Waldaa Amantoota Wangeela kana'aan Sabbataa

Waldaa Amantoota Wangeela kana'aan Sabbataa Gospel Believers Canaan Churh Is To Fulfill Christ's Mission Through Holistic Teaching, Evangelism, Discipleship And Healing For Healthy And Godly Nations.

To proclaim the Gospel throughout the world and make disciples of all kinds of people. "Go therefore and make disciples of all the nations, baptizing them in the name of the Father and of the Son and of the Holy Spirit, teaching them to observe all things that I have commanded you; and lo, I am with you always, even to the end of the age" (Matt. 28:19-20). "And He said to them, Go into all the world and preach the gospel to every creature" (Mark 16:15).

17/05/2026
17/05/2026

Far. Amanuel

08/05/2026

በወክታዊ ጉዳይ የቤተክርስቲያናችን አስተያየት ሐሰተኛ ሐዋርያትና ነቢያት በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እየተበራከቱ ትልቅ ውዥንብርና ጉዳት እያስከተሉ ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ በተአምርና በትንቢት ሕዝቡን ይስባሉ፤ ከዚያም "እግዚአብሔር ሾመኝ፤ ተናገረኝ" እያሉ ያለ ምንም ተጠያቂነት ቤተክርስቲያንን ይመራሉ። ሕዝቡን በፍርሃትና በሐሰት ትንቢት ይቆጣጠራሉ፤ ገንዘብ ይበዘብዛሉ፤ የእግዚአብሔርን ጸጋ በገንዘብ ይሸጣሉ፤ ቅዱስ ዘይት፣ ውኃና ጨው በውድ ዋጋ ያቀርባሉ፤ ከቃሉ ውጭ የሆኑ አዳዲስ ትምህርቶችን ያስፋፋሉ። ከዚህም ሌላ፣ በሚናገሩት ትንቢት ቤተሰቦችን ይበትናል፤ አማኞችና አብያተ ክርስቲያናትና ይከፈላሉ፤ በዚህም ምክንያት ጥላቻ፣ መለያየትና ስነ ልቦናዊ ቀውስ በብዙዎች ሕይወት ውስጥ አለ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ቀጥታ ከመቅረብ ይልቅ ወደ ሐዋርያው ወይም ወደ ነቢዩ ሲሮጥ መታየቱ ነው። በክርስትና ውስጥ ከሁሉ የሚበልጠው ስም የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ቢሆንም፣ በእነዚህ ቤተክርስቲያንዎች ግን የ"ነቢዩ" ወይም የ"ሐዋርያው" ፎቶ፣ ስምና ዝና ከክርስቶስ ስም በላይ ከፍ ብሎ ይታያል ይህም ከጣዖት አምልኮ ምንም አይለይም። በመጨረሻም፣ በእነዚህ ሐሰተኞች መጥፎ ተግባር ምክንያት ክርስትና እንደ ኋላ ቀርነትና ተቆጥሮ ብዙ የተማሩና የነቁ ሰዎች ከቤተክርስቲያን እንዲርቁ ሰበብ እየሆነ ይገኛል ይህም ለቤተክርስቲያን ትልቅ ኪሳራ ነው።
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መዋቅራዊ በሆነ መንገድ "ሐዋርያ" እና "ነቢይ" የሚሉ የሹመት ስሞችን ላለመቀበል የወሰነችው፣ በአሁኑ ዘመን በሚታየው የተሳሳተ አጠቃቀምና በሥርዓት አልበኝነት ምክንያት እንደሆነ ይገመታል፡፡ መሪዎቹ "ሐዋርያ" እና "ነቢይ" የሚሉትን የሹመት ስሞች (Titles) ላለመቀበል መወሰናቸውን እናከብራለን፣ ነገር ግን አገልግሎቶቹ (Functions) በመጽሐፍ ቅዱስ የታዘዙና ዛሬም ለቤተክርስቲያን ዕድገት አስፈላጊ ናቸው። ኤፌሶን 4፡11-13 የሚናገረው ስለ "ሹመት" ሳይሆን ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ስለሰጣቸው "ስጦታዎች" ነው። እነዚህ ስጦታዎች የተሰጡት "ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማስታጠቅ" ነው። ቤተክርስቲያን ዛሬም ምእመናን እንዲታጠቁና እንዲበስሉ ካስፈለጋት፣ እነዚህ አምስቱም የጸጋ ስጦታዎች (ሐዋርያዊ፣ ነቢያዊ፣ ወንጌላዊ፣ እረኝነትና አስተማሪነት) ያስፈልጓታል።
