Inter Religious Council of Ethiopia

Inter Religious Council of Ethiopia A non governmental organization working extensively on peace and social matters for a better social and community life.

 !====================ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን...
26/05/2026

!
====================
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺ 447ኛው የኢድ አል–አድሃ (አረፋ) ክብረ በዓለ በሰለም እና በጤና አደረሳችሁ ሲል በዛሬው ዕለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የጉባኤው የእንኳን አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ለንባብ ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች በሙሉ እንኳን ለ1ሺ 447ኛው ታላቁ የኢድ አል–አድሃ (አረፋ) ክብረ በዓለ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ በማለት የአክብሮት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ታላቅ መስዋዕትነትን፣ ልባዊ ጽናትን፣ ትዕግስትን ከሁሉ በላይ ለፈጣሪ መገዛትን እና በእርሱ ላይ ያለ እውነተኛ መተማመንን የሚያመለክት መንፈሳዊና ማሕበራዊ ጥልቅ ትርጉም ያለው ድንቅ ክብረ በዓል ነው፡፡

ይህ ክብረ በዓል የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ያለ ልዩነት ከምንጊዜውም በላይ በመተሳሰብ፣ በመጠያየቅ፣ በመርዳዳት እና በደስታ የሚያከብሩት ታላቅ የፍቅርና የአብሮነት ክብረ በዓልም ነው፡፡

ነብዩ ኢብራሂም በሕልማቸው የበኩር ልጃቸውን ለፈጣሪ መስዕዋት አድርገው ሲያቅርቡ ከተመለከቱ በኋላ ለውድና እና ለበኩር ልጃቸው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤ ልጄ ሆይ እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኘ አይቻለሁ፣ አንተስ ምን ታስባለህ ብለው ይጠይቁታል፡፡ ልጃቸውም አባቴ የታዘዝከውን ሳታጓድል ፈጽም በማለት ያለ ማቅማማት ይመልስላቸዋል፡፡ (ሱረቱ–ሳፋት፤ 120)

ነብዩ ኢብራሂም የልጃቸውን ምላሽ ከሰሙ በኋላ ልጃቸውን ለፈጣሪ መስዕዋት አድርገው ወደ ሚሰውበት ቦታ ከልጃቸው ጋር ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ በጉዞአቸውም ልጃቸው ምንም አይነት ተቃውሞ ሳያሰማ ይልቁኑ ነብዩ የታዘዙትን እንዲፈጽሙ በሚየበረታታ መንፈስ ወደ መስዕዋቱ ቦታ ጉዞአቸውን አቀኑ፡፡ ምንም እንኳን ልጃቸው ቢያበረታታቸውም የታላቁን አላህ ትዕዛዝ እንዳይፈጽሙ በመንገዳቸው ላይ ብርቱ ፈተና አጋጥሟቸው ነበር፡፡

ያጋጠማቸውን ሁሉም ፈተና በጽናት አልፈው ነብዩ ኢብራሂም ከአንዴም ሁለቴ ልጃቸውን ለማረድ/ ለመሰዋዕት ቢሞክሩም ቢላዎው ሊቆርጥላቸው አልቻለም፡፡ በዚህ መሀል ነው ታላቁ ፈጣሪ ነብዩ ኢብራሂም ለፈጣሪ ትዕዛዝ ያላቸውን ጥልቅ መገዛት በመመስከር በልጃቸው ላይ ምንም እዳያደርጉ በምትኩ ግን የመስዕዋት በግ ማዘጋጀቱን የገለጸላቸው፡፡

ነብዩ ኢብራሂም እጅግ ፈታኝ ትዕዛዝ እና ፈተና ቢገጥማቸውም ፈጣሪን የሁሉ የበላይ እና የሕይወታቸው ዋና አድርገው በፍጹም ልባቸው ለፈጣሪ የተገዙ በመሆናቸው ከባዱን ትዕዛዘ እና እጅግ አስቸጋሪውን ፈተና በጽናት አልፈው እስከ ዛሬ ድረስ የሚታውስ፣ የሚተረክ እና የሚተነተን የእምነት፣ የመስዕዋትነት፣ የመታዘዝ ገድል መፈጸም ችለዋል፡፡ ይህ ታሪክ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ለሰው ልጆች ትምህርት ሲነገር ይኖራል፡፡

