ውዳሴ ማርያም

ውዳሴ ማርያም ሰይጣን እንኳን አንተን ለመጣል ዓቅም ካለው፥ እግዚአብሔር አንተን ለማንሣት'ማ እንዴት?

12/07/2024
እንኳን አደረሳቹ
11/07/2024

እንኳን አደረሳቹ

01/11/2013 ዓመተ ምሕረትከ
06/08/2021

01/11/2013 ዓመተ ምሕረትከ

22+07+2012 ዓመተ ምሕረትከበአምላኩ አማላጅነቱን ኑና ተማጸኑት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልአክ ነው። አሁንም ይህ ዓለም በአማላጅነቱ አምኖ...
31/03/2020

22+07+2012 ዓመተ ምሕረትከ
በአምላኩ አማላጅነቱን ኑና ተማጸኑት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልአክ ነው። አሁንም ይህ ዓለም በአማላጅነቱ አምኖ ጸበሉን ቢጠጣ ከክፉ በሽታ እንደሚፈወሱ ቃለ ኪዳን ተሰጥቶታል፣ ኢትዮጵያዊውን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ዑራኤል አምላክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቶሳውያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆች ከመከራ ሥጋ ፤ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን።

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜንየካቲት ዘጠኝ ሰማዕቱ ቅዱስ ጳውሎስ ሶሪያዊ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ከሃድያን ይዘው ምላሱን በመቁረጥ፣ በእሳት በማቃጠል፣ የብረት...
17/02/2020

