ነህምያ የአገልግሎት ሕብረት-Nehemiah Christian Service Ministry

ነህምያ የአገልግሎት ሕብረት-Nehemiah Christian Service Ministry Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ነህምያ የአገልግሎት ሕብረት-Nehemiah Christian Service Ministry, Religious Center, Addis Abeba, Addis Ababa.

11/05/2026

"ትምህር ፡ እና ፡ አገልግሎት"

11/05/2026

ትምህርትና ስርዓተ ፡ ፆታ ፡ ግንኙነት...

በታላቅ ፡ ድል ፡ ተጠናቋል...."እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ::" ሉቃ.17:10................
11/05/2026

በታላቅ ፡ ድል ፡ ተጠናቋል....

"እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ::" ሉቃ.17:10
....................................

በወልቂጤ ፡ ከተማ ፡ የሚገኙ ፡ የአድቬንቲስት ፡ ወጣቶች ፡ ላይ ፡ አተኩሮ ፡ የተዘጋጀው ፡ ልዩ ፡ የተማሪዎች ፡ መድረክ ፡ ተጠናቋል።

"ለሁሉም ፡ ነገር ፡ ጊዜ ፡ አለው" በሚል ፡ ርእስ ፡ ተማሪዎች ፡ሁሉንም ፡ ነገር ፡ በጊዜው ፡ ይፈፅሙ ፡ ዘንድ ፡ ትኩረት ፡ ያደረገው ፡ ይህ ፡ ፕሮግራም ፡ በብዙ ፡ መለኪያ ፡ በነህምያ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ ታሪክ ፡ ውስጥ ፡ እጅግ ፡ ደማቁ፣ ስኬታማው እና ፡ ህያው፡ መድረክ ፡ ተደርጎ ፡ የሚወሰድ ፡ ነው።

በዚህ ፡ ፕሮግራም ፡ ከ250 ፡ በላይ ፡ የሚሆኑ ፡ ተማሪዎች ግንቦት ፡ 1 ፡ እና ፡ 2፣ 2018 ዓ.ም ፡ ለሁለት ፡ ተከታታይ ፡ ቀናት ፡ የታደሙበት፣ ከፍተኛ ፡ መነሳሳት ፡ የታየበት ፡ ወጣቶች ፡ ከእለት ፡ ተለት ፡ የትምህርት፣ የአገልግሎት እና ፡ የስርዓተ-ፆታ ፡ ህይወታቸው ዙሪያ ፡ከገሃዱ ፡ ዓለም ፡ ያልራቁ ፡ ህያውና እውነተኛ(authentic) ትምህርት ፡ ያገኙበት ፡ መድረክ ፡ ሆኖ ፡ አልፏል።

የዚህን ፡ ልዩ ፡ የወጣቶች ፡ (የተማሪዎች)፡ መድረክ ፡ ዝርዝር ፡ የፕሮግራም ፡ ይዘት ፡ የምስል ፡ እና ፡ የተንቀሳቃሽ ፡ ምስል ፡ ማስረጃ ዎች፣ ወደፊት ፡ በፈረጅ ፡ በፈረጁ ፡ የምናቀርብ ፡ ይሆናል። ለቅምሻ ፡ ያክል ፡ ጥቂቶቹን ፡ የፎቶና ፡ ፡ የተንቀሳቃሽ ፡ ምስሎቹን ፡ እነሆ፡-

"እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ::" ሉቃ.17:10

በወልቂጤ ፡ ከተማ ፡ የሚገኙ ፡ የአድቬንቲስት ፡ ወጣቶች ፡ ላይ ፡ አተኩሮ ፡ የተዘጋጀው ፡ ልዩ  ፡ የተማሪዎች ፡ ፕሮግራም  ፡ ዛሬ ፡ በይፋ ፡ ተጀምሯል።በዚህ ፡ ፕሮገራም ፡  ከወጣቶ...
08/05/2026

በወልቂጤ ፡ ከተማ ፡ የሚገኙ ፡ የአድቬንቲስት ፡ ወጣቶች ፡ ላይ ፡ አተኩሮ ፡ የተዘጋጀው ፡ ልዩ ፡ የተማሪዎች ፡ ፕሮግራም ፡ ዛሬ ፡ በይፋ ፡ ተጀምሯል።

