መምህር ግርማን ወደ አገልግሎት መልሱልን

መምህር ግርማን  ወደ አገልግሎት መልሱልን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from መምህር ግርማን ወደ አገልግሎት መልሱልን, Religious organisation, Addis ababa, Addis Ababa.

17/04/2026

መስገድ ስትጀምር ....+

17/04/2026

መስገድ ስትጀምር .......+++++

05/04/2026

የአምልኮት ሀይል

ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት በአሜሪካንበአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት እና በአካባቢው የሚገኙ ማህበረ ምዕመናን ባደረጉት መንፈሳዊ አገልግሎት ጥሪ መሠረት እሑድ ከሚያዝያ  11 እስከ ሚያዝያ 13 Apr...
05/04/2026

ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት በአሜሪካን

በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት እና በአካባቢው የሚገኙ ማህበረ ምዕመናን ባደረጉት መንፈሳዊ አገልግሎት ጥሪ መሠረት እሑድ ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 13 April 19th To Tuesday April 21st ሰዓት 10am to 5:30pm የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል ትምህርትና የፈውስ የጠበል አገልግሎት ይከናወናል! ይህንን መንፈሳዊ አገልግሎት ከመላው አህጉራት እና ከተማ ለመሳተፍ የምትመጡ ምዕመናን አገልግሎት የሚከናወንበት የቦታ አድራሻ location ሜሪላንድ Patuxent River Park Pavilion 16000 Croom Airport Road Upper Marlboro, MD 20772 መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን

አዘጋጅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማህበረ ምዕመናን ኮሚቴ Beth Saida Orthodox group of Maryland 📞 240 605 4111

ሰው ከፍቅር ልዕልና ሲድርስ ኃጥእ፣ ጻድቅ፣ መናፍቅ፣ አማኝ፣ ዘመድ፣ ባዕድ ሳይል ሁሉን ይወዳል ይላሉ አባቶቻችን:: (፪ኛ የጴጥሮስ መልእክት አንድምታ) ይሄን ፍቅር ግሪኮች አጋፔ ሲሉ ጠርተውታል:: መጽሐፍም እግዚአብሔር “ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና" የሚለው ስለዚህ ሁሉን ስለሚወድ ፍቅር ነው:: (ዮሐ. ፫፥፲፮) ይሄ የፍቅር ልክ፥ ጠበል ነው:: ደዌያትን ሁሉ የሚፈውስ ኃያል ጠበል!

እስቲ እኛም ከዚህ ጠበል እንቋደስ:: እንቋደስና ሕመምተኛዋን ዓለም እንፈውሳት:: ዙሪያችንን እንጂ ሁሉንም መፈወስ አይጠበቅብንም:: በመሠረቱ ፍቅር አንድ ሆኖ ተዘርቶ ብዙ ፍሬ ሆኖ ይበቅላል:: ይሄም ፍሬ የመረረውን ያጣፍጣል፤ ተስፋ ለቆረጠው ተስፋ ይቀጥላል፤ ውስብስብንም ሁሉ ያቀላል:: አልገባ ብሎን እንጂ የመኖር ክብደቶች የተጫኑን የፍቅር ትከሻ ስለሌለን ነው:: ዓለም የተሸናፊዎች መድረክ አይደለችም የሚሉ ርእዮቶች ዕውቀቶቻችን ከበው ስለመሸናነፍ አፎካክሩን እንጂ በፍቅር ከተቃመስነው ተፈጥሮ የተሰጠውስ በቂ ነበር:: እስቲ ፍቅርን ላለመስጠት ፍቅር አልተሰጠኝምን እንተው:: ፍቅር የምንረከበው ስጦታ ሳይሆን የምናቀብለው አስተሳሰብ ነው:: ሁለንተናችን ለአስተሳሰባችን ይገዛልና፥ ፍቅር ማሰቢያችን ከሆነ የነፍስያችን ውበት በሥጋ መልካችን ይታያል:: በዚህም መታየት ውስጥ በሰማይ የተፈቀደው በጎ ፈቃድ ለምድርም ይገለጣልና ከዚያን ወዲያ ርሃብና ጦርነት አይኖሩም᎓᎓ መከራና ሥቃይ ቦታ አያገኙም:: ሰልፍና ሁከት ሊታወቁ አይችሉም:: አስቀድመው የሞሉ ጽዋዎች እንኳ ቢኖሩ በረከት እንጂ መቅሠፍት አያፈሱም:: ምክንያቱም ፍቅር የቋጠረው ደመና የሕይወት እንጂ የጥፋት ውኃን አይይዝም:: ሕግጋትም ቢሆኑ በአንዱ ትእዛዝ ተፈጽመዋልና ስለ ኃጢአት የሚዘጉት አንድም መቀርቀሪያ አይኖርም::

