Nigat

Nigat This page is about telling the real truth that Ortodox church have.......

22/04/2025

ሰሞኑን ከወደ ኦርቶዶከስ መንደር የደለበው ኑፋቄ ለምን ተነካ በሚል ጫጫታው በዝቷል። የሚገርመው ግን የጫጫታው ብዛት "ድንግል ማርያም የዓለም ቤዛ አይደለችም" የሚለውን አንድን የእውነት ቃል መቀየር አለመቻሉ ነው።

14/02/2025

2296 likes, 133 comments. “Replying to @ይህም ያልፋል በክርስቶስ ምልጃ እናምናለን 🙏🏾 Fekadu @ዘረያህዌ .Christian.✠ (ጆን) Mohammed @ወንድማ ችሁ አሊዬ Tina✝️ Belayneh @ሸልፈኛው @ቃሌ/Kale...

14/02/2025

2205 likes, 103 comments. “ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ #እምነት #መታዘዝ”

14/02/2025

1723 likes, 303 comments. “@ሐዋርያዊ መልሶች - Apostolic Answers”

09/02/2025

8574 likes, 960 comments. “ #ድነናል በፀጋው ድነናል ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቡራከአቸው ይደረብን”

መልካም የልደት በዓል!!!
04/01/2023

መልካም የልደት በዓል!!!

ምንም እንኳ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ስምምነት ባይኖርም፣ የኬልቄዶን ጉባኤ (451 ዓ.ም) 4ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እየተባለ ይጠራል፡፡ ይሁን እንጂ ጉባኤውን ቀረብ ብለውያጠኑት ሰ...
15/01/2021

ምንም እንኳ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ስምምነት ባይኖርም፣ የኬልቄዶን ጉባኤ (451 ዓ.ም) 4ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እየተባለ ይጠራል፡፡ ይሁን እንጂ ጉባኤውን ቀረብ ብለውያጠኑት ሰዎች ጉባኤውን በጉባኤነት ለመቀበል የሚቸገሩባቸውን በርከት ያሉ ምክንያቶች ያነሳሉ፡፡ እኔም ካስተዋልኳቸው ነጥቦች መካከል የተወሰኑትን በተከታታይ የማቀርብ ሲሆን ለአሁኑ በርዕስ ደረጃ ብቻ ልጠቁም፡፡

የመጀመሪያው፣ የኬልቄዶኑ ጉባኤ ከመከናወኑ በፊትና በኋላ የሊዮ አቋም አንድ አልነበረም፡፡ ለምሳሌ፣ ለምዕራቡ ገዢ ቫለንቲነስ፣ ለእናቱና ለእህቱ ለፑልቼሪያ በላከላቸው ደብዳቤዎች ውስጥ ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ (በኋላ የወንበዴዎች ጉባኤ ያለው) እግዚአብሔርን በመፍራት የተከናወነ ጉባኤ እንደ ነበር ገልጿል፡፡

ሁለተኛው፣ የኤፌሶኑ ጉባኤ (449 እ.ኤ.አ) ከመከናወኑ አስቀድሞ ሊዮ ለአውጣኬ በጻፈለት ደብዳቤ የንስጥሮሳውያንን የሁለት ባሕርያት እምነት ለመቃወም ያደረገውን ጥረት ማድነቁንና ለፍላቪያን በላከው ደብዳቤም አውጣኬን በቅን ልብ እንዲያየው ያሳሰበው መሆኑን ይታወቃል፡፡

ሦስተኛው፣ ሊዮ ጦማሩን ያዘጋጀው ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ ከመከናወኑ አስቀድሞ ሲሆን፣ ንጉሥ ማርሲያንና ንግሥት ብርክልያ ከ450 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡለት አድርጓል፡፡ ይህም ማለት ጉባኤው የተካሄደው በፊርማቸው ያጸደቁትን ጦማር በዓለም አቀፍ ጉባኤ ስም ሕጋዊ ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡

አራተኛው፣ በጉባኤው መጀመሪያ ላይ በሮሙ ጳጳስ ሊዮ የተወከሉ መልእክተኞች “የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የበላይ” ብለው በሚጠሩት በሊዮ በተሰጣቸው ተልእኮ መሠረት ዲዮስቆሮስ ከጉባኤው እንዲወጣ መጠየቃቸውና እርሱ ካልወጣ ጉባኤውን ለቀው እንደሚወጡ ማሳወቃቸው ነው፡፡ በዚህ መሠረት ዲዮስቆሮስ እንዲወጣ ተደረገ፡፡