በዚህ ፡ ፕሮገራም ፡ ከወጣቶች ፡ የእለት ፡ ተለት ፡ ህይወት ጋር፡ በቀጥታ ፡ ግንኙነት ፡ ባላቸው ፡ ፅንሰ ፡ ሀሳቦች ዙሪያ ፡ ለምሳሌ ፡ ትምህርት፣ አገልግሎት ፡ በተለይ ፡ የመዝሙር ፡ አገልግሎት ፡ እና ፡ ፡ Relationship አስመልክቶ ፡ ለየት ፡ ያሉ ፡ መርሃ ፡ ግብሮች ፡ ተነድፈዋል። ነገ ቅዳሜ ፡ ግንቦት ፡ 1 ፡ እና እሁድ ፡ ግንቦት ፡ 2 /2018 ፡ ዓ.ም ፡ ሙሉ ፡ ቀን ፡ መርሃ ፡ ግብሮቹ ፡ ይቀጥላሉ። በዚህም ፡ እድሚያቸው ፡ ከ14-30 ፡ ዓመት ፡ የሚሆኑ ፡ እስከ ፡ 200 ፡ የሚጠጉ ፡ ወጣቶች ፡ የዚህ ፡ ልዩ ፡ ጊዜ ፡ ተሳታፊ ፡ ለመሆን ተመዝግበዋል።

በኛ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ እንደሆነች ፡ የአምላካችን ፡ ፈቃድ ፡ ልዩነት ፡ የሚፈጥር ፡ ጊዜ ፡ እንደሚኖረን ፡ ተስፋ ፡ እናደርጋለን።

# ኑ ፡ በፈረሰው ፡ በኩል ፡ አብረን ፡ እንገንባ

# ጥረቶቻችን ፡ ሁሉ ፡ ወደ ፡ ዘላለማዊ ፡ ግብ ፡ ያመራሉ

የአንድነት ፡ መርሃ ፡ ግብር....የወልቂጤ ፡ የነህምያ ፡ ቤተሰቦች ፡ ከወልቂጤ ፡ 7ተኛ ፡ ቀን ፡ አድቬንቲስት ፡ አጥቢያ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያናት ፡ ጋር ፡ በመተባበር ፡ ከግንቦት ፡ 1...
02/05/2026

የአንድነት ፡ መርሃ ፡ ግብር....

የወልቂጤ ፡ የነህምያ ፡ ቤተሰቦች ፡ ከወልቂጤ ፡ 7ተኛ ፡ ቀን ፡ አድቬንቲስት ፡ አጥቢያ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያናት ፡ ጋር ፡ በመተባበር ፡ ከግንቦት ፡ 1-2/2018 ፡ ዓ.ም ልዩ የወጣቶችየአብሮነት ፡ መርሃ ፡ ግብር ፡ አዘጋጅቷል።

በዚህ ፡ ፕሮግራም ፡ ለመሳተፍ የሚመዘገቡ ታዳጊዎች ከዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

✓ እድሜ ፡ 14-30 ዓመት የሆነ/ች

✓ በስልጠና ወቅት ስልክ ፡ ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት ፈቃደኛ የሆነ/ች

✓ ግንቦት 1/2018 ዓ.ም (ቅዳሜ ከሰዓት) እና ግንቦት 2/2018 ዓ.ም (እሁድ ሙሉ ቀን) በሚኖሩት መርሃ ግብሮች በሙላት ለመሳተፍ ፈቃደኛ ፡ የሆነ /ች

✓ ያለ አስገዳጅ ምክንያት ፕሮግራሙን አቋርጦ ላለመውጣት የሚፈቅድ/የምትፈቅድ

✓ ተሳታፊ ፡ ለመሆን ፡ በሶስቱም አጥቢያዎች አስቀድሞ በሚነገረው ማስታወቂያ መሰረት ፡ ለምዝገባ ፡ በተሰጠው ፡ ቀነ ፡ ገደብ ፡ ውስጥ ፡ ለፕሮግራሙ ፡ የተመዘገቡ

✓ የምዝገባ ቀናት ሚያዚያ 24 (ቅዳሜ) እና 25 (እሁድ) /2018 ዓ.ም ብቻ ፡ ይሆናል፡፡ ወጣቶች በእለቱ ፕሮግራም የሚታደሙት ወይም ፡ የሚስተናገዱት ፡ በተመዘገቡበት ፡ የመረጃ ቅፅ ፡ መሰረት ብቻ ይሆናል።