ሐዋርያትና ነቢያት መሠረት ጥለው አልፈዋል የእግዚአብሔር ቃል በኤፌሶን 2፡20 ላይ በግልጽ ይናገራል። ይህ መሠረት ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ የተጣለና የማይለወጥ ነው። ይኸውም መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ከተቀመጠው መሠረት በቀር ሌላ መሠረት ማንም ሊያኖር አይችልም፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (1 ቆሮንቶስ 3፡11) በማለት እንደመሰከረው፣ የቤተክርስቲያን መሠረት የክርስቶስ ትንሳኤ ምስክር የሆኑት 12ቱ ሐዋርያት እና በሐዋርያ ጳውሎስ አማካይነት አንድ ጊዜ ተጥሎ አልቋል። ስለዚህ ማንኛውም ሐዋርያ ወይም ነቢይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ አዲስ ትምህርት ወይም መገለጥ ቢያመጣ፣ በቃሉ ሚዛን ውድቅ ይደረጋል። ጳውሎስ በገላትያ 1፡8 ላይ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ለዚህ ትልቅ ማረጋገጫ ነው፦ “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።” ይህ የሚያሳየው የሐዋርያት ትምህርት (Apostolic Doctrine) ሙሉ፣ የተሟላና ለማንኛውም ተጨማሪ መገለጥ ዝግ መሆኑን ነው። ከዚያ በኋላ አዲስ ዶክትሪን አይጨመርም። ዛሬ የሚኖሩ አገልጋዮች “ሐዋርያ” ተብለው ቢጠሩም፣ አዲስ መሠረት መጣል አይደለም የሚጠራባቸው፤ ነገር ግን በአስቀድሞ በተቀመጠው መሠረት ላይ መገንባት ነው።
የጥንቶቹ ሐዋርያት መጽሐፍ ቅዱስን በመጻፍና መሠረቱን በመጣል ረገድ የማይደገም ሥራ ሠርተዋል። ነገር ግን ዛሬ ያሉ ሐዋርያዊና ነቢያዊ ጸጋ ያላቸው ሰዎች ሥራ አዲስ መሠረት መጣል ሳይሆን፣ በተጣለው መሠረት ላይ ሕንፃውን ማስፋፋት ፤ መገንባት ነው። ዛሬም ወንጌል ያልደረሰበትን አድማስ የሚሰብሩ (ሐዋርያዊ ስራ) እና ቤተክርስቲያን ከመለኮታዊ መስመር እንዳትወጣ በቃሉ የሚመክሩ (ነቢያዊ ስራ) አገልጋዮች የሕንፃው ግንባታ አካል ናቸው። የኤፌሶን 4፡11–13 ክርክር በተለይ “ሁላችን ወደ አንድነትና ወደ ሙሉ ብስለት እስክንደርስ ድረስ” በሚለው ሐረግ ላይ ይመሠረታል። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ወንጌላውያን፣ እረኞችና አስተማሪዎችን ሰጠ፤ ይህም ቅዱሳንን ለማብቃት፣ ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት፣ እና የክርስቶስን አካል ለማነጽ ነው።
እነዚህ አገልግሎቶች የተሰጡት ሁላችንም ወደ እምነት አንድነትና ወደ ሙሉ ብስለት እስክንደርስ ድረስ ነው፤ ይህም በተግባር ክርስቶስ ዳግም እስኪመጣ ድረስ ማለት ነው።
ስለዚህ፣ ቤተ ክርስቲያን ገና ፍጹም አንድነትና ሙሉ ብስለት ስላልደረሰች፣ እነዚህ ስጦታዎች ገና ያስፈልጋታል። በዚህ መሠረት፣ ሐዋርያትና ነቢያትም እንደ አገልግሎት ስጦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መኖራቸው እንደሚቀጥል ይገልጻል፤ ነገር ግን ይህ አዲስ ዶክትሪን ለመመስረት ሳይሆን፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽና ለማብቃት ነው።
አገልግሎቱ የለም" ብሎ መደምደም መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን ስጦታ እንደመገደብ ሊቆጠር ይችላል። ይልቁንም፣ "ሐዋርያዊና ነቢያዊ ጸጋ ያላቸው አገልጋዮች በቤተክርስቲያን መዋቅርና በመሪዎች ሥር ሆነው፣ ለቃሉ እየታዘዙ እንዲያገለግሉ ሥርዓት ቢበጅላቸው ይሻላል"1 ቆሮንቶስ 14፡32 "የነቢያት መናፍስት ለነቢያት ይገዛሉ" እንደሚል፣ አገልግሎቱ በሥርዓት እንዲመራ እንጂ እንዲታገድ አልታዘዘም።

