Apostolic Generation Christian Ministry

Apostolic Generation Christian Ministry Let's Preach The Gospel of Christ to Every Nation!

 #በኢየሱስ ንግግር ወደ አብ መሄድ" ማለት ብዙ ኪሎ ሜትር ተጉዞ ወደ ሌላ ፕላኔት መሄድ ማለት ነውን❓ ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ አብ በእኔ ይኖራል ብሏልና ደግሞም እግዚአብሔር መንፈስ ነው...
21/08/2026

#በኢየሱስ ንግግር ወደ አብ መሄድ" ማለት ብዙ ኪሎ ሜትር ተጉዞ ወደ ሌላ ፕላኔት መሄድ ማለት ነውን❓

ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ አብ በእኔ ይኖራል ብሏልና ደግሞም እግዚአብሔር መንፈስ ነው መንፈስ ደግሞ በሁሉ ስፍራ ይኖራል ስለሆነም ወደ አብ መሄድ" ማለት ኪሎ ሜትር ተጉዞ ወደ ሌላ ፕላኔት መሄድ ማለት አይደለም ይልቁንም ያ የተናቀው፣ የተገረፈውና የሞተው "ሰውነቱ" (ሥጋው) ወደ መለኮታዊ ክብሩ መመለሱን የሚያሳይ ነው።

✍️ዮሐንስ 17፥5 ላይ "ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አሁን አንተ በእራስህ ዘንድ አክብረኝ" እንዳለ፣ ወደ አብ መሄድ የሥጋ መክበር (Glorification) ነው። ቃል በአብ ዘንድ ክብር ነበረው ያን ክብር ቀርቶ ሥጋ ስሆን እንደ ሰው ሆነና በአብ መልክ ይኖር የነበረው ቃል የባሪያን መልክ በመያዙ ምክንያት ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አሁን አንተ በእራስህ ዘንድ አክብረኝ አለ ማለት ነው። እንዲህ ሲባል መልሰህ ቃል አድርገኝ ሳይሆን ሰው የሆነው ኢየሱስ ወደ አብ በመሄድ በአብ ክብር ወይንም በአባትነት መኖሩን ነው የሚያጎላ።

✍️በተጨማሪም
ወደ አብ መሄድ" ማለት "ማንነቱን ማሳየት" ነው
​ኢየሱስ ወደ አብ መሄዱን ሲናገር ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሳይሆን፣ በምድር ላይ በውርደትና በድካም (በመራብ፣ በመጠማት፣ በመሰቀል) ውስጥ የነበረው ማንነቱ አልፎ፣ ቀደም ስል ደምጹ እንደ ብዙ ውሆች ወደ ሚያስፈራው ወደ መለኮታዊ ስልጣን ሙሉነት መሄዱን የሚገልጸው ስለዚህ "ወደ አብ መሄድ" ማለት ወደ ሙሉ ክብሩ መመለስ ማለት ነው።

✍️በተመሳሳይ
​ "የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ"
​ኢየሱስ ራሱን "የሰው ልጅ" (Son of Man) ብሎ መጥራቱ የሁላችንንም የሰውነት ባሕርይ ወክሎ ነው። ስለዚህ፡
​እርሱ ሲከብር፣ ሰውነት (ሰብአዊነት) አብሮ ከበረ ማለት ነው።
​ቀደም ሲል ሞትና ውርደት የሰው ልጅ መጨረሻ ይመስል ነበር፤ እርሱ ግን ያንን "ሰውነት" ይዞ እስከ መለኮት ክብር (እስከ አብ) ድረስ ከፍ በማድረጉ፣ ለሰው ልጅ አዲስ የክብር በር ከፈተ።
​ ሁለቱ ለምን ተያያዙ?
​"ወደ አብ መሄድ" እና "መክበር" አንድ ናቸው። ምክንያቱም፦
​አብ ማለት የክብር ሁሉ ምንጭ ነው።
​መሄድ ማለት ደግሞ ያንን ክብር መጎናጸፍ ነው።
ኢየሱስ "የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደረሰ" ሲል፣ እግዚአብሔር በለበሰው ሥጋ (በሰውነቱ) አማካኝነት ሞትን ድል አድርጎ፣ ያንን የሰውነቱን ማንነት ወደ መለኮታዊ ክብሩ ከፍ ሊያደርገው መሆኑን መናገሩ ነው።
​ባጭሩ፦
ኢየሱስ ወደ አብ ሄደ ማለት በለበሰው ሥጋ (በሰውነቱ) ውስጥ ሆኖ ይሠራው የነበረውን የተዋረድ ሥራ ጨርሶ፣ አብ ባለው ክብር ያ ሥጋ እንዲከብር አደረገ ማለት ነው። ስለዚህ የኢየሱስ መክበር የሰው ልጅ ተስፋና ትልቅ ክብር ማሳያ ሆነ።
Follow👇
ቃሉ ይናገር- 𝐋𝐞𝐭 𝐓𝐡𝐞 𝐖𝐨𝐫𝐝 𝐒𝐩𝐞𝐚𝐤
Apostolic Generation 󱢏

