Prophetess kidist markos

Prophetess kidist markos prophetess kidist markos is a women of God whom God has raised for the people of Ethiopia.
(2)

ወንጌል ያሸንፋል
25/08/2026

ወንጌል ያሸንፋል

አብረን ስንሆን ማእበሉን እናነሳለን በሰላም ወደቡ ጋር እንደርሳለን  ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው። መዝ 107፥30 ህይወት እንደ መኪና መሪ ሳትሆን እንደ መርከብ መሪ ናት ብዙ ውጣ ውረድ እ...
24/08/2026

አብረን ስንሆን ማእበሉን እናነሳለን በሰላም ወደቡ ጋር እንደርሳለን
ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው። መዝ 107፥30

ህይወት እንደ መኪና መሪ ሳትሆን እንደ መርከብ መሪ ናት ብዙ ውጣ ውረድ እና ከየአቅጣጫው ወጣ ወጣ ያሉ የህይወት ጉጠት እና ግልጽ ያልሆኑ የጉዞ ጎዳናዎች አሏት።
በመኪና ጉዞ ላይ አውሎ ንፋስ ቢነሳ መኪናን አቁሞ ንፋሱን ማለፍ ወይም መሪውን በአንድ እጅ መያዝ ይቻላል ።

የህይወት ጉዞ ግን እንደዚያ አይደለም። ምንም ቢገጥምህ የመኪናን መሪ ለሁለት አትይዝም የመርከብ መሪ ግን ከባድ አውሎ ንፋስ ሲነሳ በባህር ጥልቀት ውስጥ ብቻውን አይመራም።
​በግዙፉ ውቅያኖስ ላይ ኃይለኛ ነፋስና ማዕበል ሲመታህ የመርከቡን መሪ ከሚረዳህ ከሚያጸናህና ከጎንህ ካለ ውድ አጋርህ ወድጅህ ጋር አብራችሁ አዙራችሁ ያንን ፈተና ታልፉታላችሁ።

​ማዕበል በረታ ብሎ ውቅያኖሱ ሲናወጥ እይታን ወደ ጎን ወይም ወደ ስጋቱ ማዞር መርበሽንና ሚዛንን መሳት ያስከትላል። ነገር ግን አውሎ ንፋሱ ሲጸና እይታን ቀጥታ ወደፊት ወደ አድማስ እና ወደሚደረስበት ሰላማዊ ወደብ ማድረግ ከጎንዬሽ የውድቀት ከፍረሃት መንገድ ላይ ከመቅረት ይታደጋል።
የመርከብ መሪ ግዙፍ በመሆኑ የሚሰጠው ምላሽ ቀስ በቀስ እና በጋራ ጥንካሬ ላይ የሚመጣ ነው።
ማዕበሉ መርከቧን ሲገፋት መሪውን በሰከነ በታቀደ እና በማይበጠስ አብሮነት አጥብቆ መያዝ ኃይልን ይሰጣል።

ምንጊዜም እርግጠኛ መሆን ያለብን ​በሕይወት ውቅያኖስ ውስጥ የሚነሱት ከባባድ ነፋሳት ቋሚ አይደሉም።
የተነሳውን አውሎ ንፋስ ግን በትብብር እና ከታመነ አጋር ጋር ሲሆን ይህ ህብረት ተደምሮ ማዕበሉን ሰንጥቆ ለማለፍ ብቸኛው የድል ቁልፍ ይሆናል።
ዛሬ ምክር አለኝ በህይወት ባህር ላይ አውሎ ንፋሱ ቢያንገበግበንም መሪውን አብረን በመተባበር አጥብቀን እንያዝ እይታችንንም የተነሳው ማእበል ላይ ሳፍሆን ከፊት በሚታየው ብርሃን ላይ እናድርግ አብረን ስንሆን ማዕበሉ ያንሳል ወደብም ጋር ይደረሳል።

