ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር

ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር ይህ የፌስቡክ ገፅ የደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ ገፅ ነው።

24/07/2024
2 ቀን ቀረው
23/07/2024

2 ቀን ቀረው

ኑ አብረን እንጓዝ የገጠሪቱንም ቤተክርስቲያን እንጎብኝ
22/07/2024

ኑ አብረን እንጓዝ
የገጠሪቱንም ቤተክርስቲያን እንጎብኝ

እባክዎ ለሁሉም ሼር በማድረግ መረጃውን ያድርሱልን።
10/11/2022

እባክዎ ለሁሉም ሼር በማድረግ መረጃውን ያድርሱልን።

በደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበርና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ታኅሣሥ 02 / 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ለሚደረገው መንፈሳዊ ጉባዔ የመግባቢያ ሰነድ የመፈራረም ስነ ሥርዓት...
07/11/2022

በደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበርና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ታኅሣሥ 02 / 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ለሚደረገው መንፈሳዊ ጉባዔ የመግባቢያ ሰነድ የመፈራረም ስነ ሥርዓት ተካሂዷል።

በዚህ የስምምነት ፊርማ ላይ ከደጆችሽ አይዘጉ የማኅበሩ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጆኒ ግርማ እና ከማኅበረ ቅዱሳን የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ አማካኝነት በሁለቱ ማኀበራት መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈጽሟል።

በመግለጫቸውም የሚዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባዔ ''ኅብረታችን ለቤተ ክርስቲያናችን'' በሚል መሪ ቃል የሚከወን ሲሆን በዕለቱም ስለሀገራችንና ቤተ ክርስቲያናችን በብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ፣ በገዳማት አባቶችና የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ ምዕመናን የተሳተፉበት የፀሎት መርኃ ግብር ይደረጋል ብለዋል።

ከዚህ ጉባዔ የሚገኘው ገቢም በጅማ ሀገረ ስብከት ለሚደረጉ የቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንደሚውል በመጠቆም ሕዝበ ክርስቲያኑም የተለመደውን አብሮነት በዚህ ለዚህ ሰናይ ምግባር በማሳየት የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ጥቅምት 28/2015 ዓ.ም

“ኅብረታችን ለቤተ ክርስቲያናችን” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ ታኅሣሥ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ታላቅ ጉባኤ ሊከናወን ነው፡፡“ኅብረታችን ለቤተ ክርስቲያናችን” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም ...
06/11/2022

“ኅብረታችን ለቤተ ክርስቲያናችን” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ ታኅሣሥ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ታላቅ ጉባኤ ሊከናወን ነው፡፡

“ኅብረታችን ለቤተ ክርስቲያናችን” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ ታኅሣሥ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ታላቅ ጉባኤ ለማከናወን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመክፈቻ መግለጫ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ሰጥተዋል፡፡

የጉባኤው አዘጋጆች ማኅበረ ቅዱሳን እና ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበራት ሲሆኑ ዓላማው ኦርቶዶክሳዊ ኅብረታችንን በማጠናከር ስለ ሀገር፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ስለ ወገኖቻችን በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ የጸሎትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ማካሄድ ነው፡፡ ገቢውም ለጅማ ሀገረ ስብከት ማኅበራቱ ለሚያከናውኑት መንፈሳዊ አገልግሎት የሚውል መሆኑ ተነግሯል፡፡

የመክፈቻ መግለጫው ላይ የተገኙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንደገለጹት “ማዕተቤ ከሚበጠስ አንገቴ ይበጠስ" ብለው ሊቆርቡ የሄዱ ሞተው የቀሩበትን ሀገረ ስብከት እንድንረዳና የሞቱለት ክርስትና እንደገና እንዲያብብ የቀረበ ጥሪ በመሆኑ ሁላችንም መገኘት ይኖርብናል” በማለት ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ኅብረት በአለመኖሩ ምክንያት በሀገር ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ችግር አጋጥሞናል፡፡ እንዲሁም ዘመኑና ትውልዱ በአለመገናኘታቸው ሊከፈት የሚገባው ብዙ ቤተ ክርስቲያን ተዘግቶ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ተግዳሮቱ ቢበዛም መልካም ዕድልም አለውና ያላየነውን እንድናይ፣ ደክመን ከሆነ እንድንነቃ፣ ሰንፈን ከሆነ እንድንበረታ ያደርገናልና ማኅበራቱ ለእግዚአብሔር በመታዘዝና የአባቶችን ፈቃድ በማስቀደም ይህንን ታላቅ ጉባኤ እንዲዘጋጅ ማድረጋችሁ መልካም ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በየቤታችን ሆነን ስለቤተ ክርስቲያናችን ጉድለት፣ ስለ ምእመኑ ጉዳት ሁሉ የምናስብ ቢሆንም የገጠሪቱን ቤተ ክርስቲያን ሄዶ መጎብኘት ባይቻልም ማኅበራቱ በአዘጋጁት ጉባኤ መገኘት እና አስተዋጽዖ ማድረግ ሄዶ እንደመጎብኘት ነውና ሁላችንም ልንገኝ ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

