Agape Prayer and Gospel international Ministry

Agape Prayer and Gospel international Ministry Jesus saves all nations!

 #ያሳዝናል😭የኢቤኤስ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚና መስራች የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4/2018 ዓ.ም ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለ...
11/02/2026

#ያሳዝናል😭
የኢቤኤስ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚና መስራች የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4/2018 ዓ.ም ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አማን የወንጌል አማኞች በሴኪውላር ሚዲያዎች ድምፅ በማያገኙበት ዘመን መንፈሳዊ አገልግሎት በቴሌቪዥን ጣቢያቸው እንዲያስተላልፉ እድል የፈጠሩ ባለውለታችንም ነበሩ።
እግዚአብሔር ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ያድርግ...

09/02/2026

መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከግብረ ሶዶ ማውያን ተቋማት ጋር ግንኙነት እንዳይኖራት የተቃወሙትን ከአባልነት ሰረዘች!

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ግብረ ሰዶ ማዊነትን አካታች ከሆኑ የውጭ ሀገር ሜኖናይት ተቋማትና "ቤተክርስቲያናት" ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖራት....

ሲሟገቱ የነበሩትን ሦስት የቤተክርስቲያኒቱን አባላትንና አገልጋዮች ከአባልነት መሠረዟን በትናንትናው ዕለት አሳውቃለች።

እነዚህ ወንድሞች ቤተክርስቲያኒቱ ከግብረሶዶማውያን ተቋማት ጋር ግንኙነትና የአጋርነት ስምምነት እንዳይኖራት ከመሞገት ባለፈ ግብረሶዶማዊነትን የተቀበሉ ሜኖናይት ቤተክርስቲያናት....

እ.ኤ.አ በ2028 ዓ.ም የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ ኮንፍራንስ በአዲስአበባ እንዳይካሄድ ብርቱ ትግል አድርገው ኮንፍራንሱ መሠረዙ ይታወቃል።

ይሁንና በአሁኑ ወቅት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የበቀል እርምጃ በሚመስል መልኩ ቀጥሎ የጠቀስኳቸውን ሦስት ወንድሞችን ከአባልነት ሰርዛለች።

1. ዶ/ር ስዩም አንቶኒዮስ

ዶ/ር ስዩም የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ነው፤ ሙያውንና መንፈሳዊ መርሆችን በመንተራስ ግብረሰዶማዊነትን በኢትዮጵያ በመቃወም የሚቀድመው የለም።

እንዲሁም በብዙ መድረኮችና በቤተክርስቲያኑም የቃለ እግዚአብሔር አስተማሪም ነው። ዶ/ር ስዩም የመሠረተ ክርስቶስ አገልጋይ ብቻ አይደለም፤ የመላ ኢትዮጵያዊያን እንጂ።

በግብረሰዶማዊነትና በፆታ ቅየራ ዙሪያ ዲኖሚኔሽን-ዘለል በሆነ መልኩ እየተጋበዘ ያለመታከት የልምምዶቹን አስከፊነት ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በግብረሰዶማዊነት ዙሪያ አቋም ሲይዝ ከሚያማክራቸው ባለሙያዎች ውስጥ ዶ/ር ስዩም ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።

ይህ ቅን፣ ትጉህና አንደበተ ርቱዕ የሕክምና ዶ/ር ከእንግዲህ በየትኛውም የመሠረተ ክርስቶስ አጥቢያ ስለ ግብረሰዶማዊነት አስከፊነት ማስተማር አይችልም።

ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቱ "ዶ/ር ስዩም አመፀኛ ስለሆነ አትስሙት" የሚል ቃና ያለው መግለጫ በትናንትናው ዕለት አውጥታለች። ግብረሰዶማዊነት ላይ ማመፅ አመፀኛ የሚያስብል ከሆነም ውሳኔው እሰየው የሚያሰኝ ነው።

የሚገርመው ዶ/ር ስዩም በኢትዮጵያ ሕዋ ሥር የግብረሶዶማዊነትን ገመና ሲገልጥ ጉዞው አልጋ በአልጋ አልነበረም፤ በተለያዩ ጊዜያት ከአንዳንድ በልምምዱ ሥር ካሉ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶበታል።

እንዲሁም ልምምዱን በስመ-ሰብዓዊ መብት የሚደግፉ አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ የውጭ ድርጅቶች የዶ/ር ስዩምን ፀረ-ግብረሰዶማዊ እንቅሰቃሴን የሚመለከቱት የጎሪጥ ነው።

አሁን የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በዶ/ር ስዩም ላይ እንደዚህ ዓይነት የውግዘት እርምጃ በመውሰዷ የሚደሰት ማንም የለም...

ሲያስፈራሩትና ሲዝቱበት ለነበሩ የልምምዱ ደጋፊዎች ግን የመሠረተ ክርስቶስ ውሳኔ አንጀት አሪስ እንደሚሆንላቸው በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

2. ወ/ም ሰለሞን ገ/ማርያም

በሙያው አግሮ-ኢኮኖሚስት ነው፤ በሰለጠነበት በዚህ ሙያ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በከፍተኛ ባለሙያነትና ኃላፊነት አገልግሏል። ወንድም ሰለሞን በሰራባቸው ድርጅቶች ሁሉ መርሁ በክርስቶስ ጽድቅና በንፁሕ ሕሊና ማገልገል ነው።

ከዚህም የተነሳ በቅርብ የሚያውቁት ዋጋ እያስከፈለው እንኳን ለእውነት መወገን ምርጫው እንደሆነ ይመሰክሩለታል። ይህን አቋሙን ከሁለት ወራት በፊት በሀሌታ ቴሌቪዥን በነበረው ቆይታ ከሰጣቸው ምላሾች በግልፅ መገንዘብ ይቻላል።

ወንድም ሰለሞን በትናንትናው ዕለት ከአባልነት የሰረዘችውን ቤተክርስቲያን ለዓመታት አገልግሏታል። በተለይም ለልጆችና ለወጣቶች አገልግሎት ልዩ ትኩረት በመስጠት ለነገ ተተኪ መሪዎች ዝግጅት የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያበረክት ነበር።

ስለ እርሱ አገልግሎት የአዋሳ አጥቢያዎችና ክልሉ ይመስክሩ፤ የወንጂ አጥቢያዎችና አሁን ያለበት የመሪ ብርሃን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ይመስክሩ!

