Muslim Ummah ሙስሊም ኡማህ

Muslim Ummah ሙስሊም ኡማህ ለሙስሊም ኡማህ ኢስላማዊ ዳእዋ ፣ከተላያዩ አሊምችና ኡስታ?

 ክፍል_2 አላህ እንዲህ ብሏል፦"አላህም ነፍሱን (ቁጣውን) ያስጠነቅቃችኋል።" (አል_ዒምራን፡ 28)  #ሐዲሥ 50/398  ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እ...
27/11/2025



ክፍል_2

አላህ እንዲህ ብሏል፦

"አላህም ነፍሱን (ቁጣውን) ያስጠነቅቃችኋል።" (አል_ዒምራን፡ 28)

#ሐዲሥ 50/398

ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ጀሀነም በመጭው ዓለም ሰባ ሺህ ልጓም ያላት ሆናና እያንዳንዱን ልጓም ሰባ ሺህ መላኢክት ይዞት፥ እየተጎተተች ትቀርባለች፡፡" (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር

፨ ገለጻው እውነተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ የጀሀነምን ታላቅነትና አስፈሪነት ለመግለጽ የቀረበ ምሳሌያዊ አነጋገር ሊሆንም ይችላል። ዞሮ ዞሮ የተፈለገው የሰው ልጅ በመጭው ዓለም የሚጠብቀው እጣ ፈንታ ሊያስፈራው እንደሚገባ ማስታወስ ነው።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

   አላህ እንዲህ ብሏል፦(وَإِيَّـٰىَ فَٱرْهَبُونِ ﴿٤٠﴾)"እኔንም ብቻ ፍሩ።"  (አል_በቀራህ፡ 40)  #ሐዲሥ 50 / 397 የእውነተኞች ሁሉ እውነተኛ የሆኑት የአላህ መል...
26/11/2025





አላህ እንዲህ ብሏል፦

(وَإِيَّـٰىَ فَٱرْهَبُونِ ﴿٤٠﴾)
"እኔንም ብቻ ፍሩ።" (አል_በቀራህ፡ 40)

#ሐዲሥ 50 / 397

የእውነተኞች ሁሉ እውነተኛ የሆኑት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ነግረውናል በማለት ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል ፦ "ከእናንተ አንዳችሁ የሚፈጠርበት ነገር ከእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀናት (የዘር) ፈሳሽ ሆኖ ይቆያል። ከዚያም ለተመሳሳይ ጊዜ የረጋ ደም ይሆናል። ከዚያም ለተመሳሳይ ጊዜ የተላመጠ ሥጋ ይሆናል። ከዚያም መላኢካ ተልኮ ነፍስ ይዘራበታል። (መላኢካ) አራት ነገሮች ይታዘዛል። ሲሳዩን፣ የሚሞትበትን ወቅት፣ ሥራውንና እድለቢስ (ሸቂይ) ወይም እድለኛ (ሰዒድ) መሆኑን (እንዲጽፍ)። ከርሱ ውጭ ሌላ አምላክ በሌላው (አምላክ) እምላለሁ! ከእናንተ አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል አንድ ክንድ ያክል ርቀት እስኪቀረው ድረስ የጀነት ሰዎችን ሥራ ሲሠራ ይቆያል። (ትንሽ ሲቀረው) የተጻፈበት ይቀድመውና የእሳት ሰዎችን ሥራ በመሥራት እሳት ይገባል። ከእናንተ አንዳችሁ የእሳት ሰዎችን ሥራ ሲሠራ ይቆይና (ሊገባበት) አንዲት ክንድ ሲቀረው የተጻፈው ቀድሞት የጀነት ሰዎችን ሥራ በመሥራት ጀነት ይገባል።" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ በቀዷ ቀደር _መልካምም ሆነ ክፉ_ ሁሉም ነገር ከአላህ እንደሆነ ማመን ያሻል።
2/ ሐዲሡ ወደ መልካም ሥራ ሰዎች እንዲሽቀዳደሙና በርሱው እንዲዘወትሩ ያነሳሳል።
3/ የሰዎች ስኬታማነት የሚለካው በፍጻሜያቸው ነው። እናም በተሠሩት መልካም ሥራ መኮፈስ መዝናናት የሚቻልበት ሁኔታ የለም።
4/ አንድ መልካም ሥራ የሠራ ሰው ንጹሕ እንደሆነ ሊያቆየው ይገባል። በክፉ ሥራ ሊበክለው አይገባም።
5/ ሁሌም በአላህ መታገዝ፣ ፍጻሜ እንዲያምር አላህን መጠየቅ፥ ክፉ ፍጻሜን መፍራትና ከርሱ በአላህ መጠበቅ ያስፈልጋል።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #የሰዎችን  #ውጫዊ  #እንቅስቃሴና  #ተግባር ( #አምኖ)  #መቀበልና  #ውስጣቸውን  #ለአላህ  #መተው    #ሐዲሥ 49 / 396  ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዐ) ተከታዩን ሲናገሩ አድም...
25/11/2025