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት ዘጠኝ ሰማዕቱ ቅዱስ ጳውሎስ ሶሪያዊ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ከሃድያን ይዘው ምላሱን በመቁረጥ፣ በእሳት በማቃጠል፣ የብረት ችንካሮችን በእሳት አግለው በአፉና በጆሮዎቹ የቸነከሩበትና በመጨረሻውም አንገቱን የሰየፉት ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡
+ በሶርያ አገር ላሉ መነኮሳት ሁሉ አባት የሆነ ታላቁ አባ በርሱማ ዐረፈ፡፡ እርሱም እንደ ኢያሱ ፀሐይን ገዝቶ ያቆመ፣ ዝናብንም በጸሎቱ ያዘነበ ነው፡፡ ንስጥሮስን ካወገዙትና ሃይማኖታችንን ከጠበቁልን አባቶች አንዱ ሲሆን ከሃድያን በክፋታቸው አሠቃይተውታል፡፡ በድንጋይም ወግረው ሊገድሉት ቢሉ የወረወሩት ድንጋይ ወደ ራሳቸው ወደ ወርዋሪዎቹ የሚመለስ ሆነ፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ጳውሎስ ዘሶርያ፡- ወላጆቹ በሶርያና በእስክንድርያ የሚኖሩ ሀብታም ነጋዴዎች ነበሩ፡፡ እነርሱም በጣም ብዙ ገንዘብ ትተውለት ሞቱ፡፡ በወቅቱ ከሃዲያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቶስ ያመኑትን ሁሉ እያሠቃዩ እንሚገድሏቸው በሰማ ጊዜ ተነሥቶ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት መንገዱን ይመራው ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለየ፡፡
ጌታችንም መልአኩ ቅዱስ ሱርያልን ላከለትና ስለ ስሙ የሚደርስበትን ጽኑ መከራና ሥቃይ በመጨረሻም የክብር አክሊልን እንደሚቀዳጅ ነገረው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወዲያው ተነሥቶ ወደ እንዴና ከተማ ሄዶ በከሃዲው መኰንን ፊት ስለ ጌታችን ክብር መሰከረ፡፡ መኰንኑም ይዞ ራቁቱን አሠቃቂ ግፍርፋትን ካስገረፈው በኋላ በእሳት እንዲያቃጥሉት አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም ቅዱሱን በእሳት ለበለቡት፡፡ በሌላም ጊዜ መኰንኑ ቅዱስ ጳውሎስን ከእሥር ቤት አውጥቶ ለጣዖቱ እንዲሠዋ በማባበል ብዙ ገንዘብ አመጣለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ወላጆቼ ሲሞቱ ያወረሱኝን ብዙ የወርቅ ወቄት ሽጨ ለድኆች መጽውቼ በጌታዬ ስም የታመንኩ ሰው እንዴት ወደተናቀ ያንተ ገንዘብ እመለሳለሁ›› በማለት የረከሱ ጣዖታቱንም ጨምሮ ረገመበት፡፡ መኰንኑም በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ የብረት ችንካሮች በእሳት አግሎ በአፉና በጆሮዎቹ ቸነከረበት፡፡ አሁንም መልአኩ ቅዱስ ሱርያል መጥቶ ከሕማሙ ሁሉ ፈወሰው፡፡ ዳግመኛም መኮንኑ መርዛማ እባቦችን በላዩ ሰደዱበት ነገር ግን እባቦቹ አልነኩትም፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ እየመሰከረና በሚያደርጋቸው ተአምራትም ብዙዎችን ስላሳመነ እንዳይናገር ብለው ምላሱን ቆረጡት፤ ነገር ግን ጌታችን አዳነው፡፡ በመጨረሻም መኰንኑ ከእንዴና ወደ እስክንድርያ ወስዶት በዚያ ብዙ ካሠቃየው በኋላ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም አስቀድሞ መልአኩ ቅዱስ ሱርያል እንደነገረው ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ የክብር አክልን ተቀዳጀ፡፡ ዕረፍቱም የካቲት 9 ሆነ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ተገለጠው ታዩ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
