Mavuno Church Addis Ababa

Mavuno Church Addis Ababa English and Amharic speaking church meeting every Sunday morning from 9am - 11am for Amharic & 10am - 1pm for English. t.me//mavunoet

Moreover,
from Monday to Friday 12pm -1:30pm lunch time prayer

Book series throughout the week.

24/02/2023
25/12/2022

ሚዚዚ መጀመር የምትፈልጉ በሜሴንጀር አሳውቁን። If you want to start MIZIZI please contact us via messenger.

የመጽሐፍ ምልከታ ፕሮግራምቀን አስርBook reflectionDay TenBook title: Changing into his likenessAuthor: Watchman Neeአቅራቢ፡ ደራራ እስራኤልእግዚ...
28/12/2021

የመጽሐፍ ምልከታ ፕሮግራም
ቀን አስር

Book reflection
Day Ten

Book title: Changing into his likeness
Author: Watchman Nee

አቅራቢ፡ ደራራ እስራኤል

እግዚአብሔር እስራኤልን ከባርነት ነጻ ለማውጣት ለሙሴ በዚህ ስም ተገለጠለት::

“. . .እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ አለው።. . .”
ዘጸ 3፡6

እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው። ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ። የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው። ዘጸ 3፡15

ሶስቱ ቁልፍ ሰዎች (አብርሃም፣ ይስሃቅ፣ እና ያዕቆብ)

የእነዚህ የሶስቱ ሰዎች ሕይወትና ልምድ፤ የእግዚአብሔር ምርጦች የሚሄዱበትን መንገድ የሚያሳይ ነው፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ያመንን እኛ አሁን የእግዚአብሔር እስራኤል ነን፡፡

1ኛ- አብርሃም(የመለኮት ምርጫ)

የእግዚአብሔር የመዋጀት ስራ የጀመረው ከአብርሃም ነው፡፡
ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው፥ ሮሜ 4፡11

ከእርሱ በፊት እንደነበሩት እንደ ኖህ፣ ሄኖክና አቤል እንኳ ያለ ህይወት የነበረው አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር የድህነት ስራው መጀመሪያ አደረገው ።
የቤዛነት ስራው የተጠናቀቀውና ሙሉ የሆነው በክርስቶስ ነው፣ ይሁን እንጂ የጀመረው አብርሃም ጋር ነበረ፡፡
- የአብርሃም ጥሪ የመውረስ ጥሪ ነበር፤ የመሬት ጥያቄ፣ ታላቅ ሕዝብ የመሆን (ሕዝብን በእርሱ በኩል የመሰብሰብ)
መሬት በብሉይ ኪዳን ወሳኝ ጉዳይ ነበር፡፡ ምድሩን ለመያዝ መሬቱን መርገጥ ያስፈልግ ነበር፡፡
- አሁን እግዚአብሔር ወደ ምድር የሚወርድበት መርገጫ መሬት አለው፤ እርሷም ቤተክርስቲያን ናት፡፡
- የእግዚአብሔርን ጥሪ በመቀበል ደረጃ አብርሃም የመጀመሪያው ሰው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሲጠራ ጣኦት አምላኪ ነበር፡፡
- በአብርሃም በኩል እግዚአብሔር ለሰው ልጅ አዲስን ግንኙነት አስተዋወቀ፡፡

2- ይስሐቅ (የክርስቶስ ተምሳሌት)

የተወደደ - አንድ ልጅ - ዕብ 11፡17

ከእናቱ ሞት በኋላ የቤተክርስቲያን ምሳሌ የሆነችው ሚስቱ ርብቃ ከሩቅ ሀገር መጣችለት፤ አንድ ደም አንድ ቤተሰብ የሆነች፡፡
የተወለደው፣ የኖረው፣ የሞተውም እዛው ከነዓን ነበር፡፡
ዮሐ 3፡13- በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡
በራሱ የሚያደርገው ምንም ነገር አልነበረም፡፡
ዮሐ 5፡19- አብ ሲያደርግ ያየውን እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፡፡
ዘፍ 26፡23-24 “ስለባሪያዬ ስለአብርሃም ዘርህን አበዛለሁ”
እስማኤል ከአጋር(ሕግ) ይስሐቅ ግን ከሳራ(ጸጋ)
ጸጋ የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው፡፡
ሀጢአተኞች ለድህነት ተስፋቸው የእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው፡፡
አማኞችም በክርስትና ሕይወት ተስፋቸው ይኸው ጸጋ ነው፡፡

3- ያዕቆብ (ትክክለኛ ለውጥ)