#የሰዎችን #ውጫዊ #እንቅስቃሴና #ተግባር ( #አምኖ) #መቀበልና #ውስጣቸውን #ለአላህ #መተው



#ሐዲሥ 49 / 396

ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዐ) ተከታዩን ሲናገሩ አድምጫለሁ በማለት ዐብደላህ ኢብኑ ዑትባህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ)፥ አስተላልፈዋል፦ “በነቢዩ (ﷺ) የሕይወት ዘመን የሰዎች (እውነተኛ) ማንነት በራዕይ (ወሕይ) ይገለጽ ነበር። ራዕዩ (ወሕዩ) ተቋርጧል። ስለዚህም አሁን ማንነታችሁን የምንወስነው በገሃድ በምናየው ሥራችሁ ነው። መልካም (ባሕሪና ተግባር) ያሳየንን እናምነዋለን። እናቀርበዋለን። ውስጡን የመፈተሽ መብት አልተሰጠንም። ውስጡን አላህ ይፈትሸዋል። ክፉ (ባሕሪና ተግባር) ያሳየንን ደግሞ አናምነውም። እውነት ብለን አንቀበለውም። ውስጡ መልካም እንደሆነ ቢናገረም። (ቡኻሪ ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ሰዎችን በግልጽ ከሚያሳዩት ባሕሪና ሥራ አንጻር ብቻ እስልምናቸውን መቀበል ግድ ነው። ውስጥን መፈተሽ የሰዎች መብት አይደለም።
2/ መልካም ኒይያ (ልበ-ውሳኔ) ከሸሪዓዊ ቅጣት አያድንም።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #የሰዎችን  #ውጫዊ  #እንቅስቃሴና  #ተግባር ( #አምኖ)  #መቀበልና  #ውስጣቸውን  #ለአላህ  #መተው    #ሐዲሥ 49 / 395  ጁንዱብ ኢብኑ ዐብደላህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፥ የ...
24/11/2025