መዝሙር 107፥23
በመርከቦች ወደ ባሕር የሚወርዱ
እነርሱ የእግዚአብሔርን ሥራ፥
በጥልቅም ያለችውን ድንቁን አዩ።
በታላቅ ውኃ ሥራቸውን የሚሠሩ፥

29: ዐውሎንም ጸጥ አደረገ፥
ሞገዱም ዝም አለ።

30: ዝም ብሎአልና ደስ አላቸው፤
ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው።

ይህ ብዙዎችን የሚያፅናና መልክት ነውና ሼር እያደረጋችሁ ብዙዎች ጋር እንዲደርስ አድርጉት

ነቢይት ቅድስት ከትውልድ ማስነሳት ቤተክርስትያን

የእግዚአብሔርን ምክር መጠቀም በእግዚአብሔር እውቀት ውስጥ መኖር ነው በሕይወት ዘመናችን ውጤታማ እና እውነተኛ የስኬት ሰው መሆን እንፈልጋለን? አውቃለሁ በልባችን ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌላቸው...
23/08/2026

የእግዚአብሔርን ምክር መጠቀም በእግዚአብሔር እውቀት ውስጥ መኖር ነው
በሕይወት ዘመናችን ውጤታማ እና እውነተኛ የስኬት ሰው መሆን እንፈልጋለን?
አውቃለሁ በልባችን ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እቅዶች እና የናፍቆት ዘሮች ተከምረዋል። ነገር ግን ትልቁ ምስጢር ያለው እዚህ ላይ ነው የሰው ሃሳብ በእግዚአብሔር ምክር መፅናት አለበት።
​እኛ የምንዘራው የትኛውንም መልካም ዘር የእግዚአብሔር ፀሐይና ዝናብ ስታበራለት እና ስታጠጣው እንጂ በእኛ ጥረት ስለተዘራ ብቻ አያድግም አያብብም።
ስለዚህ የሂይወታችንን መርከብ ከእግዚአብሔር ጽኑ ምክር ጋር አጥብቆ ማሰር ማዕበል ቢገፋው ፈጽሞ የማይሰጥምን የህይወት ቁመና እና። ከእርሱ ጋር ስንጓዝ የእያንዳንዱ እርምጃችን ፍፃሜ እና ስኬት ብርሃን ማለቂያ የሌለው ሰላም ይሆናል
​በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። (ምሳሌ 19፥21)።
መዝሙር 73፥24
በአንተ ምክር መራኸኝ፤
ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።

የእግዚአብሔር ምክር ለውርደት ሳይሆን ለክብር ያስረክበናል
በእግዚአብሔር ምክር መመራት ይሁንልን

ነቢይት ቅድስት ማርቆስ ከትውልድ ማስነሳት ቤተክርስትያን

እንዲህ ፀለይኩላችሁ።የህይወታችሁ እስራት ይበጠስ ።የአመታት ፍርሃታችሁ እንደሰም ይቅለጥ። የተቆለፈባችሁ የውድቀት በር በታላቅ ድምፅተነቅሎ ይውደቅ ።ትላንት በእግራችሁ ላይ የነበረ ሰንሰለት ...
20/08/2026

እንዲህ ፀለይኩላችሁ።
የህይወታችሁ እስራት ይበጠስ ።
የአመታት ፍርሃታችሁ እንደሰም ይቅለጥ።
የተቆለፈባችሁ የውድቀት በር በታላቅ ድምፅ
ተነቅሎ ይውደቅ ።
ትላንት በእግራችሁ ላይ የነበረ ሰንሰለት ዛሬ ለድላችሁ መረገጫ ይሁንላችሁ ።
ከጥላቻ እስር ከጭንቀት ግዛት ከሽንፈት አዙሪት ከዚህ ሰአት ጀምሮ ነፃ ሁኑ ።
አድማስን የሚቀድ ክንፍ ይሰጣችሁ
የተሸሸገው ብርሃናችሁ ለአለም ይብራ ።
እግዚአብሔር እንደባለስልጣን የምታዙበት እንደባለቤት የምትጠይቁበት የመረዳት ኃይል ውስጥ ያስገባችሁ ።