በትንቢተ ኢሳይያስ (9፥6) ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ «ኃያል አምላክ» ተብሎ መጠራቱ ዝም ብሎ ተራ ገላጭ ስም አይደለም፤ ይልቁንም እርሱ እውነተኛው ኃያል አምላክና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስ...
12/08/2026

በትንቢተ ኢሳይያስ (9፥6) ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ «ኃያል አምላክ» ተብሎ መጠራቱ ዝም ብሎ ተራ ገላጭ ስም አይደለም፤ ይልቁንም እርሱ እውነተኛው ኃያል አምላክና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው።
​ይህንን እውነት መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያረጋግጥልናል፦

​✍️ « » ?

​በነቢዩ ኤርምያስ መጽሐፍ ላይ «ኃያል አምላክ» የተባለው ማን እንደሆነ ተጽፎ እናገኛለን፦
​«ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።» > — ኤርምያስ 32፥18
​ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት « » የተባለው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። በዚህም መሠረት ኢየሱስን « » ስንለው፣ እርሱ እራሱ «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር» መሆኑን እየመሰከርን ነው።

​✍️ታዲያ » ?
​በቀጣይም «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር» ማለት ማን እንደሆነ ደግሞ በትንቢተ ሚልክያስ ላይ ተገልጿል፦

​«እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ #አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር...» > — ሚልክያስ 1፥6

​በዚህ የጽሑፍ ክፍል መሠረት «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር» የተባለው አባት (አብ) እንደሆነ ግልጽ ነው።

​እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አያይዘን ስንመለከታቸው የሚከተለውን እውነት እናገኛለን፦

✍️​መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን «ኃያል አምላክ» ይለዋል።

✍️​«ኃያል አምላክ» ደግሞ «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር» ነው።

✍️​«የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር» ደግሞ «አባት (አብ)» ነው።

​ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስን «ኃያል አምላክ» ሲለው፣ በቀጥታ እርሱ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወይም አብ መሆኑን እየተናገረ ነው።

​ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን «የእግዚአብሔር ልጅ» የተባለው ቃልም ሥጋ በሆነው በሥጋው (በሰውነቱ) በኩል ሲሆን፤ በአምላክነቱ ግን እርሱ እራሱ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር (አብ) ነው። አሜን ስለዚህ ታላቅ ብርሃን እግዚአብሔር ይመስገን 🙌
Apostolic Generation 󱢏

 #ከማን ጋር ነው  #የተጣለነው  ከማን ጋር ነው  #የታረቅነው? የሥላሴ ትምህርት የተወሳሰበው እምነቱ ሲጋለጥ ! ​የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቁ እውነት ነው። ነገር ግን ይህንን እ...
14/07/2026

#ከማን ጋር ነው #የተጣለነው ከማን ጋር ነው #የታረቅነው? የሥላሴ ትምህርት የተወሳሰበው እምነቱ ሲጋለጥ ! ​የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቁ እውነት ነው። ነገር ግን ይህንን እርቅ የሥላሴ ትምህርት ከሚያስተምረው የሦስት አካላት ክፍፍል አንጻር ስንመዝነው፣ እርስ በርሱ የሚጋጭና የማይገጥም ሆኖ እናገኘዋለን።

ጥሉ ሆነ እርቁ ከአብ ጋር ከሆነ፣ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መቼ ተታረቅን?

