Pastor Amanuel Nigussie

Pastor Amanuel Nigussie "created in Christ Jesus unto good works, which God hath before ordained that we should walk in them."

 የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያንእሁድ ማለዳ“ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ።”(...
04/06/2025


የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
እሁድ ማለዳ
“ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ።”
(ዘፍጥረት 35፥3)

• እግዚአብሔር አምላክ በመከራ ቀን ሰምቶናል
• ስለዚህም ከእኛ ጋር ነበረ አብሮንም አለ
• መከራችንን ሁሉ አስረስቶናል ያስረሳናል
“ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረሳኝ፤”
(ዘፍጥረት 41፥51)
• ዋጋ በከፈልንበት ስፍራ ባርኮናል ያበዛናልም።

የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ቱሉ ዲምቱ

አንዳንድ ነገሮች ከቃላት በላይ ናቸው።😭😭😭😭"ምን ይባላል?" ተብሎ "ዝም" ነው።በዝምታ ውስጥምእንኳንእግዚአብሔር አዋቂ ነውደግሞ መልካም ብቻ ነው።😭😭😭😭😭ቸር እግዚአብሔር ለመላው ቤተሰብ እ...
02/06/2025

አንዳንድ ነገሮች ከቃላት በላይ ናቸው።
😭😭😭😭
"ምን ይባላል?" ተብሎ
"ዝም" ነው።
በዝምታ ውስጥም
እንኳን
እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ደግሞ መልካም ብቻ ነው።
😭😭😭😭😭

ቸር እግዚአብሔር ለመላው ቤተሰብ እና ወዳጆች መፅናናትን ይስጥ።

 • እሁድ• በክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያንእርሱ ሲመጣ የደከምንበት ውጤት ይመጣል።“እርሱም፦ መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው...
27/05/2025


• እሁድ
• በክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
እርሱ ሲመጣ የደከምንበት ውጤት ይመጣል።

“እርሱም፦ መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።”
(ዮሐንስ 21፥6)

በህይወት መንገድ በመውጣት እና መግባት ብዙ ድካም ያስተናገዳችሁ
መረብ ከዓሳው ጋር አልገናኝ ብሏችሁ ወደ ዳር ለመውጣት ጥቂት ሜትር ቀርቶአችሁ ላላችሁ ሁሉ በድካማችሁ በዚያው ቦታ
ተስፋ ቆርጣችሁ መረባችሁን እየሰበሰባችሁ ባላችሁበት በዚያው ሰዓት ሁሉን ቻይ ጌታ ይምጣላችሁ።
ልትቆሙ በቃጣችሁበት ቦታ ቀጥሉ
ደከሙ በተባላችሁበት ቦታ ብርታታችሁ ይሰማ
የለም ካላችሁበት ቦታ አግኙ
ለሀዘን የታቀደው በደስታ ይለወጥላችሁ
መረባችሁ አሳ ጥፍራችሁ መብል ይያዝላችሁ

አቅመቢስነት ከብርታት
አለመቻል ከኤልሻዳዩ ጋር ይገናኝላችሁ።
እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይምጣላችሁ።

ዘውትር እሁድ
በክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ቱሉ ዲምቱ

 #አትሳቱ“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ...
20/05/2025

#አትሳቱ

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥
መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።”
(ያዕ 1፡16)

• ስለ ምን? አትሳቱ
1. ስለ አባት እግዚአብሔር

- እርሱ የብርሃናት አባት ነው።
- በእርሱ ዘንድ መለዋወጥ የለም።
- በመዞርም የሚሆን ጥላ በእርሱ ዘንድ የለም።

2. ሰለ ስጦታ እና በረከት ምንጭ

የበጎ ስጦታና የፍጹም በረከት ምንጩ አባት እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
በጎ ስጦታ የስጦታ ተቀባዩን ልብ የሚያሳርፍ ፍጹምም በረከት
የሰጪውን ማንነት የሚገልጥ ነው፡፡
ዘመን የማይሽረው የማያረጅ የማይሰለች
እንከን የሌለበት (
ከተቀባዩ ፍላጎት ጋር በእርግጥ የሚታጣም
የፍጹም በረከት መገኛው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡

3. በአባት እግዚአብሔር ፊት ስላላችሁ ማንነት አትሳቱ።

“ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።”
• በገዛ ፈቃዱ
• ለፍጥረቱ በኩራት እንድንሆን
• በእውነት ቃል ወልዶናል፡፡
ስለዚህ አትሳቱ ፍጹም በረከት በጎ ስጦታ ሁሉ ከላይ ናቸው፡፡

የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
አዱስ አበባ ; ኢትዮጵያ

 ፡፡እሁድ ማልዳበክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያንፓ/ር አማኑኤል“እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?፤ መንገዱን ማን አዘዘለት? ...
12/05/2025

፡፡
እሁድ ማልዳ
በክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
ፓ/ር አማኑኤል
“እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤
እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?፤ መንገዱን ማን አዘዘለት?
ወይስ። ኃጢአትን ሠርተሃል የሚለው ማን ነው?
ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ።
ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል፤ ሰውም ከሩቅ ያየዋል።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም።
የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።”
(ኢዮ. 36: 22)
እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው
1. አይሳሳትም
2. ይራራል
3. ያስተምራል

በህይወታችን በሚገጥሙን አስቸጋሪ ፈተናዎች እግዚአብሔር አምላክ ቅን ፈራጅ ነው
አይሳሳትም መማለጃ አይቀበልም አይታለልም
“ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል” (ኢሳ 11፡4) ፃድቅ አምላክ ነው፡፡
ደግሞም እግዚአብሔር አምላክ ለልጆቹ የሚራራ የርህራሄ አምላክ ነው፡፡ እስከመጨረሻ አያስጨንቅም እንደ መከራ ብዛት ነፍሳችንን በማጽናናት ደስ ያሰኛል በናይን ከተማ ለዚያች መበለት ጌታ እንደራራ ቃሬዛውን ነክቶ የሞተውን በህይወት እንደሰጣት እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሀዘናችሁ ይራራል፡፡
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤”(መዝ 103፡11)
ኤሊሁም እንዳለው
“እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?”
ከመከራችን ውስጥ ትምህርት ከምናልፍበት መንገድ ለሌሎች መማሪያ የሚሆን ጠቃሚ ነገር ማውጣት የሚችል እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ፈታኝ ነው ያለውን የህይወት ጎዳና አልሻገረውም ያልነውን ያንን ሰባራ ድልድይ እየገጠመ የህይወት ጥያቄ ስንክሳሩን ሁሉ ጉቶ እና ደንቃራ አሳልፎ አሻግሮን ሲያበቃ ለእኛ አስተምሮ ህይወታችንን ማስተማሪያ አድርጎ እኛን አስተማሪ የሚያደርገን እግዚአብሔር ይባረክ፡፡

የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
ቱሉ ዲምቱ አዲስ አበባ

 “......እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ” (ዕብ. 12፡2)በክ...
28/04/2025


“......እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥
በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ”
(ዕብ. 12፡2)
በክርስትና ህይወት መንገድ ሩጫን ለመጨረስ አስቸጋሪ የሚሆነው እና ትዕግስትን የሚፈትነው የመንገዱ ርዝመት ሳይሆን በመንገድ ላይ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች እንቆቅልሾች እና ታማኝ ወዳጅ ማጣት የመሳሰሉ ደግሞ ለአይን የሚያምሩ ሩጫን የሚያዘገዩ የገዛ ምኞቶቻችን ናቸው፡፡
በተለይም የዕብራውያን ፀሐፊ
“.....የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን.....” ይለናል፡፡
ልናያቸው የሚገባ የእምነት ጽናትና መልካም የሆነ የህይወት ምልልስ ያላቸው የእምነት አባቶች እንደ ደመና በዙሪያችን ቢኖሩም ሩጫችንን በትዕግስት ሮጠን ለመጨረስ አይናችን ሊያርፍበት የሚገባ የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ የሆነው
ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
ወይንም ደግሞ ምኞቶቻቸውን ተከትለው ለመሄድ ሲሉ መንገዳችሁን አኗኗራችሁን እና ትምህርታችሁን ለገዛ ሀሳባቸው እንዲመች አድርገው የሚያጣምሙ ሰዎች በበዙበት በዚህ ዘመን ከሩጫችሁ ስራቸውን ዓመፃቸው እንዳያስቆማችሁ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ሩጫችሁን በትዕግስት ልትሮጡ ትችሉ ዘንድ አይናችሁን ከክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ማንሳት አይገባቸሁም፡፡
ምኞታቸውን የሚከተሉ ሰዎች እግዚአብሔር ከሰጣቸው ኃላፊነት እና ቦታ በቀላሉ ይነቀላሉ፡፡ የልብ ሀዘን እና ጉዳትን ጥለውላችሁ ይሄዳሉ።
ዴማሰ ለዚህ ጠንካራ ምሳሌ ነው፡፡
“ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤” (2ኛ ጢሞ. 4፡10)
ዴማስ የሄደው ይሄንን ዓለም ወዶ ነው፡፡
እግዚአብሔር በረዳን መጠን በዚህ በምንኖርበት ዘመን በስፍራችን በመሆን በትግስትና በጽናት ክርስቶስን ብቻ እየተመለከትን ሩጫችንን ልንፈፀም ይገባል፡፡
ከሩጫችን የሚያስተጓጎሉን ጥያቄዎች ቢኖሩብን እንኳን ለእግዚአብሔር ፣ ለእግዚአብሔር ቤትና እግዚአብሔር ለሰጠን ስራ ደግሞም የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር ለሚተጉ ዋኖቻችን ታማኞች ልንሆን ይገባናል፡፡
“ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።”
(ሉቃስ 12፥37)
አማኑኤል ንጉሴ (ፓ/ር)
የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ ; ኢትዮጵያ