አባ በርሱማ፡- የዚኽም ወላጆቹ ሳሚሳጥ ከሚባል አገር የተገኙ ናቸው፡፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ የሚኖር አንድ ደገኛ ጻድቅ አባ በርሱማ ከመወለዱ አስቀድሞ ስለ እርሱ ለአባቱ ትንቢት ነገረው፡፡ ‹‹የትሩፋቱ ዜና በሶርያ አገር ሁሉ የሚሰማ ጣዕም ያለው ፍሬ ከአንተ ይወጣል›› በማለት የሚሆነውን ሁሉ አስረዳው፡፡
አባ በርሱማ በተወለደ ጊዜ እግዚአብሔርን ወደማወቅ ሲመጣ ከወላጆቹ ሸሽቶ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ደርሶ በዚያ ስሙ አብርሃም ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጠ፡፡ እርሱም ወላጆቹን ስለፈራ ከዚያ ገዳም ሰደደውና አባ በርሱማ ሄዶ በአንድ ዓለት ውስጥ ገብቶ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ ከትሩፋት ተጋድሎውም ብዛት የተነሣ ዜናው በሶርያ አገር ሁሉ ተሰማ፡፡ ብዙ ደቀመዛሙርትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፡፡ ነገር ግን በዚያ ቦታ ላይ ያለው ውኃ እጅግ መራራ ነበር፡፡ አባ በርሱማም ደቀ መዛሙርቱ በተሰበሰቡ ጊዜ በውኃው ላይ ጸልዮ እጅግ መራራ የነበረውን ውኃ ለውጦ ግሩም ጣዕም ያለው አደረገው፡፡ እግዚአብሔር ሌሎች ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በአባ በርሱማ እጅ አደረገ፡፡ በአንዲትም ዕለት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከበዓቱ ርቆ ሳለ የፀሐይ መግቢያ ሰዓት ደረሰ፡፡ አባ በርሱማም ወደ ጌታችን በጸለየ ጊዜ ወደ በዓቱ እስኪደርስ ድረስ ፀሐይ ቆመችለት፡፡
በሌላም ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- ረዓም የምትባል አገር ነበረች፡፡ ሰዎቿም ከሃዲዎች ናቸው፡፡ በላያቸውም ዝናብ የተከለከለ ሆነ፡፡ በተጨነቁም ጊዜ ወደ አባ በርሱማ መጥተው ለመኑት፡፡ እርሱም ስለ ክህደታቸው ገሠጻቸውና ‹‹በእግዚአብሔር ብታምኑ ዝናብን ያዘንብላችኋል›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አሁን በአንተ ጸሎት ዝናብ ካዘነበልን እናምንበታለን›› አሉት፡፡ አባ በርሱማም ወደ ጌታችን በጸለየ ጊዜ ለእነዚያ ሰዎች ወዲያ ዘነበላቸው፡፡ እነርሱም በጌታችን አመኑ፡፡ እንዲዚሁም ሰዎቿ ከሃድያን የሆኑ ሌላ አገረ ነበረች፡፡ አባ በርሱማ ወደ እነዚህ ሰዎች ሄዶ በቃሉ ትምህርትና በተአምራቱ እግዚአብሔርን ወደማወቅ መለሳቸው፡፡ የጣዖቶቻቸውንም ቤቶች አፈረሰ፡፡
