31/05/2026
ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረቶች የተሰጠ የጋራ አቋም መግለጫ
ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረቶች የጋራ አቋም መግለጫ በሳሮ ማሪያ ሆቴል ሰጥተዋል።
እኛ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መስራች አባላት መካከል 5ቱ አብያተ ክርስቲያናት
1.የኢትዮጵያ አንድነት በክርስቶስ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲናት ህብረት
2. የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት
3 የኢትዮጵያ የፍቅር ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ህብረት
4. ርኆቦት አብያተ ክርስቲያናት ህብረት
5. ኢቬንጄልካል ካረዝማቲክ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት፤
በማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28 ከቁጥር 16-20 ባለው ክፍል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን በሰጠው መለኮታዊ ተልዕኮ መሰረት በዚህ ዘመን ያለን አብያተ ክርስቲያናት ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ በማድረስ መጽሃፍ ቅድሳዊ ተልዕኮአችንን መወጣትና ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲጨመሩ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንዲሆኑ መስራት ቀዳሚ ተግባራችን ነው ።
ከላይ በተጠቀሰው መሠረት አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረቶች በተለያዩ ወቅታዊ ሀገረዊ ጉዳዮች ላይ ከተወያየን በኋላ፣ የወንጌል አመኙን ጴንጤቆስጤያዊ፣ መንፈሳዊ ማህበራዊና ሀገራዊ አንድነትን ለማስጠበቅ የሚከተለውን ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