21/03/2026
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🔥🔥🔥መገናኘቱ🔥🔥🔥
እግዚአብሔር አይራራም
ሆዱም አይንሰፈሰፍም
ከራራስ ለማነው የሚራራው
ከሱ ውጪ ሌላ ስለሌለ ለማንም አይራራም; ደኑን ይመነጥረዋል ይጨረግደዋል እንጂ የሚራራለት የለውም!
የሚራራም የሚንሰፈሰፍም ካለ - እሱ ሰይጣን ነው!
የእግዚአብሔር እርህራሄም ከተባለም ዘለፋና ተግሳጹ አካሉ ላይ የተለጠፈውን አፈር ከድሜ ማብላቱ ነው!
እረፍቱም ደስታውም ሰላሙም ያለው በዚሁ ነው!
የአካሉ ግንኙነትም የተሰገሰገውን ለማንጻት, የተደፈነውን ለመክፈት, ስለሆነ ከዚህ ውጪ ሌላ አጀንዳ የለውም!
{እርስ በእርስ ግንኙነት ማድረጉም ለመንጻት እና ለመንጻት ብቻ ነው}
መገናኘቱ ከዚህ ውጪ ሌላ ዓላማ የለውም!!!
ሌላው ደባል ግንኙነት ከአጋንንት ነው!!!
ስለሆነ ፈጽሞ ከጓደኝነት, ከዝምድናም, ከቀረቤታም, ከትዳር አጋርነት, ከመዋለድ, ከመዛመድ, ከመጋመድ, ከመላላስ, ከመንተራስ, ከውለታ, የፀዳና የተቀደሰ ግንኙነት ነው።
በመሆኑም ፈጽሞ የባለቤቱ መልክ እና ፈቃድ ብቻ በአካል እስኪቀር ድረስ አካል በእሳት, በተግሳጽ, በዘለፋ, በትችት ናዳ, በእቶን ነበልባል, ለዘለዓለም ይነጥራል🔥
መቼሜ ቢሆን መቼም አካል ከአካል ጋር ጓደኛ አይሆንም,
ሁሌም ቢሆን መንፈስ አካሉን እርስ በእርስ ያጠባብቀዋል!
ሁሌም መንፈስ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ መፈጸም እርስ በእራሳችንላይ እየተገለጠ, ክፋ ደግ እያነጋገረን, እያጣላን, እያገሳሰፀን, እያናከሰን, እያባላን, አንድነትን እያፀና በእሳቱ አካሉን እያጠራ; ጨለማውን ይፈጽመዋል እንጂ :-አካሉን ከዚህ ውጪ ለሆነ ግንኙነት አሳልፎ አይሰጠውም!!!
ጓደኛ, ቤተሰብ, የጎን ወዳጅ, እርስ በእርሳችን እንዲያደርገን ለአጋንንት አይተወንም!
ሁሌም አንመቻችም!
አንዋደድም!
ፍሬንዶች አይደለንም!
በመንፈስ እነጨራረሳለን!
ማለቃችን ካልቀረ ደግሞ በጊዜ ብናልቅ ይሻለናል! አጋንንትን ደባል ይዘን የስቃያችንን ዘመን ከምናራዝም!!!
*ከዚህ ውጪ የሆነው ግንኙነት- አጋንንትን ና ግባብኝና ኑርብኝ በሎ መጋበዝ እና አጋንንትን ስቦ ወደራስ ማስገባትም ነው*
ሁሌም በእሳት እንታጠባለን;
እሳት ለብሰን እሳት ጎርሰን እንውላለን, እናድራለን,
አንራራም, እርህራሄ ከአጋንንት ነው;
ያለው አንዱ ነው; ሌላው ሌባ ነው!
ለሌባ አንራራም!
ሰይጣንንም ጓደኛ አናደርግም!
አንወደውም!
ሁሌም አፈር ከድቤ እናስግጠዋለን!
እሱም አይወደንም ግን ምንም አያመጣም!
እንደ ድራጎን ሁሌ እሳት እንተፋለን🔥
ሳንበርድም ወደአፈር እንመለሳለን🔥
እሳቱ ይቀጣላል...🔥🔥🔥
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