Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia

Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia The Ethiopian Catholic Church (ECC), is the presence of the Universal Catholic Church in Ethiopia

11/09/2026
11/09/2026

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለ2019 አዲሱ ዓመት የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈች
*************

የቀድሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ብጹዕነታቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ አዲሱ ዓመት የተጣሉ የሚታረቁበትና ይቅር የሚባባሉበት፣ ፍጹም ሰላምና ፍቅር የሚሰፍንበት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የዕርቅና የምሕረት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ፣ ሕዝቡ ላለፉት መልካም ነገሮች ሁሉ አምላክን እንዲያመሰግን፣ ጥፋቶችና ኃጢአቶች ደግሞ በትሕትና ይቅርታንና ምሕረትን እንዲለምን ጥሪ አቅርበዋል።

የሰው ልጅ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ዕድገትና እውቀት ለሰብዓዊ ክብርና ለፍትሕ ማሰፈኛ ሊጠቀምበት እንደሚገባም በማሳሰብ፣ የሰውን ልጅ ክብርና ሰብዓዊነት የሚረግጡ መሣሪያዎችንና ተግባራትን ማከናወን ስህተት መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ ሕመምተኞችን፣ የታሰሩትንና በጭንቀት ውስጥ ያሉትን ወገኖች በማሰብና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል።

በሰናይት ሰይፉ

11/09/2026

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2018 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቀድሞ ሊቀጳጳሳትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለ2019 አዲሱ ዓመት በዓል የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በመልዕክታቸው አዲሱ ዓመት ለወደፊት እንዲሻሻሉ ለምንፈልጋቸው ነገሮች የእግዚአብሄርን ፀጋ የምንጠይቅበት ነው ብለዋል።

እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ዘመን የመቅረፅ ኃላፊነት አለበት ነው ያሉት።

አዲሱን ዓመት በእርቅ፣ተባብሮ በመስራት እና ችግረኞችን በመርዳት ማሳለፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

11/09/2026

The Apostolic Nuncio in Ethiopia has urged the newly installed Archbishop of the Catholic Archdiocese of Addis Ababa to emulate the leadership of Christ as he begins his pastoral ministry.

In his Sunday, September 6 homily during the installation of Archbishop Tesfaye Tadesse Gebresilasie, Archbishop Brian Ngozi Udaigwe encouraged the new Archbishop to embrace a style of leadership rooted in love, unity and service as he shepherds the people of God.

The Nuncio reminded the Ethiopian Church leader that Jesus “gave an example of how to guide and govern the people.”

In a Monday, September 7 report following the installation, Archbishop Udaigwe, who also represents the Holy Father in Somalia and Djibouti, further called on the faithful and members of the Clergy to work closely with Archbishop Tesfaye and support him in his new pastoral responsibility.

He expressed gratitude to members of the Congregation of the Comboni Missionaries of the Heart of Jesus (MCCJ) for offering Archbishop Tesfaye to the church.

Pope Leo XIV appointed Archbishop Tesfaye Metropolitan Archbishop of Addis Ababa on 12 June 2026. He had previously been serving as Titular Bishop Cleopatris since February 2025.

Archbishop Tesfaye succeeds 77-year-old Berhaneyesus Demerew Cardinal Souraphiel, who has been serving the Catholic Archdiocese of Addis Ababa for about 27 years.

The new Archbishop’s September 6 installation took place during a solemn Eucharistic celebration lasting more than four hours and was held under the theme, “Looking back with gratitude, walking forward with hope.”

Archbishop Tesfaye was born in Harar, eastern Ethiopia, and made his perpetual profession with the MCCJ in 1994 before being ordained a Priest in 1995.

He holds a Licentiate in Theology from the Pontifical Gregorian University and a Diploma in Islamic Studies from the Pontifical Institute of Arabic and Islamic Studies in Rome. He also pursued Islamic studies at the Dar Comboni for Arabic Studies in Cairo, Egypt, and attended a formation course at the Pontifical Salesian University in Rome.