✓ ለዚህ ፡ ፕሮግራም ፡ ለመመዝገብ በወልቂጤ በቁ. 2 አድቬንቲስት ቤ/ክ ሞላ ወርቁ(+251 92 313 4678)፤ በወልቂጤ ቁ.1 አድቬንቲስት ቤ/ክ ጌታያውቃል (+251924560965)፤ በወልቂጤ ቁ.4 አድቬንቲስት ቤ/ክ ደሳለኝ ፡ ወርቁ (+251 96 938 4978 ) ማግኘት ፡ ይቻላል።

✓ ተመዝጋቢዎች ፡ በፕሮግራሙ ፡ ወቅት ፡ ማስታወሻ ፡ እና ፡ እስክሪፕቶ ፡ በመያዝ ፡ በንቃት ፡ መሳተፍ ፡ የሚፈቅድ/የምትፈቅድ ፡ መሆን ፡ ይጠበቅባቸዋል።

✓ አዝናኝ ፡ ጨዋታዎች ፡ (games)፤ የቡድንና ፡ የጋራ ፡ ውይይቶች ፣ የውጤታማ ፡ ተማሪዎች ፡ ተሞክሮ፣ አገልግሎት እና ፡ ተማሪነት (የአዳዲስ መዝሙር ፡ አወጣጥ ፡ መሰረታውያን፣ የመዝሙር ፡ ታሪኮችና መዝሙሮች) ፣ የፍቅር ፡ ግንኙነቶች ፡ እና ተማሪነት ፣ተማሪነት እና ፡ የህይወት ፡ ጫናን ፡ መቋቋም፣ ጊዜና የመህበራዊ ፡ ሚዲያ ፡ አጠቃቀም ፣የሻይና ፡ የምሳ ፡ መርሃ ፡ ግብሮች ፡ የፕሮግራሙ ፡ አካሎች ፡ ናቸው።

፡ ✓ የፕሮግራሙ ፡ ቦታ ፡ በወልቂጤ ፡ ቁ.2 ፡ አድቬንቲስት ፡ ቤ/ክ ፡ ቅጥር ፡ ግቢ ፡ እንዲሁም ፡ ወጣ ፡ ባለ ፡ ቦታ ፡ ይሆናል፡፡

# ኑ ፡ በፈረሰው ፡ በኩል ፡ አብረን ፡ እንገንባ

# ጥረቶቻችን ፡ ሁሉ ፡ ወደ ፡ ዘላለማዊ ፡ ግብ ፡ ያመራሉ

ዛሬ በቤ/ክናችን የሚታዩ  ጉልህ የታሪክ አሻራዎች  የተሰሩት የመስዋዕትነት ህይወት ለመኖር በመረጡ ፣  አገራቸው አትረፍርፋ  ለመስጠት የምትችለውን የኑሮ ድሎት በመተው  ወደ ሶስተኛው ዓለም...
18/04/2026

ዛሬ በቤ/ክናችን የሚታዩ ጉልህ የታሪክ አሻራዎች የተሰሩት የመስዋዕትነት ህይወት ለመኖር በመረጡ ፣ አገራቸው አትረፍርፋ ለመስጠት የምትችለውን የኑሮ ድሎት በመተው ወደ ሶስተኛው ዓለም ገጠር መንደሮች ለመውረድ በፈቀዱ ሚሲዮናዊ ልቦች ነው።

ሚሲዮናዊነት የራስንና የቤተሰብን የጥቅም ስሌት አይሰራም። በሞቀው ለመዋል የቀዘቀዘውን፣ ባደገው ለመክተም ያለደገውን አልፎ ና ጥሎ አይሄድም። ይልቅስ የቀዘቀዘው እንዲግል ያላደገው ደግሞ እንዲያድግ በክርስቶስ ፀጋ ጥቂትም ቢሆን መስዋዕትነት ባለው መንገድ ለመራመድ ይመርጣል።

ይህ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን የዘመን ሀሳብ በዚህ በኛ ዘመን ይቀሰቀስ ዘንድ ያስፈልገዋል። ይህን መሰል ባህርይ ግን በአንድ ጀንበር አይገኝም። ከትንሽ በመጀመር መልመድን ይሻል።

# ኑ በፈረሰው በኩል አብረን እንገንባ

# ጥረቶቻችን ሁሉ ወደ ዘላለማዊ ግብ ያመራሉ

በእርግጥ መሰል የተፅዕኖ ማእከላትን ያበረታታ ቤ/ክ ውጤታማ የወንጌል ጥረት አከናወነ! ሰዎችንም በልዩ ሁኔታ ለእግዚአብሔር መንግስት አደመ !..................................
31/03/2026

በእርግጥ መሰል የተፅዕኖ ማእከላትን ያበረታታ ቤ/ክ ውጤታማ የወንጌል ጥረት አከናወነ!