በዚህ ዘመን የምንኖር እኛ አማኞች የፈጣሪን ስም ከመጥራት ባሻገር በፈጣሪ ላይ በፍጹም ልባችን በመታመን፣ ፈጣሪ ለሰጠን መንፍሳዊ እና ማሕበራዊ ትዕዛዞች በመገዛትና በመፈጸም መኖር ብንችል በምድር ሰላም በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል፡፡

ምክንያቱም የፈጣሪ ትዕዛዝ መረዳዳት፣ መተጋጋዝ፣ መዋደድ፣ አንዳችን ለአንዳችን በጎ ማስብ እና ማድረግ ስለሆነ ነው፡፡ እነዚን መንፍሳዊ እና ማሕበራዊ እሴቶች በሚጠብቁና በሚያስጠብቁ አማኞች ሕይወት ፈጣሪ እጅጉን ይደሰታል፡፡ በምድርም በረከት እና ሀሴት እጅጉን ይበዛል፡፡

ዓለም የፈጣሪን ትዕዛዝ እና ፈቃድ ወደ ጎን በመግፋት ለእኔ ብቻ በሚል መንፈስ ተለክፋለች፡፡ አንድ ሰው አንድን ነገር ጥቅም ያስገኝልኛል ብሎ ካሰበ በፈጣሪ በክብር የተፈጠረውን የሰውን ልጅ ሕይወት እሰከማጥፋት የሚደርስ እርምጃ ይወስዳል፡፡ የሰው ልጆች የመለያየት እና የመጠላላት አንዱና ዋንኛ ምክንያት ለእኛ የምንፈልገውን ነገር ለሌላው እንዲሆን አለመፍቀድ ወይም መከልከል ነው፡፡

ለሰው ሁሉ ርህራሄ፣ ቸርነት፣ ምህረት፣ ፍቅር ወዘተ ይገባል፡፡ እኛም ሁላችን ለሰው ልጆች የሚገባውን መልካም ሁሉ ነገር በማድረግ የስጋችንን ክፉ ምኞት ዕለት ተዕለት ልንገድል ይገባል፡፡ የዚህ በዓል አንዱና ዋንኛ መገላጫ ለስው ልጆች ማስብ፣ ፍቅር ማሳየት እና እንክብካቤ ማድረግ ነው፡፡

የኢድ አል–አድሃ (አረፋ) ክብረ በዓለ በውስጡ የያዛቸው የመታዘዝ፣ የመረዳዳት፣ የርህራሄና የፍቅር እሴቶች የሰው ልጆች ያላቸውን ጠንካራ የእርስ በእርስ ትስስር ይበልጥ የሚያጸኑና የሚያጠናክሩ ከመሆናቸውም ባለፈ ካለፈው የበደል ታሪክ በመወጣት ለወደፊት ዕርቅና ሰላም እንዲሁም አብሮነት ቅድሚያ በመስጠት ሕይወታችንን መምራት እንደሚገባን የሚያስገነዝቡ ሕያው ትምህርቶች ናቸው።

ይህ የመሰዋትነት እና የታላቅ ፍቅር መግለጫ ክብረ በዓል ሲከበር የተቸገሩ ወገኖች ካልተቸገሩ ወገኖች እኩል በዓሉን በተመሳሳይ እንዲያከብሩ የሚደረግበት፤ የመረዳዳት መንፍሳዊ ትዕዛዝ የሚከወንበት፣ ሰው ሁሉ በፈጣሪ ፊት እኩል መሆኑን የሚገነዘብበት ነው፡፡

ኢድ አል አድሃ የችግረኞች ቤተ የሚደምቅበት፣ ልጆቻቸው ከምጊዜውም በላይ የሚደሰቱበት፣ መደጋገፍ ፣ መረዳዳት፣ ፍቅር የሚልቅበት ክብረ በዓል ነው፡፡

