24/11/2025
“በብሔር በሀበ ፈለስኩ ………..”
እንዲል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየመጣ ያለው የአካባቢ ተወላጅ የሆኑ ትሩፋት አገልጋይ የማግለል እና ማሸማቀቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና አላስፈላጊ ደረጃ እየደረሰ ነው
በቅኔ ማህሌት በቤተመቅደስ በአውደምህረት አንያችሁ እያሉ ማባረር እና ከአገልግሎት ማራቅ እንደትልቅ ስራ እና መሪነት ደረጃ የሚያዩ አለቆች ፀሀፍት እና አገልጋይ ካህናት ተበራክተዋል ፧ ደጀፀኝ እያሉ የነበረውን ታሪክ ተረስቶ፧
ዛሬም ያየነው የሰማነው ይህንን ይመሰክራል እውነት የሽሮሜዳ ዲያቆናት አገልግሎት ለብዙ ደብራት አገልግሎት ትኩረት እንዲሰጡ መነሳሳት የፈጠሩ የአገልግሎት ፍቅር ያላቸው ቀናኢ የቤተክርስቲያን ልጆች ለመሆናቸው ምስክር ለመሆን አይኔን አላሽም
ይህንን አገልግሎት እና የአገልግሎት ፍቅር መደገፍ ሲገባ አናቃችሁም መባል እንደ አንድ የአዲስ አበባ ልጅ እና የችግሩ ቀማሽ እንደሆነ ሰው በጣም ያማል “የበሬውን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ“ አለሁ አበው
-የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ውዝግብ
-የአገልጋዮች መገፋት
-የአዲስ አበባ ልጅ በአደገበት በሰራው ደብር መገፍት እና መሰደብ ባይተዋር ማድረግ ሊቆም የሚገባው መሆኑ አምናለሁ ለዚህም ከጎናችሁ ነን
እግዚአብሔር ሀይል ይሁነን
ዲ/ን ቅዱስ