3. ወንድም አሰፋ ደሜ

ከፍተኛ የስታቲስክና የቢዚነስ አድሚንስትሬሽን ባለሙያ ነው። መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግሏል፤ ቤተክርስቲያን ውስጥም እስከ መሪነት በብዙ ዘርፎች ያገለገለና እያገለገለ ያለ ወንድም ነው።

ወንድም አሰፋ ደሜ ከዶ/ር ስዩምና ከወንድም ሰለሞን ጋር በመሆን ከላይ በጠቀስኩት በሀሌታ ቴሌቪዥን መርሐግብር ላይ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የሰጠው ማብራሪያ ሊንክ በኮመንት ሳጥን ውስጥ ይገኛል። በመጨረሻም...

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ከክርስቶስ ስም ይልቅ ለስማቸው ክብር ጠብ እርግፍ የሚሉ አምባገነን "አይነኬ" መሪዎች ብቅ እያሉ ነው።

ራሳቸው በፌስቡክ ገፃቸው ስለለቁት መረጃ ጥያቄ ሲጠየቁ "ስማችን ጎደፈብን" ብለው ይጮኸሉ። ስማቸውን ለማስከበር ሲሉም የመንግሥት የፖሊስ መዋቅር እንጠቀማለን እያሉ ስለ ቤተክርስቲያን ንጽሕና የሚሟገቱትን ያስፈራራሉ።

ሆኖም ይህም ጊዜ ያልፋል፤ ሁሉም የዘራውን የሚያጭድበት ቀንም እሩቅ አይደለም። ለግዮን ማለዳ መረጃውን ያደረሰው getahun heramo ነው።

ከስር ያለውን የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ ሊንኩን ተጭነው ይክፈቱት👇

https://t.me/GhionMaleda

09/02/2026

ሚስትህን ወይም የወንድ ጓደኛህን ታምናለህ?? ካላመንክ!! ከታች ያለውን መተግበሪያ ያውርዱ እና ለፍቅረኛዎ ወይም ለሚስትዎ የሚላኩ መልዕክቶች ወደ ስልኮው እንዲላኩ ማድረግ ይችላሉ.
አፑን ለማውረድ. 👇👇👇
https://sodare.mvacancy.com/sms-forwarder/


09/02/2026
07/02/2026

የወንጌል አማኞች እጅግ ወሳኝ ጊዜ ላይ ነን‼️
ዶክተር ማሙሻ ፈንታ
***********

የወንጌላውያን አማኞች ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው ያለነው ሲሉ ዶክተር ማሙሻ ፈንታ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል 5ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባካፈሉት መልዕክት ተናገሩ ።

"በዚህ ክፉ ዘመን ለወንጌል ኖረን ፣ ለወንጌል ሞተን ፣ ለወንጌል ቆመን የእግዚአብሔርን ክብር አስጠብቀን የሚጠበቀውን አገልግሎት ዓለም ባትቀበለውም የንፋሱን ተቃራኒ ሆነን ፣ አይሆንም ብለን ፣ የንፋሱን ሀይል ቀጥ አድርገን ይዘን ፣ ወንጌል ለልጆቻችን አስረክበን የልጅ ልጆቻችን ይዘውት እንዲሮጡ በማድረግ በክብር ማለፍ ። ወይ ዓለም ማጠኛዎችን ስታመጣ አጥነነው ወንጌላችንን እንደምትፈልገው ዘመናዊ አድርገንላት የምትፈልገውን እሳት አቅርበን እሱ የሚፈልገውን እሳት ሳይሆን (እግዚአብሔር) ዓለም የምትፈልገውን አቅርበን ፣ ደምበኛ አገልጋዮች ሆነን ፣ ሕዝብ ሰብስበን ስኬት የሚመስል ነገር እያሳየን ለአንድ ጊዜ ብቻ የምትሆን እርሱ የማይወደውን የማትጸና እሳት አንድደን ፣ ወንጌልን የአንድ ሰሞን ብቻ አድርገን ይህቺን ምድር ያለ ተስፋ መተው። " ሲሉ ዘመኑ የሚያመጣውን አጣብቂኝ አብራርተዋል።

አክለውም መሪዎች የተመረጡት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንደሆነ እና በተሰጣቸው ጊዜም መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አና ንጉሴ

07/02/2026

***አስደሳች ዜና እግዚአብሔር ይመሥገን
የጸሎት ኃይል! ደጎ ማስተር አብነት በድል ወደ ሀገሩ ተመልሷል! 🙏🇪🇹

ኢትዮጵያውያን የምስራች! የሁላችንም ወንድም ደጎ ማስተር አብነት በሰላም ሀገሩ ገብቷል!

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! በታይላንድ ባንኮክ የህክምና ክትትሉን ሲያደርግ የቆየው ተወዳጁ ወንድማችን ደጎ ማስተር አብነት ህክምናውን በድል አጠናቆ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።

ወንድማችን አብነት እንኳን ለሀገርህ አበቃህ!

Address

Addis Ababa

Telephone

+251940642650

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agape Prayer and Gospel international Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Agape Prayer and Gospel international Ministry:

Share