19/01/2025
*የዩኒየኑ ምርጫ በሰላም ተጠነቀቀ 👇*
1ኛ ጴጥሮስ 5፡2-4:-² በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን *መንጋ ጠብቁ* ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤³ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤⁴ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን *የክብርን አክሊል* ትቀበላላችሁ።
እነሆ ኢትዮጵያ ዩኒየን 8ኛ ዙር ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡ በዚህም መሠረት ዩኒየንን ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የሚመሩ መሪዎች፣ በተወካዮች አማካይነት ከጥር 6-8/2017 ዓ/ም በደቡብ ምዕራብ ፊልድ በአንሾ ተመርጠዋል፡፡
ምርጫውንም አስፈፃሚዎች፣ ከአፍሪካ ድቭዥን፡-1ኛ ፓ/ር ቬንጃሚን ማድሻ (የድቭዥኑ ፕሬዝደንት) እና 2ኛ ፓ/ር ጀስቲን ቡዋልያ (የድቭዥኑ ገ/ያዥ) ሲሆኑ፣ ጥር 7 የበፊቱ ሪፖርት ቀርቦ፣ በምርጫ ዙሪያ ሴሜናር ተሰጥቷል፤ ቀጥሎ ጥር 8/2017 ላይ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ ተካሂዷ፡፡ኃላፊነትና የኃላፊነት ቦታ የወሰዱ ሰዎች ስም ዝርዝር 👇
1. የዩኒየኑ ፕሬዝደንት-ፓ/ር ሙላቱ ተክሌ
2. .የዩኒየኑ ም/ፕሬዝደንት-ፓ/ር ፀጋዬ ኦቦላ
3. .የዩኒየኑ ጻሐፊ-ፓ/ር ሌንጫ ተክሌ
4. የዩኒየኑ ገ/ያዥ- ወንድም እሼቱ ተፈራ
5. የዩኒየኑ ወንጌል ዘርፍ መሪ-ፓ/ር ብርሃኑ ኤርሞሎ
6. የዩኒየኑ ወጣቶች ክፍል መሪ-ወ/ም አዳነ ያየ
7. የዩኒየኑ መልካሙ ሳምራዊ ዘርፍ መሪ-እህት ሂሩት ኤርጅኖ
8. የዩኒየኑ የጤና ዘርፍ መሪ-ፓ/ር ደረጄ ጉዳታ
9. የዩኒየኑ ትምህርት መሪ-ወ/ም አሰፋ ለዕመንጎ
10. የዩኒየኑ ቤትና ቤተሰብ ዘርፍ- ፓ/ር ሌንጫ ተክሌ
11. የህትመት ክፍል መሪ-እህት ኤልሳቤጥ ወ/ማሪያም
12. የሚድያ መሪ-ወ/ም እሼቱ ተፈራ
👉 *ፋይናንስ ኮሚቴ* 👇
1.ወ/ም እሼቱ ተፈራ-ገ/ያዥ
2.ወ/ም አዳነ ያየ
3. ወ/ም መለሰ አቡራ እና
4. ወ/ም ኤብሳ ተክሌ ናቸው፡፡
👉 *ኦድተሮች* 👇
1. መ/ር ተሸመ መኮንን
2. ወ/ዊ ደሞዜ ጉዬ
👉 *የዩኒየኑ ቦርድ ኮሚቴ* 👇1.ፓ/ር ሙላቱ ተክሌ -ፕሬዝደንት
2. ፓ/ር ፀጋዬ ኦቦላ-ም/ፕሬዝደንት
3. ፓ/ር ሌንጫ ተክሌ-ጻሐፊ
4. ወ/ም እሼቱ ተፈራ-ገ/ያዥ
5. ፓ/ር ብርሃኑ ኤርሞሎ ሚሽናሪ
6. እ/ር ሳቀታ መኮንን- የም/ወለጋ ፊልድ ፕሬዝደንት
7. እ/ር ኤልያስ ለዕመንጎ-የደቡብ ምዕራብ ፊልድ ፕሬዝደንት
8. እ/ር አዳነ ያየ- የሲዳማ ፊልድ ፕሬዝደንት
9. ፓ/ር ዘላለም አዲሱ-የደቡብ ፊልድ ፕሬዝደንት
👉 ከጥር 8/2017 ማታ እስከ ጥር 10/2017 ዓ/ም ማታ ድረስ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡን በብዙ በኩል ስባርክ ቆይቷል፡፡ ከምዕራብ ወለጋ፣ ከሲዳማ፣ ከደቡብና ከደቡብ ምዕራብ ፊልዶች የመጡ የግልና የቡድን መዘምራን፣ የአንሾ ቤ/ክ ህጻናትና እናቶች ዘምረዋል፤ ስብከተ ወንጌል በአፍሪካ ድቭዥን መሪዎች ፓ/ር ቬንጃሚን እና ፓ/ር ጀስቲን ቡዋልያ በኩል ቀርቧል፤ ለህሙማን የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፤ ለመሪዎች እና ለሕዝብ ፀሎት ተደርጓል፡፡
እግዚአብሔር ይመስገን!
IMS Ethiopia Media