Tewahido Melis Alat

Tewahido Melis Alat This page is created in order to share the ideology of EOTC

24/02/2019

 ብዙዎች ሐሰተኞች ነብያትም ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ከዐመፅም ብዛት የተነሳ ፍቅር ከብዙዎች ዘንድ ትጠፋለች፡፡ እስከመጨረሻዉ የምታገሥ ግን እርሱ ይድናል፡፡ ማቴ 24፣11-13

17/02/2019

#ቤተ ክርስቲያን ስንሳለም ሶስት ጊዜ የምንሰግድበት ምሥጢር ....
።።።።።።።
መጀመሪያ
ሰግደን ስንነሳ አፈር ነበርን ሰው አርገህ ፈጥረህ ቁመን እንድንሄድ ቀና ብለን እንድንራመድ አደረከን ብለን ነው
።።።።።።።።
ሁለተኛ
ሰግደን ስንነሳ በኀጢአት ምክንያት ተሰነካክለን ብንወድቅም በንስሃ ታነሳናለህ ስንል ነው
።።።።።።።
ሶስተኛ
ሰግደን ስንነሳ ሙተን ወደመቃብር ብንወርድም በኋለኛው ዘመን በትንሳኤ ዘጉባኤ ከመቃብር ታነሳናለህ ስንል ነው
።።።።።።።።።
ወድቀን መስገዳችን ተፈጥሮአችን ከመሬት መሆኑን ለመግለፅ ሲሆን መነሳታችን ሀገራችን በሰማይ መሆኑን ለመግለፅ ነው
።።።።።።።።።
የምሥጢር ባለቤት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምታደረገው ሥርዓት ሁሉ በምሥጢር የተሞላ ነው ሰማያዊት ቤተ ክርስቲያን ለዘለዓለም ኑሪልኝ

 # የተለያዩ የክርስትና ሀይማኖቶች እንዴት ተመሰረቱ? ________________________________ #ክፍል ፩በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አመን! መጽሐፍ ቅዱስ አ...
14/01/2016