ቃለ ሕይወት ራሷ የተመሠረተችው "ሐዋርያዊ" በሆነ ተልእኮ ነዉ ወንጌልን ወደማይታወቁ አካባቢዎች ይዘው የሄዱ፣ አብያተ ክርስቲያናትን የተከሉና መከራ የተቀበሉ ቀደምት አባቶች የሠሩት ሥራ በትክክለኛ ትርጉሙ "ሐዋርያዊ አገልግሎት" ነው። ስሙን ባንጠቀምበትም አገልግሎቱን ግን እየኖርንበት ነው። ስለዚህ ስጦታውን መካድ የቤተክርስቲያኒቱን የውልደት ታሪክ መካድ ሊሆን ይችላል።
የተከበራችሁ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ በዘመናችን ባለው የሐሰተኞች ግራ መጋባት ምክንያት ያሳያችሁት ጥንቃቄ የሚደነቅ ነው። ነገር ግን፣ ሐሰተኞች ስላሉ እውነተኛውን ስጦታ መከልከል የለብንም። ኤፌሶን 4፡11-13 ላይ የተጠቀሱት አምስቱ ስጦታዎች ቤተክርስቲያንን ወደ ሙሉ ሰውነት የሚያደርሱ ‘መድኃኒቶች’ ናቸው። መድኃኒቱን አላግባብ የሚወስዱ ሰዎች ስላሉ ብቻ መድኃኒቱን ከፋርማሲያችን (ከቤተክርስቲያን) ማስወጣት የለብንም። ይልቁንም በመጽሐፍ ቅዱሳዊ 'ባላይነት ሥር ሆኖ ለመዕመኑ አገልግሎት እንዲሰጡ ሥርዓት ማስያዝ ያስፈልጋል።
ከ12ቱ ውጭ የተጠቀሱ ሐዋርያትና ነቢያት ፤ ጳውሎስ1ቆሮ. 15:8-9 / ገላ. 1:1ከ12ቱ ውጭ ነበር፤
በርናባስ ሐዋ. 14:14"ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ" ተብሏል፤የይሁዳና የሲላስሐዋ. 15:32"እነርሱም ነቢያት ስለ ነበሩ"፤አንጾኪያ ነቢያትሐዋ. 13:1በርናባስ፣ ስምዖን፣ ሉቅዮስ፣ ሙናዔን፤የቆሮንቶስ ነቢያት1ቆሮ. 14:29-32ጳውሎስ "ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት ይናገሩ" አለ፤አጋቡስሐዋ. 11:28 / 21:10-11ረሃብ ተነበየ — ጳውሎስ መታሰሩን ተነበየ፡፡ ቀደምት ቤተክርስቲያን ሐዋርያትና ነቢያት ከ12ቱ ውጭ ነበሯት ይህ ዛሬም ይቀጥላል።
ልዩነቱ ግን ዛሬ ቅዱሳት መጻሕፍት አይጨምሩም፣ ሥልጣናቸውም ከቃሉ በታች ነው!
መፍትሔው ምንድን ነው?
1. ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት መሠረት መመለስ አለባት። ይህም ማለት፦ የቃሉ የበላይነት፦ ማንኛውም ትንቢትም ሆነ መገለጥ በመጽሐፍ ቅዱስ መመዘን አለበት።
ትክክለኛ ትምህርት፦ አማኞች በራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስን አጥንተው ስህተትን መለየት እንዲችሉ ማስተማር። ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ ሕዝቡ ቃሉን ስለማያውቅ ነው — ምክንያቱም "ቃሉን የሚያውቅ ሕዝብ ሐሰቱን ይለያል!" (ዮሐ. 8፡32)።
ሐሰተኛ ሐዋርያትና ነቢያት ደሮም ዛሬም ወደ ፊትም ይኖራሉ፣ ቃሉ መርመምሩ ይላል እንጅ አልግሎቱን አትቀበሉ አይልም ፡፡ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠበቁ ማቴዎስ 7:15-16፣ሁሉን መርምሩ፤ መልካሙን ያዙ 1 ተሰሎንቄ 5:21፣ መርምሩ 1 ዮሐንስ 4:1 መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኞች ስለሚነሱ አገልግሎቱን አቁሙ ሳይሆን የሚለው ለዩ መርምሩ እውነተኛውንም ያዙ ነው የሚለው። የምርመራው መስፈርት ምንድን ነው? ትምህርት ከቃሉ ጋር ይስማማል? (ገላ. 1:8-9) ፍሬ ሕይወቱ ምን ይመስላል? (ማቴ. 7:16) ትንቢት የሚናገረው ይፈጸማል? (ዘዳ. 18:22) ትኩረት ወደ ክርስቶስ ያዞራል ወይስ ወደ ራሱ? (2ቆሮ. 11:4) ምንጭ ከክርስቶስ ነዉ፤ ከስጋ፤ ከሴጣን ነዉ የ መጣ ዉብሎ ምንጭን መመርመር አስፈላጊ ነዉ (1ዮሐ. 4:2) ለምሳሌ የቤርያ ሰዎች (የሐዋርያት ሥራ 17፡11) የቤርያ ሰዎች ሐዋርያው ጳውሎስን እንኳን ሳይቀር መርምረው ነው የተቀበሉት፤ የኤፌሶን ቤተክርስቲያን (ራእይ 2፡2) ጌታ ኢየሱስ የኤፌሶን ቤተክርስቲያንን ያመሰገናት ሐዋርያትን ስለከለከለች ሳይሆን መርምራ ስላወቀች ነው፡፡ ሐሰተኞች መኖራቸው እውነተኛው አገልግሎት እንዲቆም ምክንያት ሊሆን አይገባም። ሐሰተኛ አስተማሪ ስላለ 'አስተማሪ' አንሾምም አንልም፤ ሐሰተኛ እረኛ ስላለ 'እረኛ' አንሾምም አንልም። በተመሳሳይ ሐሰተኛ ሐዋርያና ነቢይ ስላለ አገልግሎቱን መከልከል መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። የመሪዎች ድርሻ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መመዘኛ በመጠቀም እውነተኛውን ከሐሰተኛው መለየትና አማኞችን ከመታለል መጠበቅ ነው። አገልግሎቱን መከልከል ግን ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን የሰጠውን ስጦታ እንደ መመለስ ይቆጠራል።

2. ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያው ሐዋርያትና ነቢት መሠረት መመለስ አለባት ስንል ልክ እንደ ሐዋሪያት ዘመን ቤተክርስቲያን ኤፌሶን4:11 ላይ የተጠቀሱት አምስቱ ቢሮ (ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ወንጌላውያን፣ እረኞችና አስተማሪዎች) ቤተክርስቲያን መምራት አለባት፡፡ወደ ሐዋርያት ትምህርት፣ ወደ አምስቱ ቢሮ ሥርዓት፣ ወደ መንፈስ ቅዱስ አመራር መመለስ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት መለኮታዊው አሠራር በድርጅታዊ መዋቅር እየተተካ መሆኑን የሚያሳዩ ግልጽ ምልክቶች አሉ፤ ይኸውም ቤተክርስቲያን እንደ መንፈሳዊ አካል መመራት ሲገባት እንደ ዓለማዊ ተቋም በመዋቀሯ መሪዎች ከጸጋ ይልቅ በዝምድና ወይም በሀብት የሚመረጡበት የአስተዳደር የበላይነት መስፈኑ፣ "ቦርድ" እና "ኮሚቴ" የመሰሉ ቢሮክራሲያዊ መዋቅሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የአምስቱ ቢሮዎች ድርሻ በመውሰድ መንፈሳዊ መሪዎችን በአስተዳደራዊ ሥራ እንዲጠመዱ ማድረጋቸው፣ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱሳዊው መለኮታዊ ሹመት በምርጫ ቅስቀሳና በድምፅ ፉክክር በመተካቱ የምርጫ ፖለቲካ የመለኮታዊውን አሠራር ትርጉም ማደበዝዙ ዋነኞቹ ተግዳሮቶች ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ የእነዚህ ቢሮዎች መጠሪያዎች ቢኖሩም ተግባራቸው ተቀይሮ እናገኘዋለን፤ ይህም በተለይ አምስቱም የአገልግሎት ዘርፎች በአንድ "ፓስተር" ላይ ብቻ ተከምረው በመታየታቸውና ግለሰቡ ሐዋርያም፣ አስተማሪም፣ ወንጌላዊም ለመሆን በሚያደርገው ጥረት የክርስቶስ አካል የሆነው ስልታዊ የሥራ ክፍፍል እንዲዳከም ማድረጉ እንዲሁም የ"ሐዋርያ" እና የ"ነቢይ" ስሞች ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው (Function) ይልቅ እንደ ማዕረግ (Title) ብቻ መታየታቸው ትልቁ ችግር ሆኖ ይታያል
(ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ወንጌላውያን፣ እረኞችና አስተማሪዎች) ቤተክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የነበሩት በክርስቶስ ሥልጣን ሥር ሆነው ነበር። ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1-5 ላይ በሐዋርያት መካከል ቀዳሚ ሆኖ ይናገር ነበር፤ ጳውሎስ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ ሆኖ አገልግሏል (ሮሜ 11:13)። ሐዋርያት አንድ ላይ በመሆን ለቤተክርስቲያን ትምህርትና አቅጣጫ ይሰጡ ነበር ዋና ምሳሌም የኢየሩሳሌም ጉባኤ ነው (ሐዋ. 15)። ሐዋርያት በተጨማሪ በየቦታው ሽማግሌዎችን ይሾሙ ነበር፤ እነዚህ ሽማግሌዎች "እረኞች" ወይም "ጳጳሳት" ተብለውም ይጠሩ ነበር በየጉባኤው ያስተዳድሩ ነበር (ሐዋ. 14:23፤ ቲቶ 1:5፤ 1ጢሞ. 3:1-7፤ 1ጴጥ. 5:1-4)። የሚያስደንቀው ግን ታላላቆቹ ሐዋርያት ራሳቸው "ሽማግሌ" የሚለውን ማዕረግ ይጠቀሙ ነበር። ሐዋርያው ዮሐንስ ከ12ቱ አንዱ፣ የኢየሱስ ቅርብ ወዳጅ፣ የዮሐንስ ወንጌልና ራእይ ጸሐፊ "ሐዋርያ" ብሎ ሳይጠራ በ2ኛ ዮሐንስ 1 እና 3ኛ ዮሐንስ 1 ላይ ራሱን "ሽማግሌ" ብሎ ጠርቷል። እንደዚሁም ጴጥሮስ ዋና ሐዋርያ ቢሆንም በ1ጴጥሮስ 5:1-2 ላይ "ከእናንተ ጋር ሽማግሌ ሆኜ" ብሎ ራሱን ከሌሎቹ እረኞች ጋር አስተሳስሯል። ይህ ሐዋርያት ሥልጣናቸውን ለበላይነት ሳይጠቀሙ፣ በትሕትና አብረው ያገለግሉ እንደነበር ያሳያናል ይህም ሐዋርያዊ አመራር ዋና ምልክቱ ነው።