#የሰዎችን #ውጫዊ #እንቅስቃሴና #ተግባር ( #አምኖ) #መቀበልና #ውስጣቸውን #ለአላህ #መተው



#ሐዲሥ 49 / 395

ጁንዱብ ኢብኑ ዐብደላህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፥ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ የሙስሊሞች ጦር ወደ አጋሪዎች አዘመቱ። (ሁለቱ ኃይሎች) ተገናኙ። ከአጋሪዎች መካከልም ከሙስሊሞች አንዱን (በመግደል) ከፈለገ የሚገድል (አልሞ የማይስት) አንድ አጋሪ ነበር። ከሙስሊሞች መካከል አንዱ _ ኡሳማ ኢብኑ ዘይድ ነው ብለን እናስባለን_ ሰውየው እስኪዘናጋ ጠብቆ (ሊገድለው) ሰይፍ ሲያነሳ (አጋሪው)፦ “ላ ኢላሀ ኢልለላህ” አለ። ግና ገደለው። ብስራት (መልዕክት) ነጋሪው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ ቀረበ። ጠየቁት፡፡ የሆነውን ሁሉ ይነግራቸው ጀመር። የሰውየውን ሁኔታና ምን እንደ ፈፀመ ሲነግራቸው (ገዳዩን) ጠርተው “ለምን ገደልከው?” ሲሉ ጠየቁት፡፡ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሙስሊሞችን አወከ። እገሌን፥ እገሌን ገደለ” በማለት ስሞችን ዘረዘረላቸው። “ዘመትኩበት፡፡ ሰይፍ ሲያይ ላ ኢላሀ ኢልለላህ አለ” ሲልም (ምክንያቱን) ነገራቸው። የአላህ መልዕክተኛም፥ “ገደልከውን?” አሉት፡፡ “አዎ” አላቸው። “በዕለተ ትንሳኤ ላ ኢላሀ ኢልለላህ ስትመጣ ምን ልታደርጋት ነው?” አሉት፡፡ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምሕረት ይጠይቁልኝ” አላቸው። “በዕለተ ትንሳኤ ላ ኢላሀ ኢልለላህ ስትመጣ ምን ልታደርጋት ነው?” ከማለት ውጭ ያከሉት ነገር የለም። (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር

፨ ይህና ከዚህ ቀደም የተወሳው ሐዲሥ የሚተርኩልን አንድ ዓይነት ክስተት እንደሆነ ዑለሞች ይናገራሉ። የትረካ ስልቱ የተለያየው ሐዲሡን ያስተላለፉት ግለሰቦች በመለያየታቸው ነው። ስለዚህ ለላይኛው ሐዲሥ የተዘረዘሩ አስተምህሮዎችን ይህም ሐዲሥ ያስተምራል።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #የሰዎችን  #ውጫዊ  #እንቅስቃሴና  #ተግባር ( #አምኖ)  #መቀበልና  #ውስጣቸውን  #ለአላህ  #መተው    #ሐዲሥ 49 / 394ኡሳማ ኢብኑ ዘይድ (ረ.ዐ) ተከታዩን አስተላልፈዋል፦ የ...
23/11/2025

#የሰዎችን #ውጫዊ #እንቅስቃሴና #ተግባር ( #አምኖ) #መቀበልና #ውስጣቸውን #ለአላህ #መተው



#ሐዲሥ 49 / 394

ኡሳማ ኢብኑ ዘይድ (ረ.ዐ) ተከታዩን አስተላልፈዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የጁሀይና ጐሣ አባል ወደ ሆነው ጁሀይና ወደ ተባለ ጦር አዘመቱን። ሰዎችን በጧት መጣንባቸው (ማልደን ዘመትንባቸው)። እኔና አንድ የአንሷር ሰው ከነርሱ ከሆነ አንድ ሰው ጋር (ፍልሚያ) ተገናኘን። ስንከበው “ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም” አለ። የአንሷሩ ሰው እጁን ሰበሰበ። እኔ ግን በጦር ወግቼ ገደልኩት፡፡ መዲና ስንገባ ይህ (ድርጊቴ) ለነቢዩ (ﷺ) ተነገራቸው። “ኡሳማ ሆይ! ላ ኢላሀ ኢልለላህ ካለ በኋላ ገደልከውን?” አሉኝ። “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ያላት እኮ ከግድያችን ለመጠበቅ ነው” አልኳቸው። “ላ ኢላሀ ኢልለላህ ካለ በኋላ ገደልከውን?” አሉኝ በድጋሜ። ከዚያን ቀን በፊት ባልሰለምኩ ብዬ እስክመኝ ድረስ (ይህን ጥያቄ) ደጋገሙት፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)