> 1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፣ 4፤7

አግልግሎትን በጉጉት ለምትጠብቁ የፊታችን እሁድ በ20/07/2018 ዓ ም  የቦሌ ለሚ  ሰሚት (ኢንዱስትሪ መንደር ጊቢ ውስጥ) አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የወንጌልና  የፀበል ...
27/03/2026

አግልግሎትን በጉጉት ለምትጠብቁ የፊታችን እሁድ በ20/07/2018 ዓ ም የቦሌ ለሚ ሰሚት (ኢንዱስትሪ መንደር ጊቢ ውስጥ) አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የወንጌልና የፀበል አገልግሎት ይከናወናል ላልሰሙት አሰሙ
ማሳሰቢያ የወንበር እጥረት ስላለ መቆም ለማትችሉ የራሳቸውን መቀመጫ እንድትይዙ እናሳስባለን
አድራሻ ከሁሉም አቅጣጫ ወደ ሰሚ ት ኮንዶሚኒየም ወይም በር ሶስት መጨረሻው አደባባይ ኢንዱስትሪ መንደር ግቢ ውስጥ

 #​የበረከት ጥሪ!​የመምህር ግርማ ወንድሙ ቀጣይ መንፈሳዊ አገልግሎት እሁድ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ብዙዎቻችሁ አገልግሎቱ መቼ እንደሆነ ስትጠይቁ ስለነበረ፣ ይኸው መረጃውን አ...
24/03/2026

#​የበረከት ጥሪ!

​የመምህር ግርማ ወንድሙ ቀጣይ መንፈሳዊ አገልግሎት እሁድ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ብዙዎቻችሁ አገልግሎቱ መቼ እንደሆነ ስትጠይቁ ስለነበረ፣ ይኸው መረጃውን አድርሰናችኋል። እናንተም ለሌሎች በማጋራት (Share በማድረግ) የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ አድርጉ።

​አድራሻ፦ መገናኛ - ጎሮ - ለሚ ኢንዱስትሪ (ከሰሚት ኮንዶሚኒየም በ3ኛ በር በኩል ገባ ብሎ)።

ከሁለት ዓመታት በላይ በገበያ ላይ ያልነበረውየመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ“በማለዳ መያዝ” ቅጽ ፩ እና ቅጽ ፪ መጻሕፍትበዛሬው ዕለት እንደገና ታትመው በገበያ ላይ ውለዋል።*****...
13/03/2026

ከሁለት ዓመታት በላይ በገበያ ላይ ያልነበረው
የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ
“በማለዳ መያዝ” ቅጽ ፩ እና ቅጽ ፪ መጻሕፍት
በዛሬው ዕለት እንደገና ታትመው በገበያ ላይ ውለዋል።

************************************************
( 📅 መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ )

ብዙዎቻችሁ እንደጠየቃችሁት በወረቀት እጥረት ምክንያት ለሁለት ዓመታት ያህል የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙመጽሐፍ በቤተ-ሳይዳ እንዳልነበረ ይታወቃል።
መጽሐፉ እንደገና በሚታተምበት ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ (Social Media) እንደምናሳውቃችሁ የገባነውን ቃል መሠረት አድርገን አሁን “በማለዳ መያዝ” ቅጽ ፩ እና ቅጽ ፪ እንደገና ታትመው በገበያ ላይ ውለዋል።
📚 መጽሐፉን እንደ ቀድሞ በቤተ-ሳይዳ የመጻሕፍትና የንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ መደብር ብቻ ማግኘት ይችላሉ።

