ???

ፋሲካችን ክርስቶስ ነው!!!            " ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷአልና" 1ቆሮ 5:7      የመስዋዕት በግ ሆኖ ክርስቶስ ስለ እኛ ታርዷል!!! እናም ፋሲካችን ነው!!!  ስለዚህ ይ...
23/04/2022

ፋሲካችን ክርስቶስ ነው!!!
" ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷአልና" 1ቆሮ 5:7
የመስዋዕት በግ ሆኖ ክርስቶስ ስለ እኛ ታርዷል!!! እናም ፋሲካችን ነው!!! ስለዚህ ይላል መፅሀፍ "...በቅንነት እና በእውነት ቂጣ ..እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም።"
ከፋሲካ ከታረደው በግ ከክርስቶስ ሞት መስዋትነት በሁዋላ የሚጠበቀው መሻገር አዲስ ሕይወት ብቻ ነው!! የምስዋትነቱ ፍሬ አዲስ ሕይወት ነው!!አሮጌው እርሾ መወገድ አለበት ይሄ እሮጌው እርሾ ምንድነው ስንል?
1.ትዕቢት(መመካት)
2.ክፋት
3.ግፍ
ይሄ አሮጌ እርሾ ተወግዶ እርሾ የሌለው አዲስ ሕይወት አይነት እንኖር ዘንድ !! ክርስቶስ ታርዷል!!! የእግዚአብሔር ፀጋ ይብዛልን!!!

19/04/2022

ሆሣዕና....ስቀለው!!!!
እነዚህ ሁለት ቃሎች በአንድ ሳምንት ውስጥ በአንድ አይነት ሕዝብ በጩኸት የተነገሩ ሁለት ቃሎች ናቸው!!! ሆሣዕና ማለት አሁን አድነን አሁን አቅና ማለት ነው!! ፈጣን እግዚአብሔራዊ ትድግና የሚማፀን ቃል ነው። ማቴ 21:7-9 እናም አድነን ድረስልን ፍጠን (ሆሣዕና) ብለው ጮኹ!!!
ማዳኑን ትድግናውን የምንፈልግበት በቶሎ ጌታ እንዲደርስልን የምንፈልግበት ብዙ ነገሮች ይኖሩን ይሆናል??ስለዚህም ሆሣዕና ማለት መልካም ነው!!! ይሄው ሕዝብ በዚሁ ሳምንት ከፍ ባለ ድምፅ ጮኾ* ስቀለው ስቀለው* ሲል ግን ያስደነግጣል!!!ማቴ27:23"...ስቀለው እያሉ ጮኹ፣..."
ሆሣዕና ከዛ ከቀናት በሁዋላ ስቀለው ስቀለው ሁለት ፅንፍ የረገጠ ቃል !! ዛሬ ክርስቶስን የምሰቅልበት አደባባይ የለም ነገር ግን በሕይወት አደባባያችን (በስራችን) እንሰቅለዋለን!!
ይሄ አንድ ሕዝብ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተናገረው ሁለት ቃል ነው!!! ሆሣዕና.... ከዛ ደግሞ ስቀለው!! ሆሣዕናችን ይፅናልን!! በሆሳዕና ጀምረን በስቀለው ከመጨረስ እግዚአብሔር ይጠብቀን!!!