ነቢይት ቅድስት ከትውልድ ማስነሳት ቤተክርስትያን

18/08/2026
ትልቅ ስራ
18/08/2026

ትልቅ ስራ

በነዚህ ቀናት በሚገለጠው የእግዚአብሔር እጅ ምክንያት በአዲስ ምስጋና እንደገና በእግዚአብሔር እና በትውልዱ ፊት መቆም የምትችሉበት ተአምራት እግዚአብሔር ያደርግላችዋል። ፕሮግራማችን ማክሰኞ ...
09/08/2026

በነዚህ ቀናት በሚገለጠው የእግዚአብሔር እጅ ምክንያት በአዲስ ምስጋና እንደገና በእግዚአብሔር እና በትውልዱ ፊት መቆም የምትችሉበት ተአምራት እግዚአብሔር ያደርግላችዋል። ፕሮግራማችን ማክሰኞ ዘጠኝ ሰአት ይጀምራል ይምጡ ተጋብዘዋል

በባዶ እጅ የሚዘጋጅ ምኞት እንጂ ውጤት የለም ።ተስፋ የነገን በር የሚከፍት ወርቃማ ቁልፍ ነው ነገር ግን መክፈቻው ብቻውን በሩን አይገፋልንም የእኛ ጉልበት ያስፈልጋል። ተስፋ ማለት ጨለማውን...
05/08/2026

በባዶ እጅ የሚዘጋጅ ምኞት እንጂ ውጤት የለም ።

ተስፋ የነገን በር የሚከፍት ወርቃማ ቁልፍ ነው ነገር ግን መክፈቻው ብቻውን በሩን አይገፋልንም የእኛ ጉልበት ያስፈልጋል። ተስፋ ማለት ጨለማውን ማየት ትቶ ኮከቦችን መፈለግ የሚጀምር የአዕምሮ ብርሃን ነው።
ነገር ግን ያ ብርሃን ወደ መሬት ወርዶ እውን እንዲሆን ላብና ጥረት ሲጨመርበት ብቻ ነው ትርጉም የሚኖረው ካልሆነ ግን በባዶ እጅ የሚዘጋጅ ምኞት እንጂ ውጤት አይሆንም።

አቢጊያ አብነት ።

ለወፍ በቆሎ አይሰጥም ይበዛባት እና ያንቃታልለአደባባዮች የሳይክል መብራት አይገጠምም ያንስበታልልክ የሳተ እውነት   ከትከሻ በላይ የሆነ ኃላፊነት ያለዝግጅት የሆነ አገልግሎት ያለእውቀት የሆ...
03/08/2026

ለወፍ በቆሎ አይሰጥም ይበዛባት እና ያንቃታል
ለአደባባዮች የሳይክል መብራት አይገጠምም ያንስበታል

ልክ የሳተ እውነት ከትከሻ በላይ የሆነ ኃላፊነት ያለዝግጅት የሆነ አገልግሎት ያለእውቀት የሆነ መሪነት የመቅሰፍት ያህል ከባድ ናቸው። ስለዚህ ለወፍ በቆሎ አይሰጥም በቆሎን ሊውጥ የሚችል የጎሮሮ ዝግጅት የላትም ።

በሕይወት ውስጥ ትልቁ ስሕተት ማጣት ብቻ ሳይሆን ከልክ በላይ መብዛትም ጭምር ነው። እያንዳንዱ ፍጥረት የራሱ የሆነ ልክና ሚዛን አለው።
​በዚህ እውነታ ውስጥ ሁለት ዓይነት የተዛቡ ጽንፎች በግልጽ ይታያሉ። አንደኛው ወገን ዝግጅት ሳያደርጉ አቅማቸውና ትከሻቸው ሳይጠናከር ከትልቅ ኃላፊነትና ከግዙፍ ዕድል ጋር የሚጣላ ነው።
ልክ እንደሚያንቃት ወፍ ከአቅማቸው በላይ የጎረሱት ክብር ዝና ሃብት መድረክ ጎሮሮአቸው ላይ ተሾንቁሮ በመጨናነቅ ሲሰቃዩ ይኖራሉ።

