Gizachew kumie

Gizachew kumie Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gizachew kumie, Church of God, Addis Ababa.

12/03/2025
ለምኝልኝ ካንች ጋ እኮ ምንም የለውእመ እግዚአብሔር ልእለ ፍጡር  ድርሳነ አምላክ ረቂቅ መምርበዝምታሽ ከሚጮሁ ስለበለጥሽ የአምላክ አይን ከአርያም አንችን አየሽ የፈጣሪም የፍጡርም አይን ማረ...
23/02/2025

ለምኝልኝ ካንች ጋ እኮ ምንም የለው

እመ እግዚአብሔር ልእለ ፍጡር
ድርሳነ አምላክ ረቂቅ መምር
በዝምታሽ ከሚጮሁ ስለበለጥሽ
የአምላክ አይን ከአርያም አንችን አየሽ
የፈጣሪም የፍጡርም አይን ማረፊያ
ለሀጥዑ ጠለ ምረት ህይወት ካፊያ
ለወደቀው ማንነቴ ካንች በቀር ውዳጅቱ
እንዳልገማ አርከፍክፊ ለህይወቴ ትንሽ ሽቱ
ልጀ እንድትይኝ ባይገባኝ በክፋቴ ባስከፋሽም
ቅንጣት ታክል ጽድቅ ፈልገሽ ከባሪያሽ ዘንድ ባታገኝም
በጎደፈው ማንነቴ በገለማው አንደቨቴ ስለምንሽ
ትንሽ ብቻ ለምኝልኝ አንችን ፈጥሮ ካከበረሽ
ኪዳነ ምህረት በኪዳንሽ ቃል ኪዳንም ከገባልሽ
አምላክ ሊፈጽመው በቅዱስነቱ ለማለልሽ
ከበላየሰብ ምታንስ ስራ ትንሽ እንኳን ብታገኝ
ኪዳንየ ወለላይቱ እባክሽን እንዳትተይኝ
ድንጋይ እንኳን ብወረውር ምን ውስጤ ቢከፋ
ቤቴን ሰርትዋል ብለሽ ለምኝ የኔ ሚዛን እንዲደፋ
እመ ምህርት እመብርሃን ለምኝልኝ እንዳልጠፋ
እናቴን መበደሌን አልዘነጋም ጥፋቴንም አምናለሁኝ
ሽህ ጊዜ እንኳን ብበድልሽ ከዛም በላይ ይቅር በይኝ
ሀጢያት መልኬን አጥፍቶታል እንዳልጠፋሽ እይኝ አተኩረሽ
አውጭኝ ከጥልቁ ውስጥ ከረግረጉ ስንፍናየን ታውቂዋለሽ
ተነሽልኝ ውበቴ ሆይ መድመቂያየ ብለሽ ማረው
ይምረኛል ከኔ ጋ እንጅ ካንች ጋ እኮ ምንም የለው
የካቲት 16 2017 ግዛቸው

ቆይ ህይወትን የምንኖራት ግን በየትኛው ነው በእጣ ፈንታ ነው? ባጋጣሚ ነው? ወይስ በምርጫ ? በየትኛው ስንኖር ነው ትክክል ? በየትኛው ስንኖር ነው ስህተት ? ስህተት የሆነውን ማስተካከል ...
16/05/2022

ቆይ ህይወትን የምንኖራት ግን በየትኛው ነው በእጣ ፈንታ ነው? ባጋጣሚ ነው? ወይስ በምርጫ ? በየትኛው ስንኖር ነው ትክክል ? በየትኛው ስንኖር ነው ስህተት ? ስህተት የሆነውን ማስተካከል እንችላለን ?ወይስ ሌላ እጣ ፈንታ ሌላ አጋጣሚ ሌላ ምርጫ እንጠብቃለን ?ከተሳሳትንስ እጣ ፈንታን በእጣ ፈንታ አጋጣሚን ባጋጣሚ ምርጫን በምርጫ ነው ምናስተካክለው? ወይስ እጣ ፈንታን በምርጫ አጋጣሚን በእጣ ፈንታ ምርጫን ባጋጣሚ ነው የምናስተካክለው ? ደግሞ ሌላ ጥያቄ ምርጫን እንመርጠዋለን ፡አጋጣሚም ያጋጥመናል እጣ ፈንታ ግን ምንድን ነው ?

ቁልቢ
11/06/2021

ቁልቢ

ላለፉት አመታት,.,,,,,,,በኖርኩባት ዘመን ከወዜ ከላቤ ,,,,,,,አውቃለሁ ለመብል መድከሜንመተኛት ከሆነ መፍትሄው ለችግሬ ማቃልለያው እስኪ ደሞ ተኝቸ ልየው ደስታየን እንዳልመው መከራና ...
16/09/2020

ላለፉት አመታት,.,,,,,,,በኖርኩባት ዘመን
ከወዜ ከላቤ ,,,,,,,አውቃለሁ ለመብል መድከሜን
መተኛት ከሆነ መፍትሄው ለችግሬ ማቃልለያው
እስኪ ደሞ ተኝቸ ልየው ደስታየን እንዳልመው
መከራና ስቃይ ችግሮቸ እስኪያልፉ
እኔ እንደተኛሁኝ ዘመናት ይለፍፉ
ባይሆን ችግር አልፎ ጥሩ ዘመን መጥቶ
በምን አልባት ተስፋ ልቤ ተነሳስቶ
እነሳ እንደሆነ ድካም ከጅ,,ግሬ ወጥቶ
ደስታየ በርክቶ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ችፍሬ ተፈቶ
መጓዝ ሲሰለቸኝ መተኛት መረጥኩኝ
ህልሜ እውን እስኪሆን እንዳትቀሰቅሱኝ

26/01/2020

ማወቅ ከሆነ ጥፋታችን
ባለማወቅ ውስጥ ሰይጣን እኛ ነታችን ደብቀን
ማንም ሳያስታርቀን ኖረን ነበር ተፋቅረን
ማወቃችን የበዛ መስሎን አነሰና የእኛነታችን አበዛው
ካለማወቅ ነበር ለካ መላክነታችን ነፍስ ሚዘራው
ዶክተር መምራኑ ፖሊስ ወታደሩ
ሁሉም ባንድ ቢሰሩ ይሆን ነበር ጥሩ
ዶክተሩ ካውቀ ኩላሊት ይሰርቃል
ዳኛውም ካወቀ ፍርድን ያጣምማል
መምህሩም ካወቀ መጥፎ ያስተምራል
ፖሊስም ካውቀ ንብረትን ይሰርቃል
ወታደር ካወቀ ሀገርን ይሸጣል
ገበሬም ካወቀ እንክርዳድ ይዘራል
ተማሪም ካወቀ መጥፎውን ይማራል
ጠቢብም ካወቀ ጎራዴ ይሰራል
ጋዘጠኛ ቢያውቅም ሃሰትን ይዘግባል
ሹፌርና ፓይለት ሲያቁ ንብረት ያወድማሉ
በቃ ምን አለፋን ማወቅ ከሆነ ጥፋታችን
እንመለስ ወደ ድሯችን ወደ አለማውቃችን
እንደኛ አባባል እንደ አባቶቻችን እንዳልሰለጠኑት
ላሊበላ አክሱምን ካንድ ድንጋይ ካቆሙት
አለማወቅ ከሆነ ጥበብ ሚያስጠብበን
ወደ ነበርንበት እንሂድ ተመልሰን ማወቁ ይቅርብን
እንዳይሆን መጥፊያችን

Address

Addis Ababa
443969

Telephone

+251918443969

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gizachew kumie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category