አባ በርሱማ የጸሎት ቦታ አዘጋጅቶ በዚያ ሳይቀመጥ 54 ዓመት ቆሞ በተጋድሎ ኖረ፡፡ በደከመውም ጊዜ ግደግዳ ተደግፎ ያንቀላፋል እንጂ አልተቀመጠም፡፡ በየሰባት ቀኑም ይጾማል፡፡ የከበረ አባ ስምዖን ዘዓምድ የዚህን የአባ በርሱማን ዜና ሰምቶ ሊያየውና ሊባረክ ስለወደደ መልእክተኛ ላከበት፡፡ ይኸውም እጅግ የከበሩ አባ ስምዖን ዘዓምድ ሰውነታቸውን እጅግ ከመጉዳታቸው የተነሣ ሊጎበኟቸው የሚመጡት ቅዱሳን የሞቱ ይመስላቸው ነበር፡፡ የክርስቶስን መታሰርና መቸንከር አስበው ሰውነታቸውን በቀጭን ገመድ አጠላልፈው በጣም በኃይል አጥብቀው ስላሰሩት ገመዱ የሰውነታቸውን ሥጋ እየቆራረጠ ይጥለው ነበር ከቁስሉም የሚወጣው ደምና መግልም እየሸተተ ቢያስቸግራቸው መነኮሳቱ ሳይቀሩ ይገፏቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ስምዖን ቁመቱ ስልሳ ክንድ የሆነ የድንጋይ ምሰሶ ላይ ወጥተው በዚያ ሆነው ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረጉ፣ ሕሙማንን እየፈወሱ፣ ወንጌልን ሳይቀመጡ ቆመው እያስተማሩ 12 ዓመት የኖሩ ናቸው፡፡ አባ ስምዖን አባ መርሱማን ለማየትና በረከትን ለመቀበል ሽተው መልዕክተኛ ሲልኩባቸው አባ በርሱማ ሄደና አገኛቸው፡፡ እርስ በእርሳቸውም በረከትን ከተቀባበሉ በኋላ አባ በርሱማ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡
ከዚህም በኋላ አባ በርሱማ በሶርያ አገር እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰበከ፡፡ በፊታቸውም ብዙ ተአምራትን እያደረገና እያስተማረ ብዙዎችን አሳመናቸው፡፡ ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ (ታናሹ) ዘንድ በመሄድም በቀናች ሃይማኖት ጸንቶ እንዲኖርና ፈሪሃ እግዚአብሔርን አስተማረው፡፡ ንጉሡም ብዙ ወርቅ ቢሰጠው አባ በርሱማ ግን አልወስደም አለ፡፡ ከዚህም በኋላ በአንጾኪያም አገር ላይ በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ሥልጣን እንዲኖረው ንጉሡ ጻፈለት፡፡ ለዚህም ምልክት ቀለበቱን ሰጠው፡፡ በከሃዲው ንስጥሮስ ምክንያት 200 የከበሩ ቅዱሳን ሊቃውንት በኤፌሶን በተሰበሰቡ ጊዜ ይህም ቅዱስ አባ በርሱማ ከእነርሱ አንዱ ነው፡፡ ከሌሎቹም ቅዱሳን ሊቃውንት ጋር ሆኖ ንስጥሮስን አወገዘው፡፡ ዳግመኛም ንጉሡ በአንጾኪያ አገር ያሉ መኳንንት፣ መሣፍንትና ሹማምንት ሁሉ ለአባ በርሱማ እንዲታዘዙለት ደብዳቤ ጻፈ፡፡ አባ በርሱማም በበጎ ሥራ ሁሉ እንደበረቱ በሃይማኖትም እንዲጸኑ የሚያዝ ደብዳቤ በመጻፍ በንጉሡ ቀለበት እያተመ ለሀገሮች ሁሉ ይልክ ጀመር፡፡ በዚህም ጊዜ ክፉዎች ሰዎች አባ በርሱማን ጠሉት፡፡ ወደ ንጉሡም ዘንድ ገብተው ‹‹አባ በርሱማ እንደ ዓለም ሰው ሆኖ ይበላል ይጠጣል፣ መልካም ልብስንም ይለብሳል›› ብለው ነገር ሰሩበት፡፡ ንጉሡም ይህንን ያረጋግጥ ዘንድ ከጭፍሮቹ አንዱን በድብቅ ይከታትል ዘንድ ወደ አባ በርሱማ ላከው፡፡ ያም የተላከው አባ በርሱማን ከቀድሞው የተነየ ሆኖ ስላላገኘው ሄዶ ለንጉሡ ነገረው፡፡ ንጉሡም አባ በርሱማን ወደ እርሱ አስመጥቶ ባየው ጊዜ በሁሉም ነገር እንደቀድሞው ሆኖ ቢያገኘው ዳግመኛም ታላቅ ክብርን አከበረውና ወደቦታው መለሰው፡፡
