ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት Dewha knowladge and dev't org

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት Dewha knowladge and dev't org

ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት Dewha knowladge and dev't org Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት Dewha knowladge and dev't org, Religious organisation, Addis ababa, Addis Ababa.

19/03/2024

" إن الحسنات يذهبن السيئات ذلك ذكرى للذاكرين "
"በእርግጥም መልካም ስራ መጥፎ ስራን ያብሳል።" /ሁድ፣ 114/
★★★ ★★★ ★★★

ምንጊዜም መዕሲያ በሰራህ ጊዜ ለራስህ:– "ዘመቻው ላይ ለጊዜው ተረትቻለሁ፣ ነገር ግን ዋናውን ጦርነት አልተሸነፍኩም! " በል።
ቁምና ዉዱእ አድርገህ ሁለት ረከዓ በመስገድ ለማገገም ሞክር።
ወንጀል የፈፀምክባቸውን ጣቶችህ ኢስቲግፋር ቁጠርባቸው፤
ሐራም በተመለከትክበት አይንህ ቁርአንን አንብብበት።
አላህ ዘንድ የፀፀተኞች ለቅሶና መዋደቅ ከሷሊሖች ጣዓ አይተናነስም።
እናም አላህ _ሱብሐነሁ ወተዓላ_ራሱን (አልገፉር) ብሎ የጠራው ወደሱ እንድትመለስ ስለሚፈልግ ብቻ ነውና እጅ አትድጥ።

#ረሳኢሉን ሚን አልቁርኦን

ነስሩ ከድር

19/03/2024

" إن الحسنات يذهبن السيئات ذلك ذكرى للذاكرين "
"በእርግጥም መልካም ስራ መጥፎ ስራን ያብሳል።" /ሁድ፣ 114/
★★★ ★★★ ★★★

ምንጊዜም መዕሲያ በሰራህ ጊዜ ለራስህ:– "ዘመቻው ላይ ለጊዜው ተረትቻለሁ፣ ነገር ግን ዋናውን ጦርነት አልተሸነፍኩም! " በል።
ቁምና ዉዱእ አድርገህ ሁለት ረከዓ በመስገድ ለማገገም ሞክር።
ወንጀል የፈፀምክባቸውን ጣቶችህ ኢስቲግፋር ቁጠርባቸው፤
ሐራም በተመለከትክበት አይንህ ቁርአንን አንብብበት።
አላህ ዘንድ የፀፀተኞች ለቅሶና መዋደቅ ከሷሊሖች ጣዓ አይተናነስም።
እናም አላህ _ሱብሐነሁ ወተዓላ_ራሱን (አልገፉር) ብሎ የጠራው ወደሱ እንድትመለስ ስለሚፈልግ ብቻ ነውና እጅ አትድጥ።

#ረሳኢሉን ሚን አልቁርኦን

السلام عليكم و رحمة الله وبركاتهእንኳን ለተከበረው ታላቁ የረመዷን ወር አላህ በሰላም አደረሰን፤ደውሃ የትምህርት እና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት አባላቶቹን በልዩ ሁኔታ እንኳ...
10/03/2024

السلام عليكم و رحمة الله وبركاته
እንኳን ለተከበረው ታላቁ የረመዷን ወር አላህ በሰላም አደረሰን፤

ደውሃ የትምህርት እና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት አባላቶቹን በልዩ ሁኔታ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል፤ የደውሃ ቤተሰብ በመሆን የመጀመሪያ ረመዷናችንን ስንፆም ከፍ ያለ ደስታ ይሰማናል፡፡

🌟🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌟

ይህ ረመዷናችሁ እምር ፍክት ያለ እንዲሆን በየእለቱ አስተማሪ የሆኑ መልዕክቶችን በግሩፓችሁ ላይ በፅሁፍም፣በምስልም፣በድምፅም የምንለቅላችሁ መሆኑን ከወዲሁ እየገለፅን የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ድረገፆቻችንን በመከተል ይከታተሉ።

🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨
እንኳን ለተከበረው ታላቁ የረመዷን ወር አላህ በሰላም አደረሳችሁ ✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙

ደውሃ የትምህርት እና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት

የደውሃን የማህበራዊ ሚድያ ድረገፆቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ተከታተሉን።

DEWHA ISLAMIC EDUCATION AND DEVELOPMENT ORGANIZATION:

https://t.me/Dewha1C

https://youtube.com/?si=8569RXOfk9mpAZEB

https://www.tiktok.com/?_t=8jrvrXalbjZ&_r=1

https://www.facebook.com/profile.php?id=61555763643960

10/03/2024
10/03/2024

ዝሆኖቹ የዓመቱን ወርቃማ ሰዓታት ይዘርፉን ይሆን !?
★★★

ኢማሙ ማሊክ እንደወትሮው የነብዩ _ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም_ መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው ሀዲስ ያቀራሉ...
በዙሪያቸው ያሉ ደረሳዎቻቸውም ትምህርቱን በትኩረት እየተከታተሉ ነው...ድንገት ያልተለመደ ድምፅ ተሰማ፡-
"ትልቅ ዝሆን፣ትልቅ ዝሆን …" የሚል…