More: https://www.aciafrica.org/news/24007/apostolic-nuncio-in-ethiopia-urges-newly-installed-archbishop-to-lead-with-love-and-unity

11/09/2026
11/09/2026

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለ2019 አዲሱ ዓመት የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈች
++++++++++++++++

- የዘመን መለወጫ በዓልን ስናከብር ምእመናን በችግረኞች መካከል በመገኘት፣ በክርስቲያናዊ ስነምግባር አቅም የሌላቸውን በመደገፍና የችግራቸው ተጋሪ በመሆን ማክበር እንደሚገባ የቀድሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ አሳሰቡ።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት፤ አዲሱን ዓመት ስንቀበል የሰላምና የዕርቅ ዘመን እንዲሆን፣ የሰው ልጅ ሕይወት ትርጉም የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር በማሰብ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

አሁን ያለው ዘመን የማኅበራዊ ግንኙነት መድረኮች በስፋት የሚንቀሳቀሱበትና በርካታ ድምፆች የሚሰሙበት መሆኑን ያነሱት ብፁዕነታቸው፤ ኅብረተሰቡ መልካሙንና ጠቃሚውን ድምፅ ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆን ይኖርበታል። ጎጂና አፍራሽ የሆኑ መልዕክቶችን ለማስወገድና ለመሸሽ ማመንታት እንደማይገባው አሳስበዋል።

ቤተክርስቲያን የቴክኖሎጂ ዕድገትን እንደማትቃወም የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ፤ ነገር ግን ሰው በዚህች ምድር ላይ ልዩ ጥሪ፣ ኃላፊነትና ክብር ያለው ፍጡር በመሆኑ፣ ይህንን ሰብዓዊ ክብር የሚጋፋ ወይም የሚያጠፋ መሣሪያ መሥራትና መተግበር ስህተት መሆኑን አመልክተዋል። በመሆኑም የሰው ልጅ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ዕድገትና መሣሪያዎች ለሰብዓዊ ክብርና ለፍትሕ ማስፈኛ ብቻ ሊጠቀምባቸው እንደሚገባ መክረዋል።

አዲሱ ዓመት ሰላም የሚሰፍንበት፣ ሀገሪቱ ከእርስ በርስ ግጭት ወጥታ ዜጎች በሙሉ ተረጋግተው የሚኖሩባት፣ የእውቀት ጮራ ለሁሉም የሚደርስበት፣ ስደትና መፈናቀል የሚያበቃበት ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በመስከረም ሰይፉ

#2019ዓም #ኢትዮጵያ

10/09/2026

የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የቀድሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳትና የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት

የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የቀድሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዜዳንት የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከ...
10/09/2026

የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የቀድሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዜዳንት የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
"ጌታን አመስግኑ ቸር ነውና" (መዝ 136፤1)

በክርስቶስ የተወደዳችሁ ብፁዓን ጳጳሳት

ክቡራን ካህናት

ገዳማውያንና ገዳማውያት

መላው ምዕመናንና ምዕመናት

እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ከአገራችሁ ውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውናና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃድ ያላችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ



እንኳን ለ2019 ዓመተ ምህረት የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ! እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር እነሆ ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገረን፤ አዲስ ዓመት መጣልን፤ ክብርና ምስጋና ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! ዳዊት በመዝሙሩ 136፤26 እንደሚለን የሰማይን አምላክ ልናመሰግን ያስፈልጋል።

ያለፈውን ስናስብ የምናመሰግንባቸው ወቅቶች እነሆ ብዙ ናቸው፡፡ በመሆኑም በግልም ሆነ በጋራ በቤተሰብም ውስጥ ሆነ በማኅበረሰብ ለተከናወኑ ቁም ነገሮች ምስጋናን እናቅርብ፡፡

ማመስገን አመስጋኙን ያሳድገዋል፡፡ ማመስገን ትሕትናን ገልጾ በረከትን ያመጣል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 4፤7 "ሁሉንም ከአምላክ ተቀብለህ ለምን ምንም እንዳልተቀበልክ ትሆናለህ?" የሚል ያቀርባል፡፡ በእርግጥም ምስጋናና ውዳሴን መርሳት በ2018 ዓ/ም ውስጥ የተቀበልነውንና የተደረገልንን ችላ ማለት ነው፡፡ ራሳችንን ስንመረምር ንሰሐ የምንገባባቸውም ጊዜያት አያሌ ናቸው፡፡ ከአምላካችንም ጋር ሆነ ከወንድም እህቶቻችን ጋር ግንኙነታችን እንዴት ነበረ? ባልንጀራችንንም እንደ ራሳችን ያልወደድንበት ወቅቶች ብዙ አልነበሩምን? እግዚአብሔርን በፍፁም ልባችን፤ በፍፁም ኃይላችን፤ በፍፁም ነፍሳችን ያልወደድንባቸው ወቅቶችስ አልነበሩምን? ይህንንስ ትዕዛዝ ሁልጊዜ ፈጽሜያለሁ በማለት ደፍሮ መናገር የሚችልስ ማነው?