መናፍቁ ንጉሥ መርቅያን የኬልቄዶንን ጉባኤ በሰበሰበ ጊዜ የንጉሡ አማካሪዎች አባ በርሱማን እንዳያስመጣ ንጉሡን መከሩት፡፡ ምክንያቱም ጉባኤያቸው የሐሰትና የክህደት ስለሆነ አባ በርሱማም ንጉሡን ሳያፈራና ሳያፍር ለሰው ፊትም ሳያደላ ተከራክሮ ረቶ እንደሚያሳፍራቸው ስለሚያውቁ ነው፡፡ እነርሱም የክብርን ባለቤት አንዱን ክርስቶስ ኢየሱስን ወደ ሁለት የከፋፈሉበት ይህ ጉባኤያቸው በተፈጸመ ጊዜ የከበረ አባ በርሱማ ተጣላቸው፡፡ በመንቀፍና ቃላቸውንም በመሻር አወገዛቸው፡፡ እነርሱም ወንጅለው በጽሑፍ አደርገው ወደ ንጉሡ ከሰሱት፡፡ ንጉሡም አባ በርሱማን ወደ እርሱ አስመጣው ነገር ግን በላዩ ያደረ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ስላለ ሊቃወመው አልቻለም፡፡ በዚህም ጊዜ አባ በርሱማ በሊቁ በቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ ስላደረገችው የክፋት ሥራና ግፍ ንግሥቲቱን ረገማት፡፡ እርሷም ጥቂት ጊዜ ቆይታ በክፉ አሟሟት ሞተች፡፡
ከዚህም በኋላ መናፍቃኑ አባ በርሱማን የሚቃወመት ሆኑ፡፡ ምእመናን ሁሉ እንዳይታዘዙለት በአገሮች ሁሉ ጽፈው ላኩ፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ አልተቀበላቸውም ነበር፡፡ ዳግመኛም አባ በርሱማን በጎዳና ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ 200 መናፍቃን ሰዎች ከመናፍቃን ኤጲስቆጶሳት ጋር ተስማሙ፡፡ በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ ጠየቁትና አብረው ሲጓዙ በመንገድ ላይ ሳሉ ሁሉም ትላልቅ ድንጋዮችን አንስተው በአባ በርሱማ ላይ ጣሉ ነገር ግን ድንጋዮቹ በተአምራት ወደራሳቸው ወደ ወርዋሪዎቹ እየተመለሱ ብዙዎቹን አቆሰሉ፡፡ በዚህም ጊዜ በፍርሃት ከእርሱ ሸሹ፡፡
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር አባ በርሱማን ከዚህ ዓለም ሊወስደው በወደደ ጊዜ መልአኩን ወደ እርሱ ልኮ ከ4 ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም እንደሚያርፍ ነገረው፡፡ በዚህም ጊዜ አባ በርሱማ በዙሪያው ወዳሉ አገሮች ሁሉ ምእመናንን ያጽናና መልእክትም ያደርስ ዘንድ ረድኡን ላከው፡፡ ረደኡም ሲዞር የከበረች የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ወደምትኖርበት ቦታ ደረሰና እጅ ነሣት፡፡ እርሱም በዚያ ስለ ከሃዲው ንጉሥ መርቅያን እያለቀሰ ሲለምን ከመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ‹‹አባ በርሱማ ወደ እግዚአብሔር ስለከሰሰው ያ ከሃዲ መርቅያን ሙቷልና አትፍራ›› የሚል ቃል ወጣ፡፡ ረድኡም ይህን ሲሰማ እጅግ ደስ ብሎት መልእክቱን አድሶ ምእመናንን አጽናንቶ ወደ አባቱ ዘንድ ተመለሰ፡፡ አባ በርሱማም ረድኡን ባረከውና በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ከበዓቱም ደጃፍ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተልክሎ ታየ፡፡ ምእመናንም ሁሉ ይህንን ከሩቅ አይተው ወደ እርሱ መጡ፡፡ እርሱንም ዐርፎ አገኙትና ከሥጋው ተባረኩ፡፡ ከእነርሱም ስለመለየቱ እጅግ አዘኑ፡፡
የአባ በርሱማ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!

