Ethiopian Visionary Churches Fellowship - የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ethiopian Visionary Churches Fellowship - የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት

Ethiopian Visionary Churches Fellowship - የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በየዘመኑ ባለራዕዮች ይነሳሉ! ባለራዕይ አይሙት! The Visionary must not die!

ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም*******የመጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ የሽኝትና ቀብር ሥነ-ሥርዓት የክርስቶስን ወንጌል ከፍ በማድረግ ተከናወነ።በቅድሚያ መጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ ቤተሰቦች፣ የራ...
21/04/2023

ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም
*******

የመጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ የሽኝትና ቀብር ሥነ-ሥርዓት የክርስቶስን ወንጌል ከፍ በማድረግ ተከናወነ።

በቅድሚያ መጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ ቤተሰቦች፣ የራዕይ ተካፋዮች፣ በአገልግሎት የምትመስሏት እንዲሁም የክርስቶስን የምስራች ወንጌል ምክንያት ሆና ያደረሰቻችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች ሁሉ በዚህች የወንጌል አርበኛ በስጋ ከመካከላችን በመለየቷ ምክንያት ለሁሉም የመንፈስ ቅዱስ መጽናናት ይሁን እንላለን።

እንዲሁም በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጪ ከተለያዩ አካባቢዎች በቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝታችሁ አብሮነታችሁን ላሳያችሁ የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ኅብረታችን ያለውን ታላቅ አክብሮት እየገለጸ በተለይም ለለሚ-ኩራ ክ/ከተማ መሪዎች ኅብረቱ ታላቅ ምስጋናን ለማቅረብ ይወዳል።

በድጋሚ ለመላው ቤተሰቦች፣ የራዕይ ተካፋዮች፣ በአገልግሎት የምትመስሏት፣ እንዲሁም የክርስቶስ ሠላም ቤ/ን ቤተሰቦች የመንፈስ ቅዱስ መጽናናት ይሁን እንላለን።

የመጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ ሽኝትና ቀብር ስነ-ስነስርዓት***የኅብረታችን አባል የሆነችው የክርስቶስ ሰላም ቤ/ን ባለራዕይ የነበሩት መጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ በስጋ ተለይተውን ወዳገለገሉትና ወ...
20/04/2023

የመጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ ሽኝትና ቀብር ስነ-ስነስርዓት
***

የኅብረታችን አባል የሆነችው የክርስቶስ ሰላም ቤ/ን ባለራዕይ የነበሩት መጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ በስጋ ተለይተውን ወዳገለገሉትና ወደሚወዱት ጌታ በመሄዳቸው ለቤተሰቦቿ፣ ወዳጆቿ፣ በአገልግሏት ለሚመስሏት በመሉ ኅብረታችን በድጋሚ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ለመግለጽ ይወዳል።

ነገ አርብ በ13/08/15 ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በመኖሪያ ቤታቸው ሽኚት ተደርጎ 6 ሰዓት ኮተቤ በሚገኘው የካ 05 መካነ-መቃብር የቀብር ስርዓታቸው እንደሚፈጸም በጌታ ፍቅር ለማሳወቅ እንወዳለን።

መኖሪያ ቤታቸው:- ጎሮ ሚካኤል ፍሊንትስቶን ወይም ከኮብል ማደያ ገባ ብሎ

የቀብር ቦታ:- የካ 05 መካነ መቃብር (ከኮተቤ የካ ኪዳነምህረት ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ አዲሱ አስፓልት መሃል)

የቤተሰቦቻቸው ስልክ:-
+251922116122
+251915068040

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም የሐዘን መግለጫ*******"ሄደች ወደ አምላኳ"-------------------------የምስራቋ ሴት፣ ታላቅ የወንጌል ጀግና፣ በገጠር ከተማ፣ በጫካ በረ...
19/04/2023

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም

የሐዘን መግለጫ
*******

"ሄደች ወደ አምላኳ"
-------------------------

የምስራቋ ሴት፣ ታላቅ የወንጌል ጀግና፣ በገጠር ከተማ፣ በጫካ በረሃ ወንጌልን ይዛ የዘመተች የክርስቶስ ወታደር፣ መጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ ሳትሰስት እድሜዋን ሕይወቷን ወደ ሠጠችው ወደ አምላኳ ሄደች።