''ጥበብን አግኝ፣ማስተዋልንም አግኝ።'' ምሳ 4፣5ሁሉም ሊሳተፍበት የሚገባ ልዩ የሆነ ስልጠና ልባም ሕይወት የስልጠና ተቋም ከደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር ጋር በመተባበር የ...
28/10/2022

''ጥበብን አግኝ፣ማስተዋልንም አግኝ።'' ምሳ 4፣5

ሁሉም ሊሳተፍበት የሚገባ ልዩ የሆነ ስልጠና
ልባም ሕይወት የስልጠና ተቋም ከደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ

እሑድ ጥቅምት 20 /2015 ዓ.ም ከ5 :00 ሰዓት ጀምሮ

ካዛንቺስ በሚገኘው ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን 5ኛ ፎቅ ላይ

እባክዎ ስለሚጠቀሙበት እርስዎም ተገኝተው ወዳጆችዎን ይጋብዙ።

ስልጠናው በNLP ዘርፍ ከ15 ዓመት በላይ ልምድ ባለው ባለሙያ ይሰጣል።

ለበለጠ መረጃ +251910669676 ወይም +251912033021 ይደውሉ።

ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር።

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር።
26/09/2022

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።

ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር።

''በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ'' መዝ 64 ፣ 11እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ አሸጋገራችሁ እያልን መጪው ዓመት ለሀገራችን ሰላም ለሕዝቦቿም አንድነት ለቤተክርስቲ...
10/09/2022

''በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ'' መዝ 64 ፣ 11

እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ አሸጋገራችሁ እያልን መጪው ዓመት ለሀገራችን ሰላም ለሕዝቦቿም አንድነት ለቤተክርስቲያንም ክብር የሚሆንበት እንዲሆን እየተመኘን አበባን በሜዳ የሚያፈካ ፣ ዘመንንም በዘመን የሚተካ እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዓመት ያድርግልን።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት ሕክምናዎን ጨርሰው ወደ መንበርዎ ስለተመለሱ የተሰማንን መንፈሳዊ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለ...
06/09/2022

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት ሕክምናዎን ጨርሰው ወደ መንበርዎ ስለተመለሱ የተሰማንን መንፈሳዊ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን። በቀጣይም በሙሉ ጤንነት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንዲመሩ በመመኘት ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንና ኢትዮጵያን እንኳን ደስ ያለን እንላለን።

ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር።
ፎቶ:- ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስቲንግ

ሰብስክራይብ በማድረግ አገልግሎታችንን ይደግፉ።ትምሕርቱን ተመልክተው ሼር በማድረግ ሌሎች እንዲማሩበት ያድርጉ።ያልናችሁን ስለምታደርጉልን አስቀድመን ለማመስገን እንወዳለን።
30/08/2022

ሰብስክራይብ በማድረግ አገልግሎታችንን ይደግፉ።

ትምሕርቱን ተመልክተው ሼር በማድረግ ሌሎች እንዲማሩበት ያድርጉ።

ያልናችሁን ስለምታደርጉልን አስቀድመን ለማመስገን እንወዳለን።

በቤተ ክርስቲያናችን የቅዳሴ ክፍል ላይ ከቅዱስ ቁርባኑ የማይቀበል ይሰደድ የሚል ቃል ቃለ፡፡ በቤተ ክርስቲያችን ደግሞ አሁናዊ ሁኔታው አስቀድሶ ከሚቆርበው በአንጻራዊነት አስቀድሶ ሳ...

ደጆችሽ አይዘጉ ዓመታዊ የአባላት አጠቃላይ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት አደረገበአዲስ አበባ ዋናው ማዕከል ጽ/ቤት ማኅበሩ ጠቅላላ የዓመታዊ ጉባዔውን ያከናወነ ሲሆን በዚህ ጉባዔ ላይ የዋና ማዕከል...
28/08/2022

ደጆችሽ አይዘጉ ዓመታዊ የአባላት አጠቃላይ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት አደረገ

በአዲስ አበባ ዋናው ማዕከል ጽ/ቤት ማኅበሩ ጠቅላላ የዓመታዊ ጉባዔውን ያከናወነ ሲሆን በዚህ ጉባዔ ላይ የዋና ማዕከል አባላት ፣ የጅማ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚዎች ፣ የሊሙ ገነት ንዑስ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚዎች ፣ የአጋሮ ንዑስ ማዕከል ተወካዮች ተገኝተው የ2014 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል። አያይዘውም እያንዳንዱ ማዕከልና ክፍላት የ2015 ዓ.ም ዕቅዳቸውን አቅርበው በጠቅላላ ጉባዔ አጸድቀዋል።

በዚህም ጉባዔ ካህናት አባቶች ፣የማኅበሩ ጠቅላላ አባላት አባላት ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈውበት በማኅበራችን አጠቃላይ የአገልግሎት ሂደት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ምክክር ተደርጓል። በዚህ ጉባዔ ላይ ማኅበራችንን በላቀ ደረጃ ለረዱን የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። አንድነታችንን የሚያጸናውን የጋራ ማዕድ ተቋድሰን ደስ በሚል ሁኔታ መርኃ ግብራችንን አጠናቀናል።

ይህ ጠቅላላ የአባላት ጉባዔ እንዲሳካ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share