ሁለተኛዎቹ ደግሞ ለትውልድ የሚተርፍ ሰፊ እውቀትና ብርሃን ይዘው ከኃይላቸውና ከብቃታቸው በታች በሆነ ጥበብ በመታሰር ለመውጣት ሲታገሉ የሚታዩ ናቸው።

​ዝግጅት ሳይኖር የሚመጣ ጸጋ እውቀት ሳይኖር የሚሰጥ ሹመት እና ትከሻ ሳይጠናከር የሚጫን ኃላፊነት በረከት ሳይሆን መቅሰፍት ነው።
በሉቃስ 12፥48 ላይ ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል እንደሚል ትልቅ ዕድልና ጸጋ ሁልጊዜም ብዙ ዝግጅት ጥልቅ እውቀት እና ሰፊ ትከሻ ይሻል።

አቅማችንን ዝግጅታችንን እና ኃላፊነታችንን በአግባቡ ማመጣጠን የዕለት ተዕለት ጥበብ ሊሆን ይገባል ትክክለኛው ነገር በትክክለኛው ልክ ሲሰጥ ብቻ ነው ሕይወት ፍሬያማ የምትሆነው።
​ይህንን እውነት በሁለት ምሳሌዎች ማየት ይቻላል፡

በመጀመሪያ ​ለወፍ በቆሎ አይሰጥም ያንቃታል ገና ባልበሰለ አእምሮ ግዙፍ ሀብት መሪነት እና ከባድ ኃላፊነት ሲሰጥ ሕይወትንና ትውልድን አደጋ ውስጥ መክተት ይሆናል።

​ሁለተኛው ለአደባባዮች የብስክሌት መብራት አይገጠምም ያንስባታል።
ግዙፍ ራዕይ ላለው ትልቅ ታሪክ ለሚሠራ እና ለሰፊ ሕዝብ ለታጨ ማንነት ከመድረክ የጠበበ አመለካከትና ትንሽ አስተሳሰብ ፈጽሞ አይመጥነውም የአድባባይ ብርሃን የትውልድ መፍቴን የያዘን ሰው የሳይክል መብራት በምታክል እውቀት ለማስቆም መሞከር ትልቅ መቸገር ነው ።
​ሚዛኑን የሳተ ማንኛውም ስጦታ ወይም ዕድል ደስታው አጭር ነው
ኃላፊነትም ከዝግጅት ጋር ሲመጣጠን ብቻ ነው እውነተኛ ውበት የሚኖረው።
ከክብደት በፊት ትከሻን ማጠናከር እና ራስን ማዘጋጀት ከሁሉ በላይ የጥበብ ሁሉ ጥበብ ነው።
​እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና (ገላትያ 6፥5) ልካችንን አውቀን መቆም ሕይወታችንን የተስተካከለና የሰመረ ያደርገዋል።

ነቢይት ቅድስት ማርቆስ ከትውልድ ማስነሳት ቤትክርስትያን

ድል ከፍርሃት ማህፀን አይወለድም ።የሚፈራህ አካል እንጂ ያሸነፍህ አካል ጠላትህ ሆኖ በአንተ ጉዳይ ላይ ጊዜውን አያጠፋም ።የጠላትህ ፍርሃት የድልህ መጀመሪያ ነውአንዳንዶች ጠላት የሆኑብህ ስ...
31/07/2026