ይህንን ለማለት እንደማንችል ማስተዋል ከፈለግን የቅዱሳንና የጻድቃንን ንግግር መስማት ይበቃናል፡፡ ቅዱሳንና ጻድቃን ትላልቅ ኃጢአተኞች እንደሆኑ በድፍረት ይናገራሉ፡፡ ምክንያቱም ምናልባት ለብዙዎቻችን የማይታየው ይታያቸዋልና ነው፡፡ በጣም ንፁህ በሆነ ቤት ውስጥ ብጣሽ ወረቀት ወይንም ትንሽ ቆሻሻ እንደሚታየው ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን እና ጻድቃን አዘውትረው "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ካሉ እኛም የበለጠ "ጌታ ሆይ ማረኝ ! ጌታ ሆይ ማረን!" ልንል ይገባናል፡፡

​በብሉይ ኪዳን ነቢያት ዘወትር የእግዚአብሔርን ምህረት ለሕዝባቸው ይለምናሉ፡፡ እኛም ላለፈው ኃጢያቶቻችን ምህረትን ልንለምን ይገባናል፡፡ በፍፁም አልተሳሳትኩም የሚባል ስህተት የለምና፡፡ ኃጢአትን መካድ በራሱ ኃጢአት ነውና። በሉቃስ ወንጌል ምዕ.18፣9-14 ላይ እንደምናነበው ጽድቅን አግኝቶ የተመለሰውን ቀራጭ ማስታወስ እጅጉን ይጠቅማል፡፡ ምክንያቱም በትህትናውና ምህረትን በመለመኑ ጽድቅን አግኝቶ ሲመለስ በአንጻሩ እራሱን እንደመልካም ሰው ብቻ እየቆጠረ የተመጻደቀው ፈሪሳዊ ከበረከት ሸሸ፡፡

አዲሱን ዓመት ስንቀበል ለወደፊት እንዲሻሻሉ ወይንም እንዲለወጡ የእግዚአብሔርን ፀጋ የምንጠይቅበት ወቅት ነው፡፡ የሰላምና የዕርቅ ዘመን እንዲሆንልን፤ የእግዚአብሔር ምሕረትና ፍቅር እንዲገዛንና የአምላክን ፀጋ በመምረጥ ሕይወታችን ትርጉም የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲመጣልን ተስፋ በማድረግ አዲሱን ዓመት እንጀምረው፡፡

​ ዘመናችን የማኅበራዊ ግንኙነት ዘመን ነው፡፡ ብዙ ድምፆችን እንሰማለን፡፡ ነገር ግን የሚሻለውንና የሚያስፈልገውን የምንለይበትን ፀጋ ከእግዚአብሔር መቀበልን አንዘንጋ፡፡ መልካሙን ለማስተናገድ ፈቃደኛ እንሁን፡፡ ነገር ግን ጎጂውንና አፍራሹን ለመሸሽ አናመንታ፡፡ እግዚአብሔር የሚወደውን የሰው ልጅን ክብር የሚያስጠብቀውን ለመቀበል አንፍራ፡፡ በአንጸሩ ፈጣሪ የሚወደውን፣ ከፈሪሃ እግዚአብሔር የራቀውን ጥበብ የሌለበትን ከመሸሽ ወደ ኋላ አንበል፡፡

​ከዚሁ ጋር በተያያዘ ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በቅርብ ጊዜ ለዓለም ሁሉ ስለ ሰው ልጅ ክብር በተጻፈው የቤተክርስቲያን ሐዋሪያዊ መልዕክታቸው የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡፡ "በታላቅነቱ ሁሉ በእግዚአብሔር የተፈጠረው የሰው ልጅ ዛሬ ወሳኝ በሆነ ምርጫ ላይ ይገኛል፤ አዲስ የባቢሎን ግንብ መገንባት ወይም እግዚአብሔርና የሰው ልጅ አብረው የሚኖሩባትን ከተማ መገንባት"፡፡

​የመልዕክቱ ፍሬ ሐሳብ የሰው ልጅ የደረሰበትን ቴክኖሎጂና አስተውሎት መሰል መሳሪያ ለሰው ልጅ ክብርና ለፍትህ እንዲጠቀምበት ይጋብዛል፡፡ በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ እራሱ በሰራው መሣሪያ ሰውን ዝቅ ካደረገ ፈጣሪንም ከደፈረ የባቢሎን ግንብ ታሪክ ተደገመ ማለት ነው፡፡ የዚያን ዘመን ሰዎች በትምክህታቸው ረጣሪን ለመቆጣጠር ፈለጉ፡፡ እርሱ ድረስ የሚደርስ ግንብ የሠሩ መስላቸው፡፡

ነገር ግን በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 11 እንደምናስተውለው ሰዎች እንኳን እግዚአብሔር ላይ ሊደርሱ፣ ይልቁንም እግዚአብሔር እነርሱን ለማግኘት እንደወረደ እናነባለን፡፡ በእነርሱ አመለካከት ወደ ከፍተኛ ስፍራ ደርሰዋል ነገር ግን ቅዠት ነበር፡፡