በመሆኑም የኢድ አል አድሃ (አረፋ) ክብረ በዓልን ስናከብር በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና በሃይማኖታዊው መመርያ መሰረት የታመሙትን እና በችግር ላይ ያሉትን በመጠየቅ እና በመርዳት ከሁሉ በላይም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም እና እድገት ዱዓ በማድረግ እንዲሆን የአደራ መልክታችንን እያስተላለፍን በድጋሜ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺ 447ተኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ፣ በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የፍስሃ በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

 !================ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖታዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃ...
24/05/2026

!
================
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖታዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል ባዛሬው ዕለት በድምቀት ባካሄደው ሀገር አቀፍ የአደባባይ የሰላምና የአብሮነት የጸሎት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት ተቋማቱን ስርዓተ ጸሎት በተከተለ መልክ ለሀገር ሰላም እና እድገት የአደባባይ ጸሎት/ዱዓ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች እና ካህናት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እየተመሩ ለሀገር ሰላም እና እድገት ጸሎት አካሂደዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት አባቶች እና አገልጋዬች በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን እየተመሩ ለሀገር ሰላምና እድገት ዱዓ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የሃይማኖት አባቶች እና አገልጋዮች በካውንስሉ ፕሬዝዳንት ቄስ ደረጀ ጀምበሩ እና በካውንስሉ ጠቅላይ ጸኃፊ ፓስተር ጌትነት ለማ (ዶ/ር) በመመራት ለሀገር ሰላም እና እድገት ጸሎት አካሂደዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶችና አገልጋዬች በብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ተወካይ እየተመሩ ለሀገር ሰላም እና እድገት ጸሎት አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች እና አገልጋዬች በበኩላቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት ፓስተር ታደሰ አዱኛ እየተመሩ ለሀገር ሰላም እና እድገት ጸሎት አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

 !=====================ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖታዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል...
24/05/2026

!
=====================
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖታዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል ባዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የአደባባይ የሰላምና የአብሮነት የጸሎት መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደል የኢትዮጵያዊነት ብልጫው፣ የማሸነፊያ የሚስጥር ቁልፋ በአባቶቻችን ፀሎት በእናቶቻችን ዱአ የፈጣሪን ፍቃድ መጠየቃችን ነው ሲሉ የጉባኤ መክፈቻ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንደ አይን ጥቅሻ ተለዋዋጭ የሆነው አለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ይዞት በመጣው ፈተና እና እድል ፊት ለፊት እንገኛለን ያሉ ሲሆን እኛ ኢትዮጵያውያን ሁላችንንም በሚያሰባስበው ጥላ፣ በአካልም በመንፈስም ባዋሃደን የሀገር ፍቅር ተሳስረን፣ ልዩነታችን አጥር ሳይሆን በህብር ቀለም የደመቀ ውበት ሆኖን፣ ኢትዮጵያ ስለምትባል የጋራ አጀንዳችን ዘላቂ ሰላም፣ ዘመናትን የተሻገረው ጠንካራ ሀይማኖታዊ እሴቶቻችንን ለማፅናት እዚህ ተገናኝተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያዊነት ብልጫው፣ የማሸነፊያ የሚስጥር ቁልፋ በአባቶቻችን ፀሎት በእናቶቻችን ዱአ የፈጣሪን ፍቃድ መጠየቃችን ነው ያሉት ጠቅላይ ፀሐፊው ዛሬም እንደ ትላንቱ አንድነታችንን ለማፅናት፣ ሰላማችንን ለመጠበቅ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ተቋም የምናደርገው ጥረት ሳናቋርጥ የፈጣሪ ፈቃድ ለመጠየቅ የፀሎት ጉልበት እንደሚያስፈልገን እናምናለን ብለዋል።