አምስተኛው፣ በጉባኤው ላይ የተከሰተውና በበርካታ ጸሐፊዎች ትኩረት ያልተሰጠው፣ ዲዮስቆሮስ የተወገዘበት ሒደት ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዲዮስቆሮስን ጉዳይ እንዲመረምር ከተቋቋመው ቡድን ውስጥ አንዱ በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘ፣ በኬልቄዶን ጉባኤ እንዲገባ በመደረጉ ከጳጳሳት ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶበት የነበረና የዲዮስቆሮስ ከሳሽ ተብሎ በጉባኤው እንዲገኝ የተደረገ ሰው ነው፡፡

ስድስተኛ፣ ጉባኤው ከንጉሥና ከሮም ጳጳሳት ተጽዕኖ ነጻና ገለልተኛ አልነበረም፡፡ አስቀድመው ያቀዱትን ሐሳባቸውን ነው ተግባራዊ ያደረጉበት፡፡

ስባተኛ፣ በኬልቄዶን የተሰበሰቡት አባቶች የእምነት መግለጫ ያዘጋጁት በንጉሥ ማርሲዮን ተደጋጋሚ ጫና ነው፡፡ እንዲሁም የእምነት አቋም መግለጫውን እንዲያዘጋጅ የተመረጠው ቡድን አርቅቆ ያቀረበው “አንድ አካል አንድ ባሕርይ” የሚል ሲሆን የፖፕ ሊዎ መልእክተኞች፣ ይህ ሐሳብ “አንድ አካል ሁለት ባሕርያት” በሚል ቃል ካልተተካ በቀር ጉባኤውን ለቀን እንወጣለን በማለታቸው “አንድ አካል አንድ ባሕርይ” የሚለው ወጥቶ “አንድ አካል ሁለት ባሕርያት” በሚል ቃል እንዲተካና እንዲጸድቅ የተደረገ ነው፡፡

ስምንተኛ፡- ጉባኤው የቀደመውን የእምነት መግለጫ ወይም የእምነት መግለጫው የተመሠረተበትን አስተምህሮ ሳያወግዝ ሌላ ዐዲስ መግለጫ ያዘጋጀ ነው፡፡ የቄርሎስን ትምህርት አላወገዘም፣ ዲዮስቆሮስንም ያወገዘው በአስተዳደራዊ ግድፈት እንጂ በትምህርት ችግር አይደለም፡፡ እነዚህ አባቶች የሚያምኑት “አንድ አካል አንድ ባሕርይ” ሲሆን ኬልቄዶን ግን ይህንን ትምህርት ሳያወግዝ ከትምህርቱ ጋር የሚቃረን “አንድ አካል ሁለት ባሕርያት” ብሎ መግለጫ አወጣ፡፡
ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት የኬልቄዶንን ጉባኤ የማይቀበሉበት ምክንያት በአጭሩ ይህን ይመስላል፡፡

ባዩ ታደሰ፣ “ኦርቶዶክሳውያን” የሚፈሩት ኦርቶዶክሳዊ እውነት፡ “የቃላት እንጂ የመሠረተ እምነት ልዩነት የለንም”፣ ህዳር 2013፤ገጽ 53-79

በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ እርዷቸውም ኢያሱ ከግብጽ ከወጡት ሕዝብ መካከል ሙሴን ተክቶ የእስራኤልን ሕዝብ እየመራ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ተስፋይቱ ምድር የገባ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በእግዚአ...
27/12/2015

በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ እርዷቸውም ኢያሱ ከግብጽ ከወጡት ሕዝብ መካከል ሙሴን ተክቶ የእስራኤልን ሕዝብ እየመራ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ተስፋይቱ ምድር የገባ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በእግዚአብሔር የተመረጠና የተጠራ በመሆኑ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር እንደነበረው ሁሉ እርሱም በቀጥታ በመነጋገር ምን ማድረግ እንደሚገባው ግልጽ መመሪያ ይቀበልና የሚያበረታ ቃልን ይሰማ እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ ይህንንም ‹‹... ባሪያዬ ሙሴ ሞቷል አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነስታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህንን ዮርዳኖስን ተሻገሩ፡፡ ለሙሴ እንደነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻለሁ፡፡ ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጢያውያንን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል፡፡ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም አልተውህም፡፡ ለአባቶቻቸው እሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁባቸውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወርሳለህና ጽና አይዞህ፡፡ ነገር ግን ጽና እጅግም በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜ መንገድህ ይቀናልሃል፣ ይከናወንልሃልም፡፡ በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና አይዞህ አትፍራ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን? (ኢያ 1፥1-9) የተባለለትን በማንበብ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ሙሴም በዚያ የዘመኑ ፍጻሜ ላይ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት ‹‹... አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋር እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው እንዲሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ትገባለህና እርስዋንም ለእነርሱ ታወርሳለህና ጽና አይዞህ በፊትህም የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው ከአንተ ጋር ይሆናል አይጥልህም አይተውህም አትፍራ አትደንግጥ›› (ዘዳ 31፥7፡8) እንዳለው እናነባለን፡፡ በእንደዚህ ያለ ሁኔታ የተጠራውና ማረጋገጫ የተሰጠው ኢያሱ ነው ይህንን ታላቅ ኃላፊነትና አደራ ተቀብሎ የእስራኤልን ሕዝብ እየመራ ዮርዳኖስን የተሻገረው፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ምዕራፎችና ቁጥሮች ውስጥ የተገለጠ የተስፋይቱን ምድር ለመውረስ የተዘጋጀ ሕዝብ እንዳለ እሙን ነው፡፡ ስለ ርስት መውረስ ሲታሰብ ይህም ሕዝብ ትኩረት ተሰጥቶት ሊታሰብ ይገባዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ነው በዚህ ስፍራ ሕዝቡ ስላለፈበት የጉዞ ዘመን ታሪክ (ውጣ ውረዱን) ማሳየት የፈለግሁት፡፡ እንደሚታወቀው ሕዝቡ ከአብርሃም ዘር የተገኘ የኪዳን ሕዝብ በመሆኑ አስቀድሞ በተነገረለት የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ለ430 ዓመታት በግብጽ ምድር በባርነት የኖረ፣ እንደ ተስፋ ቃሉም በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ ከግብጽ ባርነት ነጻ ወጥቶ ወደታሰበለትና ወደተዘጋጀለት ምድር እየገሰገሰ ያለ ሕዝብ ነው፡፡መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚያረጋግጥልን ይህ ሕዝብ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፈ በተለይም በምድረ በዳ ይጓዝ በነበረበት ጊዜ በሚያጋጥሙት ጊዜያዊ ችግሮች የተነሳ በማጉረምረም እግዚአብሔርን የተፈታተነ፣ ከ20 ዓመት በታች ያለው ሕዝብ ብቻ ይወርሳታል እንደተባለበት ከ20 ዓመት በላይ የሆነው ከግብጽ ምድር የወጣው ሁሉ ከኢያሱና ከካሌብ በቀር በምድረ በዳ የቀረበት ሕዝብ አካል ነው፡፡ ይህ ሕዝብ ለረጅም ዘመን በምድረ በዳ የተጓዙትን እንዲሁም በዚያ የተወለዱትን ልጆችና ልዩ ልዩ እንስሳትን የያዘ በመሆኑ በጉዞ ያሳለፋቸው እያንዳንዱ ቀናት በተድላና በደስታ የተሞሉ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይልቁንም ‹‹... ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ፤ እኛ ከብቶቻችንም በዚያ እንሞት ዘንድ የእግዚአብሔርን ጉባዔ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁ? ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? ዘርና በለስ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ ነው የሚጠጣም ውሃ የለበትም ...›› (ዘኁ 20፥4-5) እና ‹‹... በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም ውሃ የለም፤ ሰውነታችንም ይህንን ቀላል እንጀራ ተጸየፈ›› (ዘኁ 21፥4፡5) እያሉ ያጉረመርሙ እንደነበር ስናይ ጉዟቸው አልጋ ባልጋ አለመሆኑን በይበልጥ እንረዳለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እየተጓዘ የመጣውን ከቅጣት የተረፈ ቅሬታ ሕዝብ ነው ኢያሱ እንዲመራ የተመረጠውና የተሾመው፡፡ ኢያሱ ይህንን የማበረታቻ ቃል ከሰማ በኋላ ከዮርዳኖስ ወዲህ ማዶ ያለውን የኢያዜርና የገለዓድ ምድር ለመውረስ ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ አልዓዛር እንዲሁም ወደ ማኅበሩ አለቆች መጥተው ጥያቄ አቅርበው የነበሩትንና ያዘዝኸንን እንፈጽማለን ብለው ለሙሴ ቃል ገብተው የነበሩትን ሕዝብ (የሮቤልና የጋድ የምናሴም ነገድ እኩሌታ) እንዲህ በማለት ይናገራቸዋል፡፡ You can download the full version by clicking the free download button below...... ትምህርተ-እግዚአብሔር !! Download Now

http://nigat.net/%e1%89%a0%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8b%b5%e1%88%9e%e1%89%bb%e1%89%bd%e1%88%81-%e1%8d%8a%e1%89%b5-%e1%89%b0%e1%88%bb%e1%8c%88%e1%88%a9-%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%8b%b7%e1%89%b8%e1%8b%8d%e1%88%9d-%e1%8a%a2/

በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ እርዷቸውም ኢያሱ ከግብጽ ከወጡት ሕዝብ መካከል ሙሴን ተክቶ የእስራኤልን ሕዝብ እየመራ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ተስፋይቱ ምድር የገባ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በእግዚአብሔር የተመረጠና የተጠራ በመሆኑ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር እንደነበረው ሁሉ እርሱም በቀጥታ በመነጋገር ምን ማድረግ…

ቤተ ክርቲያን “ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የቤተ ክርስቲያን ምንነት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የተጠሩ ሰዎች ስብስብ ጉባኤ ወይ...
05/11/2015

ቤተ ክርቲያን “ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የቤተ ክርስቲያን ምንነት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የተጠሩ ሰዎች ስብስብ ጉባኤ ወይም ማኅበር ናት እንጂ ሕንፃ ወይም ሌላ አይደለችም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቤት ለመሆን እንደሕያዋን ድንጋዮች በሚገነቡ ምዕመናን የተሞላች መንፈሳዊት ሕንፃ ናት ኤፌ. 2÷20-22 1ኛ ጴጥ.2÷4-5፡፡ ብዙ ብልቶች የያዘች አንድ አካልም ናት 1ኛ ቆሮ.12÷12-27፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ አካል ነች ይህም ሁሉን በሁሉ የሚሞላ ሙላቱ የሚገለጽባት ታላቅ መንፈሳዊ አካል መሆኗን ያመለክታል ኤፌ.1÷22-23፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት የክርስቶስ አካል ናት እንጂ ብዙ አካላት አይደለችም፡፡ ለትምህርተ ሐዋርያት የታመኑ ብዙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለአደረጃጀት እና ምዕመናንን ለመጠበቅ እንዲመች ቢኖሩም ብዙ አካላት ግን አይደሉም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተሠራች በመሆኗ የገሀነም ደጆች አይችሏትም ማቴ.16-18፡፡ ቤተ ክርስቲያን የማን ነች አንዳንዶች በተለምዶ ቤተክርስቲያኔ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይህ ስህተት ሲሆን የቤተክርስቲያን ባለቤት ራሱ የሠራት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ማቴ.16÷18 ኤፌ. 5÷23፣25-27 የሐዋ. 20÷28፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የማንም አይደለችም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ሠሪ እና ራሷም ነው ኤፌ.5÷23፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያን እረኞች አለቃም ነው 1ኛ ጴጥ.5÷2-4፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያን እረኞች ወይም አለቆች (መሪዎች) ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠየቂዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ያለው ዓላማ ያለነውርና እድፍ የሆነች ንጽሕት ቤተክርስቲያን ለራሱ ማቅረብ ኤፌ. 5÷25-27፡፡ በቤተክርስቲያን በኩል ወንጌልን ለሰዎች በማድረስ ደቀመዛሙርት ማድረግ ማቴ.28÷18-20 የሐዋ.ሥራ 1÷7-8፡፡ ለዘላለም በመንግሥቱ የሚኖር አንድ ሰማያዊ ቤተሰብ መፍጠር ኤፌ. 2÷19 የቤተ ክርስቲያን ምግባራት ቤተክርስቲያን ፣ ወንጌልን መስበክ፣ ሥርዓተ ጥምቀትን መፈጸም፣ ያመኑትን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማድረግ ማቴ.28÷18-20፣ ስርዓተ ቁርባንን መፈጸም 1ኛ ቆሮ.11÷23-26፣ ሥርዓተ ጋብቻን መፈጸም፣ ምእመናንን ማነጽ 2ኞ ቆሮ.11÷23-26፣ ሥርዓተ ጋብቻን መፈጸም፣ ምእምናንን ማነጽ 2ኛ ቆሮ.10÷8 እና ባልቴቶችንና ደሃ አደጎችን የመንከባከብ ትልቅ ኃላፊነት አለባት 1ኛ ጢሞ.5÷16 ያዕቆብ 1÷27፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ማኅበረ ምዕመናንና አገልጋዮች ለቤተክርስቲያን መሪዎች ሊታዘዙ ይገባል ዕብ.13÷17፡፡ ቤተ ክርስቲያን በሐሰት ትምህርት የተገኘውን የመለየት ሥልጣንም አላት፡፡ የቤተ ክርስቲያን አራቱ ምልክቶች “ከሁሉ በላይ የምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡ 1. ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ ክርስቶስ አንድ እንደሆነ ሁሉ በምንም ሁኔታ ይሁን ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት (ዮሐ.17÷21) ቤተ ክርስቲያን መከፋፈል አትችልም ከተከፋፈለችም አንድ መሆን አትችልም አንድ መሆን ካልቻለች ቤተ ክርስቲያን መሆን አትችልም፡፡ 2. ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ናት፡፡ ቅድስና የቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮና ባህርይ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን በመቀደሰ በመምራትና በመጠበቅ ሥራ ላይ ነው፡፡ (ኤፌ.5÷26-27) ክርስቶስም በቃሉ እድፈት ነውር እንዳይኖርባት ያነጻታል፡፡ 3. ቤተ ክርስቲያን በሁሉም ስፍራ ያለች ዓለም አቀፋዊት ናት፡፡ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን የዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን አካል ናት፡፡ ( ማቴ.28÷19፣ ማር.16÷8) 4. ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት፡፡ ጌታ ለሐዋርያት አባቴ እኔን እንደላከኝ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ (ዮሐ.20÷21) ጌታ ሐዋርያትን ደቀ መዛሙርት አድርጉ በማለት ታላቅ አደራ ሰጠቷቸዋል፡፡ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፡፡ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ (ኤፌ.2÷20)