ጥሉ ከአብ ጋር ነው እርቁም ከአብ ጋር ነው። ቆላስይስ 1:20 : ሮሜ 5:10

​ጥያቄው፦ የሥላሴ አማኞች እንደሚሉት አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በባሕርይ አንድ ቢሆኑም በአካል ሦስት ከሆኑ፣ so ሰው የተጣላውም ሆነ የታረቀውም ከአብ ጋር ብቻ እንደት ሆነ ? መጽሐፍ ሲናገር ሮሜ 5፥10“ላይ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤” ይላል እዚህጋ እግዚአብሔር የተባለው አብ እንደሆነ ግልጽ ነው። ምክንያቱም ልጁ የተባለው ወልድ ስለሆነ ። በዚህም የተነሳ በልጁ ሞት እግዚአብሔር አብ ታረቀን ማለት ነው።

በዚህ መሠረት ጥሉ ከአብ ጋር ከሆነና እርቁም በወልድ ሞት ከአብ ጋር ብቻ የተፈጸመ ከሆነ፣ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ወልድና ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር አልተጣላም ነበር ማለት ነው? ወይስ ከእነሱ ጋር የሚታረቅበት ሌላ ጊዜ አለ?🤔 ይህ ክፍፍል የሥላሴን አስተምህሮ መሠረት የሚያናጋ ነው።

​እግዚአብሔር አንድ ነው ካልን፣ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣላ ከጠቅላላው መለኮት ጋር ነው የተጣላው።
​ነገር ግን "አብ ሌላ አካል፣ ወልድ ሌላ አካል" በሚለው የሥላሴ እምነት መሠረት፣ እርቁ የተፈጸመው ከአብ ጋር ብቻ ከሆነ፣ መለኮትን ሦስት ቦታ መክፈል ስለሚሆን የሥላሴ ትምህርት እዚህ ጋ በራሱ አስተምህሮ ይፈረሳል።

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ምስጢር፦ የሚገለጠው በሥላሴ ፍልስፍና ሳይሆን በሐዋርያው ጳውሎስ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ምስጢሩም ይህ ነው።
​"እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን #ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና..." > — 2ኛ ቆሮንቶስ 5:19 ወይም አብ በወልድ ሆኖ ዓለሙን #ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር...ከራሱ ጋር የሚለው ሐሳብ ይሰመርበት።

በዚህ ክፍል ታራቅውም አስታራቅውም እግዚአብሔር አብ ሆኖ እናገኛለን ማለት ነው። ስለዚህ አንድ አካል እንጂ ሁለት አካል የለም፦ እርቅ የተፈጸመው አብ አምላክ ሌላ በሰማይ ብቻ ሆኖ ወልድን እንደ ሌላ ሁለተኛ አምላክ ወደ ምድር ልኮት ብቻ ሳይሆን እርሱ ራሱ ቃል ሥጋ በሆነው ራሱ አብ በወልድ (በሥጋ) ውስጥ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታርቋል።

​መካከለኛው ራሱ በክርስቶስ የሆነው እግዚአብሔር ነው፦ በአብና በሰው መካከል ሌላ እግዚአብሔር አልገባም። ራሱ እግዚአብሔር አብ በክርስቶስ ማለትም በሚታይ ሰውነት በወልድነቱ መካከለኛ ሆኖ ቀረበ እንጂ። ሌላ አምላክ አይደለም ። 2ቆሮንቶስ 5:19
​📌 ማጠቃለያ
​መለኮትን በአካል ሦስት አድርጎ መክፈል እርቁንና የማዳኑን ሥራ ትርጉም አልባ ያደርገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያስተምረው፣ ጥሉ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ እርቁም የተፈጸመው አብ በወልድ ውስጥ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር በማስታረቁ ነው። ስለዚህ የሥላሴ የሦስትነት አካል ትምህርት ከዚህ የእርቅ እውነት ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጋጭና ስህተት መሆኑ በግልጽ ይጋለጣል። ይደረግ

እግዚአብሔር ይመስገን። አሁንም እግዚአብሔር ይነሳ🙏👉1 ዜና 16፡10፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።   17፤ ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላ...
14/05/2026

