Brother Josh Temechu

Brother Josh Temechu “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን::” 1 ቆሮ. 1 ፥ 23

25/04/2024
ድንቅ ፍቅር!!! ሉቃስ 15:11-24👉 አንድን ሰው በከባዱ ከበደላችሁት ፥ ሲልም በብዙ ካስቀየማችሁት ፥ ዳግመኛ ለይቅርታም እንኳን ቢሆን የልቡን በር ብታንኳኩ ምላሹ በቀል ፥ አጸፋውም አስ...
19/04/2024

ድንቅ ፍቅር!!!

ሉቃስ 15:11-24

👉 አንድን ሰው በከባዱ ከበደላችሁት ፥ ሲልም በብዙ ካስቀየማችሁት ፥ ዳግመኛ ለይቅርታም እንኳን ቢሆን የልቡን በር ብታንኳኩ ምላሹ በቀል ፥ አጸፋውም አስከፊ ምላሽ ሊሆን ይችላል!!!

💙እጅግ በድለነው ፥ ሲበዛ ልቡን አሳዝነን ፥ ወደ እርሱ ወደ ሰማዩ አባት በንስኻ ስንመለስ ግን እርሱ ከሩቁ ያየናል ፥ ያዝንልናል!!!

💙 ያም ብቻ አይደለም:: ይኽ ፍቅር የሆነ አባት እኛን ተቀብሎ ፥ ከመስመር ያወጣንንና ክፋኛ የጎዳንን የራሳችንን ኃጢዓት ከላያችን ላይ አንከባልሎ ፥ በእርሱ ደስ የሚለውንና የሚወደውን አንድያ ልጁን ክርስቶስ ኢየሱስን በምህረት ያለብሰናል!!! አቤት ፍቅር!!!

"ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።"
1 ዮሐንስ 4:10

"እግዚአብሔር ፍቅር ነው።"
1 ዮሐንስ 4:16

ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ💕💕💕

Christ, the savior from sin and the Lord of my life🙏🙏🙏
29/08/2023

Christ, the savior from sin and the Lord of my life🙏🙏🙏

"ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፤ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች።"  ኦሪት ዘፍጥረት 21: 6     ሳቅ አለ ከፊትህየተዘጋ ቢመስል ነገር ያከተመጌታም "የዘነጋህ...
13/06/2023

"ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፤ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች።" ኦሪት ዘፍጥረት 21: 6

ሳቅ አለ ከፊትህ

የተዘጋ ቢመስል ነገር ያከተመ
ጌታም "የዘነጋህ" ተስፋህ የሰጠመ
በንስር ክንፍ ቢበር ዘመን አንተን ጥሎ
መጽናናትን ስትሻ የሀዘን ቢሆን ውሎ
ሚረዳህ ብታጣ የልብህን ስቃይ
ለወሬም ባይመች ፍጹም ያንተ ጉዳይ
ጥበቃህ አጥብቆ ከምሬት ጋር ቢያስርህ
የስጋህን ፈቃድ ቢያመታትር እግርህ
ልብ በል ወንድሜ የተስፋ ቃል ሰጪው
ታማኝ ነው አትስጋ አታስብ ለመጪው
ውስጥህ ይደገፈው ዳር አለው ለሊትህ
ያለህን ያደርጋል ሳቅ አለ ከፊትህ::

"ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!!!"
ጃሽ ተመቹ

07/03/2023

"ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው❤️🙏"
መዝሙረ ዳዊት 73 ፥ 1

የወንድሙን ገዳይ ይቅር በማለትና በማቀፍ ፍቅርን በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የሰበከ ትልቅ ልብ💙💙💙 ውዶች እንዲህ አይነቱን ልብ አምላክ ይቸረኝ ደግሞም ይቸረን ዘንድ ልባዊ መሻትና ጸሎቴ ነው💕💕💕

እግዚአብሔር ይርዳን!!!

01/03/2023

"እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና፡ አለኝ💙” 2 ቆሮ. 12:9

ውዶች ይኽችን ግጥም በብዙ ፍቅርና አክብሮት ጋበዝኋችሁ💕💕🙏

ተባረኩልኝ!!!

Address

Addis Ababa
00252

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Brother Josh Temechu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Brother Josh Temechu:

Share