http://nigat.net/%e1%89%a4%e1%89%b0-%e1%8a%ad%e1%88%ad%e1%89%b2%e1%8b%ab%e1%8a%95/

ቤተ ክርቲያን “ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የቤተ ክርስቲያን ምንነት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የተጠሩ ሰዎች ስብስብ ጉባኤ ወይም ማኅበር ናት እንጂ ሕንፃ ወይም ሌላ አይደለችም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቤት ለመሆን እንደሕያዋን ድንጋዮች በሚገነቡ…

ክፍል 4 - ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ! ይህ ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ” (ዮሐ 16÷28) የሚለው የጌታ ኢየሱስ ንግግር ለምን መ...
05/11/2015

ክፍል 4 - ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ! ይህ ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ” (ዮሐ 16÷28) የሚለው የጌታ ኢየሱስ ንግግር ለምን መጣ? እንዴት ሆኖ መጣ? ከመጣ በኋላስ? … የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ምናልባትም የክርስቶስን ሰው የመሆን መሠረተ ሃሳብ ያልተረዱትን ሊያስደነግጡ ይችላሉ፡፡ ይሁንና ርዕሰ ጉዳዩን አንስቶ መነጋገርና የጋራ ግንዛቤ መጨበጥ ቸል ሊባል የሚገባው አይሆንም፡፡ [ 173 more words. ]

http://nigat.net/%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8b%a8%e1%88%b1%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ae%e1%8b%8e%e1%89%bd-4/

ክፍል 4 – ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ! ይህ ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ” (ዮሐ 16÷28) የሚለው የጌታ ኢየሱስ ንግግር ለምን መጣ? እንዴት ሆኖ መጣ? ከመጣ በኋላስ? … የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ምናልባትም የ…

ክፍል 3 - በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው! በዮሐንስ ወንጌል በተጻፈልን የምዕራፎች ቅደም ተከተል መሠረት ጌታ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ማስተማር ከጀመረበት ከምዕራፍ 3 አንስቶ እስከ ምዕ...
04/11/2015