ሰዎችንም በልዩ ሁኔታ ለእግዚአብሔር መንግስት አደመ !
..........................................

“አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ” [መክ 9፥10]።

አምላካችን እግዚአብሔር የፈጠራ ሊቅ ነው። ከዘለዓለም እስከ ዘላለም ባለው ጥበቡ ስራዎችን ይነድፋል፤ በፍጽማና ይከውናል። ለዘመናት በሸመገለው እውቀቱ አለማትን ሁሉ አጽንቶ ያቆማል።

ይህንን የማሰብና የማሰላሰል እንዲሁም የመፍጠርና የማቀናጀት (to invent, innovate and coordinate) ክህሎትን ለሰው ልጆች አካፍሏል[ዘፍ1:26]።

ሁላችንም እግዚአብሔር በተለዩ ሁኔታ ያበረከተልን ተፈጥሮአዊ ክህሎቶች አሉን። እነኝህን መክሊቶቻችን ባገኘናቸው እድሎች ሁሉ በማዳበር ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ጥቅም እናውላቸው ዘንድ ታዘናል። ክህሎትን ለመልካም ነገር አለመጠቀም ሀጢያት ነው [ማቴ 25፡18፣ 26-30]።

በመጽሐፍ ቅዱስ መርህ ክህሎትን አዳብሮ መንፈስንም ስጋንም የሚጠግን ስራን በመስራት ራስን ከመቻል አልፎ ቤተሰብን፣ ማሕበረሰብን፣ ቤተ ክርስቲያንንና አገርን የሚደግፍ፣ ባለራእይ፣ ልበ ሙሉና ተስፈኛ የሆነ፣ የጥበቡና የሀይሉ ምንጭ እግዚአብሔር መሆኑን የሚያምን፣ የምድርም ሆነ የሰማይ መልካም ዜጋ የሆነ ወጣት ማፍራት የነህምያ የምንግዜም ህልም ነው [ምሳ 6፡6-11፣ ምሳ 12፡27፣ 2 ተሰ 3፡10]።

ወጣቶች ከገሃዱ የስራ ዓለም ጋር ተገናኝተው ገና በለጋ እድሜአቸው ዝንባሌአቸውን እንዲለዩ፣ የሙያ መስመራቸውን እንዲመርጡ፣ አስፈላጊውን ስልጠናም በተገቢው ጊዜ አግኝተው በተሰለፉበት የትምህርትም ሆነ የስራ መስክ ቁንጮ የሆኑ፣ በሁሉም መስክ ስብእናቸው የተገነባ፣ በስማቸው ተጠርተው በተግባርና በምሳሌ ለሌሎች እንደ አርአያ ሊቀርቡ የሚችሉ፣ የእግዚአብሔርና የሰው ልጅ ኩራት የሆኑ የሰማይ አምባሳደሮች ወደ መሆን ይጎለምሱ ዘንድ የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት አላማ ነው።

(የነህምያ የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት የስራ ፈጠራ ዘርፍ ፅንሰሃሳብ ፣ ገፅ 11-12፣ 2015 ዓ.ም)

በእርግጥ መሰል የተፅዕኖ ማእከላትን ያበረታታ ቤ/ክ ውጤታማ የወንጌል ጥረት አከናወነ!

ሰዎችንም በልዩ ሁኔታ ለእግዚአብሔር መንግስት አደመ !

# ኑ በፈረሰው በኩል አብረን እንገንባ

# ጥረቶቻችን ሁሉ ወደ ዘላለማዊ ግብ ያመራሉ

29/03/2026

ልጅነት ይሰልጥን ...!


ልጅነት የጉብዝና ወራት ስንቅ፣ ደስ በማይሉ የኋላ ዓመታት ጥግ፣ ቀን ሲያመሻሽ ብርሃን፣የነገን የህይወት እድልና ተግዳሮት ተገንዝቦ በፈተናው ለማለፍ ጥንስስ ነው።