04/04/2022

መርምረኝ!!!!
ክፍል ሰባት!!!
7.የእግዚአብሔር መገኘት!!
መዝሙረኛው መርምረኝ ሲል እራሱን ያቀረበው ለእግዚአብሔር መገኘት ነው!! እግዚአብሔር የትም ስፍራ አለ!! መዝ 139:7
"ከመንፈስት ወዴት እሄዳለሁ?
ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?"
ሰው ከእግዚአብሔር መገኘት የሚሰውርበት ስፍራ የሌለው ፍጡር ነው!! መገኘቱን በመሄድም ይሁን በመሸሽ ልናመልጠው አንችልም!! እራሳችንን አቅርበን መመርመር መፈተሽ ብቻ ብቸኛ መንገድ ነው!! መዝሙረኛው የገባው ነገር የእግዚአብሔር መንፈስ መገኘት ነው!!
መገኘቱ ሸሽተን የማናመልጠው ሄደን እርቅን የማናስቀረው እንደሆነ ማወቅ አለብን!!!
1,ከፍ ብንል አለ!!
ቁ8 "ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ ነህ" ይላል ከፍታችን ከመገኘቱ ውጪ ሊያደርገን አይችልም!! እርሱ እግዚአብሔር በዚያ አለ!!! ከፍታችን ከእይታው ከመገኘቱ ነፃ የሆነ ቀጠና የሚሰጠን ይመስለን ይሆን??? አንዳንዴ ከፍታችን በእግዚአብሔር በእራሱ አይነኬ እንደሆነ የምናስብ አለን!!ግን እውነቱ**** አንተ በዚያ ነህ**** አለ!!! የትኛውም ከፍታችን በመገኘቱ( deal) እንዳንመረመር አያደርግም!! ብዙ ሰዎች የወጡበት ከፍታ በእግዚአብሔር በእራሱ እንኳን አይነኬ እንደሆነ ያስባሉ እውነቱ ግን ይሄ አይደለም!!! አለ !!! በዚያ!! አለ!!!
2.ብንወርድ አለ!!
ቁ8 " ወደ ሲኦልም ብወርድ በዚያ አለህ" የወረድነው እስከየትም ድረስ ይሁን የነካነው ዝቅታ ከመገኘቱ ውጪ ሊያረገን አይችልም !!! በዚያ አለህ!!! ያለንበት የሕይወት ዝቅታ በፍፁም ከእግዚአብሔር መገኘት ይሰውረን አይችልም!!
3.ምንም ፈጣን ብንሆን!
ቁ9 "እንደ ንስር የንጋት ክንፍ ብወስድ
እስከ ባህር መጨረሻም ብበርር
በዚያ እጅህ ትመራኛለች
ቀኝህ ትይዘኛለች።"
ምንም ፈጣን እሮዋጭ ብንሆን የንስር አይነት ፍጥነት ቢኖረን ለመሸሸ በአንዴ የሆነ ጥግ ድረስ ብንበርር በዚያ ቀኙ ትይዘናለች!! ሸሽተን ስንጨርስ እርሱ በዚያ አለ!!
4.የትኛውም ፍጥረታዊ ሐይል ሊሸፍነን አይችልም!!
ቁ11 "በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል
ሌሊትም በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች
ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና!!!"
የትኛውም ፍጥረታዊ ነገር ከመገኘቱ ሊሰውረን አይችልም !!!
ስለዚህ በእግዚአብሔር መገኘት ፊት እንዳለን አውቀን መርምረኝ ፈትሸኝ ጠማማ ነገር ብታገኝ ከውስጤ አውጣ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ ማለት ይኖርብናል!!!
ምንም አይነት ማምለጫ የለም ከእግዚአብሔር መገኘት!!ይየን ይፈትሸን ይመርምረን !! እናም ያብጀን ይስራን!! አሜን ፀጋ ይብዛልን!!!