በያዕቆብ ሕይወት የምናየው ትምህርት፣ መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ሕይወት ያለውን የዲሲፕሊን ስራ ነው፡፡
- እግዚአብሔር በያዕቆብ ሕይወት ፈቃዱን ለመፈጸም ፈቃደኛ ነበር፡፡ ነገር ግን ያዕቆብ በሕይወቱ ያለውን መለኮታዊ አጀንዳ ለማስፈጸም በሰውኛ መንገድ ሄደ፡፡
“ያዕቆብን ወደድሁ፤ ዔሳውን ጠላሁ፡፡” “ታላቁ ለታናሹ ይገዛል”

- እግዚአብሔር ለሀጢአት ብቻ ሳይሆን ለተፈጥሯዊውም ሰው የህይወት መንገድ ቦታ የለውም፡፡
- ኢየሱስ ነጻ የነበረው ከኃጢአት ብቻ ሳይሆን በራሱ መንገድ ከመደገፍም ጭምር ነበር፡፡
- መንፈስ ቅዱስ ቀስ በቀስ ሰውኛ መንገዳችንን ያስጥለናል፡፡
- እኔ ለእግዚአብሔር የማልመች ሰው ነኝ ብለን ስናስብ፤ የያዕቆብ አምላክን እንታመን፡፡
ከመነሻው ጀምሮ ተንኮለኛና ብልጣብልጥ የነበረውን ወደ መስመር አስገባው፡፡

* የእነዚህን አባቶች ሕይወትና ልምድ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ብንመለከት ስለክርስትና ሕይወታችን ብዙ የምንማረው ቁምነገር ይኖራል!

14/12/2021

የእሁድ ጉባኤ በማቩኖ ቤተ ክርስቲያን
በ 3/4/2014 ዓ.ም
Apostolic Foundation - by Pastor Tumim Wolde

የመጽሃፍ ምልከታ ፕሮግራምቀን 9በ ሌሊሳ ታደሰBook title: Sharing JesusAuthor: D**g Field and Brett Eastmanይህ መጽሃፍ በመግቢያው ላይ በቅዱሳን ህብረት ው...
14/12/2021

የመጽሃፍ ምልከታ ፕሮግራም
ቀን 9
በ ሌሊሳ ታደሰ

Book title: Sharing Jesus
Author: D**g Field and Brett Eastman

ይህ መጽሃፍ በመግቢያው ላይ በቅዱሳን ህብረት ውስጥ ስላለው የህይወት መተናነጽ እና በርሱ ውስጥ ስለሚገኘው የህይወት እድገት አጥብቆ ያወሳል።
ነገ ግን ይህን አስደናቂ በረከት ለማግኘት ከእኛ የሚጠበቁ አስፈላጊ ግብዐቶች እንዳሉም አንስቷል፤ እነርሱም፦
እምነት፣ ሚስጥርን መጠበቅ፣ ታማኝነት፣ እንክብካቤን ማሳየት፣ ግልጽነት፣ ዋጋ መክፈክ፣ እና በቋሚነት ለመገኘት መፍቀድን የመሳሰሉ ናቸው።
በዚህ መንገድ ለማለፍ ስንፈቅድ በእምነታችን በጥንካሬም በጥልቀትም ማደግ እንችላለን።

ኢየሱስ ማን ነው?
ብዙዎች ስለ ኢየሱስ የተለያየ አመለካከት አላቸው፣ ከሰሙት ወይም እንዲህ ነው ብለው ከሚያስቡት፡-
ድንቅ አስተማሪ፣ የ አብዮት መሪ፣ ነብይ፣ ሃይማኖተኝነትን አጽንኦት ሰጥቶ የሚሰብክ መሪ፣ ወዘተ. . .

በቃሉ ውስጥ የምናገኘው ኢየሱስ እጅግ ታላቅ እና አስደናቂ ነው!

ኢየሱስ እግዚአብሄር ነው!

ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ ሊቀ ካህናቱም፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው።
ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው። ማቴ 26፡63-64

ኢየሱስ ሰው ሆነ!
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሐ 1፡14

ኢየሱስ በስልጣን አስተማረ

እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ። ማር 1፡22

ኢየሱስ በሽተኞችን ፈወሰ

ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። ማቴ 4፡23

ኢየሱስ የተተዉ የተጣሉትን ወዳጅ አደረገ

በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ። ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን፦ መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው። ማቴ 9፡10-11

ኢየሱስ የኃይማኖት ጨቋኞችን ገሰጸ

እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ። ማቴ 23፡27

ኢየሱስ ስቃይ እና መከራ ተቀበለ

የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጐውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙም፤ ብዙም የሐሰት ምስክሮች ምንም ቢቀርቡ አላገኙም። ማቴ 26፡59-60