ዛሬ ይህ የፀሎት መርሀ ግብር እኛን ከፈጣሪ ጋር ብቻ የሚያገናኝ ሳይሆን አንዱ ከሌላው ጋር የልብ ትስስር እንዲፈጥር የሚረዳ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የሚያቀራርብ የመንፈስ አንድነት የሚገነባ ድልድይ እንደሚሆን እናምናለን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት አባቶች ስለ ሀገር ዘላቂ ሰላም እና አንድነት የፀሎት መርሀ ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

24/05/2026

!
====================
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖታዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የአደባባይ የሰላምና የአብሮነት የጸሎት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ፣ አራዳ ፓርክ በኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር በይፋ በድምቀት ተጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

 !=======================ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖታዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በ...
24/05/2026

!
=======================
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖታዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የአደባባይ የሰላምና የአብሮነት የጸሎት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ፣ አራዳ ፓርክ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በይፋ የሚጀመር ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

21/05/2026

!
=============
ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የሰላምና የአብሮነት የጸሎት መረሃ ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና ተሳታፊዎች በሰዓቱ በቦታው እንዲገኙ የአክብሮት ጥሪ አስተላለፈ!

 !=====================ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከ...
21/05/2026

!
=====================
ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ፣ አራዳ ፓርክ ሀገር አቀፍ የሰላም እና የአብሮነት የፀሎት መርሀ ግብር እንደሚያካሂድ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቀ!

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ተቋሙ በተለያዩ ጉዳዮች ሀገር አቀፍ የፀሎት መርሀ ግብር እንደሚያደርግ የተናገሩ ሲሆን ሀይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የፀሎት መርሀ ግብርም ትኩረቱን ለህዝብ እና ለሀገር በሚያስፈልገው ሰላም ለይ ያደርጋል ብለዋል።

ሰላም ከሁሉም ነገር በላይ ለሕዝብ እና ለሀገር የሚያስፈልግ መሰረታዊ አጀንዳ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ጸኃፊው ይህንንም መሰረታዊ አጀንዳ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል የሃይማኖት ተቋማቱን በማስተባበር የሀገራችንን ሰላም ይበልጥ ለማጽናት የበኩሉን ኃላፊነት በመወጣት ላይ እንደሚገኝ አሳውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የሃይማኖት መሪዎች በምድር ላይ የፈጣሪ እንደራሴዎች በመሆናቸው ግጭት እንዳይቀሰቀስ ቀድሞ የመከላከል፣ የተጣሉትን የማስታረቅና ግጭትን የመፍታት እንዲሁም ሰዎችን ወደ ሰላምና ፍትህ የመምራት ተልዕኮ ያላቸው ከመሆኑ አንፃር ተልዕኮአቸውን አጠናክረው እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ሀገራዊ ሰላማችንን ይበልጥ ለማፅናት በአራዳ ፓርክ የተዘጋጀው የፀሎት/ የዱአ እና የምልጃ መርሀ ግብር በመላው ሀገሪቱ የተጀመረውን የልማት እና የእድገት ጉዞ እንዲቀጥል፣ የሞራል ልእልናን ከፍ የሚያደርግ፣ የዜጎችን ስነ ልቦና የሚያንፅ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለሚሰራው ሥራ የፈጣሪ እገዛ እና እዝነት እንዲበዛ አላማ ያደረገ መርሀ ግብር መሆኑንም ጠቅላይ ጸኃፊው አብራርተዋል።

ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ሰላም የወል ሀብታችን በመሆኑ ሰዋዊ እና ሀገራዊ ሀልፊነታችንን በትጋት እንድንወጣ አደራ ማለት እፈልጋለሁ ያሉ ሲሆን ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም ዕለተ እሁድ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የፀሎት መርሀ ግብር ለይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ ከፍተኛ የአባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ተወካዮች እንዲሁም ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ ከ 1ሺ በላይ የሚሆኑ ታዳሚዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ሀገር አቀፍ የሰላም እና የአብሮነት የጸሎት መርሃ ግብሩ በቀጥታ የሚዲያ ስርጭት የሚሸፈን በመሆኑ የሁሉም ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤዎች መርሃ ግብሩን እንዲከታተሉና ተመሳሳይ መርሃ ግብር በክልል ከተሞች ሁሉ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚያካሂዱ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