ድል ከፍርሃት ማህፀን አይወለድም ።
የሚፈራህ አካል እንጂ ያሸነፍህ አካል ጠላትህ ሆኖ በአንተ ጉዳይ ላይ ጊዜውን አያጠፋም ።

የጠላትህ ፍርሃት የድልህ መጀመሪያ ነው
አንዳንዶች ጠላት የሆኑብህ ስለፈሩህ እንጂ ስላሸነፉህ አይደለም

መጽሐፍ ቅዱስም ይህንን እውነት ሲመሰክር
ሳኦልም ዳዊትን አጥብቆ ፈራው ሳኦልም ዕድሜውን ሁሉ ለዳዊት ጠላት ሆነ ይለናል። (1 ሳሙኤል 18፡29)

በሕይወትህ ውስጥ የጥላቻ ሁሉ መነሻ ከጥንካሬ ጋር የሚመጣ ሳይሆን ከድክመትና ከፍርሃት የሚወለድ ነው። አንድ ሰው ወይም ኃይል ያለምንም ምክንያት አንተን ለመውጋት ለማጥቃት እና የዕድሜ ልክ ጠላትህ ለመሆን ከተነሳ ያ የሚያሳየው የእሱን ብርቱነት ሳይሆን የአንተን የውስጥ አቅም መፈራቱን ነው።

ሳኦል በጊዜው በእጁ ሠራዊትና ዙፋን ነበረው ዳዊት ግን በእጁ የነበረው በዕንጨት የተሰራ በገና ብቻ ነበር። ሆኖም ሳኦል ዳዊትን አጥብቆ ፈራው ምክንያቱም የውስጡ ድምፅ የወደፊቱን ድል እና የዳዊትን ከፍታ ቀድሞ ነግሮት ነበርና።

ዛሬም ቢሆን በሕይወትህ የሚዋጉህ የሚቀኑብህ እና እንቅፋት የሚሆኑብህ ሰዎች ካሉ አትደንግጥ። የሚተቹህ አቅምህን ስለፈሩ ነው የሚዋጉህ ከእነሱ በላይ የምታድግበትን ዕድል ቀድመው ስለተረዱ ነው።
የጠላት መነሳትና መብዛት የሽንፈትህ ምልክት አይደለም ከዚህ ይልቅ ታላቅ ከፍታ ላይ መድረስህን የሚሰብክ የማንቂያ ደወል ነው።
ሳኦል ዕድሜውን ሙሉ የዳዊት ጠላት ቢሆንም ዳዊትን ከእግዚአብሔር ዕቅድ ማሰናከል አልቻለም። የጠላትነት ዘመቻው ያበቃው ሳኦል በራሱ ፍርሃት ሲጠቃ ዳዊት ግን በተሰጠው ርስት ላይ በንግስናው ጸንቶ ነው።

ስለዚህ በዙሪያህ ያሉትን ተቃውሞዎች በድል አድራጊነት ተመልከታቸው። ትኩረትህ መሆን ያለበት በጠላቶችህ ጫጫታ ላይ ሳይሆን በውስጥህ ባለው በእግዚአብሔር ጥሪ እና በብርቱ አላማህ ላይ ነው።

መቼም ቢሆን አትርሳ የሚፈራህ አካል እንጂ ያሸነፈህ አካል ጠላትህ ሆኖ ጊዜ አያጠፋም። አሸናፊው በእርጋታ ድሉን ይወስዳል ፈሪው ግን በጠላትነት ይንቀጠቀጣል።
ራስህን አሳንሰህ አታስብ አንተ የተፈጠርከው ልትንበረከክ ሳይሆን በፈተናዎች ሁሉ ላይ ልትነግሥ ነውና

ነቢይት ቅድስት ማርቆስ ከትውልድ ማስነሳት ቤትክርስትያን

Address

ሰሚት ፊየል ቤት 20 ሜትር ወደ ዘመን ባንክ ሲሄዱ ኦ ቱ ሬስቶራንት 200 ሜትር ገባ ብሎ
Addis Ababa
1000

Telephone

+251912243838

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prophetess kidist markos posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Prophetess kidist markos:

Shortcuts

Share