# የተለያዩ የክርስትና ሀይማኖቶች እንዴት ተመሰረቱ?
________________________________
#ክፍል ፩
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አመን!
መጽሐፍ ቅዱስ አንድት ሀይማኖት ብቻ እንዳለችና (ኤፌ 4፣5) የቀደመችዉን መንገድ እንድንከተል (ት.ኤር 6፣ 16) ብያዘንም ዛሬ ዛሬ ብዙዎች የጥንቱን የአባቶቻችንን መንገድ መከተል እንደስህተት በመቁጠር እየሳቱ ይገኛሉ። አዉቀንም ይሁን ሳናዉቅ በእንግዳ ትምህርት እንዳንወሰድ እንድሁም “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” ስላልን ብቻ ጽድቅ እንደለሌ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል። እነዝህን ጥቅሶች እስት እንያቸዉ፤
ማቴ 7፣ 15 “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” ማቴ 7፣ 21 “በዚያ ቀን ብዙዎች፤ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።” ነገር ግን ጌታ “አላዉቃችሁም” እንደምላቸዉ ቁ 22 ላይ ይገልፃል።
2ቆሮ 11፣ 4 የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።
2ጢሞ 4፣ 3 ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።
በተጨማርም ሕዝ 13፣ 17-19፤ ገላ 1፣8 ፤ ሐ.ሥራ 15፣ 1-24፤ ዕብ 3፣14፤ ዕብ 13፣ 7-9፤ ይሁ ቁጥር 3
___________________________________
**ልዩነት ፩ “ክርስቶስ ፍጡር ነዉ።” አርዮስ (1ኛዉ ጉባኤ)
በመጀመርያ ጌታ ሐዋርያትን ባዘዛቸዉ መሠረት ህዝቡን “ደቀመዝሙር” ያደርጉ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉም በክርስቶስ ስም ያምንና ይጠመቅ ስለነበር ሐዋርያት በአንፆክያ ክርስትናን መሠረቱ ሐ.ሥራ 11፣26። ከዝህም በኃላ እስከ 325 በአንድነት ዘለቀ። ይሁንና በ325 ዓ/ም “ክርስቶስ ፍጡር ነዉ።”የምል ትምህርት በመነሳቱ 318 የአለማችን የቤቴክርስትያን ልቃዉንት ተሰብስበዉ ሰፊ ክርክር በእስክንድርያዉ አለክሳንድርያ፣ አትናቶስ እና በወቅቱ ብዙ ተቀባይነት በነበረዉ አርዮስ መካከል ከተደረገ በኃላ ፤ አርዮስና የዕርሱን ትምህርት የደገፉ 2 መምህራን ተወግዘዉ ተለይተዋል። በዝህም ጉባኤ የክርስቶስ ቤቴክርስትያን ዶግማና ስርአት ወቶላት “ኦርቶዶክስ” የምል ስያሜ ተሰጥተዋታል። የግርክ ቃል ስሆን ትርጉሙም ኦርቶ-ቀጥተኛ/እዉነተኛ፣ ዶክስ-እምነት ማለት ነዉ፡፡ በተጨማርም የፋስካ በአል አከባበር፣ ጥምቀት (የልጅነት) ፣ ስግደት (በሰንበትና ፋስካ) በዝህ ጉባኤ ተወስኖአል። (ዝርዝሩን እንተርነት ላይ the first council of Nicea ብላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ) የአርዮስን ትምህርት ስለመቃወማችን በቅዳሴ ላይ አሀዱ አብ ቅዱስ ኣሃዱ ወልድ ቅዱስ ዉእቱ መንፈስ ቅዱስ እያልን አንድነታቸዉን እንሰብካለን።
________________________________
***ልዩነት 2 ፤ የሥላሴ ፩ እና ፫ ነት (2ኛዉ ጉባኤ)
በመጀመርያዉ ጉባኤ አርዮስ ብወገዝም ተከታዮቹ (Arianism) አሁንም ትምህርታቸዉን ቀጥለዉበት ነበር። በተጨማርም የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ላይ ልዩነቶች እየሰፉ በመምጣታቸዉ ሁለተኛዉ ጉባኤ በሮሙ ንጉስ ትዮዶሰስ ቀዳማዊ ( Roman Emperor Theodosius I) በ 381 ዓ/ም ተጠርቶአል። ይህንን ጉባኤ የእስክንድርያዉ(አሁንዋ ግብፅ) ጥሞትዎስ ና የቁስጥንጥንያዉ(የአሁኑዋ ቱርክ) ናክታረስን ጨምሮ 2 መምህራን መርተዉታል። በጉባኤዉ 150 ልቃዉንት የተገኙ ስሆን የምዕራቡ ክፍል አልተገኘበትም።
በመጀመርያዉ ጉባኤ ማለትም በንቅያዉ ስለ መንፈስ ቅዱስ አልተነሳምና መቄዶናዉያን የሥላሰን ሶስት አካልነት (መንፈስ ቅዱስን) አልተቀበሉም ነበር። Because of the Council of Nicaea had not clarified the divinity of the Holy Spirit, the third person of the Trinity; it became a topic of debate. The Macedonians denied the divinity of the Holy Spirit. This was also known as Pneumatomachianism. ስለዝህም በዝህ ጉባኤ ሰባት ታላላቅ ዉሳነዎች (ዶግማና ስርአቶች) ተላልፈዋል። የመጀመርያዉ ስለ ሥላሰ ሶስትነትና አንድነት ስሆን ሌሎቹ ስለ ፓትርያርክ እና ጳጳሳት ሹመት (ስልጣን) የተሰጡ ዉሳነዎች ናቸዉ። ዝርዝሩን ከፈለጋችሁ First Council of Constantinople ብላችሁ ኢንተርነት ላይ ማንበብ ትችላላችሁ።
___________________________________
****ልዩነት ፫ “ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሳትሆን የኢየሱስ እናት ነች።” ንስጥሮስ (3ኛዉ ጉባኤ)
ይህንን የኑፋቄ ትምህርት ያስተምር የነበረዉ የቁስጥንጥንያዉ(የአሁኑዋ ቱርክ) ፓትርያርክ (ልብ ይበሉ በሁለተኛዉ ጉባኤ የፓትርያርክ ሹመት ፀድቆዋል) ንስጥሮስ ነዉ። ለዝህም በ431 ዓ/ም 200-250 የምደርሱ የቤቴክርስትያን ልቃዉንት በሮሙ ንጉስ ትዮዶሰስ ዳግማዊ ጋባዥነት ተሰበሰቡ። ጉባኤዉን የእስክንድርያዉ ስይርል (Cyril of Alexandria) በፕረዝዳንትነት መርተዉታል። ከሰኔ 21-ሃምሌ 31 ሰባት ጉባኤዎችና ክርክሮች ከተካሄዱ በኃላ የንስጥሮስ ትምህርት የንቅያዉን ዉሳኔ የምፃረርና ከአርዮስ አስተምሮ ጋር ተመሳሳይ እንድሁም ከመፅፍ ቅዱስ ውጭ በመሆኑ ተወግዞኣል። በጉባኤዉም “ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት ( The Virgin Mary was to be called Theotokos a Greek word that means "God-bearer" (the one who gave birth to God) የምል ዉሳነ ተላልፎዋል። ይሁንና ንስጥሮስና ተከታዮቹ የራሳቸዉን አስተምሮ ተከትለዋል ( Nestorian Christianity). በዝህ ጉባኤ ከንስጥሮስ ትምህርት ዉግዘት በተጨማር 8 መመርያዎች (ዶግማና ስርአት) ተላልፎበታል። ዝርዝሩን Council of Ephesus ብላችሁ እንተርነት ላይ ማንበብ ትችላላችሁ።

እንግድህ የእግዝአብሄር በተሰቦች ከላይ እንዳየነዉ ከጥንትም አንድአንድ የኑፋቄ ትምህርቶች ብነሱም በዉይይትና ክርክር አንድትዋን ቤቴክርስትያን ጠብቄዉ አቆይተዋል። በቀጣይ ክፍል ስለ 4ኛዉ ጉባኤና ክፍፍሉ እናያለን። ወስብሀት ለእግዝአብሄር!!!

05/01/2016
15/12/2015

Like my page and I will post so many things you must know about the ideology, relation ships and difference between EOTC and other Christians. Let God be with us!!!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tewahido Melis Alat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Tewahido Melis Alat:

Share