በሌላ ዘገባ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)፦ “ላ ኢላሀ ኢልለላህ ካለ በኋላ ገደልከውን?” አሉኝ። “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ያላት ሰይፍ ፈርቶ ነው” አልኳቸው። “የተናገራት ከአንጀቱ ይሁን ከአንገቱ ልቡን ከፍተህ አይተኸዋልን?” አሉ። የሰለምኩት የዚያኑ ቀን በሆነ ብዬ እስክመኝ ድረስ (ይህን አባባል) ደጋገሙት፡፡

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አንድ ሰው መስለሙን ለመቀበል ግልጽ ቃል ወይም ተግባር ማየቱ በቂ ነው። ውስጥን መፈላፈል አግባብ አይደለም። ይህ ሸሪዓዊ ድንጋጌ “ውስጡ አልሰለመም ይሆናል” በሚል ሰበብ ብቀላ ለሚሹ ወገኖች መንገድ ለመዝጋት ነው።
2/ የአላህ መልዕክተኛ በኡሳማ ላይ የሞት ብይን (ቂሷስ) ያላስተላለፉት ነገሩ ግልጽ ስላልሆነለት (ሹብሃ ስለነበረበት) ነው። የሞት ቅጣት በእንዲህ ዓይነት ሹብሃዎች ይቀራል። ይሁንና የደም ካሳ (ዲያህ) አይቀርም።
3/ ታላቅ ወንጀል የሠራ “ከዚያ በፊት ባልሰለምኩ” ብሎ መመኘት አይፈቀድለትም። ኡሳማ ይህን ያለው _ የሚፈቀድ ሆኖ ሳይሆን _ ከነቢዩ ጠንካራ ውግዘት የተነሳ ልቡ በፍርሃት ስለራደና ስለተጨነቀ ነው።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #የሰዎችን  #ውጫዊ  #እንቅስቃሴና  #ተግባር ( #አምኖ)  #መቀበልና  #ውስጣቸውን  #ለአላህ  #መተው    #ሐዲሥ 49 / 393አቢ መዕበድ ሚቅዳድ ኢብኑ አል አስወድ (ረ.ዐ) ተከታዩ...
22/11/2025

#የሰዎችን #ውጫዊ #እንቅስቃሴና #ተግባር ( #አምኖ) #መቀበልና #ውስጣቸውን #ለአላህ #መተው



#ሐዲሥ 49 / 393

አቢ መዕበድ ሚቅዳድ ኢብኑ አል አስወድ (ረ.ዐ) ተከታዩን አስተላልፈዋል። ለአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)፦ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እስኪ ይንገሩኝ። ከከሓዲያን አንዱን ባገኘውና ብንዋጋ፥ አንድ እጄን በሰይፍ መትቶ ከቆረጣት በኋላ በዛፍ ተከልሎ ‘ለአላህ እጅ ሰጥቻለሁ (ሰልሜያለሁ) ቢል’ ይህን ካለ በኋላ ልገድለው ይፈቀድልኛልን ?” ሲል ጠየቃቸው። “አትግደው” አሉኝ። “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አንድ እጄን እኮ ቆርጦታል። ከዚያ በኋላ ነው ይህችን ቃል የተናገረው” አልኳቸው። “ቢሆንም አትግደለው እርሱ ሳትገድለው በፊት የነበርክበትን ቦታ ይይዛል። አንተ ደግሞ እርሱ ይህችን ቃል ከመናገሩ በፊት የነበረበትን ቦታ ትይዛለህ፡፡” (ቡኻሪ ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ወደ ኢስላም የሚያመለክት ቃል የተናገረን ወይም መስለሙን አመላካች አንዳች ተግባር የፈፀመን ሰው መግደል ክልክል ነው።
2/ ይህን እውነታ እያወቀ የገደለው ሰው “ቂሷስ” (መገደል) ግድ ይሆንበታል። ሳያውቅ ወይም ተመሳስሎበት በስህተት የገደለ ግን የደም ካሳ (ዲያህ) መክፈል ይኖርበታል። በሶሓቦች ዘንድ በስህተት የመግደል ሁኔታ ተከስቷል። ኢስላምን የተቀበሉ አጋሪዎች “እንዳይገደሉ በመፍራት ነው የሰለሙት” በሚል የተሳሳተ መነሻ የገደሉበት ሁኔታ አለ። የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የደም ካሳ ከፍለውላቸዋል።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #የሰዎችን  #ውጫዊ  #እንቅስቃሴና  #ተግባር ( #አምኖ)  #መቀበልና  #ውስጣቸውን  #ለአላህ  #መተው    #ሐዲሥ 49 / 392  አቡ ዐብደላህ ጧሪቅ ኢብኑ ዑሸይም፥ የአላህ መልዕክተ...
20/11/2025