  Yesuus kirstoos sababafechun sagantaa Addaatu Jiraa kottaa
06/01/2026

Yesuus kirstoos sababafechun sagantaa Addaatu Jiraa kottaa

Ayyaana Galateeffannaa Fulbaana 1 2018 “Yaa Waaqayyo gooftaa ko, ani garaa koo guutuudhaan sin galateeffadha, bara baraa...
12/09/2025

Ayyaana Galateeffannaa Fulbaana 1 2018 “Yaa Waaqayyo gooftaa ko, ani garaa koo guutuudhaan sin galateeffadha, bara baraanis maqaa keetiif ulfina nan kenna.” Far. 86:1

AYYAANA IJOOLLEESagantaa waaqeffannaa Sanbata Guddaa Ganama Hagayya 24/2025
25/08/2025

AYYAANA IJOOLLEE
Sagantaa waaqeffannaa Sanbata Guddaa Ganama Hagayya 24/2025

 Dilbataa Dhuftu 18/12/2017 Ayyanaa Ijoollee  Sababeffachuun Qophii Guddan Qopha;ee Waan Jiruuf Hundumtii keessaan  Afer...
20/08/2025


Dilbataa Dhuftu 18/12/2017 Ayyanaa Ijoollee Sababeffachuun Qophii Guddan Qopha;ee Waan Jiruuf Hundumtii keessaan Aferramtaniituu

Address

Sebeta
Addis Ababa
P.BOX123427

Telephone

2510911254553

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Waldaa Amantoota Wangeela kana'aan Sabbataa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share