 !==================ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሸገር ሲቲ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተ...
19/05/2026

!
==================
ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሸገር ሲቲ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሃይማኖት መሪዎች እና አገልጋዮች የሰላም ግንባታ አቅም ማጎልበቻ የምክክር መድረክ ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ የሰላም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ባስተላለፉት መልዕክት ሰላም በዋጋ የማይተመን፣ እጅግ ውድና የላቀ የጋራ ሀብታችን ነው፤ ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት ነው፤ ሰላም ስንጠብቀው የሚበዛ፣ ስንከባከበው የሚጸና የፈጣሪ ታላቅ ስጦታና ጸጋ ነው፤ በሌላ በኩል ለሰላም ትኩረት ሰጥተን መሥራት ካልቻልን በእጃችን ያለው ሰላም በሂደት ልናጣውና ምስቅልቅል ሕይወት ውስጥ ልንገባ እንደምንችል መረዳት ተገቢ ነው በማለት የሃይማኖት መሪዎች እና አገልጋዬች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ጸኃፊው አክለውም ሰላምን ለማጽናት በጋራ መመካከር፣ እርስ በእርስ መማመር፣ መከባበር እና በአንድነት መሥራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም ስንነጋገር አንዳችን ሌላችንን መረዳት እንችላለን፤ እርስ በእርስ መተዋውቅ ለመረዳዳት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን አጽናኦት ሰጥተው አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ታላቅ የጋራ ሀብታችን የሆነውን ሰላም ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ለማጽናት እኛ የሃይማኖት መሪዎች እና አገልጋዬች ከማንም በላይ ኃላፊነት መውሰድ ይገባናል ያሉት ጠቅላይ ጸኃፊው የሃይማኖት መሪዎች አና አገልጋዬች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት በየደረጃው ከሚገኙ ምዕመናን ጋር መመካከር፣ የሚከሰቱ ችግሮችና አለመግባባቶች በፍጥነት በመፍታት፣ የሕዝባችንን የእርስ በእርስ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ሰላምን ማጽናት ይገባናል ሲሉ የአደራ መልክት እና የሰላም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በሀገራችን ሰላም ዙሪያ በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ  የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ...
12/05/2026

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በሀገራችን ሰላም ዙሪያ በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በሀገራችን ሰላም ዙሪያ በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በጉባኤው ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርሟል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በስምምነቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር የፖሊስ ዋና ስራው ወንጀልን መከላከል በመሆኑ ወንጀልን ለመከላከል ደግሞ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ማሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ አንስተው ለህዝባችን እንደ ትልቅ ምሰሶ ከሚታዩት አንዱ የማህበረሰብ ክፍል የሃይማኖት ተቋማት መሆናቸውን ገልፀዋል።

ክብር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የሃይማኖት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ልዩነት ሳናደርግ ሁሉንም እንደ ሃይማኖት አባቶቻችን አክብረን እና እኛም የህዝብ ልጆች ስለሆንን ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርበን ከሰራን በወንጀል መከላከል ሥራችን ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት፣ ችግሮችን ተቀራርቦ ለመፍታት፣ ለሀገር ሰላም በሚደረገው ድካም በጋራ ለመቆም ስለሚረዳ እንደነዚህ አይነት ትብብሮች የፀጥታ ስራዎችን ያቀላል ብለዋል፡፡

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ከሃይመኖት ጋር ተያይዘው የሚነሱ የተለያዩ ችግሮችን ለማስቀረት እና በአጠቃላይ ሀገራችን ሰላሟ ተከብሮ፣ ልማቷ በልፅጎ፣ ህዝባችን ከሀገራችን በሁለንተናዊ መልኩ መጠቀም እንዲችል ዋናው መሰረት ሰላም ስለሆነ ለዚህ ደግሞ የሃይማኖት ተቋማት ትልቅ አጋዥ እና ባለቤት መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ በበኩላቸው ዛሬ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መካከል የተደረገው የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ በጉባኤያችን ልዩ ትርጉም ያለውና ወደ ልዩ ምዕራፍ ያሸጋገረን ነው ብለዋል።