ክፍል 3 - በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው! በዮሐንስ ወንጌል በተጻፈልን የምዕራፎች ቅደም ተከተል መሠረት ጌታ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ማስተማር ከጀመረበት ከምዕራፍ 3 አንስቶ እስከ ምዕራፍ 17 ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለ ዘላለም ሕይወት ያልተናገረባቸው ምዕራፎች ቢኖሩ አራት ምዕራፎች (9፣ 13፣ 15 እና 16) ብቻ ናቸው፡፡ ታዲያ በሌሎቹ 11 ምዕራፎች ውስጥ ስለ ዘላለም ሕይወት ማስተማሩን ስናይ እርሱ የመጣበት ዓላማ ምን እንደ ሆነና ዓላማውንም ከግቡ ለማድረስ ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሠራ የሚያስገነዝብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የጌታችንን የማስተማር ሂደት ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ ለሚጠየቀው ጥያቄ ነው ወይም አይደለም የሚል መልስ በመስጠት ፋንታ ጥያቄያቸውን መሠረት አድርጎ እርሱ የመጣበትን ዓላማና የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማሳወቅ ላይ ማተኮሩ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ነው ኒቆዲሞስ ባቀረበለት የውይይት መክፈቻ ላይ ተነስቶ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ የሚሆን ጥርትና ግልጽ ያለ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ዓላማ የሚያሳይ መሠረታዊ የዳግም ልደትን አስፈላጊነት የሚያስገነዝብ መልዕክት በማስተላለፍ ገለጻውን ያጠናቀቀው፡፡ በዚህ ክፍል ጌታ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም፡፡ ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው (ዮሐ 3÷12) በማለት ስለ ማንነቱ እንደ ገለጠለትም እንረዳለን፡፡ ኒቆዲሞስ ቢገባውም ባይገባውም ደግሞም ቢቀበለውም ባይቀበለውም ከሰማይ ስለ መጣሁ የምነግርህ ነገር ሰማያዊ ነው ይህንንም ሊነግርህ የሚችል ከእኔ በቀር ሌላ ማንም የለም፤ እኔም የምነግርህ የሰማሁትንና የማውቀውን ነውና ንግግሬ እውነት ነው እያለ ነው ያስገነዘበው፡፡ ሆኖም ኒቆዲሞስ አሁንም እየተነገረው ያለውን ሊረዳው ስላልቻለ ጌታ ትምህርቱን በመቀጠል ‹‹በምድረ በዳ ሙሴ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል፡፡ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና፡፡ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አላከውምና (ዮሐ 3÷14-17) በማለት እርሱ ከሰማይ የመጣበትን አብም ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የላከበትን ፈቃዱንና ዓላማውን ሌላ ማስረጃ ተጠቅሞ ሲያብራራለት እንመለከታለን፡፡ ጌታችን በምዕራፍ 4 በያዕቆብ ጉድጓድ ዘንድ ላገኛት ሰማርያዊት ሴት የገለጠላት የከበረ እውነትም ይህንኑ ዘላለማዊ ፈቃድና ዓላማውን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በትምህርቱ ውስጥ እንደምናገኘው ሴቲቱ ከያዕቆብ ዘር ናት፤ ምንም እንኳ የትና እንዴት እንደሚከናወን ግራ ብትጋባም ለእግዚአብሔር ስግደት (አምልኮ) ሊፈጸምለት እንደሚገባ ታውቃለች፡፡ ክርስቶስ የሚባል መሲህ እንደሚመጣም ግንዛቤ አላት፡፡ ይህች ሴት አለኝ በምትለው ዕውቀቷ ላይ ተመስርታ ነው ኢየሱስን የምትሞግተው፡፡ ሴቲቱ ያዕቆብን ብታውቅና አባታችን እያለች ብትመካም ከዚያም አልፋ ኢየሱስ ይሰጥሽ ነበር እያለ ከሚነግራት የዘላለም ሕይወት ውሃ ይልቅ ያዕቆብና ልጆቹ ከብቶቹም የጠጡት ውሃ ይበልጣል እያለች የእርሷ ውሃ እርሱ ከሚሰጣት የሚሻል እንደ ሆነ ለመግለጽ ብትደክምም ጌታ የዚህችን ሴት ጉድለትና የሚያስፈልጋትን ያውቃልና በትዕግስት ነው ያናገራት፡፡ ምክንያቱም ሴቲቱ አለኝ እያለች የደረደረቻቸው ነገሮች ሁሉ ተደማምረው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊያደርሷት እንደማይችሉ ያውቃልና ነው፡፡ ሴቲቱ ግን ይህንን አልተገነዘበችም ነበር፡፡ ሴቲቱ በተመካችበት መንገድ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መድረስ ቢቻል ኖሮ ክርስቶስ ለዚች ሴት ስለ ሕይወት ውሃ ማውራት አያስፈልገውም ነበር፡፡ እርሷ ተስፋ በምታደርጋቸው መንገዶች ወደ እግዚአብሔር ሃሳብ መድረስ ስለማይቻል ነው ኢየሱስ ግን ጉድለት አለብሽ ይህ ጉድለትሽ የሚሞላው ደግሞ በእኔ ስታምኚ ነው፤ እኔም ይመጣል እያልሽ የምትጠብቂው ክርስቶስ ነኝ፤ እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘላለም አይጠማም፡፡ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እያለ የነገራት፡፡ ዛሬም ብዙዎች እንደዚች ሰማርያዊት ሴት የሚያስቆጥሩት የዘር ሃረግና የተነገረላቸው የተስፋ ቃል እንኳ ሳይኖራቸው በተረት ተረት የተቀመረ የአይሁድነት ታሪክ እየደረደሩ ለእግዚአብሔር ቅርብ ወዳጆችና የመንግስቱም ባለ መብቶች እንደ ሆኑ የሚናገሩ ሁሉ የዘር ሃረግ ወይም ከኢየሱስ ውጭ የሆነ ዕውቀት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ቅንጣት ያህል ጠቀሜታ እንደማይኖራቸው ከሰማርያዊቱ ሴት ሊማሩ ይገባቸዋል፡፡ You can download the full version by clicking the free download button below...... በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው!! Free Download