28/03/2022

መርምረኝ!!!
ክፍል ስድስት!
6,የእግዚአብሔር እውቀት!
መርምረኝ ብሎ እራሱን ሲያቀርብ እግዚአብሔር እንዲያየው የሚፈልገውን የማንነቱን ክፍል ባለፈት አምስት ፅሁፎች አይተናል!!! አሁን ደግሞ መርምረኝ ያስባለው የእግዚአብሔር ማንነትን እናያለን!!
1ኛ,የእግዚአብሔር እውቀት የላቀ ነው!!
ከእኔ በላይ አዋቂ ነህ!! ስለ እራሴ ከእኔ በላይ አንተ አዋቂ ነህ!! እያለ ነው እግዚአብሔርን!!
መዝ 139:6"..የአንተ እውቀት ከእኔ ይልቅ ተደነቀች
በረታች ወደ እርሷ ልደርስ አልችልም"
የእግዚአብሔር አዋቂነት ከሰው እውቀት እጅግ የላቀ (የበለጠ) ነው!!!ስለዚህ ሰለ እራሳችን እኛ ከምናውቀው እና ሰዎች ከሚያውቁት እውቀት በላይ እግዚአብሔር አዋቂ ነው ወይም ያውቀናል!!!ስለ እኛ ከእኛ በላይ እግዚአብሔር አዋቂ ነው። ሐና ስትፀልይ 1ሣሙ 2:3
"...እግዚአብሔር አዋቂ ነው" አለች ሰለየትኛው እውቀቱ ይሆን??? ስንል እንዲህ ትላለች ***አትታበዩ በኩራትም አትናገሩ*** ብላ ሰዎች ስለራሳቸው ያላቸውን እውቀት እና ከእውቀትታቸው ተነስተው ለእራሳቸው የሰጡትን ቦታ እና ዋጋ ትናገራለች!! ከዛ ደግሞ አስደናቂው ቃል" ስራውን ይመዝናል" ትላለች!! ሰለዚህ ስራው ተብሎ የተጠቀሰው ***ሰው*** እራሱ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም!!
ስለዚህ እግዚአብሔር አዋቂ ነው!!! ስራውን ማለትም **ሰውን** ይመዝነዋል ይሰፍረዋል አበጥሮ ያውቀዋል!! ሰዎች እራሳቸውን ከፍ አድርገው ሐናን ንቀዋት ነበር!! ስለዚህ ሰው የሚሰፈረው ልኩ የሚታወቀው በእግዚአብሔር እውቀት ብቻ ነው!!!!
2ኛ,ዘመናችንን ያውቃል!!
መዝ139:5"..አቤቱ አንተ እነሆ የቀደሞውንና የኃላውን
አወቅህ"
ያለፈው እና የሚመጣው እንዲሁም አሁን ያለንበት ጊዜ በእግዚአብሔር እውቀት ስር ነው!! የሰው የሕይወት ስጋቱ እና ቀውሱ ሁሉ በተለይ ከፊቱ ያለውን አለማወቁ ነው!! የእግዚአብሔር እውቀት ግን የኃላውንም ማለትም መጪውን የቀደመውንም (ያለፍነውን) ያውቀዋል!!
መዝ139:16"...የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ
አንድ ስንኳ ሳይኖር በመፅሐፍህ ተፃፉ"
ጊዜያችን በእግዚአብሔር እውቀት የታወቀ ነው!!! ስለዚህ በዚህ ጥልቅ የእግዚአብሔር እውቀት ፊት ነው እራሱን ያሰጣው (የገለጠው)እና መርምረኝ ያለው!!! አዎ በእውቀቱ ይመርምረን!!! አሜን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ከሁላችን ጋር ይሁን!!!

20/03/2022

መርምረኝ!!!!
ክፍል አምስት!!!
መንገዶቼን!!!
መዝ 139: 3"...መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ!!;"
ብዙ ጊዜ የደረስንባቸው እና በህይወታችን የጨበጥናቸውን ስኬት ብለን የምንጠራቸው ነገሮች አሉን!! ይሄ በኑሮ በአገልግሎት በሕይወት የደረስንበት ቦታ ለመምጣት መንገድ አለን!! ለዛ ነው መዝሙረኛው ***መንገዶቼን *** እወቃቸው ፈትሻቸው መርምራቸው የሚለው!!! ዳዊት ከእረኝነት ተነስቶ እስከ ንግስና የመጣ ሰው ነው!! ከዋሻ ኑሮ ተነስቶ እስከ ቤተ መንግሥት ኑሮ የመጣ ነው!!! ለደረሰበት ወይም ለሚደርስበት ልክ ቦታ አይደለም የሕይወት ምጡ ( ጭንቀቱ) ለመንገዱ እንጂ!!!
*** የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው*** እንደሚባለው አይደለም ያለንበት የሕይወት አለም!!! እግዚአብሔር የሚመለከው የሚመሰገነው በምንዘው በጨበጥነው አይደለም ምስጋናውም አምልኮውም ያለው በመንገዱ ላይ ነው!!
እስራኤል ከወረሰው አገር ወተት እና ማር ከሚያፈሰው ይልቅ በምድረ በዳ እግዚአብሔር ሕዝብን የመራበት መንገድ
ድንቅ የእግዚአብሔር መገለጥ የሞላበት እና ዛሬም እግዚአብሔር የሚመለክበት መታሰቢያ አለው!!!
መንገዳችንን ይመርምረው ይፈትሸው የሰው መንገድ ከእግዚአብሔር የራቀ ነው ግድ የለም ይፈተሽ እስኪ !!! እኛ ሁሌ በያዝነው በጨበጥነው ወይም በደረስንበት መታወቅ ነው የምንፈልገው!!!
እግዚአብሔር መንገዳችንን አዲፈትሽ ከፈቀድን እርሱ መንገዳችንን ያነፃል!! የእኛ ማንነት በሰው ፊት የሚለካው በያዝነው ነገር ሲሆን በእግዚአብሔር ፊት ግን ነገሩን ባገኘንበት መንገድ ብቻ ነው የምንለካው!! እግዚአብሔር የስኬታችን(የመድረሻችን) አምላክ ሳይሆን. የመንገዳችን አምላክ ነው!! የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ይብዛልን አሜን!!

