MHRT Church Ethiopia

MHRT Church Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MHRT Church Ethiopia, Religious organisation, Addis Ababa.

29/05/2025
06/05/2025

የሰው ልጅ ዓለሙ እግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔር አሳን ሲፈጥረው ከውሃ (ከባህር) ጋር ነው ያወራው፡፡
ዘፍ 1፡20-23 “እግዚአብሔርም አለ፦ ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ። እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ ብዙ፥ ተባዙም፥ የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”
እግዚአብሔር ዛፍን ሲፈጥር ለአፈር (ለመሬት) ነው ያወራው፡፡
ዘፍ 1፡11-12 “እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።”
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር እራሱ መጥቶ ነው የሰራው፡፡
ዘፍ 1፡26-27 “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።”
ውሃ ያለ ዓሳ ውሃ ነው ውሃ እንደሆነ ይቀጥላ፡፡ ዓሳ ያለ ውሃ መኖርም መተንፈሰወም አይችልም ምክኒያቱም ውሃ ለዓሳ የመኖሩ ምከክኒያት ነው፡፡
አፈር (መሬት) ያለ ዛፍ አፈር (መሬት) እንደሆነ ይቀጥላል፡፡ ዛፍ ግን ከአፈር ከተነቀለ መጠውለግ፣ መድረቅ እና መሞት ይጀምራል፡፡
ሰውም ያለ እግዚአብሔር የሞተ ነው፣ ያለ እግዚአብሔር ሰው ምንም ነው፡፡ ምክኒያቱም ሰው የተሰራው በእግዚአብሔር ደግሞም ለእግዚአብሔር ስለሆነ ነው፡፡ የሰው ልጅ ዓለሙ እግዚአብሔር ነው፡፡
አሜን መጋቢ ያሬድ ለሜሳ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911686318

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MHRT Church Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share