እግዚአብሔር ይመስገን። አሁንም እግዚአብሔር ይነሳ🙏
👉1 ዜና 16፡10፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። 17፤ ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፤ 18፤ እንዲህም አለ፡— ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤ 19፤ ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው። 20፤ ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።

📌አሁንም እግዚአብሔር መመንጠር ያለበትን መንጥሮ፣መቆረጥ ያለበትን ቆርጦ፣መገደል ያለበትን ገድሎ፣በደሙ ዋጃትን የተቀደሰ ህዝቡን ከውድቀት ከዘንዶ መንጋጋ ያወጣል።🙏
👉ኢሳይያስ 51:9፤ የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፥ ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን? 10፤ ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅኸው፥ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጠሊቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?

እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም ይባረክ!

እግዚአብሔር ብቻውን መራው ፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። ዘዳ 32፥12 ቃሉ የጸና ነው።እግዚአብሔር ብቸኛ መሆኑን ለሚጠራጠሩ ሰዎች አሁንም አትጠራጠሩ እግዚአብሔር ብቸኛ አምላክ ...
10/05/2026

እግዚአብሔር ብቻውን መራው ፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። ዘዳ 32፥12 ቃሉ የጸና ነው።

እግዚአብሔር ብቸኛ መሆኑን ለሚጠራጠሩ ሰዎች አሁንም አትጠራጠሩ እግዚአብሔር ብቸኛ አምላክ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታ እግዚአብሔር እነ ብቸኛ ነኝ ፡ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም። ብሎ በተለያዩ ቦታ ገልጸዋል።

ያ ብቸኛ አምላክ ነው የመጣው ሌላ ሁለተኛ አካል አይደለም። ኢሳ 59፥15 እግዚአብሔርም አየ፥ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ። ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው። ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፥ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቍር አደረገ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፥ በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ። *

ስለዚ ለሰው ልጅ ኃጥያት ስጋ ለብሶ ወደ ምድር የወረደው ከወረደ ቦኃላ ሞትን አሸንፍ ወደ ሰማይ ያረገው ያ ብቸኛው አምላክ ራሱ ነው።

@የአንድ አምላክ ልጆች

ሰላም ለቅዱሳን በሙሉ! የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በምስራቅ አያት አጥቢያ የህብረት መዘምራን የተዘጋጀውን “ዛሬም ኢየሱስ ሙላቴ” የተሰኘውን የህብረት...
20/04/2026

ሰላም ለቅዱሳን በሙሉ!

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በምስራቅ አያት አጥቢያ የህብረት መዘምራን የተዘጋጀውን “ዛሬም ኢየሱስ ሙላቴ” የተሰኘውን የህብረት ዝማሬ ቁጥር 2 አልበም ሲያቀርብላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።

ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለብዙዎች መታነጽና መጽናናት እየሆነ ያለው የዝማሬ ጸጋ አሁንም በተለያየ አቅጣጫ እያደገና እየሰፋ ስላለ ክብር ይህንን ጸጋ ለሚያፈስሰው የብርሃናት አባት ይሁን!

የዝማሬ አልበሞችን ለማዘጋጀት ብዙ መስዋዕትነትን ይጠይቃልና ይህንን የዝማሬ አልበም በታላቅ ያዘጋጁትና መዘምራንን ጨምሮ በተለያየ መንገድ የተሳተፉትን ሁሉ የቤተክርስቲያን አምላክ ኢየሱስ በማያልቀው በረከት እንዲባርክ ጸሎታችንም ምኞታችንም ነው።

አልበሙ በቅርብ ቀናት ውስጥ በApostolic Songs መተግበሪያ ላይ ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ቅዱሳን ሁሉ ዝማሬዎቹን በተለያዩ የግዢ አማራጮች በማውረድ ጸጋውን፣ ቤተክርስቲያንን እና አገልግሎቱን ትደግፉ ዘንድ በኢየሱስ ፍቅር እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል
ሚያዚያ 2018 ዓ.ም
Apostolic Songs

28/03/2026

#ኢየሱስ ሕይወት ሰላም የሆነልኝ

 113 አድስ ነፍሳት ተጨመሩ በአጠቃላይ 12,409 ሰዎች በሐዋርያት ትምህርት ተጨመሩ።በዓለም አቀፍ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን 35ኛው ዙር ዋራ በቴል ጉባኤ ከ መጋቢት 3-6/2018 ዓ.ም በ...
22/03/2026