ኢየሱስ በሁሉ ተፈተነ

ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። ዕብ 4፡15

ኢየሱስ ፈጽሞ ኃጢአትን አላደረገም

እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።1ዮሐ 3፡5

ኢየሱስ ሞተ፣ ከሞት ተነሳ፣ አሁንም በህያውነት አለ

አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። 1ቆሮ 15፡20

ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግን እንዲችል መንገድን ከፈተ
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። ዮሐ 3፡16 17

ስለ መከራችን ይራራል

ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። ዕብ 4፡15

ኢየሱስ ይወደናል
ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ። ኤፌ 3፡19
ኢየሱስን ማወቅ እና ከእርሱ ጋር ህብረትን መጀመር በህይወታችን ልናገኘው እና ልናደርገው ከምንችለው ነገር ሁሉ ውዱና ትልቁ ነገር ነው፡፡
“ተከተለኝ” ከሚለው ከመጀመሪያው ቃል ጀምሮ፣ በአገልግሎቱ፣ በሞቱ፣ እንዲሁም በትንሳኤው ሰዎችን ወደ ራሱ በመሳብ የታወቀ ጌታ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ቃሉን ስናነብ ይህ መንገድ ለአማኞች አልጋ በአልጋ የሆነ እንዳልሆነ እንገነዘባለን።
ስለዚህ በዚህ ክርስቶስን የማጋራት የአብሮነት ጉዞ ውስጥ የሚያስፈልጉን አምስት መሰረታዊ ነገሮች እነኚህ ናቸው፦
1፡ ሕብረት Fellowship
2፡ ደቀመዝሙርነት
3፡ አገልግሎት
4፡ ምስክርነት
5፡ አምልኮ

እነኚህ 5 መሰረታዊ አላማዎች በግልም ሆነ ደግሞም በአንድነት እንደ ቤተ ክርስቲያን ለሚኖረን መንፈዊ እድገት እጅግ ጠቃሚዎች ናቸው።
እነዚህን ነገሮች ትኩረት በሰጠናቸው እና በእነርሱ ላይ በሰራን ቁጥር በመንፈሳዊ ህይወታችን እጅግ እየጠነከርን እንሄዳለን።

1፡ ሕብረት (Fellowship) ልባችንን ከሌሎች ልብ ጋር ማገናኘት ነው።
ይህም ህይወታችንን ከሌሎች ጋር ለማጋራት እና የሌላውንም በጥሞና ለመከታተል ነው።
ስለዚህ ልባችንን ከፍተን ከልብ የሆነን የጠለቀን ህብረት እንመስርት።

2፡ ደቀመዝሙርነት (Discipleship)
ይህ ጥሪ ኢየሱስን ወደ መምሰል የማደግ ጥሪ ነው።
ይህም ቃሉን በማግኘት መንፈሳዊ መረዳትን በመጨመር ተግባራዊ የሆነ ልምምድ ውስጥ መግባት ነው።

3፡ አገልግሎት (Ministry)
ይህ እውነት ሌሎችን በፍቅር ማገልገል ማለት ነው።
ሌሎችን ለማገልገል አጋጣሚዎችን ማግኘትና መጠቀም ማለት ነው፡፡
ይህ መንገድ የክርስቶስን ፍቅር ለሌሎች የምናካፍልበት መንገድ ነው።

4፡ ምስክርነት (Evangelism)
ይህ መንገድ፣ የያዝነው እውነት በውጭ ካሉት ጋር የሚዛመድበት መንገድ ሲሆን፣ ያሉበትን ሁኔታ እንድናውቅ ታሪካቸውን እንደንሰማ እና እኛም ጌታ በህይወታችን የሰራውን ስራ በማውራት የእግዚአብሔርን ፍቅር እንድንገልጥ ነው።
5፡ አምልኮ (worship)
እግዚአብሔርን ለማክበር ህይወትን ለርሱ መሰዋት ነው።
ይህም ለርሱ ህልውና ትልቅ ትኩረት በመስጠት የሚኖት ህይወት ነው።

freedom prayeri am a fearless influencermy past is forgiven, my future is securemy present is not for me, but for the on...
13/12/2021

freedom prayer
i am a fearless influencer
my past is forgiven, my future is secure
my present is not for me, but for the one who set me free
the die has been cast, i have stepped over the line
no more prayer-less living, cheap giving and selfish dreaming
i am fully surrendered to God, and to following the vision of this house
i will gladly pay the cost, contagiously spreading his love
playing my role in the mavuno family, to make disciples everywhere
until the whole world is changed, and every sector of society
i align myself to God's purpose, i will be who he calls me to be
i surrender to be shaped and molded, through his word
and through his family, until my will and his will are completely aligned
and i become everything that God created me to be, i am Fearless Influencer!