#የሰዎችን #ውጫዊ #እንቅስቃሴና #ተግባር ( #አምኖ) #መቀበልና #ውስጣቸውን #ለአላህ #መተው



#ሐዲሥ 49 / 392

አቡ ዐብደላህ ጧሪቅ ኢብኑ ዑሸይም፥ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የሚከተለውን ሲናገሩ ሰምቻለሁ፥ በማለት አስተላልፈዋል፦ “’ላ ኢላሀ ኢልለላህ’ ያለና ከአላህ ሌላ በሚመለኩ (የሐሰት አማልክት) ሁሉ የካደ ገንዘቡም ደሙም እርም ናቸው። (ከዚህ ምስክርነት በኋላ) እርሱን የመቆጣጠሩ (ውስጡን የማየቱ) ተግባር የአላህ ብቻ ይሆናል።” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የሰዎችን የቃል ምስክርነት መቀበል፥ በግልጽ የተናገሩትንና የሚሠሩትን ብቻ ማመን ተገቢ ነው።
2/ የውስጣቸውን ለአላህ መተው ይገባል።
3/ ከአላህ ውጭ ከሚመለኩ የሐሰት አማልክት ሁሉ መጽዳት (በራእ) ግዴታ መሆኑን ይህ ሐዲሥ ያሳያል።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #የሰዎችን  #ውጫዊ  #እንቅስቃሴና  #ተግባር ( #አምኖ)  #መቀበልና  #ውስጣቸውን  #ለአላህ  #መተው   አላህ እንዲህ ብሏል፦  “ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትን...
19/11/2025

#የሰዎችን #ውጫዊ #እንቅስቃሴና #ተግባር ( #አምኖ) #መቀበልና #ውስጣቸውን #ለአላህ #መተው



አላህ እንዲህ ብሏል፦

“ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው። አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና። (አት-ተውባህ፡ 5) (ሙስሊሞች ሆነዋልና ተዋቸው። አትግደላቸው። አትዋጓቸው። ከውጭ ያያችሁትን የሙስሊምነት ምልክት ብቻ ተቀበሉ።

#ሐዲሥ 49 / 391

ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሰዎችን፥ ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ ፥ እንዲሁም ሶላትን ደንቡን ጠብቀው እስኪሰግዱና ዘካም እስኪሰጡ ድረስ እንድዋጋቸው ታዝዣለሁ። ይህን ከፈፀሙ ደማቸውም ሆነ ገንዘባቸው ከኔ የተጠበቀ ነው። ከኢስላም ግዴታዎች ጋር በተያያዘ ካልሆነ በቀር። (ይህንን ከፈፀሙ) እነርሱን የመቆጣጠሩ (ውስጣቸውን የማየቱ) ተግባር ለአላህ የሚተው ይሆናል።” (ቡኻሪ ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አጋሪዎችን ኢስላምን እስኪቀበሉ መዋጋት ግዴታ እንደሆነ ሐዲሡ ያሳያል። ወዶ የመግባታቸው ምልክቱ ግን ሸሃዳን (የእምነት ምስክርነትን) በቃል መመስከራቸውና በግልጽ የሚታዩ ኢስላማዊ ተግባራትን ማከናወናቸው ነው። ለምሳሌ መስገዳቸው፣ ዘካ መስጠታቸውና ፆም መፆማቸው።
2/ ወደ ኢስላም መግባታቸውን ካወጁ ገንዘባቸው፣ ደማቸውና ክብራቸው እርም ይሆናል። የውስጥ እምነታቸውን ግን ለአላህ የሚተው ይሆናል። እምነታቸው ከልብ ከሆነ ስኬትን ያገኛሉ። ለማስመሰል ከሆነም ይቀጣሉ። እኛ ግን ይህን ሁሉ እንድንመራመር መብቱ አልተሰጠንም። የላይ ምስክርነታቸውን ብቻ ተቀብለን እንደሙስሊም መቁጠር ግድ ይሆንብናል።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #መልካም  #ሰዎችን፣  #ደካሞችንና  #ድሆችን  #የማወክ  #አደገኛነት  አላህ እንዲህ ብሏል፦ “እነዚያንም ምእምናንንና ምዕምናነትን ባልሠሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግል...
18/11/2025