ጾመ ሰብአ ነነዌ ፣ የነነዌ ሰዎች ጾምጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለ...
10/02/2020

ጾመ ሰብአ ነነዌ ፣ የነነዌ ሰዎች ጾም

ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም (፳፻፲፪ ዓ.ም) የካቲት ፪ ቀን ትጀመራለች፡፡

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌን፤ የነነዌ ሰዎችን ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው /ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡ በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡

ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡

ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡

ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡

ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡

ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡ ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡
ምንጭ፡- ማቅ ድህረ ገጽ

ዛሬ፡የካቲት27፡ቀን እንኳን፡ለኢትዮጵያዊው፡ጻድቅ፡ታላቁን፡ገዳም፡ማኅበረ፡ሥላሴ፡ለመሰረቱና፡እንደ፡መሶበ፡ወርቅ፡ከፍ፡አድርገው፡ላስባረኩ፤ንጉሥ፡ሱሱንዮስ፡የካቶሊክን፡እምነት፡በተቀበለ፡ጊዜ፡ምላሱ፡ተጎ...
06/03/2019

ዛሬ፡የካቲት27፡ቀን እንኳን፡ለኢትዮጵያዊው፡ጻድቅ፡ታላቁን፡ገዳም፡ማኅበረ፡ሥላሴ፡ለመሰረቱና፡እንደ፡መሶበ፡ወርቅ፡ከፍ፡አድርገው፡ላስባረኩ፤ንጉሥ፡ሱሱንዮስ፡የካቶሊክን፡እምነት፡በተቀበለ፡ጊዜ፡ምላሱ፡ተጎልጉሎ፡የነበርው፡በመስቀላቸው፡ባርከው፡ለፈወሱት፡ለታላቁ፡አባት፡ለአቡነ፡ዓምደ፡ሥላሴ፡ለዕረፍት፡በዓልና፡በታላቁ፡በቈስጠንጢኖስ፡ዘመን፡ለነበረ፡ለከበረ፡አባት፡ለአንጾኪያ፡አገር፡ሊቀ፡ጳጳሳት፡ትምህርቱ፡በዓለም፡ለመላ፡ቁጥሩ፡ከሠለስቱ፡ምዕት፡ለሆነ፡ለታላቁ፡አባት፡ለአንስጣስዮስ፡ለዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡ከሚታሰበው፦ከመድኃኔዓለም፡ከስቅለቱ፡መታሰቢያ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
