Bole Medhanealem felegeyordanos Sunday school

Bole Medhanealem felegeyordanos Sunday school Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bole Medhanealem felegeyordanos Sunday school, Religious organisation, Addis Ababa.

How well do you know about the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Faith and Order?Study basic church lessons at Bole Medhanealem Cathedral Felege Yordanos Sunday school every Sundays from 3:30 - 6:30 (local time).Starts on Meskerem 11,2007Registration Place - Sunday school at the secretary's everyday from 3:00 - 1:00 (local time)For more info contact - +251118436638 0911421174 - www.felegeyordanos.org

አምላከ ዮሐንስ ለአመቱ በሰላም ያድርሰን አሜን
07/07/2024

አምላከ ዮሐንስ ለአመቱ በሰላም ያድርሰን አሜን

ከቅዱሳን ክብር ይበልጣል የማርያም ክብርየአብን ቃል ለመቀበል በሚገባ ተገኝታለችበቅድስና በድንግልና አጊጣለችእንኳን ለእናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽህተ ንጹሃን ድንግል ማርያም ክብረ በዓል አደ...
28/06/2024

ከቅዱሳን ክብር ይበልጣል የማርያም ክብር
የአብን ቃል ለመቀበል በሚገባ ተገኝታለች
በቅድስና በድንግልና አጊጣለች

እንኳን ለእናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽህተ ንጹሃን ድንግል ማርያም ክብረ በዓል አደረሳችሁ መልካም በዓል 🤗

 #ጰራቅሊጦስ"በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።...
22/06/2024

#ጰራቅሊጦስ
"በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር" የሐዋ.ሥራ 2፥1

በዓለ ጰራቅሊጦስ በደብራችን በታላቅ ድምቀት የሚከበር በመሆኑ ሁላችሁም በበዓሉ ላይ በመገኘት በረከት ትቋደሱ ዘንድ ተጋብዛችኋል።

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ።

??  ?,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,🔴⏩ሰኔ 12 የገናናው መልዓክ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ...
18/06/2024

?? ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

🔴⏩ሰኔ 12 የገናናው መልዓክ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል ስለምን እናከብራለን ካልን ደግሞ ቅድስት አፎምያ ያዳነበት ዕለት ስለሆነ ነው።

❗ታሪኩ እንዲህ ነው :- 👇👇👇

🔵⏩ ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ እርሷም በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ደገኛ ሴት ናት፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡

🔴👉 ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደ ደረሰባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡

🔷👉 ባሏም ታሞ ሞቶ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን መነኮሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡ እርሷም "ከቤትገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ" አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም "እኛማ በነግህ ጸልየናል?" አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን."... እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ" አላት፡፡

🔷➡ ቅድስት አፎምያም "አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ አትጸልዩ ያልከኝ ጌታ ምጽዋት አበድር እመስዋዕት ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? እርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?" ብላ ሞገተችው፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡

🔴👉 ከላይ እንዳየነው ..በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡

🔵👉 ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

🔷👉 በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡

🔴👉 ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሳሰሉትን እየጠቀሰ ለማሳመን ቢሞክርም ቅድስት አፎምያ ቅዱስ ሚካኤል ከሆንክ በትረ መስቀልህ የታለ ብላ ባሏ ያሳለላት የቅዱስ ሚካኤል ስእል ቤቷ ነበረና ቅዱስ ሚካኤል ከሆንክ ይህ ያንተ ስእል ነውና ተሳለመው አለችው እሱም ተናዶ ዘሎ አነቃት ያንጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት ወርዶ በበትረ መስቀሉ ቀጥቅጦ በጦሩ ወግቶ ሠይጣንን ድል ነስቶ አፎምያን ከእደ ሰይጣን አድኗታል።