13/03/2022

መርምረኝ!!!
ክፍል አራት!!
ፍለጋዬን!!(motive)
ሰው ሁሉ የእራሱ የሆነ ***ፍለጋ*** አለው!!! የሰው ፍለጋ በእግዚአብሔር ይመረመር ዘንድ ግድ ነው!!!መዝ139:3"...ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ"
**ፍለጋ** አለን ሰው ከሆንን ይሄ የምንፈልገው ነገር ግን የምፍልግበት ልብ (motive) በእግዚአብሔር ካልተፈተሸ እና ካልነፃ በምንፈልገው ነገር በእራሱ ልንጠፋ እንችላለን!!!እስኪ እግዚአብሔር ፍለጋችንን ይመርምረው!!
ዮሐ6:24"...ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርኒዬም መጡ"
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈልገው አገር አቋርጠው መጡ!! ይሄ ፍለጋ ተፈተሸ ተመረመረ!!! የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ነገር ግን የምፈልግበት ልብ ይፈተሽ??
ዮሐ6:26"...የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና
ስለ ጠገባችሁ...ነው""
ጌታን ከመፈለግ በላይ ምን ትልቅ ፍለጋ አለ?? ጌታን ማገልገል ከመፈለግ በላይ ምን ፍለጋ አለ??? ይሄ ፍለጋ እንኳን ሲፈተሽ ሲመረመር ቆሽሾ ሊገኝ ይችላል !!!ሌላውማ ፍለጋችን አንዴት ቆሽሾ ይገኝ ይሆን??? መርምረኝ ጠማማውን ነገር ከልቤ አውጣ የዘላለምን መንገድ ምራኝ!!!አሜን!!ተባረኩ!!

06/03/2022

መርምረኝ!!
ክፍል ሶስት!!!
3. የሰው አሳብ!!!
የሰው የአሳብ አለም በእግዚአብሔር ከልተመረመረ እና ተፈትሾ ካልተስተካከለ እጅግ አደገኛ ነው!!መዝ139:2
"...አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።"
የሰው አሳብ በእግዚአብሔር ይመረመር ይፈተሽ ዘንድ ግድ ነው መዝሙረኛውም ለዚህ ነው የአሳብ አለሙን እግዚአብሔር ይመረምረው ይፈትሸው ዘንድ የፈቀደው!!!
1.የሰው አሳብ ከንቱ ነው!!!
መዝ94:11"የሰዎች አሳብ ከንቱ እንደሆነ እግዚአብሔር
ያውቃል።"
ምን ተጨንቀን የምናስበው ነገር ቢኖረንም በእግዚአብሔር እውቀት እና አሳብ ፊት እጅግ ከንቱ ሆኖ ይገኛል!!
2.የሰው አሳብ በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሳ ነው!
2ቆሮ10:5"...የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔር እውቀት ላይ
የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር እናፈርሳለን።"
የሰው አሳብ በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሳ ነው!! ለዚህ ነው የሰው( imagination world) በእግዚአብሔር ካልተፈተሸ እና ካልተሰራ እጅግ የከፋ የሚሆነው።
3.ሰው በአሳብ የእግዚአብሔርን ጠላት ነው!!
ቆላ1:21"...በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁ...."
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ጠብ ሁሉ የሚጠነሰሰው በአሳብ አለሙ ውስጥ ነው ስለዚህ እግዚአብሔር የአሳብ አለማችንን ይፈትሸው ክፋትን ቢያገኝበት ያንን ክፋት ይንቀለው!!!
4.ሰው አሳብ ከእግዚአብሔር አሳብ የራቀ ነው!!
ኢሳ55:9"...ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል እንዲሁ...
አሳቤ ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
የሰው አሳብ ከእግዚአብሔር አሳብ እጅግ የራቀ ነው!! ስለዚህ በእግዚአብሔር እውቀት የሰው የአሳብ አለም ይመረመር ዘንድ ይገባል!!! መርምረኝ ምንህን ሲባል
*** አሳቤን*** አዎ የአሳባችንን አለም እግዚአብሔር ፈትሾ ያፅዳው !!!