ልጅነት ከትንሽ ከተማ ከገጠር ቢበቅል፣ ከማታነበው እናት ከማይፅፈው አባት ቢፈልቅ ፤ አማርጦ ባይበላ ፤ የጎደፈ ቢለብስ ፤ ለዓለሙ ስልጣኔ፣ ለትምህርት ቱርፋት ባይተዋር ቢመስል ሁለተናዊ ስልጠና ቢቀበል፤ ቢማር ቢመራመር፣ የህይወት እውቀት እንዲሰበስብ ቢመራ፣ የእጅ ሙያ ክህሎት ቢቀስም ፣ ቋንቋ ቢማር፣ ንግድ ስራ ቢያውቅ፣ እርሻ ቢሰለጥን፣ እግዚአብሔር ማፍቀርና መፍራት ቢለምድ በአጠቃላይ ለራስ ለቤተሰብና ለሰው ልጆች ሁሉ ጥቅም ከእውኑ ዓለም ጋር ተጋፍጦ ለመሰረታዊ የኑሮ እውነት ተዘጋጅቶ እንዲያድግ ቢታገዝ በምድር ሳለ በማገልገል የሚደሰት በሚመጣውም ዓለም ደግሞ የይለፍ ማረጋገጫ የሚያገኝ ነው ።

በእርግጥ ዛሬ ልጅነትን ያስተማረ ያሰለጠነ ቤተክርስቲያን ውጤታማ የወንጌል ጥረት አከናወነ።
አገርንም ህዝብን ለእግዚአብሔር መንግስት አደመ።

ልጅነት ይሰልጥን ...!

# ኑ በፈረሰው በኩል አብረን እንገንባ

# ጥረቶቻችን ሁሉ ወደ ዘላለማዊ ግብ ያመራሉ

የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት የትምህርት ዘርፍ  ፅንሰ ሀሳብ ....( የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት አጭር መግለጫ 2015 ዓ.ም ገፅ 4 ላይ በቀጥታ የተወሰደ) የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት...
23/03/2026

የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት የትምህርት ዘርፍ ፅንሰ ሀሳብ ....

( የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት አጭር መግለጫ 2015 ዓ.ም ገፅ 4 ላይ በቀጥታ የተወሰደ)

የነህምያ የአገልግሎት ሕብረት ትኩረት በኤደን የጀመረውን፣ በመለኮት የተጸነሰውን፣ አእምሮን፣ መንፈስንና አካልን የሚያጎለምሰውን እውነተኛ ትምሕርት ለዓለም በማበርከት ላይ ያለችውን የሰባተኛው ቀን
አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን መደገፍ ነው[ሉቃ 2፡52፣ ዘዳ 6፡5፣ መዝ 119፡108፣ ዘዳ 11፡1፣ ምሳ 8፡1-6፣ እዩብ 28፡28፣ 2ጤሞ 3፡16- 17]

የጸሎት፣ የማማከር፣ የማሰልጠን አገልግሎት እንደ አስፈላጊነቱ በማበርከት ያለው መልካም ባህሪይ እንዲጎለብት፣ ተሃድሶ የሚያስፈልገውም እንዲታደስ በማገዝ የአድቬንቲስት የትምህርት ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን አስተዋጾ እናደርጋለን።

ታዳጊዎች ልክ እንደነ ዳንኤል በጥበብና በማስተዋል በውጤትም ልቀው እንዲገኙ ማበረታቻ እንሰጣለን። የአቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች እንደተቻለን መጠን ቁሳዊና ስነልቦናዊ ድጋፍ እናደርጋለን።

ከበተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ልምድ ያካበቱ የህብረቱ ሙያተኞች ተደራጅተው በአካልም ሆነ በርቀት ተገኝተው በትምህርት መዋቅሩ ውስጥ ዐብይ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ የማስተባበር ሚና እንጫወታል።

ከዚህ የትምህርት ፅንሰሃሳብ በመነሳት ነህምያ የአገልግሎት ሕብረት በተሰለፉበት የትምህርት ደረጃ ቁንጮ የሆኑ በሁሉም መስክ ስብዕናቸው የተገነባ በስማቸው ተጠርተው በተግባርና በምሳሌ ለሌሎች እንደ አርአያ ሊቀርቡ የሚችሉ ወጣቶችን ለማፈራት በማለም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የነህምያ የአድቬንቲስት የትምህርት ልቀት ሽልማት (Nehemiah Award for Adventist Excellence in Education) እንደ ማበረታቻ ይሰጣል።

# ኑ በፈረሰው በኩል አብረን እንገንባ

# ጥረቶቻችን ሁሉ ወደ ዘላለማዊ ግብ ያመራሉ

የነህምያ አገልግሎት ሕብረት የግብርናና የገጠር ኑሮ ዘርፍ ፅንሰሃሳብ ..... (ነህምያ የአገልግሎት ሕብረት መግለጫ ገፅ 8, 2015 ዓ.ም  ላይ በቀጥታ የተወሰደ )"ሰው ይኖርበት ዘንድ መ...
20/03/2026

የነህምያ አገልግሎት ሕብረት የግብርናና የገጠር ኑሮ ዘርፍ ፅንሰሃሳብ .....