ታዲያ የሰው ልጅ የሚከብረው በእግዚአብሔር የተሰጠውን መልክ በፍቅር ሲጠብቅ መሆኑን ከረሳና ይህንን መልክ ወደ ባርነት የሚወስድ መንገድ ከተከተለ ዕጣ ፈንታው የባቢሎን ግንብ ሰዎችን ዓይነት ሲሆን ነው ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ግልጽ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ ቤተክርስቲያን ቴክኖሎጂን አትቃወምም፡፡ ሆኖም ቤተክርስቲያን አደራ የምትለው ግን ሰው በዚች ምድር ላይ ልዩ ጥሪ፤ ልዩ ሃላፊነት፤ ልዩ ክብር አለውና ይህንን የሚረሳ ወይንም የሚያጠፋ መሣሪያ መሥራት ስህተት ነው የሚል ነው፡፡

​እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ዘመን የመቅረፅ እንዲሁም ታሪክ የእያንዳንዱ ሰው ክብር የሚጠበቅበት፤ ፍትህ የሚሰፍንበትና የሚስፋፋበት፤ ወንድማማችነትና እህትማማችነት በግልጽ የሚታይበት ስፍራ እንዲሆን የመምራት ሃላፊነት መውረስ አለበት፡፡ ሆኖም እያንዳንዱ ዘመን ሰብዓዊነት የጎደለውና የበለጠ ፍትህ የሌለው ዓለም የመፍጠር አደጋ ተደቅኖበታል፡፡ የሰው ልጅ እውነተኛ ማንነቱን የማበላሸት አደጋ በሚረጋገጥበት ጊዜ ሁሉ እና ክርስቲያኖች የሰው ልጅ ሚስጥር እውነት ሆኖ የሚገለፀው በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት መሆኑን በማወቅ ኣይኖቻችንን ወደ እርሱ እናንሣለን፡፡ እውነትና ሕይወት በሆነው በክርስቶስ እያንዳንዳችን ወደ ሙላት እናድጋለን፡፡

​በመጨረሻም ሁላችንም በዚህ አዲስ ዓመት እውነተኛ ሰላምን እግዚአብሔር እንዲሰጠን እንፈልጋለን፡፡ ከእርስ በርስ ጦርነት ወጥተን፣ ሁሉም ጠግቦ የሚኖርበት የእውቀት ጮራ ለሁሉም የሚደርስበት፣ ስደትና መፈናቀል የሚያበቃበት፤ የተጣሉ እንዲታረቁ፤ ያልተማሩ እንዲማሩ፤ በበጎ ፈቃድ ተባብሮ በመጣር በአገራችን የተስተካከለና ፍፁም የሆነ ሰላም እንዲሰጠን በሙሉ ልባችን እንፀልይ እንመኝ፡፡

ይህን የዘመን መለወጫ በዓል ስናከብር በችግረኞች መካከል በመገኘትና ችግራቸውን በማቃለል የችግራቸው ተሳታፊዎች በመሆን ክርስቲያናዊ ተግባራችንን እንፈጽም፡፡

​አዲሱ ዓመት ለታመሙት ምህረትን፤ ላዘኑት መጽናናትን፤ ለታሰሩት መፈታትን፤ በጭንቀት በችግርና በመከራ ውስጥ የሚገኙትን ወገኖችንንን እግዚአብሔር ሰላሙንና ፍቅሩን ፀጋውን የሚሰጣቸው የምህረት ዓመት ያድርግልን፡፡

​ልዑል እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት ይባርክልን፣ ይቀድስልን፣ ሰላሙን ያውርድልን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን በጥበብ እንድንመራ ያድርገን፡፡


በድጋሚ ሁላችሁንም እንኳን ለ2019 ዓ/ም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

እግዚአብሔር አዲሱን ዘመናችንን ይባርክልን

የ2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ግጻዌ ከዚህ መልዕክት ጋር በተያያዘው መስፈንጠሪያ በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ድረገጽ ማግኘት እንደሚችሉ እንገልጻለን።
07/09/2026

የ2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ግጻዌ ከዚህ መልዕክት ጋር በተያያዘው መስፈንጠሪያ በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ድረገጽ ማግኘት እንደሚችሉ እንገልጻለን።

Each year, the Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia – Liturgical Commission prepares the annual liturgical calendar for both the Ge’ez and Latin Rites. This calendar outlines the daily celebrations, liturgical colors, World Days observed during the year, Scripture readings, and public holi...

Address

Wawel Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share