#መልካም #ሰዎችን፣ #ደካሞችንና #ድሆችን #የማወክ #አደገኛነት

አላህ እንዲህ ብሏል፦
“እነዚያንም ምእምናንንና ምዕምናነትን ባልሠሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ።” (አል አሕዛብ፡ 58)

“የቲምንማ አትጨቁን። ለማኝንም አትገላምጥ።” (አድ-ዱሓ፡ 9-10)

ይህን ምዕራፍ የሚመለከቱ በርካታ ሐዲሦች ተላልፈዋል። ከነርሱ ውስጥ ባለፈው ምዕራፍ የተወሳው “የኔን ወዳጆች ጠላቱ አድርጎ የያዘ” የሚለው አንዱ ነው። “ለየቲሞች ማዘን” በሚለው ምዕራፍ የተወሳውና በሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ የተላለፈው ሐዲሥም ከዚሁ ይፈረጃል። በዚህ ሐዲሥ ውስጥ የአላህ መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፦ “አቡበክር ሆይ! አስቆጥተሃቸው ከሆነ አላህን አስቆጥተሃል” ማለታቸው ይታወሳል።

#ሐዲሥ 48 / 390

ጁንዱብ ኢብኑ ዐብደላህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ “የሱብሒን ሶላት ‘በጀመዓ’ (በሕብረት) የሰገደ በአላህ ጥበቃ ሥር ነው። አላህ በጥበቃው ሥር ያዋለውን ሰው (ተተናኩላችሁ) (ለብቀላ) እንዳይፈልጋችሁ (ተጠንቀቁ)። አላህ በጥበቃው ሥር ያዋለውን ሰው (በመጉዳቱ) ሳቢያ (ለበቀላ) የፈለገውን ሰው ያገኘዋል። ከዚያም ጀሃነም እሳት ውስጥ በፊቱ ይደፈዋል።” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የሱብሒ ሶላትን በጀማዓ መስጂድ ውስጥ የሰገደ ሰው በአላህ ጥበቃ ሥር ነው።
2/ ይህን ሰው መተናኮል አላህን ያስቆጣል። አላህ የተቆጣበትና ለብቀላ የፈለገው ሰው የትም አያመልጥም። እሳት ውስጥ ያስገባዋል።
3/ ይህ ሐዲሥ የሱብሒን ሶላት አዘውትሮ በጀማዓ የሚሰግድን ሰው ክብርና ልቅና ያሳያል።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #አላህ  #አንድን  #ሰው  #የመውደዱ  #ምልክቶች   #ሐዲሥ 47 / 389ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ባልደረባቸውን ...
17/11/2025