ጉባኤው የቤተ-እምነቶች የጋራ ውክልና ያለው ጉባኤ ከመሆኑ አንጻር የሰላም ጉዳይ ትልቁ አጀንዳ አድርጎ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ዘላቂ ሰላም በሀገሪቱ እንዲሰፍን ከማስቻሉም በላይ በተለይ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረጉ ግጭቶችና ብሽሽቆች እዚህም እዚያም የሚስተዋሉ በመሆኑ ይህንን ከመፍታት አኳያ ሰነዱ እየተደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት የበለጠ የሚያግዝ እና የበለጠ የሚያስተሳስር መሆኑን ተናግረዋል።

የተለያዩ የእምነት አባቶች ሰነዱ ሰላምን ለማስከበር ያለውን ጠቀሜታ ገልፀው የየእምነቱ ተከታዮች የሀገራችንን ሰላም ለማጽናት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የየድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ሥራ አመራሮች ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው ጽ/ቤት ጋር በጋራ፣በትብብር አብረው በሚሰሯቸው ተግባራት ዙሪያ በጥልቀት ተወያዩ ።በውይይቱ የጉባኤው ጠ...
11/05/2026

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ሥራ አመራሮች ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው ጽ/ቤት ጋር በጋራ፣በትብብር አብረው በሚሰሯቸው ተግባራት ዙሪያ በጥልቀት ተወያዩ ።
በውይይቱ የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ክቡር ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጨምሮ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና የፕሮጀክቱ ሥራ አመራሮች ተገኝተዋል ።

 !========================ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኤአይ እና ዳታ ሳይንስ (Artificial...
07/05/2026

!
========================
ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (የኢሃተጉ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኤአይ እና ዳታ ሳይንስ (Artificial Intelligence and Data Science) ላይ ትኩረት ያደረገ የአንድ ቀን የአቅም ግንባታ ስልጠና ለጉባኤው የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ ለአዲስ አባበ እና ለኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በአይዳታ ቴክኖሎጂ (iData Technology) ከፍተኛ ባለሙያዎች በኩል በዛሬው ዕለት እንዲሰጥ አደረገ፡፡

በስልጠና መድረኩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ባስተላለፉት የስልጠና ማስጀመርያ መልዕክት ዘመኑ የሚጠይቀውን ዕውቀት እና ክሕሎት በየጊዜው በመገንባት ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ መቀጠል ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ በመሆኑ በኤአይ እና በዳታ ሳይንስ ላይ ያለንን ግንዛቤ የሚያጎለብት የአንድ ቀን ስልጠና መዘጋጀቱን በመግለጽ ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቀት በመከታተል ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት ጉባኤውን ይበልጥ ለማሳድግ እና ለማጠናከር እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል፡፡

በስልጠናውም ዳታን እንዴት ወደ መረጃ፣ መረጃን እንዴት ወደ እውቀት እና ተግባር መለወጥ እንደሚቻል ሰፊ ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡

በተያያዘም ኤአይን ለሰላም ግንባታ ሥራ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በተለይም መረጃዎችን በየጊዜው በመሰብሰብ እና በመተንተን የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቅያ ጥቆማዎችን ወይም ትንበያዎችን እንዴት ማውጣት እንደሚቻል በስፋት ተብራርቷል፡፡

በመጨረሻም ሳይበር ሴኩሪትን (Cybersecurity) በተመለከት ገለፃ የተሰጠ ሲሆን እንዴት ዳታዎችን በኢንተርኔት ከሚደረግ የሳይበር ጥቃት እና ዘረፋ መከላከል፣ መለየት እና ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ሰፊ ገለፃ ተሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: https://web.facebook.com/irce7

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:00
Tuesday 08:30 - 17:00
Wednesday 08:30 - 17:00
Thursday 08:30 - 17:00
Friday 20:30 - 17:00

Telephone

+251115544157

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Inter Religious Council of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Inter Religious Council of Ethiopia:

Share