113 አድስ ነፍሳት ተጨመሩ በአጠቃላይ 12,409 ሰዎች በሐዋርያት ትምህርት ተጨመሩ።

በዓለም አቀፍ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን 35ኛው ዙር ዋራ በቴል ጉባኤ ከ መጋቢት 3-6/2018 ዓ.ም በታላቅ መንፈሳዊ ጉብኝት ተካሄደ።

በጉባኤ 12,296 አድስ ነፍሳት በሐዋርያት ትምህርት እንደተጨመሩ የተነገረው ስሆን ይህ ሪፖርት የተነገረው በ እሁድ ጉባኤ ከምሳ መልስ ስሆን እስከ ማጠቃለያ ባለው ግዜ 113 ነፍሳት በሐዋርያት ትምህርት የተጨመሩ መሆኑን ስንሰማ እጀግ ደስ ብሎናል።

በአጠቃላይ በ ኮንፈረንሱ 12,409 አድስ ነፍሳት በሐዋርያት ትምህርት ተጨመሩ።
ገና ነው ተአምራቱ
እግዚአብሔር ይመስገን 🙏
ወንድማችሁ ነኝ

የዘማሪ ዶ/ር    መልዕክት! ይነበብ!"ወዳጄና ጋደኛዬ ትሁቱ የእግዚአብሔር ሰው፣ የአሁኑ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ኢሳያስ አሻ አሁን የደረሰበት የሀላፊነት ...
16/03/2026

የዘማሪ ዶ/ር መልዕክት! ይነበብ!

"ወዳጄና ጋደኛዬ ትሁቱ የእግዚአብሔር ሰው፣ የአሁኑ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ኢሳያስ አሻ አሁን የደረሰበት የሀላፊነት ደረጃ የደረሰው ፣ በሄደበተት የቅንነት መንገድና ለእግዚአብሔር በተሰጠ ህይወቱ ነው። ከወንም ኢሳየያስ /ቢሾፕ / ጋር ከ35 ዓመታት በላይ በጣም በቅርበት እንተዋወቃለን፣ በሚገባ አውቀዋለሁ እሱም እንዲሁ ያውቀኛል። በተለይ የበለጠ እንድንቀራረብ እና አዉቀዋለሁ ለማለት ያስቻለኝ ምክንያት፣ የአዲስ አበባ ሰበካ የወጣትች መሪ ሆነን ባገለገልንበት ወቅት አብረን ስናገለግል ብዙ የመቀራረብ በተደጋጋሚ አብሮ የማገልገል አጋጣሚው ሰፊ ነበር።ወንም ኢሳያስ /ቢሾፕ/ ንፁህ ልብ እና በጎ ህሊና ያለው በሳል ሰው፣ ማስመሰል ጨርሶ የማይታይበት፣ ላመነው ብቻ የሚኖር፣ ለመሪዎቹ አክብሮት ያለው፣ ሰዎችን ከልቡ የሚወድ፣ የአገልጋይነትና የመሪነት ፀጋ የተጎናጸፈ፣ የእውቀት ሰው በሁኔታዎች በዝቅታ እና በከፍታ የማይለዋወጥ ባለራእይ ነው።ዛሬ ለደረሰበት የአገልግሎት ደረጃ የሚመጥን ፀጋም ሆነ እውቀት የተጎናጸፈ የእዚአብሔር ባሪያ ነው። ቀደም እንዳሉት አስደናቂ መሪዎች እግዚአብሔር በእሱም ቤተክርስቲያን ወደሚቀጥለው ምእራፍ ያሻግራል።ገና ከጅምሩ በዋራ 12,994 ሰዎች መጠመቃቸው እግዚአብሔር ከሱ ጋር ስለመሆኑ ምልክት ነው። ይህንን ዜና በምድረ አሜሪካ ሆኜ በሶሻል ሚዲያ ስሰማ ስለሰራው ድንቅና ስለዳኑት ነፍሳት እግዚአብሔርን አመስግኜአለሁ።ወዳጄ እና ውዱ ጋደኛዬ ይከናወንልህ።"

Address

Gofa Sefer
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apostolic Generation Christian Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share