“ጲላጦስ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም፦ ይሰቀል አሉ።”( ማቴዎስ 27፥22 )የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያንአዲስ አበባ ; ኢትዮጵያ
21/04/2025

“ጲላጦስ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም፦ ይሰቀል አሉ።”
( ማቴዎስ 27፥22 )

የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ ; ኢትዮጵያ

19/04/2025
 ፋሲካችን ክርስቶስ ተነስቶአል!‭"ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤"(መዝሙር 103:2)ልዩ የክርስቶስ ኢየሱስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓልበክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስ...
18/04/2025


ፋሲካችን ክርስቶስ ተነስቶአል!
‭"ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤
ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤"
(መዝሙር 103:2)
ልዩ የክርስቶስ ኢየሱስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል
በክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
እሁድ ማለዳ ከ፫ ሠዓት ጀምሮ
ውለታ ያለበት ሁሉ
ለእግዚአብሔር ለአምላካችን ምስጋና እናቀርባለን ።

አድራሻ
ከቱሉ ዲምቱ አለም ባንክ መንገድ ከንግድ ባንክ አጠገብ ባለው ህንፃ ስር ያገኙናል
+251956880303/0966109910

 ? ?“እርሱም አለ፦ በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።”(ዘፍጥረት 3፥10)የኔ ትውልድመልካሙን ሽሽቶ ክፋውን ይኖራልከፍቅር ተደብቆ በጥላቻ ይኖራልመሆንን ት...
14/04/2025

?
?
“እርሱም አለ፦ በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።”
(ዘፍጥረት 3፥10)
የኔ ትውልድ
መልካሙን ሽሽቶ ክፋውን ይኖራል
ከፍቅር ተደብቆ በጥላቻ ይኖራል
መሆንን ትቶ መባልን ይሸሻል ።
ጥርሱ እየሳቀ ውስጡ ይሸነግላል ።
በሰው ግለት ይበርዳል
በወዳጁ ውድቀት ለራሱ ስኬትን ያልማል ።
በሌሎች ስብራት ራሱን ይጠግናል 🤔
የኔ ትውልድ
አይነኬ ነው። አጥፍቶ ይይበቃል
ይቅርታን ይሸሻል ቦታ ይቀይራል
ከመኖር ነፃነት ወጥቶ
ፍቅር የሆነውን የእግዚአብሔርን ህግና ነፃነት ቸል ብሎ ትቶ
ሲጋለጥ ሲዋረድ ይጋለጣል ጫካ ገብቶ ።
መርጦ ይወዳል ቶሎ ይጠላል ።
እሱ ይከበር እንጂ ማንንም አያከብርም
ቃሉን ያጥፋል
እምነቱን ይክዳል
የኔ ትውልድ
ያለልክ ይወዳል ያለ ገደብ ይጠላል።

“ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም።”
(መዝሙር 34፥14)

የክርስቶስ ምሳሌዎች ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ, ኢትዮጲያ

Address

Addis Ababa
000

Telephone

+251915683568

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Pastor Amanuel Nigussie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Pastor Amanuel Nigussie:

Share