26/06/2026
#እንኳን ለ50ኛው የወርቅ ኢዮቤልዩ አደረሳችሁ!
"እስከዚህ ድረስ #እግዚአብሔር ረድቶናል።"
(1 ሳሙኤል 7፥12)
ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አባል ቤተ እምነቶች፣ ለቦርድ አመራሮች፣ ለወዳጆችና አጋሮች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያና በውጭ ሀገራት ለምትገኙ የኅብረቱ ደጋፊዎች በሙሉ፣ #እንኳን ለኅብረታችን 50ኛ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ባለፉት 50 ዓመታት እግዚአብሔር በጸጋው ኅብረታችንን ጠብቆና መርቶ ባርኮታል። ወንጌልን በማስፋፋት፣ ቤተ ክርስቲያንን በማጠናከር እና በአንድነት መንፈስ አብረን በማገልገል ያደረጋችሁትን ውድ አስተዋጽኦ በከፍተኛ አክብሮትና #ምስጋና እናስታውሳለን።
ያለፈውን በምስጋና እያሰብን፣ ወደፊቱንም በተስፋ እየተመለከትን፣ ጌታ በቀጣዮቹ ዘመናት ከዚህ የበለጠ ለክብሩና ለመንግሥቱ መስፋፋት እንዲጠቀምብን ጸሎታችን ነው።
#መልካም 50ኛ የወርቅ ኢዮቤልዩ!
ለእግዚአብሔር ብቻ ክብር ይሁን!
መጋቢ ሰንበቶ ባሼ
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምክትል ፕሬዝደንት
የህብረቱን ማሕበራዊ ሚዲያዎች በመቀላቀል አዳዲስ መረጃዎች ይከታተሉ።
Telegeram ;- https://t.me/ECFEmaterial
Youtube;- https://www.youtube.com/-et
tiktok;- https://www.tiktok.com/
Follow እና Share ስለምታደርጉ እናመሰግናለን።