ከዚህ ቀደም የመዲና ሰዎች ዝሆን አይተው አያውቁምና ዝሆን በማየታቸው የተፈጠረው ወከባ አይደንቅም ነበር።

የኢማሙ ማሊክ ደረሳዎች በሙሉ ዝሆኑን ለማየት እየተጣደፉ ኢማሙን ጥለዋቸው ሄዱ ...ከያህያ ቢን የሕያ አልለይሲ በስተቀር።

ኢማሙም የሕያን " ዝሆኑን ለማየት አብረሀቸው ለምን አልሄድክም፣ ወይስ ዝሆን ላንተ አዲስ አይደለም?" ሲሉ ጠየቁት።

እርሱም " መዲና የመጣሁት የርሶን ዒልም ለመቅሰም እንጂ ዝሆን ለማየት አይደለም " ሲል መለሰ።

ይህን ክስተት በደንብ ካጤንነው ወደ መዲና ለምን እንደመጣ እና አላማው ምን እንደሆነ ከተሰብሳቢዎቹ ጠንቅቆ የሚያውቀው አንዱ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፤ ስለዚህ አልተዘናጋም፣ ትኩረት ሊያስቱ በሚችሉ አማላይ ነገሮች አልተሸነገለም።

በዚህም ምክንያት ኢማሙ ያህያ ቢን ያህያ አል-ለይሲ የኢማሙ ማሊክን አል-ሙወጠእ የተሰኘውን የሐዲስ ኪታብ በመዘገብ ልዩ ቦታ የሚሰጣቸው ሆነው እናገኛቸዋለን።

ሌሎች ጎደኞቹ የነበሩ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን ታሪክ አልጠቀሳቸውም።

በእኛ ጊዜም የዝሆኑ ታሪክ ይደገማል...ነገር ግን በተለያዩ ምስሎች...እና በተለያዩ መንገዶች...በተለይ በረመዷን።

በረመዷን ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፡–

1ኛ/ ግቡን ወስኖና ለይቶ... በረመዷን ውስጥ ማሳካት የሚፈልገውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤

2ኛ/በተለያዩ የዝሆን አይነቶች የተጠመደ... ፊልሞች፣ ገደብ የለሽ እንቅልፍ፣ ጫት እየቃሙ ማምሸት እና ሌሎች የዚህ ዘመን ዝሆኖች.. ‏ስለዚህ ከዘመኑ ዝሆኖች እንጠንቀቅ
የዓመቱን ወርቃ ሰዓት ይዘርፉናልና።

ረመዷን ከሪም!



ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ማህበር ከባቲ መረዳጃ ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የረመዳን መግቢያ የረመዳን ስንቅ ፕሮገራም ታላላቅ ዑለማኦች በተገኙበት በቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ ...
02/03/2024

ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ማህበር ከባቲ መረዳጃ ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የረመዳን መግቢያ የረመዳን ስንቅ ፕሮገራም ታላላቅ ዑለማኦች በተገኙበት በቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ ተካሂዷል።

በእለቱም ዑለሞች በጣፋጭ አንደበታቸው ቀልብ የሚስብ መልእክታቸውን አካፍለውናል።

የደውሐ መስራች የሆኑት የአፍሪካ ቲቪ ፈታዋ ፕሮግራም ድምቀት የሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ ጣሂር የድርጅቱን አላማና እቅድ በአጭሩ ለታዳሚዎች ገለፃ አድርገው ሙስሊሙ ማህበረሰብም በዚህ በተቀደሰ አላማ ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ አጋርነቱን እንዲገልፅ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የረመዳን ስንቅእንግዶች ቦታቸውን ይዘዋል፣መድረክ መሪውም ፕሮግራሙን ለመጀመር ......
25/02/2024

የረመዳን ስንቅ

እንግዶች ቦታቸውን ይዘዋል፣
መድረክ መሪውም ፕሮግራሙን ለመጀመር ......

ታላቅ የደእዋ ጥሪ ነገ በጧት ቢላሉል ሀበሽ መሰብሰቢያ አዳራሽ አይቀርም ። ይህ ሁሉ ሊቀ ሊቃውንት ነገ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እናንተን ይጠብቃሉ።አይቀርም።
24/02/2024

ታላቅ የደእዋ ጥሪ

ነገ በጧት ቢላሉል ሀበሽ መሰብሰቢያ አዳራሽ አይቀርም ።

ይህ ሁሉ ሊቀ ሊቃውንት ነገ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እናንተን ይጠብቃሉ።

አይቀርም።

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251956553033

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት Dewha knowladge and dev't org posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ደውሐ የትምህርትና የልማት ኢስላማዊ ድርጅት Dewha knowladge and dev't org:

Share