የእሁድ ጉባኤ በማቩኖ ቤተ ክርስቲያን በ 3/4/2014 ዓ.ምApostolic Foundation - by Pastor Tumim Wolde 1ኛ ጴጥሮስ 2 (አዲሱ መ.ት)¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯²¹ የተጠራች...
13/12/2021

የእሁድ ጉባኤ በማቩኖ ቤተ ክርስቲያን
በ 3/4/2014 ዓ.ም
Apostolic Foundation - by Pastor Tumim Wolde
1ኛ ጴጥሮስ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ የተጠራችሁትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌን ሊተውላችሁ ነው።
²² “እርሱ ኀጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም።”
²³ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራ ሲደርስበት አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
²⁴ ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።

11/12/2021

Apostolic Foundation by Pastor Bezalem Belay

የመጸሃፍ ምልከታ ፕሮግራምቀን 8በ ናትናኤል ሙልጌታ የመጽሃፉ ርዕስ፡ ኢየሱስ ማን ነውጸሃፊ፡ ተሾመ ዳምጠው (መጋቢ)  ስለኢየሱስ መማር ለምን አስፈለገ?ሁሉ የተፈጠረው በርሱ፣    እግዚአብሄ...
10/12/2021

የመጸሃፍ ምልከታ ፕሮግራም
ቀን 8
በ ናትናኤል ሙልጌታ

የመጽሃፉ ርዕስ፡ ኢየሱስ ማን ነው
ጸሃፊ፡ ተሾመ ዳምጠው (መጋቢ)

ስለኢየሱስ መማር ለምን አስፈለገ?

ሁሉ የተፈጠረው በርሱ፣ እግዚአብሄር የሚናገረው በርሱ፣ ሁሉን የሚጠቀልለው በርሱ፣ እግዚአብሔር የሚታወቀው በርሱ፣ የሃጢያት ይቅርታ የሚሆነው በርሱ ዕብ. 1፡1-3፣ 7፡23-25፣ ሉቃ. 10፡22፣ 1ቆሮ.1፡30-31

መለኮታዊነቱ፡

የእግዚአብሔር ቃል ነው ፣
እግዚአብሔር ነው፣
ጌታ ነው፣ ይህ ማለት ያህዌ ነው
አምላክ ነው ፣
የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣ አንድያ ልጅ፣ የበኩር ልጅ
{ወላጆቹ መንገድ እንጂ ምንጭ አይደሉም፡፡ በነሱ መጣ እንጂ ከነሱ አልተገኘም፡፡}

የፍጥረት ፈጣሪ፣ በእግዚአብሔርና በፍጥረት መካከል ያለ መካከለኛ፣ ሁሉን የያዘ፣ በርሱ ካልሆነ በቀር የተገጣጠመ የሌለ፡፡

በመጀመሪያ ቃል ነበር ፣ ፍጥረትን ያስገኘ ምክንያት divine reason
ቃልም የእግዚአብሔር ንግግር ነበር አይልም፡፡ እግዚአብሔር ነበር ይላል፡፡ ቃል ሃሳብ ሳይሆን ማንነት ያለው ስለሆነ ነው፡፡
ሁሉን የፈጠረ ቃል ሁሉን ለማዳን በሰውነት ወደ ዓለም ገባ፡፡

ዘፍጥረት -- እግዚአብሔር ፈጠረ ‹--› ዮሐንስ -- ቃል ፈጠረ

ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ - ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ነበረ፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ መጣ ይላል እንጂ የእግዚአብሔር ልጅ ሆነ አይልም፡፡
እስራኤላዊያን መሲሁ የተገኘባቸው/source/ ሳይሆኑ የመጣባቸው መንገዶች/channel / ናቸው፡፡

የሰው ነፍስ ኢየሱስን ከማወቅ ጋር ባላት ግንኙነት የዘላለም ዕድል ፈንታዋ ይወሰናል፡፡ ሆኖም ግን በቤ/ክ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ከመስማት ይልቅ ስለ ራሳቸው መስማት ያስደስታቸዋል፡፡ ብዙ ዋጋ ከፍለው ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሱትም ስለኢየሱስ ለመማርና ለመስማት ሳይሆን ስለኑሮአቸው የሚነገረውን ለማሳደድ ነው፡፡

ምልክቶቹ ስለኢየሱስ የሚነገረውን ትምህርት የሚያፀኑ ነበሩ እንጂ ሰውን ምድራዊ የሚያደርጉ አልነበሩም፡፡

ስለ እርሱ ማወቅ፣ መገለጥ የሚጠይቅ ዕውቀት ነው!

“ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር…”
“ይህንን የገለጠልህ የሰማይ አባቴ ነው፡፡”

Address

Bole Olympia, Joshua Bldg. #206
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mavuno Church Addis Ababa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Mavuno Church Addis Ababa:

Share