በዚህ ብዙ ግፊያና ንጥቂያና ተስፋ አስቆራጭ ምልክቶች በሞሉበት ወቅት፣ ከምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል አንስቶ እስከ መሃል አገር ድረስ ለብዙ አስርት አመታቶች በታማኝነት ወንጌልን በመያዝ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ዋጋ ከከፈሉ ሰዎች መካከል የምትጠቀስ ታላቅ የእግዚአብሔር ሴት ነበረች።

በመጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ ላይ የነበረው የወንጌል እሳት፣ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ሰዎች እንዳሉት ያየንበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር እንደነበረችና በዘመኗ ለትውልዱ የሚሆንን የእግዚአብሔርን አጀንዳ ስትሰራም እንደነበረች በአገልግሎቷ ፍሬዎች አይተናል።

የሰው የምድር ቆይታው አይታወቅምና ጌታ ጊዜውን አፈጠነብን። ጊዜው ፈጥኖ ወደ ጌታ ሄደች። እሷ ወደ ሚበልጠው ሄዳለች። ይሁን እንጅ በዚህ ትውልድ መካከል ስለ ወንጌል የከፈለችው ዋጋ በባለራዕይ ትውልድ መካከል ሁሌም ይታሰባል።

መጋቢት ምንዳዬ የክርስቶስ ሰላም ቤተክርስቲያን መጋቢና መሪ ስትሆን በኅብረቱ የለሚ ኩራ ክ/ከ አስተባባሪ ኮሚቴ በመሆን ትውልዱን ስታገለግል ነበር።

በመጨረሻም፣ መጋቢት ምንዳዬ መንግስቱ በዘመኗ ወዳገለገለችውና ሕይወቷን ወደ ሠጠችለት ወደ ክብሩ ጌታ በመሄዷ ደስ ቢለንም ከመካከላችን በስጋ በመለየቷ የተሰማንን ጥልቅ ኃዘን ለማስተላፍ እንወዳለን።

ሐዋርያ ዘላለም ጌታቸው (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚደንት
ሚያዝያ 11/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።

April 15, 2023***A message from the President of Ethiopian Visionary Churches Fellowship, Apostle Zelalem Getachew (Dr.)...
15/04/2023

April 15, 2023
***

A message from the President of Ethiopian Visionary Churches Fellowship, Apostle Zelalem Getachew (Dr.) regarding the Resurrection Light of Easter, which will be celebrated on Sunday, April 16, 2023;
***

"WE ARE SAVED FROM OUR ENEMY"
————-
...
Dear family of God, we notice that when the first people disobeyed the command, death appeared as the enemy of all human beings (Genesis 3:15). On the day when death was conquered, Adam accused Eve, whom he found near him, and Eve accused the serpent who was with her. Friends, what is next to us is not our real enemy, but rather a tool used by our enemy....

It is amazing that the human being leaves the force of death unnoticed which is working inside them, and searches the outside environment for their enemies and make the kings of this world, experts and scholars, rich people, tribes, religions, ... as his enemies. And the he will fight against those who are enslaved to death like him. The wise Solomon, in the days when he won all these again and again... called them all useless, was defeated by an enemy inside him and threw everything away.
...

My friends; the Gospel is a message given to the whole earth that announces the abolition of death and shines the light of resurrection on darkness. Now two thousand years have passed since your enemy was defeated by the Gospel. The light of resurrection that shines in our hearts is the one that overcomes the death of all the children of men. Therefore, the truth that we reveal to the world is this and this only.....

It is now death is abolished by the Christ. Therefore, the resurrection is preached in open. Our Gospel is the testimony of the defeat of death and the resurrection of Christ!

***

Visionary to National Revival!

Apostle Zelalem Getachew (Dr.)
President of Ethiopian Visionary Churches Fellowship

April 15, 2023
Addis Ababa, Ethiopia.

ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም***እሁድ፣ ሚያዝያ 8 ቀን 2015 ዓ.ም የሚከበረውን የትንሳዔ ብርሃን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚደንት ሐዋር...
15/04/2023

ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም
***

እሁድ፣ ሚያዝያ 8 ቀን 2015 ዓ.ም የሚከበረውን የትንሳዔ ብርሃን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚደንት ሐዋርያ ዘላላም ጌታቸው (ዶ/ር) የተላለፈ መልዕክት፤
***


“ከጠላታችን ድነናል”
———————

በጣም የሚገርመው የሰው ልጅ በውስጡ እየሠራ ያለውን የሞት ኃይል ትቶ፣ በአካባቢው ጠላቶቹን ፍለጋ ይኳትናል። የዚህ ዓለም ነገስታት፣ ጠበብት፣ ባለጠጎች፣ ነገዶች፣ ኃይማኖቶች፣ … ጠላቱ አድርጎ ይፋለማቸዋል። እንደሱ በሞት ባርነት ከተገዙ ጋር ጦርነት ገጥሞ ይዳቆሳል። ......

የተወደዳችሁ፤ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ወደድሁ እርሱም ለሞት የማይገዛ ማነው? የሚል ነው፡፡ የኃይማኖት መሪ፣ ጠቢብ፣ ባለጠጋ ወይስ ንጉስ? ወንድ፣ ሴት፣ ህጻን ወይስ ሽማግሌ? ሞት በውስጡ ሆኖ ያልገዛው ያላሸነፈውስ ማነው? ወዳጆቼ ማንም የለም፤ አይኖርምም። ሁሉም ይሞታል። ....

የተበከርከው ወንድሜ፤ በድጋሚ ልጠይቅህ እስከዛሬ ጠላትህ ማን ነበር? ማንንስ ስታሳድድ ኖርህ? ሰውን፣ ኃይማኖትን፣ እውቀትን፣ ማጣትን፣... የሞት መውጊያ የሆኑትን ውጫዊ ነገሮችን ጠላትህ አድርገህ አንዴ በማሸነፍ ሌላ ጊዜ በመሸነፍ ስትመላለስ ኖረሃል። ....

ወገኖቼ፤ ወንጌል ሞት መሻሩን የሚያውጅ በጨለማ ላይ የትንሳዔውን ብርሃን የሚያበራ ለምድር ሁሉ የተሠጠ ምስራች ነው። አሁን በወንጌል ጠላታችሁ ከተሸነፈ 2ሺህ ዓመታት አልፈዋል። በልባችን የበራው የትንሳዔው ብርሃን የሰዎች ልጆችን ሁሉ ሩጫ የገታውን ሞት የሚሻገር ነው። ስለዚህ ለዓለም ገልጠን የምንናገረው እውነት ይህና ይህ ብቻ ነው።

አሁን በክርስቶስ ሞት ተሽሯል። ስለዚህ ትንሳዔያችን በአደባባይ ይሰበካል። የተቀበልነው ወንጌላችን የሞት መሸነፍ እንዲሁም የክርስቶስ ትንሳዔ ምስክርነት ነው።

ሻሎም! መልካም የትንሳዔ ብርሃን በዓል።

*******
ባለራዕይ ወደ አገራዊ ሪቫይቫል!
*******

ሐዋርያ ዶ/ር ዘላለም ጌታቸው (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚደንት

ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፡፡

የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
09/04/2023

የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

የኢቪአክኅ 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል መርሃግብር፣ ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
09/04/2023

የኢቪአክኅ 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል መርሃግብር፣ ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል መርሃግብር፣ ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም***
09/04/2023

የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል መርሃግብር፣ ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
***

የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል መርሃግብር፣ ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም***
09/04/2023

የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ብሔራዊ ክብረ በዓል መርሃግብር፣ ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
***

07/04/2023

ባለራዕይ ወደ ሀገራዊ ሪቫይቫል..................................................................
የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል በአዲስ አበባ መጋቢት 30 2015 ዓ.ም

06/04/2023

ባለራዕይ ወደ ሀገራዊ ሪቫይቫል..................................................................
የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተክርስቲያናት ኅብረት 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል በአዲስ አበባ መጋቢት 30 2015 ዓ.ም

Address

Kirkos Sub City, Around Mexico Roundabout
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Visionary Churches Fellowship - የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopian Visionary Churches Fellowship - የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት:

Share