የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት እና ሥርዓት
The Ethiopian Orthodox Tewahido Church Faith and Order

ይህ የፌስቡክ ገጽ በእግዚያብሄር እርዳታና በድንግል ማርያም አማላጅነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ክርስቲያኖችን አንድነት ለመጠበቅ ይሰራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የቤተክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና እንዲጠበቅም የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ገጽ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች፤ ፎቶዎች፤ ቪዲዮዎች እና ማንኛውም ዶክመንት የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት፤ ዶግማ፤ ቀኖናና ትውፊት የሚጠብቅ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በመለስ በተለያዩ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሃሳቦች በጨዋነት መንፈስ ሊንሸራሸሩ ይችላሉ፡፡ ይህ ገጽ ክርስቲያናዊ በመሆኑ የሚወጡት አስተያየቶችም ሆኑ ጽሁፎች በክርስቲያናዊ ስነምግባር ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም የሚወጡት ጽሁፎችና አስተያየቶች ማንንም ሰው የማይሳደቡ፤ የማይዘልፉ፤ የማያንቋሸሹ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በአክብሮትና መግባባት እንዲሁም ሌላውን የሚያንጹ መሆን ይገባቸዋል፡፡
ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ሐዋርያት ሰማዕታትና ቅዱሳን አበው በብዙ ተጋድሎና ድካም እስካሁን ያቆይዋትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ቀጣይነት የሚያረጋግጠው በየዘመኑ የሚነሳው ትውልድ እምነቱንና ሥርዓቱን ተረካቢ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው:: ቤተ ክርስቲያን ስንል ክርስትያኖች ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኙበት የተመረጡት ክርስትያኖች ቤታቸውን ለጾሎት ቤት አድርገው የሚጠቀሙበት ቤት አንደሆነ በሐዋርያት ሥራ ም.፭፮ ቁ.፯ የተገለጸ አና በሐዋርይት ሥራ ም.፳ ቁ.፪፰ መሰርረት ክርስቶስ በደሙ የገዛቸው የክርስቶስ አካሉ የሆነች ቤተክርስቲያን መስራት አና መገልገል አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን የተገነዘበችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ አሀጉራት አብያተ ቤተ ክርስቲያን እያነፀች ተከታዮቿን ስትጥብቅ የቆየችዉ።

በመሆኑም የእኛ በሆነው ገጽ ኦርቶዶክሳዊ በሆነ ጠባይ እንሳተፍ፤ እንማማር፤ እንወያይ፤ የቤተክርስቲያናችንን አንድነት፤ ዶግማ፤ ቀኖናና ትውፊት እንጠብቅ! አንድነታችንን እናጠናክር!
ይትባረክ እግዚያብሄር አምላከ አበዊነ!

Address

Arat Kilo
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 20:00 - 08:00
Tuesday 20:00 - 08:00
Wednesday 20:00 - 08:00
Thursday 20:00 - 08:00
Friday 20:00 - 08:00
Saturday 20:00 - 08:00
Sunday 20:00 - 08:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share