+ አቡነ፡ዓምደ፡ሥላሴ(ጎጃም)፦የትውልድ፡አገራቸው፡ጎጃም፡ሲሆን፡በአጣ(ዐፄ)ሱስንዮስ፡ዘመን፡የነበሩ፡ድንቅ፡ድንቅ፡ተአምራትን፡ያደርጉ፡የነበሩ፡ገዳማዊ፡መነኵሴ፡ናቸው፡፡ጻድቁ፡ማኅበረ፡ሥላሴን፡ያቀኑ፡ታላቅ፡አባት፡ሲሆኑ፡በተለይም፡አንድ፡የሚታወቁበት፡ትልቅ፡ታሪክ፡አላቸው፡፡እርሱም፡አጣ(ዐፄ)ሱስንዮስ፡ካቶሊካውያን፡ደግፈው፡8ሺህ፡የአገራችንን፡ሊቃውንት፡በአንድ፡ቀን፡ባሳረዱ፡ጊዜ፡ንጉሡ፡ወዲያው"ኦርቶዶክስ፡ይርከስ፡ካቶሊክ፡ይንገስ"ብሎ፡ያወጀበት፡ምላሱ፡ተጎልጉሎ፡ወጣ፡፡ እንደ፡አርዮስም፡ሆዱ፡አብጦ፡አንጀቱ፡ተልቶ፡ሊሞት፡ባለ፡ሰዓት፡አቡነ፡ዓምደ፡ሥላሴ፡አዘዞ፡ድረስ፡ሄደው "ፋሲል፡ይንገሥ፡ኦርቶዶክስ፡ሃይማኖት፡ትመለስ፡የሱስንዮስም፡ምላስ፡ይመለስ"በማለት፡ተጎልጉሎ፡የወጣውን፡ምላሱን፡በመስቀላቸው፡ቢባርኩት፡ምላሱ፡ተመልሶለታል፡፡
+ አጣ(ዐፄ)ሱስንዮስ፡ግን፡ለካደበት፡ክህደት፡ቅጣቱ፡ነውና፡በመቅሰፍቱ፡ሳይድን፡በዚያው፡ታሞ፡ማቆ፡ማቆ፡ክፉ፡አሟሟት፡ሞቷል፡፡ከዚህ፡በኋላ፡አቡነ፡ዓምደ፡ሥላሴ፡የአጣ(ዐፄ)ፋሲልን፡ሹመትና፡ሃይማኖትን፡በአዋጅ፡አጽንተው፡ተመልሰው፡ወደ፡ገዳማቸው፡ማኅበረ፡ሥላሴ፡ገዳም፡ገብተዋል፡፡አጣ(ዐፄ)ፋሲልንም፡የማኅበረ፡ሥላሴን፡ገዳም፡ግዛቱን፡ከሱዳን፡እስከ፡ጣቁሳ፡ድረስ፡እንዲሆን፡በአዋጅ፡ወስነው፡ሰጥተውት፡ነበር፡ነገር፡ግን፡ላይጠቀምበትና፡ላይጸና፡ነገር፡የደርግ፡መንግሥት፡የገዳሙን፡ሥርዓት፡ከማፍረሱም፡በላይ፡ርስት፡ጉልቱን፡ነጥቆ፡ወሰደበት፡፡
+ በደርቡሾች፡ወረራ፡ጊዜ፡እንግሊዞች፡አጋጣሚውን፡ተጠቅመው፡የአቡነ፡ዓምደ፡ሥላሴን፡ቅዱስ፡ገድል፡ዘርፈው፡ወስደውታል፡፡ዛሬ፡በእንግሊዝ፡አገር፡ገድለ፡አቡነ፡ዓምደ፡ሥላሴ፡ይገኛል፡፡ጻድቁ፡የካቲት27፡ቀን፡ያረፉ፡ሲሆን፡ዐፅማቸው፡በዚያው፡በመሠረቱት፡በማኅበረ፡ሥላሴ፡ገዳም፡በክብር፡ተቀምጧል፡፡
ከአቡነ፡ዓምደ፡ሥላሴ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። በጸሎታቸው፡ይማረን!።ምንጭ፡መዝገበ፡ቅዱሳን።
+ + +
+ አባ፡አንስጣስዮስ፦ይህንንም፡ቅዱስ፡የከበሩ፡አባቶቻችም፡በኒቅያ፡ከተማ፡የአንድነት፡ስብሰባ፡በአደረጉ፡ጊዜ፡በዚህ፡ጉባኤ፡ከተሰበሰቡ፡ሊቃውንት፡አንዱ፡እርሱ፡ነው፡፡በዚህም፡ጉባኤ፡ተስማምተው፡አርዮስን፡ከባልንጀሮቹም፡የቂሣርያ፡አውሳብዮስ፡የኒቆምድያ፡አውሳብዮስና፡አርናሲስ፡ናቸው።እሊህም፡በአብያተ፡ክርስቲያናት፡ሁሉ፡ታውቀዋል፡እሊህም፡የከበሩ፡አባቶችም፡ሥርዓትን፡ሠርተው፡ወደ፡የአገራቸው፡በተመለሱ፡ጊዜ፡እሊህ፡ከኤጲስቆጶስነት፡ሹመት፡የተሻሩት፡ከሃድያኑ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡የሚሄዱ፡መስለው፡ወጡ፡ወደ፡አንጾኪያም፡ከተማ፡በአንዲት፡አመንዝራ፡ሴት፡ዘንድ፡ተሰበሰቡ፡፡ብዙ፡ገንዘብም፡ሊሰጧት፡ቃል፡ገቡላት፡ ወደ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡እንድትገባ፡ይህ፡አባት፡ከእርሷ፡ጋር፡እንዳመነዘረ፡የወለደችውም፡ልጅ፡የእርሱ፡እንደሆነ፡በዚህ፡ቅዱስ፡አባት፡አንስጣስዮስ፡ላይ፡ለካህናቱና፡ለሕዝቡ፡እንድትናገር፡አስተማሩዋት።ሕዝቡም፡እንዲህ፡አሏት"አንቺ፡ሐሰተኛ፡ነሽ፡በዚህ፡ቅዱስ፡አባት፡ላይም፡ሐሰት፡ተናግረሻል፣በከበረ፡ወንጌል፡ካልማልሽ፡በቀር፡ቃልሽን፡አንቀበልም"አሏት፡፡እርሷም፡ስለገንዘብ፡ፍቅር፡በሐሰት፡ማለች፡፡