#አላህ #አንድን #ሰው #የመውደዱ #ምልክቶች



#ሐዲሥ 47 / 389

ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ባልደረባቸውን ከአንድ የጦር ቡድን ጋር አዘመቱት፡፡ ሰውየው ባልደረቦቹን ሶላት ባሰገደ ቁጥር (የቁርአን ንባብን) የሚያጠናቅቀው በ”ቁል ሁወልሏሁ አሐድ” (ምዕራፍ) ነበር። (ከዘመቻ) ሲመለሱ (ባልደረቦቹ) ይህን (ባሕሪውን) ለአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነገሯቸው። እርሳቸውም፦ “ለምን ይህን እንደሚያደርግ ጠይቁት” አሉ። ጠየቁት፦ “እርሷ የአላህን ባሕሪያት የያዘች ምዕራፍ በመሆኗ (የቁርአን) ንባቤን በርሷ መጨረስን እወዳለሁ” አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) (ያለው ሲነገራቸው)፦ “አላህ እንደሚወዳው ንገሩት” አሉ። (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አንድ ረከዓ ውስጥ ከፋቲሐ ውጭ ሌሎች ሁለት ሱራዎችን ማንበብ ይፈቀዳል።
2/ ሶሓቦች የማያቁት ነገር ሲገጥማቸው መልዕክተኛውን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያማክሩና ፈትዋ ይጠይቁ ነበር።
3/ “አል_ኢኽላስ” ምዕራፍ ለአላህ ተገቢ የሆኑ ባሕሪያትን አካታለች፡፡ አሓዳዊነቱን ትገልጻለች፡፡ በሁሉም ጉዳይ የሰዎች መጠጊያና መመኪያ መሆኑን፥ ልጅም ወላጅም፥ ሚስትም እንደሌለው ታስተምራለች፡፡
4/ የሥራ ፍሬያማነት የሚለከው ከተፈጸመበት ዓላማ አንጻር ነው። በመሆኑም ለአላህ ሲል አንድ መልካም ተግባር የፈፀመ አላህ ይወደዋል።
5/ አንዲትን የቁርአን ምዕራፍ ሶላት ውስጥ መደጋገም ይፈቀዳል። ይህ ሶሓባ አል-ኢኽላስ ምዕራፍን በየረከዓው ይቀራ ነበር።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #አላህ  #አንድን  #ሰው  #የመውደዱ  #ምልክቶች    አላህ እንዲህ ብሏል፦“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ የሚመለስ ሰው፣ አላህ (በእነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚ...
16/11/2025

#አላህ #አንድን #ሰው #የመውደዱ #ምልክቶች



አላህ እንዲህ ብሏል፦
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ የሚመለስ ሰው፣ አላህ (በእነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚወዱትን፣ በምእመናን ላይ ትሁቶች፣ በከሐዲዎች ላይ ኃያላን የኾኑን፣ በአላህ መንገድ የሚታገሉን፣ የወቃሽን ወቀሳ የማይፈሩን ሕዝቦች በእርግጥ ያመጣል፤ ይህ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው።” (አል_ማኢዳህ፥ 54)

#ሐዲሥ 47 /388

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ “አላህ አንድን ባሪያውን ሲወደው ጂብሪልን ይጠራና፦ “አላህ እገሌን ይወደዋልና አንተም ውደደው ይለዋል። ጂብሪልም ሰውየውን ይወደዋል። ለሰማያት ነዋሪዎች፦ “አላህ እገሌ የተባለውን ሰው ይወደዋልና እናንተም ውደዱት፥ ሲል ያውጃል። የሰማያት ነዋሪዎችም ይወዱታል። ከዚያም ምድር ላይ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይሆናል። (ቡኻሪና ሙስሊም)
ሙስሊም ባሰፈሩት ዘገባ ደግሞ እንዲህ የሚል ተወስቷል። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ፦ “አላህ አንድ ባሪያውን ሲወደው ጂብሪልን ጠርቶ፡ “እኔ እገሌን እወደዋለሁና አንተም ውደደው ይለዋል። ጂብሪል ይወደዋል። ለሰማያት ነዋሪዎችም፦ “አላህ ይህን ሰው ይወደዋል። እናንተም ውደዱት” በማለት ያውጃል። የሰማያት ነዋሪዎችም ሰውየውን ይወዱታል። ምድር ላይም ተቀባይነት እንዲያገኝ ይደረጋል።
አንድን ሰው ሲጠላው ደግሞ ጂብሪልን ይጠራና፦ “እገሌ የተባለውን ሰው እጠለዋለሁና አንተም ጥላው” ይለዋል። ጂብሪል ሰውየውን ይጠላዋል። ለሰማያት ነዋሪዎችም፦ “አላህ እገሌ የተባለውን ሰው ጠልቶታልና ጥሉት ሲል ያውጃል። ከዚያም ሰውየው ምድር ላይ ተቀባይነት ያጣል።”

ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር

♦️ እዚህ ላይ ግምትና ክብደት የሚሰጠው የመልካም ሰዎች ፍቅር ወይም ጥላቻ ነው። መጥፎ ሰዎች መልካም ሰዎችን መጥላታቸው ክፉ ሰዎችን መውደዳቸው ከሐዲሡ መልዕክት ጋር አይቃረንም። አማኝ በአላህ ኑር ነገሮችን ያያል። አላህ የወደደውንም ይወዳል።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

 #አላህ  #አንድን  #ሰው  #የመውደዱ  #ምልክቶች   አላህ እንዲህ ብለዋል፦በላቸው፦ “አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና። ኀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና። አ...
15/11/2025

#አላህ #አንድን #ሰው #የመውደዱ #ምልክቶች



አላህ እንዲህ ብለዋል፦

በላቸው፦ “አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና። ኀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና። አላህም መሐሪ አዛኝ ነው።” (አል_ዒምራን፥ 31)

#ሐዲሥ 47 / 387

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ “አላህ እንዲህ ብሏል፦ “የኔን ወዳጅ ጠላት ያደረገ ጦርነት አውጅበታለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት (ተግባራት) በበለጠ ወደኔ በምንም ነገር አይቀርብም። ባሪያዬ በመጨረሻ እስኪወደው ድረስ በሱንናዎች ወደኔ ይቃረባል። በወደድኩት ጊዜ የሚሰማበት ጆሮው፣ የሚያይበት ዓይኑ ፣ የሚጨብጥበት እጁ፣ የሚጓዝበት እግሩ እሆንለታለሁ። ሲጠይቀኝ እሰጠዋለሁ። ጥበቃዬን ሲከጅል እጠብቀዋለሁ። (ቡኻሪና ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አላህ ወዳጁን በጠላትነት የሚይዙትን ይበቀላል።
2/ የአላህ ፍቅር የሚገኘው ግዴታ ያደረገባቸውን ተግባራት በመፈፀም ነው። ሱንና ተግባራትን በማከናወን ደግሞ ፍቅሩን ይበልጥ ማጠናከር ይቻላል።
3/ ግዴታ (ፈርድ) ከሱንና መቅደም አለበት፡፡ ምንያቱም ሱንናንም ፈርድንም መፈፀሙ ምንዳ የሚያስገኝ ቢሆንም ፈርድን መተው የሚያስቀጣ ሲሆን፥ ሱንናን መተው ግን አያስቀጣም።
4/ “መስሚያ ጆሮ፣ የሚያይበት ዓይኑ ... እሆንለታለሁ” ማለት እነኝህን የአካል ክፍሎችን ሐላልና መልካም ከሆኑ ነገሮች ውጭ እንዳይጠቀምባቸው እከላከልለታለሁ ማለት ነው። ወይም ደግሞ አላህ የሚወደውን ባሪያውን እንደሚረዳ ለማሳየት የተነገረ ነው።
5/ የአላህ ወዳጆች ዱዓ _ ጊዜው የቱን ያህል ቢረዝምም _ በመጨረሻ ተቀባይነት ማግኘቱ እርግጥ ነው።

Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1

Address

Belay Zeleke
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Muslim Ummah ሙስሊም ኡማህ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Muslim Ummah ሙስሊም ኡማህ:

Share