ቤተ - ሳይዳ ከስሙ እንደምንረዳዉ የምህረት እና የመዳን ቤት ነዉ። እንደትርጓሜዉ’ም ለብዙ አመታት በአባታችን በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ በተባረኩ እና በሕይወታችን ዉስጥ ከዕለት ወደ ዕለት አምልኮት ዉስጥ ዲያቢሎስ የምናሸንፍበትን መንፈሳዊ የጦር መሳሪያ የምናገኝበት የበረከት ቤት ሆኖ ለብዙዎች የሕይወት መቃናት ቀዳሚ ተጠቃሽ መሆኑ አይዘነጋም ። መንፈሳዊነትን ይበልጥ!በማስቀደም የክፋ መናፍስትን ተልዕኮ በማክሸፍ ከአባታችን የሚበረከቱልን መንፈሳዊ የበረከት እቃዎች ዛሬም ልክ እንደቀደመዉ ከሴረኞች በተለይም ዘመን ከጣለብን መተተኞች ፤ ጠንቋዮች ፤ ከደፍተራዎች ከሚባሉ የምድር ጉዶች ተለይተን እና ተፈርተን መንፈሳዊነትን እያስቀደምን ትግላችንን እንድንቀጥል አባታችን ከአገልግሎታቸዉ በተጨማሪ እለት ከእለት እንድንገለገልበት የሰጡን መንፈሳዊ የበረከት እና የአሸናፊነት ቤት ነዉ ቤተ- ሳይዳ።

በኖህ ዘመን የነበሩት አሿፊ ሰዎች በውስጣቸው ተቀምጠው በነፍሳቸው ላይ ስለሚያሾፉት ክፉ መንፈሶች መንፈሳዊ ግንዛቤ አልነበራቸውም። ለምን? ምክንያቱም ወደ ሰማይ አምላክ ቀና የሚሉበትን የመንፈስ መገዛት ተነፍገው ወደ ምድር አቀርቅረው ተቃንተው እየኖሩ መስሏቸው ሳይኖሩ ሞቱ።
ዛሬስ ስንት ሰው እየኖረ እየመሰለው በየቀኑ ወደ ሞት እየተጠጋ ይሆን?
ኖህ የጥፋት ውኃውን ደመና ያየው ከውስጡ በኩል ነው፤ እየመጣ ያለውን የውኃ ሙላት የተረዳውም በነፍስ ቃል በኩል ነው።
ዛሬም ስለ አምልኮት ኃይልና ስለሚመጣው አደገኛ ዘመን ለመረዳት የምትችሉት መንፈሳዊ ሰው ለመሆን ወስናችሁ አምልኮትን ከጀመራችሁበት ጊዜ ጀምሮ ነው።

“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራት፣ በሥጋ ምኞት፣ በስካር፣ በዘፈን፣ ያለ ልክ በመጠጣት እና በነውር ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።” (1ኛ ጴጥሮስ 4፥3)

አግልግሎቱን በጉጉት ለምትጠብቁ የፊታችን ቅዳሜ በ05/07/2018 ዓ ም  በለሚ ሰሚት(ኢንዱስትሪ መንደር ጊቢ ውስጥ) አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ ተ ክርስቲያን የወንጌልና የንግስ አገልግሎ...
12/03/2026

አግልግሎቱን በጉጉት ለምትጠብቁ የፊታችን ቅዳሜ በ05/07/2018 ዓ ም በለሚ ሰሚት(ኢንዱስትሪ መንደር ጊቢ ውስጥ) አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ ተ ክርስቲያን የወንጌልና የንግስ አገልግሎት ይከናወናል :: ላልሰሙት አሰሙ , ስለ አገልግሎቱ ፈጣን መረጃ እንዲደርሳቸሁ ቻናሉን subscribe ያድርጉ ::
ትራንስፖርት ከሁሉም አቅጣጫ ሰሚት አደባባይ ድረስ መጥተው ከሰሚት አደባባይ ወደ ሰሚት ኮንዶሚኒየም የሚወስደውን መንገድ እንደ ጨረሱ ኢንዱስትሪ መንደር ግቢ ውስጥ

12/01/2026


ጸሎት ዘር ነውና መከር አለው
ጸሎት ዕንባ ነው እና ሳቅ አለው
ጸሎት ትግል ነውና ድል አለው
ጸሎት ጩኸት ነውና መልስ አለው
ጸሎት መተንፈስ ነው ና ሕይወት አለው
ጸሎት ንግግር ነውና ማስተዋል አለው
ጸሎት መራቆት ነውና ፀጋ አለው
ጸሎት መንበርከክ ነውና ማሽነፍ አለው

#መምህርግርማ

25/12/2025

🙏🙏🙏

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1234

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መምህር ግርማን ወደ አገልግሎት መልሱልን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share