http://nigat.net/%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8b%a8%e1%88%b1%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ae%e1%8b%8e%e1%89%bd-3/

: Missing argument 2 for wptr_supress_title() in /home/nigatcom/public_html/wp-content/plugins/title-remover/title-remover.php on line 16

ክፍል 2 - እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ!      በኒቆዲሞስ ምክንያት ጌታ ኢየሱስ ለዓለም የገለጠው አንዱ እውነት እርሱ ‹‹የዓለም ብርሃን›› መሆኑን የሚያስገነዝበው ትምህርቱ ነው፡፡ እንደሚታ...
25/08/2015

ክፍል 2 - እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ! በኒቆዲሞስ ምክንያት ጌታ ኢየሱስ ለዓለም የገለጠው አንዱ እውነት እርሱ ‹‹የዓለም ብርሃን›› መሆኑን የሚያስገነዝበው ትምህርቱ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ብርሃን የሚያስፈልገው ሊታይ የሚገባውን ወይም የሚያስፈልገውን ነገር እንዳይታይ የሚጋርድ ወይም የሚከለክል ጨለማ ሲኖር ነው፡፡ በሕይወት ተሞክሯችን እንደምናውቀውም እንዲህ ዓይነቱን ጨለማ ለማስወገድና አጥርተን ለማየት ልዩ ልዩ የብርሃን ምንጮችንም እንጠቀማለን፡፡ በዚህ ክፍል የምንመለከተው ስለ ብርሃን የተሰጠ ትምህርት ግን እኛ ከምናውቀው የቀን ብርሃን የተለየ ነው፡፡ ጨለማ ተብሎ የተጠቀሰውም ጨለማ እና የምንገነዘበው የቀንን ብርሃን የሚተካው ጨለማ አይደለም፡፡ ይህንን ለማስተዋል እንዲያግዘን እስኪ ክፍሉ የሚለውን እናንብብ፡፡ ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው፡፡ ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና ሥራው እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፡፡ እውነት የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል (ዮሐ 3÷19-21) ይላል፡፡ ከዚህ የወንጌል ክፍል እንደምንገነዘበው በኒቆዲሞስና በጌታ በኢየሱስ መካከል የተደረገው ውይይት የሚጠናቀቀው በቁጥር 21 ላይ ጌታ ስለ ብርሃን ባስተላለፈው መልእክት ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ስለ ራሱ ማንነት ከገለጸባቸው ቃላት መካከል አንዱ የሆነው ‹‹ብርሃን›› በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ በጌታ የተጠቀሰውም በዚህ ክፍል ነው፡፡ የዚህን ክፍል መልእክት በተገቢው ሁኔታ ለመረዳት ጌታ ኢየሱስ እርሱ እውነተኛ ብርሃን እንደ ሆነ በአጽንዖት ከገለጠባቸው ተጨማሪ ክፍሎች ማየት ይጠቅማልና እነሆ፡፡ በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ (ዮሐ 12÷42) ፤ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም (ዮሐ 8÷12)፤ በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ (ዮሐ 9÷5) ከእነዚህ ከጠቀስኋቸው ክፍሎች ጌታ ኢየሱስ እርሱ የዓለም ብርሃን እንደ ሆነ ሲናገር እየተናገረ ያለው እኛ ብርሃንና ጨለማ እያልን ስለምንጠራው ተፈጥሯዊ ክስተት አለመሆኑንና በአንጻሩ ሰው በመበደሉ የተነሳ በሕይወቱ ውስጥ የተፈጠረውን ክፉና አመጸኛ ባህርይና ድርጊቱን (መንፈሳዊውን ጨለማ) ገልጦ የሚያሳይ የሚወቅስና፣ የሚያስተካክል የሕይወት ብርሃን መሆኑን እንደሆነ በቀላሉ እንገነዘባለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዲያቢሎስን የዚህ የጨለማው ዓለም ገዢ ይለዋልና (ኤፌ 6÷12) በዚህ ክፉ ገዢ ፈቃድና ዓላማ ሥር የሚኖረው ዓለም ነው ጨለማ ተብሎ በጌታ ኢየሱስ የተገለጠው፡፡ እንደ ጌታ ኢየሱስ አገላለጽ ሰው በተፈጥሯዊው ብርሃን ውስጥ እየኖረ በቀላሉ ሊለየው ያልተቻለው ጨለማ አለ፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ ሰው እንደ እግዚአብሔር ሃሳብና ፈቃድ የሚኖር ካልሆነ በብርሃን አለሁ እያለ የሚኖረው በጨለማ ውስጥ ነው ማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሐዋርያው ጳውሎስ በንጉስ አግሪጳ ፊት ቀርቦ ስለ ራሱ ባስታወቀበት ንግግር ውስጥ የምናስተውለው ሕዝብን ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር ለማድረግ የተጠራ መሆኑን ነው (ሐዋ 27÷17-18) ፡፡ በዚህ ክፍልም የምናስተውለው ጨለማው የሰይጣን ግዛት (ሥልጣን) ወይም ከእግዚአብሔር የተለየው አኗኗር እንደሆነ በግልጽ እንገነዘባለን ወንጌላዊው ማቴዎስ የነቢዩ ኢሳይያስን ‹‹… በዮርዳኖስ ማዶ የአህዛብ ገሊላ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው›› የትንቢት ቃል ወስዶ ትንቢቱ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተፈጸመ ያስረዳል (ማቴ 4÷14-16)፡፡ ታዲያ ከዚህ የክርስቶስ ትምህርት የምንገነዘበው በእርሱ የሚያምን ሁሉ ከዚያ የጨለማ አኗኗር (ከዲያቢሎስ አገዛዝ) ነጻ ወጥቶ በብርሃኑ በእርሱ በማመን በሕይወት ይኖር ዘንድ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ እያለ የሚያሳስብ መሆኑን ነው (ዮሐ 12÷36)፡፡ ሐዋርያትም ‹‹እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያቢሎስ የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ›› (ሐዋ 10÷38)፣ ‹‹እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ስልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር ይኸውም ዲያቢሎስ ነው በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ›› (ዕብ 2÷14) እና ‹‹ስለዚህ የዲያቢሎስን ሥራ ሊያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ›› (1ኛ ዮሐ 3÷8) እያሉ ያወጁልን ይህንኑ መሠረተ ሃሳብ ለማስገንዘብ ነው፡፡ ካነሳሁት ሃሳብ በተጨማሪ ጌታ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ባስተማረው በዚህ የወንጌል ክፍል ውስጥ ትኩረት ሰጥተን ልንመለከታቸው የሚገቡን ሃሳቦች አሉ፤ እነዚህም፦ + ብርሃን ወደ ዓለም ስለ መጣ + ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ + ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና ሥራው እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም እና + እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል የሚሉት ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣው ሰዎች በጨለማው እንዳይኖሩ የሕይወት ብርሃን ለመሆን ቢሆንም እነርሱ ግን ከብርሃኑ ይልቅ ጨለማውን በመውደድ ለብርሃኑ ያላቸውን ጥላቻና ለጨለማው ስልጣን ያላቸውን ታማኝነትና ተገዢነት ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ይህንንም ለሕይወት ወደ ጠራቸው ጌታ ከመምጣትና በእርሱ ሃሴት ከማድረግ ይልቅ ስቀለው፣ አስወግደው እያሉ በመጮህና በርባን እንዲፈታላቸው በመጠየቅ አረጋግጠዋል፡፡

http://nigat.net/%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8b%a8%e1%88%b1%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ae%e1%8b%8e%e1%89%bd-2/

ክፍል 2 - እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ!      በኒቆዲሞስ ምክንያት ጌታ ኢየሱስ ለዓለም የገለጠው አንዱ እውነት እርሱ ‹‹የዓለም ብርሃን›› መሆኑን የሚያስገነዝበው ትምህርቱ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ብርሃን የሚያስፈልገው ሊታይ የሚገባውን ወይም የሚያስፈልገውን ነገር እንዳይታይ የሚጋርድ ወይም የሚከለክል ጨለማ ሲኖ...

Address

USSR
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nigat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share