።።።። ።።።።
።።።። ።።።።።
።።።። ።።።።።

የዕርገት በዓል የሚከበርባቸውን ፲፩ድ  ገዳማትና አድባራት እንጠቁምዎ፡፡ #ሰኔ ፮ ፤  ፡፡   #፯  ፡፡(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ ጨምሩበት፡፡) /     /፩.  ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደ...
12/06/2024

የዕርገት በዓል የሚከበርባቸውን ፲፩ድ ገዳማትና አድባራት እንጠቁምዎ፡፡
#ሰኔ ፮ ፤ ፡፡
#፯ ፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ ጨምሩበት፡፡)
/ /
፩. ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ/ን፤
አድራሻው፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ልደታ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → ሜክሲኮ → ጦር ኃይሎች፤

፪. ፈረንሳይ ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም ቤ/ክ (እናትና ልጇ)፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን፥ 41 ኢየሱስ፤
ታክሲ፤ ከ4ኪሎ (6 ኪሊ) → 41 ኢየሱስ/ፈረንሳይ/

፫. ገዳመ ኢየሱስ ቤ/ክ
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፤
ታክሲ፤ ከመርካቶ → ኮልፌ፡፡
ወይም ከጦር ኃይሎች ዊንጌት/አስኮ/ → (በሚል ታክሲ) (በቀለበት መንገድ)

፬. አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኀኔዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ጋራው መድኀኔዓለም፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) (ለገሀር) (መገናኛ) (ቦሌ) → አቃቂ/ቃሊቲ

፭. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ መካኒሳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → መካኒሳ

፮. ጃቲ መካነ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ 08፥ ጃቲ፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከቦሌ) → ቃሊቲ → ጃቲ (አቃቂ በሚለው ታክሲ)፡፡

፯. የካ ኮተቤ ደብረ ምሕረት ኪዳነ ምሕረትና መድኀኔዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ኮተቤ ወረዳ 9፡፡

፰. ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት፤
ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ → አስኮ/ዊንጌት/፤

፱. ጀሞ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (ሜክሲኮ) → ጀሞ፡፡

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

ከአዲስ አበባ ውጪ የሚከበርባቸው፤
፩. መንዝ ዕመጓ ደብረ ቆጵሮስ ቅዱስ ኡር(ራ)ኤል ገዳም፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ መንዝ ሞላሌ፥ ዕመጓ፡፡
ታክሲ፤ ከላምበረት መናኸርያ→ መንዝ ሞላሌ →ዕመጓ፡፡

፪. አምቦ ኢየሱስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አምቦ ከተማ፡፡
ታክሲ፤ ከአስኮ መናኸርያ→ አምቦ፡፡

/ /
/ /

 #መዝገበ ቅዳሴ ነገ ይመረቃልታዋቂው የቅዳሴ መምህርና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት በአስተዳዳሪነት እየሰሩ ያሉ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት አባ ጥዑመ ልሳን ኪዳነ ማርያም  ከዚህ...
08/06/2024

#መዝገበ ቅዳሴ ነገ ይመረቃል
ታዋቂው የቅዳሴ መምህርና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት በአስተዳዳሪነት እየሰሩ ያሉ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት አባ ጥዑመ ልሳን ኪዳነ ማርያም ከዚህ በፊት ያሳተሙትን ባለ ምልክቱ መዝገበ ቅዳሴ በድጋሚ አሻሽለው አሳትመውታል።
ይህ መጽሐፍ እሑድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ,ም ከቀኑ 6:00 በቦሌ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመምሪያ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ቤተሰቦች በሚገኙበት ይመረቃል ስለዚህ በዚህ የአባታችን መጽሐፍ ምረቃ ላይ ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር እንድትገኙ ተጋብዛችኋል የመምህራችንና የአባታችን ጥሪ አክብረን ምረቃው ላይ እንገናኝ ። ሰላም ያገናኘን አሜን !!!