(ነህምያ የአገልግሎት ሕብረት መግለጫ ገፅ 8, 2015 ዓ.ም ላይ በቀጥታ የተወሰደ )

"ሰው ይኖርበት ዘንድ መጀመሪያ እግዚአብሔር ያቀደው የእርሱ የእጅ ስራ በሆነው በተፈጥሮ መካከል ነበር።

ይህንን ክቡር የሆነ የአምላክ ስጦታ የሰው ልጅ በሃላፊነት ተረክቦ ይንከባከበው ያበጀውም ዘንድ እግዚአብሔር አዞታል [ዘፍ 2፡15]።

በኤደን መካከል ምንም የጎደለ ነገር ባይኖር እንኳ እግዚአብሔር ለፈጠረው እንክብካቤ ሲያደርግ በዚህ ስራ ከአምላክ ጋር በመተባበር እንደ አንድ የሰማይ ቤተሰብነቱ ደስታን ያገኝ ዘንድ፣ በድንቅ የመፍጠር ችሎታው በመመሰጥ ለጌታው
ምስጋና ያቀርብ ዘንድ፣ አምላኩ ሁልጊዜም በሥራ ላይ እንዳለ ሁሉ እርሱም ያላሰለሰ ሥራ በመስራት አካሉን፣ መንፈሱን፣ አእምሮውን እንዲያድስና እንዲያጎለብት የመለኮት ፈቃድ ነበር።

ከውድቀት በኋላም የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ስላለው ግንኙነት የአምላክ እቅድ አልተቀየረም [ዘሌ 25፡ 4-5]። የሰው ልጅ ግን አደራውን ሳይወጣ የራሱን እራስ ወዳድ መርሃ ግብር በመተግበር ምድርን አጎሳቁሎ መኖሪያውን በተፈጠሮ መካከል ሳይሆን በሰዎች መካከል በማድረግ የእርሱን ተጽእኖ ለማስቀጠል በማያቋርጥ ጥረት ውስጥ ይገኛል።

ሰዎች በከተሞች ውስጥ ተጨናንቀው ከመኖራቸው የተነሳ ለብዙ በሽታዎች፣ ለበርካታ እርኩሰቶችና ውድመቶች መፈልፈያ ማእከሎች ሆነዋል [ዘፍ 11፡4፤ ዘፍ 19፤ ራእይ 16፡19፤ ራእይ 18፡15-17]።


እንደ መጀመሪያው የእግዚአብሔር እቅድ ሁሉ ነህምያ የአገልግሎት ሕብረትም የሰው ዘር ከሰው ሰራሽ የአኗኗር ዘይቤ ይልቅ የበለጠ ከተፈጥሮ ጋር የተቆራኘ፤ የአካልና የአእምሮ የመንፈስም መልካም ተጽእኖ በሚያሳርፈው በገጠር ውስጥ እንዲሆን ያበረታታል።

ወደ ቀደመው በመመለስ አካባቢውን ምቹ የመኖሪያ ስፍራ አድርጎ በማዘጋጀት ለኑሮው የሚያስፈልገውን ሁሉ የተፈጥሮ ሚዛንን በጠበቀ የአስተራረስ ዘዴ ተከትሎ በማምረት እግዚአብሔር ያበረከተውን የምድር ስብ ከጤናማነት ጋር እንዲበላ፣ ደስታውንም ማጣጣም ይችል ዘንድ ማስተማር የነህምያ ራእይ አካል ነው።

ምድር ውበቷን እንደጠበቀች የሰው ልጆች መኖሪያ ሆና እንድትቀጥል በሚደረገው ጥረት፣ ዛፎችን ከመቁረጥ ይልቅ ተጨማሪ በመትከል፣ ተፈጥሮአዊ ማዳበሪያን በመጠቀም፣ እርከን በመስራት፣ አፈራርቆ በመዝራት፣ለማሳ የዓመት እረፍት በመስጠት እንዲሁም ተጠቃሚዎቹ እግዚአብሔር የሰጠውን የተፈጥሮ ህግ አክብረው እንዲኖሩ በማስተማር ረገድ ነህምያ ጉልህ አስተዋጽዖ ያደርጋል [ራእይ 11፡17]።"

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ነህምያ የአገልግሎት ሕብረት-Nehemiah Christian Service Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share