+ ከዚህም፡በኋላ፡ከሀድያኑ፡ለንጉሥ፡ነግረው፡ ከመንበረ፡ሢመቱ፡ወደ፡አጥራክያ፡ደሴት፡አሳደዱት፡በስደትም፡ሳለ፡በርሷ፡የካቲት27፡ዐረፈ፡፡ነገር፡ግን፡ለእሊህ፡ከሃድያን፡ወዮላቸው፡የእግዚአብሔርን፡ልጅ፡ከመለኮቱ፡ባሕርይ፡ለይተው"ፍጡር፡ነው"ብለውታልና፡ይህንንም፡ንጹሕ፡አባት፡ሰይጣን፡አባታቸው፡እንዳስተማራቸው፡ከአመንዝራ፡ጋር፡አንድ፡ሁነው፡በተንኰል፡ከመንበረ፡ሢመቱ፡አውጥተውታልና።እግዚአብሔር፡ግን፡ቸለል፡አላለም፡ይህን፡አባት፡ከአሳደዱት፡በኋላ፡ያች፡አመንዝራ፡ሴት፡ጭንቅ፡በሆነ፡ደዌ፡ተይዛ፡ብዙ፡ተሠቃየች፡ለሞትም፡ተቃረበች፡ያን፡ጊዜም፡ይህ፡ሁሉ፡መከራ፡የደረሰባት፡በከበረ፡ወንጌል፡በሐሰት፡ስለማለች፡እንደሆነ፡ተገነዘበች፡፡በአንጾኪያም፡ሰዎች፡ሁሉ፡ፊት፡በደሏን፡አመነች፡፡እንዲህም፡አለቻቸው"ይህ፡ቅዱስ፡አንስጣስዮስ፡ከዝሙት፡ንጹሕ፡ነው፣እነዚያ፡ከሀድያን፡ብዙ፡ገንዘብ፡ሰጥተውኝ፡በእርሱ፡ላይ፡ሐሰት፡እንድድናገር፡በከበረ፡ወንጌልም፡በሐሰት፡እንድምል፡አደረጉኝ፡እንጂ"፡፡
+ የአንጾኪያ፡አገር፡ሰዎችም፡ኃጢአቷን፡ማመኗን፡በሰሙ፡ጊዜ፡እጅግ፡አዘኑ፡፡ካህናቱም፡በጸሎትና፡በቅዳሴ፡ጊዜ፡ስሙን፡የሚያነሱ፡ሆኑ፡፡ቅዱስ፡ዮሐንስ፡አፈወርቅም፡አመሰገነው፡በመታሰቢያውም፡ቀን፡ስለእርሱ፡ብዙ፡ቃላትን ደረሰ፡፡ለእግዚአብሔር፡ምስጋና፡ይሁን፡እኛንም፡በዚህ፡አባት፡ጸሎት፡ይማረን፡በረከትም፡ከእኛ፡ጋር፡ትኑር፡ለዘላለሙ፡አሜን።ምንጭ፥የካቲት27፡ስንክሳር።
+ "ሰላም፡እብል፡አንስጣስዮስሃ፡ፍጹመ።ትምህርታቲሁ፡ዘመልዐ፡ኲሎ፡ዓለም።እኩያን፡ዕደው፡እለ፡ተዓጽፋ፡መርገመ።ነገረ፡ሐሰት፡ላዕሌሁ፡እንዘ፡ይነቡ፡ሕሱመ።ኀበ፡ሰደድዎ፡አዕረፈ፡ወኖመ"።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የየካቲት27።
+ የዕለቱ፡ምስባክ፦"እግዚአብሔርሰ፡ንጉሥ፡ውእቱ፡እምቅድመ፡ዓለም።ወገብረ፡መድኃኒት፡በማእከለ፡ምድር።አንተ፡አጽናዕካ፡ለባሕር፡በኃይልከ"።መዝ73፥12-13።የሚነበበው፡ወንጌል፡ዮሐ19፥16-25።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡አፈወርቅ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡የጾም፡ጊዜና፡በዓል።ለሁላችንም፡ይሁንልን

Address

Addis Ababa

Telephone

+251946593998

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ውዳሴ ማርያም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ውዳሴ ማርያም:

Share