 #ይህ ምስጢር ታላቅ ነውናቲ እና ማሂ ስርአተ ጋብቻቸውን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በገኙበት ተፈፅሟል።
02/06/2024

#ይህ ምስጢር ታላቅ ነው
ናቲ እና ማሂ ስርአተ ጋብቻቸውን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በገኙበት ተፈፅሟል።

"እግዚአብሔር እውነት ነው"የሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴ የፋይናስ እና የቃለዓዋዲ ምረመራ ውጤትየቦሌ መድኃኔዓለም ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
20/11/2023

"እግዚአብሔር እውነት ነው"
የሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴ የፋይናስ እና የቃለዓዋዲ ምረመራ ውጤት
የቦሌ መድኃኔዓለም ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰበር ዜና በትግራይ የሚገኙ "ጳጳሳት" ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም የሕገ ወጥ ሢመት "የአስኬማ ጸሎት" ...
22/07/2023

ሰበር ዜና
በትግራይ የሚገኙ "ጳጳሳት" ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም የሕገ ወጥ ሢመት "የአስኬማ ጸሎት" እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ !

ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ ፣ በብፁዕ አቡነ መርሐክርስቶስ ፣ በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ እና በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሚመራው እና በቅዱስ ፍሬምናጦስ ስም የሚነግደው ሕገ ወጥ ቡድን በዛሬው ዕለት በድፍረት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ መረጥኳቸው ላላቸው መነኮሳት "የአስኬማ ጸሎት እያካሄደ እንደሚገኝ የትግራይ ቲቪ ካሰራጨው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

የ"አስኬማ ጸሎት" በሚል እያከናወኑት በሚገኘው ሥርዓት ላይ መንግስታዊው የትግራይ ቲቪ የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን እየሰጠው የሚገኝ ሲሆን በቡድኑ መሪ በብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ አማካይነት እና በሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ተባባሪነት ሕገ ወጥ ሢመቱ እየተከናወነ መሆኑ ታይቷል።

በትግራይ የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ፖለቲከኞች እንኳ ምርጫቸው ያደረጉት የሰላም እና የይቅርታ መንገድ በመርገጥ ፍቅረ ሢመት ያደረባቸው መነኮሳትን በመሰብሰብ የጨረቃ ሢመት ለማድረግ እያደረጉት ያለው ጥድፍያ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መከፋፈል ምን አልባትም ከቀድሞ ጀምሮ ሲያልሙት የነበረውን "የሀገረ ትግራይ" ምሥረታ ለማካሄድ በቅድሚያ የያዙት የፖለቲከኞች ሀሳብ መሆኑን ምሁራን ይናገራሉ።





ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/tewahedo_media

ኤጲስ ቆጶሳት ስያሜና የተመደቡባቸው አህጉረ ስብከት1. አባ ክንፈገብርኤል ተ/ማርያም ብፁዕ አቡነ  ገሪማ፦- ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀ/ስብከት2. አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ  ገብርኤል፡...
16/07/2023

ኤጲስ ቆጶሳት ስያሜና የተመደቡባቸው አህጉረ ስብከት

1. አባ ክንፈገብርኤል ተ/ማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ፦- ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀ/ስብከት

2. አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት

3. አባ ስብሐት ለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት

4. ኣባ ኣምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፡- ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት

5. አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት

6. አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፡- ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

7. አባ ዘተ/ሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፡- ሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት

8. አባ አስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፡- ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት

9. አባ ወ/ገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
(EOTC)

የፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ት/ቤት ህፃናት ክፍል          "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ"አመታዊ የፀሎት መርሃ ግብር ፎቶዋች ህፃናት በአዕምሮ በስለው በስነ ምግባር ታንፀው  እንዲያ...
12/07/2023

የፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ት/ቤት ህፃናት ክፍል
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ"
አመታዊ የፀሎት መርሃ ግብር ፎቶዋች ህፃናት በአዕምሮ በስለው በስነ ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ ወደ ሰ/ት/ቤት ይላኩ ለክረምቱ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርት ተዘጋጅቷል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Medhanealem felegeyordanos Sunday school posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share