27/02/2022

መርምረኝ!!!
ክፍል ሁለት!!!
እንቅስቃሴ Activity!!
መዝሙረኛው መርምረኝ አለ!! እግዚአብሔር እይዲፈትሸው የሚፈልገው የሕይወቱ ቦታ እንቅስቃሴው ነበር። መዝ139:2"....መቀመጤንና መነሳቴን አወቅህ"
መርምረኝ እወቀኝ አለ ....እግዚአብሔር እንዲመረምረው የሚፈልገው የሕይወቱ ቦታ እንቅስቃሴው ነው!!! ዛሬም የምናደርገው እንቅስቃሴ መቀመጥ እና መነሳታችን በእግዚአብሔር ይታይ ይፈተሽ ዘንድ መፍቀድ አለብን!!!!
በሕይወትና በኑሮ እንዲሁም በአገልግሎት መንቀሳቀሳችን ብቻ ሳይሆን መንቀሳቀሳችን ፍሬ የሚያፈራ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ይመርምረው!!ወደታች ወደላይ ማለታችን መንቀሳቀሳችን በእራሱ አይደለም ፍሬ የሚያፈራው ነገር ግን ፍሬ ሊያፈራ በምንችልበት ልክ በእግዚአብሔር ከተቃኘ ብቻ ነው።
ሉቃ 10:40-42 ይነበብ
ማርታ በብዙ ነገር ትታወክ ነበር ማርያም ደግሞ በጌታ እግር ስር ተቀምጣ. ቃሉን ትሰማ ነበር!!!
ማርታ!!
1. መባከን!!
ስለ ማርታ መፅሃፍ ሲናገር **ባከነች*** ይላል ። እንቅስቃሴዋ መባከን ተባለ!!! መባከን ማለት ኃይልን መጨረስ ይባላል!!! መባከን ሐይል መጨረስ ነው!!! አንድ ነገር ከሚያስፈልገው ሐይል በላይ ማውጣት ማለት ነው!!!
2. ያለ ስኬት መጨረስ!!
እህቷን ከሰሰቻት እንድትረዳኝ ንገራት አለችው ጌታን? ያልተሳካልኝ ሌሎች ስደክም ስላላገዙኝ ነው? ብሎ መናገር ሌሎችን መውቀስ መክሰስ !!!
መንከላወሳችን ብቻ ፍሬ የሚያፈራልን ወይም የምንሻው ቦታ የሚያደርሰን አይደለም!!! በእግዚአብሔር ይፈተሽ ይመርመር እናም እግዚአብሔር ይቀድሰው ያጥራው!!!! መርምረኝ?? አለ ምንህን ሲባል መቀመጥና መነሳቴን አለ!! Our Activity!!

21/02/2022

መርምረኝ!!!
ክፍል አንድ!

መዝሙረኛው *** መርምረኝ*** (search me) ይላል!!መዝ139:1-24 ሙሉውን እናንብበው!!! ቁጥር 23-24 "...አቤቱ መርምረኝ ልቤንም እወቅ
በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ
የዘላለምንም መንገድ ምራኝ።"
መርምረኝ በደልን በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምን መንገድ ምራኝ አለ። ሰው እራሱን በዶክተር ፊት ለኦፔሬሽን እንደሚያቀርበው አይነት ማቅረብ ነው ይሄ!!! ጤንነቴን እስኪ ፈትሸው ጤነኛነኝ አያልኩ ድንገት ከሕይወት እንዳልጎድል እንደሚል ሰው ነው እራሱን ያቀረበው።
አዎ በደልን በውስጤ ፈልግ እና ደግሞ ብታገኝ አውጣው (እይ) እና የዘላለም መንገድ ምራኝ በውስጤ ያለው ነገር ካዘጋጀክልንኝ ፍፃሜ እንዳያጎድለኝ እያለ እግዚአብሔርን እየለመነ ነው!!
እራሳችንን በእግዚአብሔር ወደማስፈተሽ መምጣት እንዴት መልካም ነገር ነው??? በእኛ የማወቅ እና የመረዳት ልክ ያላየናቸውን በደሎቻችንን ያነፃን ዘንድ መፈለግ ድንቅ ፍለጋ ነው??
በጊዜያዊው መንገድ ሳይሆን መንገዳችን በዘላለም ይሆን ዘንድ መጠማት አስገራሚ መጠማት ነው!!! በጊዜያዊ በሚጠፋ መንገድ መሄድ አልፈልግም *በዘላለም መንገድ*
ብሎ ጮኸ መዝሙረኛው!!! ክፍል ሁለት ይቀጥላል!!!

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911626064

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ Community International Church -CCI posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share